ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


"ግራ ሊያጋቡን ለሚጥሩት ምላሻችን ይህ ነው።"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ጰላድዮስ
ደቂቀ አትናቴዎስ(ዲ/ን ዘአትናቴዎስ) እና እኔ ጰላድዮስ በዕቅበተ እምነት ዘርፍ የተመረጡ ልጆችን እያስተማርን መሆኑ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ስምንት(8) ልጆችን በተጨማሪ ማሰልጠን እንፈልጋለን። ስለሆነም እድሜያችሁ ከ18 አመት በላይ የሆናችሁ እንግሊዝኛ አንብቦ/ባ መረዳት የሚችል ወይም የምትችል እና በክርስትና ላይ ጥሩ መረዳት ያላችሁ እና እስልምና ላይ መስራት የምትፈልጉ ሰዎች ከታች ባለው ፎርም ላይ እስከ ቅዳሜ ምሳ ሰዓት አሳውቁን።

ፈተና ይኖረዋል😁 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSd7WLQxB5UosUcDJpFGTMuMiUQxbIiK2Fhy-SmgFv_I-FNVFg/viewform?usp=publish-editor


Monarchical Trinity ላይ የቀጠለ ...

ባለፈው በ Monarchical Trinity ላይ ባጋራሁት ጽሑፍ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ኤጲፋንዮስን ብቻ ለምን ትጠቅሳለህ ? እስቲ ከቀጰዶቂያ አበው አንድ አባት ስጠን ፣ ሞናሪኪ ለአብ ብቻ እንደማይቀጸል የተናገረ ወይም ደግሞ ለሦስቱም አካላት በአንድነት (አንድ ባሕርይ አንድ መለኮት ናቸውና) ሊነገር እንደሚችል የገለጸ ? የሚል ጥያቄ ባቀረባችሁልኝ መሰረት ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሥራዎች ሁለት አንቀጽ ጀባ ልበላችሁ።

ዓይናችሁን አብርታችሁ ልባችሁን ከፍታችሁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ የዶ/ር ጆሽዋ ሲጅዋዴን (i.e ምናልባት የምሥራቅ ኦርቶዶክስን) Monarchical Trinity ጽንሰ ሃሳብ እንዴት እንደሚያፈራርሰው ተመልከቱ።

«It is Monarchy that we hold in honour – but not a Monarchy that is contained in one single person. For it is possible for this one person, if at variance with itself, to become a plurality of persons. But it is a plurality which consists of an equality of nature, a unanimity of will, and an identity of action, and which converges back into the One from which they come – a thing unheard of among created natures. In this case, though the sovereignty is distinct with respect to number, yet it is not divided with respect to substance (Oration 29.2)

-> ዋና ሃሳቡ :- ሞናርኪ በአንድ አካል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም።

«This I give you to share, and to defend all your life, the One Godhead and Power, found in the Three in Unity, and comprising the Three separately, not unequal, in substances or natures, neither increased nor diminished by superiorities or inferiorities; in every respect equal, in every respect the same; just as the beauty and the greatness of the heavens is one; the infinite conjunction of Three Infinite Ones, Each God when considered in Himself; as the Father so the son, as the Son so the Holy Ghost ; the Three One God when contemplated together; Each God because Consubstantial; One God because of the Monarchia (Oration 40:41)

-> ዋና ሃሳቡ :- ሦስቱም አካላት በራሳቸው አምላክ ሲሆኑ በአንድነት ግን አንድ አምላክ ናቸው ፤ አንድ አምላክ በሞናሪኪያ ምክንያት።

እኔ ደግሞ በተራዬ ልጠይቃችሁ :- ማንን ነው የምታምኑት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙን ወይስ ዶ/ር ጆሽዋ ሲጅዋዴን ?

አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ


Репост из: Children of Athanasius
Can_Justin_Martyr_Truly_Be_Called_Trinitarian_If_He_Believed_the.pdf
714.5Кб
This article thoroughly examines and offers a novel, pioneering answer to one of the strongest arguments anti-Trinitarians raise against Justin Martyr. The argument centers on Justin's statement that the Son is 'begotten by the will of the Father,' a phrase which, according to Athanasius, implies the Son was created. Consequently, anti-Trinitarians contend that Justin Martyr cannot be a Trinitarian if he believed the Son was begotten by the Father's will. By reading this article, you will be equipped to answer this false accusation and and defend your faith.

Amen, Lord Jesus, come !


በእንተ ዮስጢኖስ ሰማዕት

በዘመናዊው የነገረ አበው ጥናት በእጅጉ ከተበደሉና ካስተላለፋት መልዕክት በተቃራኒው የተረዱ (misunderstood የተደረጉ) ከምላቸው አበው መሐከል አንዱ ነው - ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት፤ በዘመንኛ ሊቃውንት (Contemporary Scholars) ዘንድ የሚስተዋለው በአሥራ ዘጠነኛው እና ሃያኛው ክፍለ ዘመን የተደረጉ የነገረ አበው ጥናቶችን ሳይመረምሩ እና ሳያጣሩ እንደ በቀቀን የመድገም አባዜ ዮስጢኖስ ሰማዕት መዓርገ መለኮታዊ (Subordinationist) ነው የሚል ዲስኩር በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመንም እንድንሰማ ምክንያት ሆኗል።

ልብ አድርጉ ! የሰማዕቱን ጽሑፍ ስታነቡ በኋለኛው ዘመን የዳበረ እና የጎለበተን የሥላሴ እሳቤ እንደ መቅድመ ልባዌ አትያዙ የሚሉ ሰዎች ናቸው እንደ ጅብራ በአካዳማዊ ክበብ ውስጥ የተደነቀረውን እና «ዮስጢኖስ ሰማዕት በመዓርገ መለኮት ያምን ነበር» የሚለውን ወጥ ስምምነት (Consensus) እንደ መቅድመ ልባዌ ይዘው የቅዱሱን ጽሑፍ የሚያነቡት - “በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?” የሚለው የጌታችን ቃል ጥሩ ተግሳጽ የሚሆናቸው ይመስለኛል።

ይህን ስል ግን ወደፊት በነገረ አበው ላይ የምሁራን ወጥ ስምምነትን (Scholarly Consensus) የሚቀይሩ እና የሚገዳደሩ ጥናቶች በሰማዕቱ ጽሐፎች ዘሪያ ሊኖር እንደሚችል ጭላንጭል ተስፋ አይታየኝም እያልኩ አይደለም - «ህልም አለኝ» እንዳለ ማርቲን ሉተር ኪንግ በአካዳማዊ እና ምሑራዊ ክበብ ውስጥ በቅዱስ ሄሬኔዎስ ላይ የዘነበው ዝናብ ለዮስጢኖስ ሰማዕትም እንደሚያካፋ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።

ይገርማችኋል ! በሃያኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ከሞላ ጎደል ሁሉም ጥናታዊ ጽሑፎች ስለ ሄሬኔዎስ የሚያትቱት የወልድን ዘላለማዊነት እንደማይቀበል (በTwo step logos theology ያምናል ተብሎ ስለሚታሰብ) ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ (በቅዱሱ ቃል ፕሌሮማ) የማይጋሩ በማዓርግ የሚያንሱ ናቸው ብሎ እንደሚያምን ነበር ፣ እንደ Jackson Lashier እና Anthony Briggman የመሳሰሉ የነገረ አበው ሊቃውንት ነገሩ የተገላቢጦሽ መሆኑን እስኪያሳዩ ድረስ።

በተመሳሳይ ወደ ፊት ቢያንስ ከእርሱ ጋር ዘመን ገጠም የሆነው አቴናግሮስ አለው የሚባለውን ያህል የጎለበተ ነገረ ሥላሴ በሰማዕቱ ሥራዎች ውስጥ የሚያሳይ ደገኛ የነገረ አበው ሊቅ እስኪመጣ በራሳችሁ የቅዱሱን ጽሑፍ እያነበባችሁ በህሊናችሁ እየገመገማችሁ እና ድምዳሜ ላይ እየደረሳችሁ ቆዩ እንጂ ስመ ጥር ምሁር ስለጻፈው ብቻ ዝም ብላችሁ አሰስ ገሰሱን እንደ ህዳር አህያ አትጫኑ።

የቅዱስ ዮስጢኖስ ጸሎት እና ምልጃው ይርዳን ይርዳችሁ !

             አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

                ✍ በዲ/ን ዘአትናቴዎስ        


አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ.pdf
482.9Кб
«ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ከሆነ ለምን ተራበ ፣ ተጠመ ፣ አንቀላፋ እንዲሁም ሰው የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ አደረገ ? ይህን ማድረጉስ አምላክ እንዳልሆነ ያሳያልን ?» የሚለውን ጥያቄ በሰፊው የዳሰስኩበት መጣጥፍ ነው።

አንብቡ አስነብቡ !


እውነተኛ ነቢይ አይደሉም!.pdf
417.5Кб
በ PDF ካልሆነ አናነብም ለምትሉ ነው።

2.3k 0 25 28 33

ሙሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ ለመሆናቸው ግልጽ እና የማያሻማ ማስረጃ «እውነተኛ ነቢይ አይደሉም» በሚል ርዕስ ወንድም ሮቤል ያዘጋጀው መጣጥፍ ነው።

የመጀመሪያ መጣጥፋ ነው ስለዚህ አንብባችሁ አበረታቱት።

https://www.sonsofathanasius.com/index.php/site/article_detail/20


ባሕር ላይ ሲራመድ.pdf
343.8Кб
በ PDF ይዘጋጅልን ስላላችሁ ነው።


የጌታ ኢየሱስ በባሕር ላይ መራመድ እንዴት አምላክነቱን እንደሚያሳይ Contemporary Scholarship በደረሰበት የታሪካዊው ኢየሱስ (The Historical Jesus) ጥናት መሰረት የተጻፈ መጣጥፍ ነው።

https://www.sonsofathanasius.com/index.php/site/article_detail/19


Is Jesus Christ All Knowing .pptx
11.6Мб
Opening Statement ቴን ጀባ ልበላችሁ።

አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

✍ ዲ/ን ዘአትናቴዎስ

3.4k 0 29 11 35

ሁሉን አላዋቂ (1).pdf
1.2Мб
ለማንበብ ከቀለላችሁ በሚል ረጅሙ መጣጥፍ በአንድ ተሰድሮ ነው።


Ustaz wehid .pptx.pptx
7.4Мб
ኡስታዝ ወሒድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ጋር ምሑራዊ እና አካዳማዊ ውይይት ለማድረግ ብቁ ላለመሆናቸው የቀረበ አነስተኛ ማስረጃ ነው፤ በዚያውም ለምን በዚህ ሰዓት ከመምህር በረከት አዝመራው ጋር መወያየት ፈልጉ የሚለውን ትክክለኛ ምክንያት አስቀምጠናል።

አንብቡ ለሌሎችም አጋሩ


ከላይ ባሰፈርነው የቁርአን ክፍል ውስጥ አላህ ራሱን ከጣዖታት ጋር እያነጻጸረ ሲናገር ፣ እርሱ ከጣዖታት መሐከል መሆኑን እየገለጸ ነውን ? ጣዖታትስ ከእርሱ ጋር እኩል መሆናቸውን እያመለከተ ነውን ? እንደዚያ ካልሆነስ ስለምን 'ይተካከላሉን' በማለት መጠየቅ አስፈለገው ? የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሳችሁ ምንድን ነው ? "

መልሳችሁ "አይ አይደለም ፤ ነገሩ እናንተ ካሰባችሁት የተለየ ነው። አላህ እዚህ ጋር እየገለጸ ያለው ጣዖታት ምን ያህል ደካማ እንደሆኑ እና ከርሱ ጋር ሊነጻጸሩ የማይችሉ እንደሆኑ ነው" [5] የሚል ከሆነ "ከመጣሽ ማርያም ታምጣሽ" እንደ ሚባለው የኢየሱስ ክርስቶስንም ከመላእክት ጋር መነጻጸር በዚህ ልክ ተረዱት እንላለን ፤ ምክንያቱም የዕብራውያን ጸሐፊ ዓላማ ለሰማዕያኑ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በመጥቅስ ማሳየት እንዲሁም እርሱ መላእክት እንኳን የሚያመልኩት አምላክ መሆኑ ማስገንዘብ ነውና።

ለዚህም ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል መጻፋ “ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።”(ዕብ 1፥6) ቅዱስ  ጳውሎስ ከብሉይ ኪዳን ጠቅሶ ያሰፈረው ጥቅስ ዘዳ 32:43 [6] ላይ የሚገኝ ሲሆን በአውዱ ጥቅሱ የሚያወራው መላእክት ለእግዚአብሔር እንደ ሰገዱ ነው ፤ ሆኖም ይህን ጥቅስ በኩር ተብሎ ለተጠራው ለኢየሱስ ክርስቶስ መዋሉ ፣ የዕብራውያን ጸሐፊ መላእክት ኢየሱስ ክርስቶስን ያመልኩታል እንጂ አይተካከሉትም እርሱ አምላካቸው ነውና የሚል ሃሳብን እንዳሰፈረ ግልጽ አድርጎ ያስረዳል [7] ።

ወደ ተነሳንበት ሐሳብ ስንመለስ እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስን "እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ" ስላለው ወልድ ዘላለማዊ አይደለም ብሎ መናገር መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ነው ፤ ምክንያቱም የዕብራውያን መልእክት ስለ ሥግው ቃል ዘላለማዊነት "አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።" (ዕብ 1:8) ፣ " ...ለዘመኑ ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም... "(ዕብ 7:3) በማለት ምስክርነት ይሰጣልና።

በተጨማሪም አብ ያለ ወልድ የኖረባት የዓይን ጥቅሻ የምታህል ጊዜ እንኳን አለች ማለት ጸሐይ ያለ ብርሀኗ የነበረችበት ጊዜ አለ እንደማለት ነው - የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ - ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ "የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ"(ዕብ 1:3) እንደሆነ ገልጿልና። ይህን እውነት ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ውብ በሆነ አገላለጽ እንዲህ በማለት ገልጾታል :-

"ንገሩኝ እስቲ ከፀሐይ የሚወጣው የብርሃን ጨረር ከክበብዋ ነው ወይስ ከሌላ ? ማንም ቢሆን ጨረሩ ከፀሐይዋ ክበብ የሚፈልቅ ስለመሆኑ የገዛ ሕሊናው የሚሰጠውን ምስክርነት ሊክድ አይችልም። ሆኖም ጨረሩ ከፀሐይዋ ክበብ የፈለቀ ቢሆንም ለቅጽበት እንኳን በመካከላቸው መቀዳደም እንደሌለ መረዳቱ አለን። ክበቧም ያለ ብርሃኗ ፈጽማ ልትታይ አትችልም። ስለዚህ ከዚህ ከምናያትና ከምንረዳት ፍጥረት የወጣው ብርሃን ከተገኘበት ክበብ ቀጥሎ ያልተገኘ ከሆነና በሁለቱም መካከል መቀዳደም ከሌለ ፤ በማይታይና ረቂቅ ባሕርይ ባለው መለኮት ዘንድ ይህ መሆኑ ምን ይደንቃል ? በዚህ አንድ ዓይነት ነገር መፈጸሙን እናስተውላለንና።

በአብና በወልድ ዘንድ በመውለድና በመወለድ መቀዳደም እንደሌለ ቅዱስ ጳውሎስ በብርሃን መስሎ:- “እርሱ የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ”(ዕብ፩፥ ፫) ብሎት እናገኘዋለን። እንዲህም ማለቱ ከአብ የተገኘና ከእርሱ ጋር በአንድነት የሚኖር መሆኑን በብርሃን መስሎ ማስረዳቱን ነው። ዘመናት በእርሱ የተፈጠሩ አይደሉምን? ማንም ሰው በአእምሮ ጠባዩን ተጠቅሞ ይህን በቀላሉ ሊረዳው ይችላል። ስለዚህ በአብና በወልድ መካከል ምንም ዓይነት መቀዳደም እንደሌለ ከአብ በኋላ የተገኘ እንዳልሆነ ከአብ ጋር አንድ ሆኖ የሚኖር መሆኑን ከቅዱሱ መጽሐፍ እንገንዘብ።"
[8]

ስለሆነም ወልድ ከአብ ጋር ያልነበረበት ጊዜ የለም ማለት ነው ፤ ታዲያ ስለምን "ዛሬ ወልጄሃለሁ" አለው ? ዛሬ ሚለው ቃል ፍጡር ጊዜን የሚያመለክት አይደለምን ?  ዛሬ የሚለው ቃል በጊዜ ሂደት ውስጥ ያለውን ሰዓት ወይንም ቀን የሚያመለክት ቢመስልም  በዕብራውያን መልዕክት አውድ ግን ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ያለውን ፍጹም ዘላለማዊነት የሚያሳይ ነው ፤ ማለትም በዘላለም ውስጥ ተከውኖ የተፈጸመ ትላንት ፣ ገና ያልሆነ ነገ የለም በዚያ ያለው ዘላለማዊ አሁን ነው። ዛሬ የሚለው ቃልም ይህን ዘላለማዊ ጊዜ ውስን በሆነው የሰውኛ ቋንቋ የሚገልጥ ነው።

ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች "ዛሬ" የሚለው ቃል ዘላለማዊ የሆነ የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳማዊ ልደት እንደሚያመለክት ያስተማሩ ሲሆን "እግዚአብሔር ዘመናትን ሁሉ የፈጠረበት ልጁን ከዘመናት ውጪ ወለደው" እንዳለ ሊቁ የሥግው ቃል ቀዳማዊ ልደት እንደ ፍጡራን በጊዜ ውስጥ የሆነ እንዳልሆነም አስረድተዋል ።

በእርግጥ "ዛሬ" በሚለው ቃል ጅማሮና ፍጻሜ የሌለውን ዘላለማዊነት መግለጽ በአይሁዳውያንም ዘንድ እንግዳ አይደለም ፤ ለአብነትም ሄሌናዊው አይሁድ ፋይሎ ዘእስክንድርያ (Philo of Alexandria) ዘዳግም 4:4 ትን ባብራራበት አንቀጹ "ማብቂያ ለሌለው ዘመን ፍጹም ትክክለኛ ስም ዛሬ ነው ።" በማለት ተናግሯል። በዚህም "ዛሬ ወልጄሃለሁ" በሚለው ቃል መነሻነት አሕመዲንም ሆነ መሰሎቻቸው የወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላለማዊ ልጅነት ለመካድ መነሳታቸው ፍጹም ስህተት እና አላወቂነት መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ይመስለኛል።


አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

           ✍ በዲ/ን በዘአትናቴዎስ የተጻፈ

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

1). ክርስቶስ ማነው ? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች ? በአሕመዲን ጀበል ፣ ገጽ.51

2). “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል። ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤ እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥”(ዕብ 10:10-12)

3). ክርስቶስ ማነው ? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች ? በአሕመዲን ጀበል ፣ ገጽ.31

4). Against The Arians 1፥13

5).https://muslimcentral.com/series/yasir-qadhi-the-parables-of-the-quran/

6). "በዕብ 1:6 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሰው ጥቅስ የትኛው ነው ? በሚለው ዙሪያ በሊቃውንት ዘንድ የተወሰነ ልዩነት ያለ ሲሆን ሐዋርያው መዝ 97:7 ትን እየጠቀሰ ነው የሚሉም አሉ ። "የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ለእርሱ ይስገዱ" የሚለው "Masoretic texts" ላይ የሌለ ቢሆንም ፣ ሐዋርያው ዘዳ 32:43 ትን ከሰብአ ሊቃናት ትርጉም እየጠቀሰ ነው የሚለው ይበልጥ ሚዛን ሚደፋ ይመስላል።" [Deuteronomy 32:8 And The Sons of God by Michael S.Heiser]

7). Christ-Centered Exposition Commentary: Exalting Jesus in Hebrews by R. Albert Mohler

8). Homily On The Gospel of John by St.John Chrysostom


«ዛሬ ወልጄሃለሁ» የሚለው ቃል ክርስቶስ ፍጡር እንደሆነ ያሳያል ?

አሕመዲን ጀበል :- "ዕብራውያን 1:5 «እግዚአብሔር፣«አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ፤ ወይስ ደግሞ «እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል» ያለው ከቶ ለማን ነው ?» ይላል። እግዚአብሔር ኢየሱስን «እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ» ሲለው ያኔ ከመወለዱ በፊት እንዳልነበር ግልጽ ነው። «ዛሬ» ፣ «ትናንት» እንዲሁም በአጠቃላይ «ጊዜ» ከተፈጠረ በኋላ ነው «ዛሬ» ሊባል የሚችለው። በኢስላምም ሆነ በክርስትና ሃይማኖት «ጊዜ» ፍጡር እንደሆነ ነው የሚታመነው። ታዲያ እንዴት «ኢየሱስ ዘላለማዊ ነው» ሊባል ይችላል ? ከመወለዱ በፊት ነበርን ?" [1]

መልስ :- የ "ክርስቶስ ማነው ? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች ?" መጽሐፍ ደራሲ ከላይ ያሰፈርነውን ጥያቄ በመጽሐፋቸው ውስጥ ደጋግመው ያነሱት ሲሆን ለአብነትም በምዕራፍ አንድ ጥያቄ ቁጥር 31 ፣ በምዕራፍ አምስት ጥያቄ ቁጥር 12 ,17 እና 18 ትን መመልከት ይቻላል ፤ አንድን ጥያቄ በዚህ ልክ ደጋግመው ማቅረባቸው "እውን አሕመዲን የጻፏቸው ጥያቄዎች ሥርዓት ባለመልኩ ቢሰደሩ 303 ይሞላሉን ?" የሚል ጥያቄ ቢያጭርም የመፍቀሬ ሰብእ ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላለማዊነት ቁልጭ አድርጎ ከሚናገረው ከዕብራውያን መልእክት ጠቅሰው የሥግው ቃልን ዘላለማዊነት ለመገዳደር መሞከራቸው ግን ትዝብት ውስጥ ይከታቸዋል።

የዕብራውያን መልእክት ምክንያተ ጽሕፈት ወደ ክርስትና የመጡ አይሁዳውያንን ለማበረታታ እንዲሁም የያዙት እምነት ከቀድሞ ሥርዓት የተሻለና የሚልቅ መሆኑን ማስገንዘብ ነው ፤ ቅዱስ እስጢፋኖስ " ...በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ... " (ሐዋ 7፥52-53) ሲል እንደተናገረ - አይሁዶች ሕገ ኦሪትን በመላእክት መቀበላቸውን በመጥቀስ ወደ ክርስትና የመጡ አሕዛብ ላይ ራሳቸውንን ከፍ ከፍ ያደርጉ ነበርና የዕብራውያን ጸሐፊ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ በላይ እንደሆነ ፣ እርሱ ከመላእክት ሁሉ እንደሚበልጥ ፣ ክህነቱ ከብሉይ ኪዳን ክህነት እንደሚሻል እንዲሁም የእርሱ መሥዋዕት ከብሉይ ኪዳን መሥዋዕትም ሁሉ እንደሚልቅ ይረዱ ዘንድ መልእክቱን ጽፏል።

የመልእክቱንም ዋና ሃሳብ ይገነዘቡ ዘንድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስን በብሉይ ኪዳን ነቢያት ጋር ፣ ከመላእክት ጋር እንዲሁም በሕገ ኦሪት ከነበረው የክህነት ሥራ ጋርም በማነጻጸር መልእክቱን ጽፏል [2]። የሚያስደንቀው ነገር ግን  አሕመዲን የአብ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክት ጋር መነጻጸሩ አምላክነቱ ይጋፋል ብለው ማመናቸው ነው ፤

"... በተምሳሌታዊ አገላለጽ(symbolic expression) «ልጄ ነህ» ነህ ማለት እንጂ በተግባር መወለዱን አያመለክትም። ይህ ባይሆንማ ኖሮ በጭራሽ ከመላዕክት ጋርም ባልተነፃፀረ ነበር።" [3]

በእውነቱ አሕመዲን "በተግባር መወለዱን" ሲሉ ምንን ለማመልከት እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም ፤ ሆኖም ሙግቱን ጠበብ ለማድረግ ያህል ጥያቄያቸውን አቃንተን ለመረዳት እንሞክር። "በተግባር መወለዱን" ሲሉ እኛ ክርስቲያኖች እንደምንለው "በባሕርይ መወለዱን" ለማመልከት ሽተው  ይመስላል ፤ ይህን ግምታችንን የሚያጠናክረው ደግሞ "ወልጄሃለሁ" ሚለው ቃል ተምሳሌታዊ አገላለጽ ነው ማለታቸው ነው። በዚህም ሙግታቸውን አቃንተን ብናስቀምጠው ይህን ይመስላል ብዬ እገምታለሁ ፤

"ኢየሱስ ክርስቶስ ልጅ ተብሎ ሲጠራ መላእክት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች በተባሉበት አግባብ ነው እንጂ የባሕርይ ልጅነትን የሚያመለክት አይደለም (ዘፍ 6:1-4 ፣ኢዮብ 1:6 ፣2:1)። ይህ ባይሆንማ ኖሮ በጭራሽ ከመላዕክት ጋርም ባልተነጻጸረ ነበር ።"

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክት ጋር መነጻጸሩ ልጅነቱ የባሕርይ አይደለም እንድንል ያደርገናል ማለታቸው ደራሲው ምን ያህል ከመጽሐፍ ቅዱሳ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ነገሮችን በንጽጽር ሲያቀርብ በሚነጻጸሩት ነገሮች መሐከል የሚገኝን የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ለማመልከት እንጂ ተመሳሳይ መሆናቸውን ለመግለጽ አይደለም።

ለምሳሌ ጠቢቡ ሰለሞን "... ጥበብ ከቀይ ዕንቁ ትበልጣለችና" (ምሳሌ 8:11) ማለቱ ቀይ ዕንቁ እንደ ጥበብ ናት ለማለት ሽቶ አይደለም ጥበብ ምን ያህል ከቀይ ዕንቍ እንደምትልቅ ለማሳየት ነው እንጂ። ዳግመኛም ልበ አምላክ ንጉሥ ዳዊት “ ... በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።” (መዝ 84፥10) በማለት ሲዘምር በእግዚአብሔር ቤት እና በኃጥኣን ድንኳን መካከል ያለውን ልዩነት ለመግለጽ እንጂ የኃጥኣንን ድንኳን ከእግዚአብሔር መቅደስ ጋር እያስተካከለ አይደለም።

በዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ነገሮችን ወይንም አካላትን ለንጽጽር ሲያቀርብ በመሐከላቸው የሚገኘውን ልዩነት ለማመልከት እንጂ አንድ ዓይነት ናቸው ለማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው ፤ ቅዱስ አትናቴዎስ  ሐዋርያው በመልእክቱ መላእክትን ከጌታችንንና መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በማነጻጸር  ማስቀመጡ መላእክትና ኢየሱስ ክርስቶስ ሊነጻጸሩ የማይችሉ መሆናቸውን ለማሳየት እንጂ የባሕርይ አንድነት አላቸው ለማለት እንዳልሆነ እንዲህ በማለት በሚያምሩ ቃላት አስገንዝቧል :-

"በተመሳሳይ መላእክት እና ወልድ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም ፤ በዚህም ' ይልቅ ' የሚለው ቃል የሚያነጻጸር ሳይሆን ሊነጻጸሩ የማይችሉ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው ፣ ምክንያቱ በባሕርይ ይለያያሉና ።" [4]

ምናልባት ከላይ ያሰፈርነውን መልስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው በቀደመው ሙግታቸው በመጽናት "በዚህም አለ በዚያ ወልድ ከመላእክት ጋር በንጽጽር መቀመጡ ልጅነቱ እንደ መላእክት ያለ እንጂ የባሕርይ እንዳልሆነ ያሳያል" ብለው ይናገሩ እንደሆን ከቁርአን አንድ አያ ጠቅሰን እንጠይቃቸው። በሱራ 16:75 - 76 ላይ አላህ ራሱን ለጋስ በሆነ ባለጸጋ ሰው ፣ ጣዖታትን ደግሞ ምንም ሥራ በማይችል ባሪያ መስሎ በማቅረብ ራሱን ከጣዖታት ጋር በማነጻጸር እንደተናገረ ተጽፎአል ፤ እንዲህ በማለት :-

۞ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا عَبْدًا مَّمْلُوكًا لَّا يَقْدِرُ عَلَىٰ " شَيْءٍ وَمَن رَّزَقْنَاهُ مِنَّا رِزْقًا حَسَنًا فَهُوَ يُنفِقُ مِنْهُ سِرًّا وَجَهْرًا ۖ هَلْ يَسْتَوُونَ ۚ الْحَمْدُ لِلَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

በምንም ላይ የማይችለውን በይዞታ ያለውን ባሪያና ከእኛ መልካም ሲሳይን የሰጠነውን እርሱም ከእርሱ (ከሰጠነው) በምስጢርና በግልጽ የሚለግሰውን (ነጻ) ሰው አላህ (ለጣዖትና ለርሱ) ምሳሌ አደረገ፡፡ (ሁለቱ) ይተካከላሉን ምስጋና ለአላህ ይኹን፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡"


ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ አትበሉኝ ሲል ተናግሯልን ?

በክርስቶስ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው።

ለስም አጠራሩ ክብር ምሥጋና ይግባውና የጌታችን ክርስቶስን አምላክነት መቃወም የዕለት ግብራቸው ያደረጉት ተንባላት መጽሐፍ ቀመስ ያልሆነውን ምዕመን ግራ ለማጋባት ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ መቅጠፍ ልምዳቸው ነው ፤ ታዲያ በዚህ ጥርሳቸውን በነቀሉበት የማሳሳት ተግባር ከከንፈራቸው የማይለዩት አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አለ። ጥቅሱም እንዲህ ይነባል፦ 

“በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።” (ማቴ 7:21)

ታዲያ ሙስሊሞች ይህን የጌታ ንግግር  ይጠቅሱና “ኢየሱስን ይሉታልን? ይህ ከሆነ መንግስተ ሰማያት መግባት አይፈልገጉም ማለት ነው። ... ኢየሱስን የሚለው ማን ነው? ሙስሊሞች ወይስ ክርስቲያኖች? 'አላውቃችሁም ፣ እመሰክርባቸዋለሁ' ያለውስ ማንን ነው? ክርስቲያኖችን! ... እና መንግስተ ሰማያት መግባት አይፈልጉም? ለምን ሌላ ትርጉም በመስጠት ራስዎን ያታልላሉ?... ታዲያ እንዴት ተታለሉ?” [1] ይሉናል ለመሞገት እየቃጣቸው።

በእውነቱ ሌላ ትርጉም የሰጠው ፣ ራሱንስ ያታለለው ማን ነው ? የሚለውን በዚህች መጣጥፍ አመልክተን ፣ ከዚያም ሻገር በማለት በጠቀሱት ጥቅስ የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አሳይተን እንቋጫለን - መልካም ንባብ !

ጅማሯችንን ክፍሉ የሚገኝበትን ዓውድ ከመገምገም እናድርግ ፤ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 7:21 የተራራው ስብከት ተብሎ በሚጠራው የወንጌል ክፍል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5 እስከ 7 ያለውን የሚሸፍን ፣ ጌታችን ለሐዋርያት ክርስቲያናዊ ምግባርን ያስተማረበት ክፍል ነው።

ይህን በአዕምሯችን ይዘን ሙስሊሞቹ ከሚጠቅሱት ክፍል ቀደሞ የተቀመጡትን የጌታ ቃሎች ስንመለከት በቁጥር 15 ላይ እንዲህ ይላል፦ “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” ፤ እነዚህ ተኩላዎች ብሎ የጠራቸው ሐሰተኛ ነቢያቶችን ከእውነተኛዎቹ እንዴት እንደምንለያቸው ሲናገር ደግሞ ቁጥር 20 ላይ "ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ" ብሏል።

ቀጥሎም ቀደም ብሎ ከሐሰተኞች ነብያት እንድንጠነቀቅ የነገረን በማጽናት ጌታችን “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” ሲል አክሏል ፤ በዚህም ከዚህ በመነሳት ጌታችን ፍሬ ስለሌላቸው (እምነቱን ይዘውት ነገር ግን ምግባራቸው እሾህ ስለሆነ ሰዎች) እየተናገረ እንጂ በጠቅላላው ስለ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያኑ እያወሳ አለመሆኑን መገንዘብ እንችላለን። 

እንዲሁም ይህንኑ ጥቅስ በተቃራኒ ንባብ (contrario reading) ስናነብ "... ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ ..." የሚለው የጌታ ቃል ምግባረ ብልሹ በከንፈራቸው ብቻ አማኞች የሆኑት የሚመለከት ሲሆን ይሄ አስተብቅዖታቸው የማይሰማው ስለ ምግባራቸው ብልሹነት ነው ፤ ማለትም ጥቅሱ በተቃራኒ ንባብ ሲነበብ የቀና ፣ በጎ እና ፍሬያማ ምግባር ያላቸው ክርስቲያኖች "... ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ ..." ቢሉ መንግስተ ሰማያት መግባት ይችላሉ ፣ ስህተት ውስጥም አልወደቁም እንዲሁም ክርስቶስ በሚገባ «ጌታ» ተብሎ ይጠራል የሚል ነጥብ ያስይዛል።

እጅን በአፍ የሚያስጭነው ደግሞ የክርስቶስን አምላክነት ለመቃወም በጠቀሱት ማቴ 7:21 ላይ "... ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ ..." የሚለው ቃል ባስተውሎ ከተመለከትነው የክርስቶስን አምላክነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መሆኑ ነው ፤ እንዴት ? በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አምላክ በዕብራይስጥ ቋንቋ "አዶናይ ያሕዌ/ጌታ እግዚአብሔር" እየተባለ ይጠራ የነበረ ሲሆን [2] ሰብአ ሊቃናት "አዶናይ ያሕዌ(אֲדֹנָי יַהְוֶה)" የሚለውን ቃል ወደ ግሪክ "κύριε κύριε/ጌታ ጌታ" ብለው ተርጉመውታል - ይህም አምላክነትን የሚያሳይ ሲሆን ለአምላክ ብቻ የሚውል መጠሪያ ነው።

በዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 7:21 እና 25:11 ላይ ይሄንኑ አገላለጽ መጠቀሙ አምላክነቱን ይገልጣል ፤ ይህን በተመለከተ በዘመናዊ የሐድስ ኪዳን ጥናት ፕሮፌሰር የሆነው Charles L.Quarles በማቴዎስ ወንጌል ማብራሪያው ላይ እንዲህ ይላል፦

"ድርብ ጥሪ የሆነው ‘κύριε κύριε’ የኢየሱስን አምላክነት እውቅና የሚሰጥ ሆኖ ተቀምጧል። ይህ ድርብ ጥሪ በሰባ ሊቃናት ትርጉም (LXX) ውስጥ አሥራ ስምንት ጊዜ ተጠቅሷል ፤ ሁልጊዜም ያህዌን ለመጥቀስ እና በተለምዶም የመለኮታዊው ስምና ማዕረግ የሆነውን ‘አዶናይ ያህዌ’ን ለመተርጎም ያገለግል ነበር።” [3]

ነገር ግን አንዳንዶች ይህን አረዳድ በመቃረን "...ጌታ ሆይ ፣ ጌታ ሆይ ..." የሚለው በብሉይ ኪዳን "አዶናይ ያሕዌ" የሚለው በግሪክ ሲገለጽ ሳይሆን በቀላሉ ልመናን ፣ የስሜት መሰበርን የሚያመለከት ነው በማለት ይሞግታሉ ፤ Jason A. Staples የተባለው ሊቅ "...ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ..." የሚለውን ሀረግ በተመለከተ የሚቀርቡ ከላይ ያነሳነውንና ሌሎች አረዳዶችን ከመዘነ በኋላ ሀረጉን እንዴት መረዳት እንደሚገባን እንዲህ በማለት ይደመድማል፦

"የ ‘κύριος’ ድርብነት እና እነዚህ አባባሎች በማቴዎስና በሉቃስ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉበትን መንገድ ስንመለከት፣ እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ራሱን ለመግለጽ የመለኮታዊውን ስም ተጠቀመበት ከሚለው ድምዳሜ ማምለጥ ይከብዳል። ይህ ደግሞ የግሪክን መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያውቅ ማንኛውም የአንደኛ ክፍለ ዘመን አንባቢ ሊስተው የማይችል ነው።” [4]

Scott Brazil የተባለውም ሌላ ሊቅ እንዲህ ይለናል ፦

“ድርብ ጥሪ የሆነው κύριε κύριε የሚለው ቃል ለከፍተኛ ስሜት አጽንዖት ለመስጠት የተደጋገመ ሳይሆን፣ በግሪክ የብሉይ ኪዳን ትርጉም (LXX) ውስጥ ለመለኮታዊው ስም (ለእግዚአብሔር ስም) እንደ ምትክ ያገለግል ነበር።” [5]

በመጨረሻም ለጥቅሱ ሌላ ትርጉም የሰጠው ፣ ራሱንስ ያታለለው ማን ነው? የሚለውን እንድትለዩ ፍርዱን ለአንባቢያን በመተው መጣጥፋን እዚህ ጋር የምቋጭ ይሆናል።

            አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

           ✍ በዲ/ን አናሲሞስ የተጻፈ

https://t.me/ZeathanAmharic


🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

1). ክርስቶስ ማን ነው? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች በኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ፣ ገጽ 29 - 30

2). ኢሳይያስ 28:16 ፣ ሕዝ 37:21

3). Matthew ; exegetical guide to the greek new testament by Charles L.Quarles ,pp.153

4). ‘Lord, LORD’: Jesus as YHWH in Matthew and Luke by Jason A. Staples

5). Jesus and YHWH - texts in the synoptic gospels by Scott Brazil , pp.101


ክርስቶስ ከአብ ተለይቶ መገለጹ እግዚአብሔር እንዳልሆነ ያሳያልን ? (አርቲክል አይደለም 👎)

በክርስቶስ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው።

ገና በጠዋቱ ከአንድ የይሖዋ ምስክር አማኝ ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተን ጥቂት ስለ ክርስቶስ አምላክነት እያወራን ነበር ፤ ታዲያ ይሄው ወንድም በምልልሳችን መሐከል ድሮ የማውቃትን አንዲት የቆየች ሙግት አነሳና ፈገግ አስባለኝ ፣ ሌላ ጊዜ እናንተንም ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ሙግቱንም መልሱን ጀባ ልበላችሁ።

ሙግቱ :- በመዋዕለ ስብከቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙውን ጊዜ ራሱን ከእግዚአብሔር (ይሖዋ/ያህዌ) እየለየ ይናገር ነበር ፣ ማለትም እግዚአብሔርን በሦስተኛ መደብ ይጠራው ነበር ራሱንም ከእርሱ ነጥሎ ይገልጽ ነበር ፤ ለአብነትም በዮሐ 14:1 “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።” የሚለው የኢየሱስ ቃል እግዚአብሔር እና ክርስቶስ የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸውን ያመለክታል ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር እና ክርስቶስ እና (καὶ) በሚል ቃል ተያይዘው እንዲሁም ተለያይተው ተቀምጠዋልና። [1]

መልሳችን :- በመጀመሪያ ደረጃ ሙግቱ በኦርቶዶክሳዊ የነገረ ሥላሴ አስተምሕሮ ላይ የተነሳ ቢሆንም ይህን አስተምሕሮ ግምት ውስጥ ያስገባ ወይንም ያገናዘበ አይደለም ፤ እኛ ክርስቲያኖች እንደ ሰባልዮሳውያን ክርስቶስ አብ ነው አንልም በተቃራኒው በተገባ በወልድ እና በአብ መሐከል የአካል/የማንነት ልዩነት አለ ብለን እናምናለን እንጂ።

በዚህም በተጠቀሰው ጥቅስ መሰረት እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው አብ መሆኑን ከተማመንን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ከአብ እና(καὶ) በሚል ቃል ለይቶ ማስቀመጡ ሁለት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ወይንም አብ ወልድ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው ፤ ስለሆነም የምታነሱት ጥቅስ እኛ ከምናመነውን ነገር ጋር የተስማማ ግፋ ቢል የሚያጠነክር እንጂ የሚቃረን አይደለም።

በተጨማሪም ኢየሱስ ክርስቶስ አብን እግዚአብሔር ብሎ ጠርቶ ራሱን እና በሚል ቃል ከአብ ጋር አጣምሮ መግለጹ የአብን አምላክነት የሚያሳይ እንጂ ወልድን ከአምላክነት የሚያርቅ አይደለም ፤ ስለ ሁለት ምክንያቶች :-

1). ይህ ዓይነቱ የአነጋገር መንገድ በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥም የሚገኝ ሲሆን በእናንተ የአረዳድ መንገድ የምንጓዝ ከሆነ ስህተት ውስጥ እንወድቃለን ፤ ለምሳሌ ሐዋ 5:29 “ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ ... ” ይላል ፤ ይህን ጥቅስ በእናንተ ሙግት መሰረት ከተረዳነው ጴጥሮስ ከሐዋርያት እና (καὶ) በሚል ቃል ተያይዞ እና ተለይቶ ተቀምጧልና ሐዋርያ አይደለም ማለት ይኖርብናል - ይህ ደግሞ ትልቅ ስህተት ነው። [2]

2). ሲቀጥል ቁጥር 1 ላይ ባሰፈርነው ሙግት መሰረት ቅዱስ ጴጥሮስ ከሐዋርያት እና (καὶ) በሚል ቃል ተለይቶ መቀመጡ ስለ ቅዱሱ ሐዋርያነት በአዎንታዊ ባይገለጽም እርሱ ሐዋርያ ነው ብለን የምናምነው በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሐዋርያ መሆኑ ስለተገለጸ ነው ፤ አይደል እንዴ ? (ምላሻቸው አዎ ነው የሚሆነው ብዬ እገምታለሁ)

በተመሳሳይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ራሱን እግዚአብሔር ብሎ ከጠራው ከአብ እና በሚል ቃል ለይቶ ሲገልጽ የአካል ልዩነትን እያመለከተ እንጂ ራሱን ከአምላክነት እያራቀ እንዳልሆነ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ እግዚአብሔር/አምላክ ተብሎ መጠራቱ ያስገነዝበናል።


አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

✍ በዲ/ን ዘአትናቴዎስ የተጻፈ

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

1). -> Should you believe in the Trinity ? By Watchtower Society , pp.14,16

-> ክርስቶስ ማነው ? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች በአሕመዲን ጀበል ፣ ገጸ.30

2). Does John 17:3 Disprove the Trinity ? By Paul George


ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ክርስቶስ ፍጡር ነው ብሏልን ? (ክፍል 1)

በክርስቶስ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው።

“ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ” እንዲል ሀገርኛው ብሂል የነገረ መለኮት ሊቃውንት እና የቤተ ክርስቲያን ጠበቆች ለዓመታት ከመናፍቃኑ ጋር የተሟገቱባቸው እና ድል የነሱባቸውን ያረጁ ያፈጁ ሙግቶች ዘግይተው ያወቁት ተንባላት ሙግቶቹን እንደ አዲስ እያነሱ - ከሐዋርያነ አበው እስከ የሁለተኛው ክፍለ ዘመን ዐቃቢያነ እምነት በአጠቃላይ ቅድመ ኒቂያ የሚገኙ አባቶች ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሥላሴ አላስተማሩም - ብለው መለፈፍ መጀመራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ታዲያ በዚህ የሐሰት ክሳቸውና ቅጥፈታቸው ራዳር ውስጥ ከገቡ አባቶች መሐከል የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ አንዱ ነው ፤ በዚህም በዚች አጭር መጣጥፋችን ቅዱሱ ላይ ከሚነሱ ቅጥፈቶች መሐል ለአንዱ መልስ የምንጽፍ ይሆናል - መልካም ንባብ !

ቅዱስ አግናጥዮስ ወደ ሰርሚኔስ ሰዎች በላከው መልዕክቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፍቃድ እና ኃይል የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ገልጿል ፤ እንዲህ ሲል :-

“በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ተሰቀላችሁ በማይናወጽ እምነት መጽናታችሁን ፣ እርሱ በእውነት በሥጋው የዳዊት ዘር ፣ በእግዚአብሔር ፍቃድ እና ኃይል ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መሉ በሙሉ አምናችሁ በፍቅር በክርስቶስ ደም በኩልም መታነጻችሁን አይቻለውና።” [1]

“ሆኖም” ይላሉ ተንባላት ከላይ የሰፈረውን የቅዱስ አግናጥዮስ ቃል ይጠቅሱና “አትናቴዎስ በእንተ አርዮሳውያን 3.30.59,67 ላይ ክርስቶስ በአብ ፍቃድ ነው የተወለደው ማለት ክርስቶስ ፍጡር ነው ማለት እንደሆነ አስተምሯል ፤ ስለሆነም በራሳችሁ አባት መሰረት አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ አስተምሯል - ወይስ ሁለቱ አባቶች ይጋጫሉ ?” በማለት ይሞግታሉ።

በእርግጥ ያቀረቡት ሙግት ደካማ ቢሆንም በቀጥታ ምላሽ ከመስጠታችን በፊት አስቀድመን ቅዱስ አግናጥዮስ ከኒቂያ ጉባኤ ፊት አውራሪው አትናቴዎስ ጋር በተስማማ መልኩ የክርስቶስን ዘላለማዊ ልደት (Eternal Generation) እንዳስተማረ ጥቂት ማስረጃ እናቅርብ።

ቅዱስ አግናጥዮስ በሰባቱ መልዕክታት ውስጥ ፍንትው እና ቁልጭ አድርጎ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጊዜ በፊት የነበረ ዘላለማዊ መሆኑን መስክሯል ፤ ለአብነትም እነዚህ አንቀጾች እንመልከት :-

“... ከጊዜ ጅማሮ በፊት ከአብ ጋር የነበረው ፣ በመጨረሻም በተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ...”[2]

“... ከጊዜ ሁሉ በላይ ፣ ዘላለማዊ እና የማይታይ ቢሆንም ስለእኛ የሚታይ የሆነ ፣ የማይዳሰስ እና መከራ የማይቀበል ቢሆንም በእኛ መከራ የሚቀበል የሆነ ፣ ስለ እኛም በሁሉ ነገር የተሰቃየ እርሱን ፈልጉት።” [3]

አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ክርስቶስ ዘላለማዊ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ከአብ የወጣ (የተወለደ) እንደሆነም ጭምር በመልዕክታቱ ውስጥ ገልጿል ፤ “... ከአብ የወጣው ወደ እርሱም የሄደው”[4] የሚለው ቃሉ ይህን የሚያረጋግጥ ነው። ታዲያ በቅዱስ አግናጥዮስ ድርሳናት ላይ ጥናት ያደረጉ ዘመናዊ የነገረ አበው ሊቃውንት እንደገለጹት ክርስቶስ ከጊዜ በፊት የነበረ ዘላለማዊ መሆኑን የሚያመለክተውን የቅዱሱን ቃል «ወልድ ከአብ የወጣ» እንደሆነ የሚገልጸውን አንቀጽ ስናነብ ግምት ውስጥ ልናስገባው ይገባል። [5]

በዚህም ቅዱስ አግናጥዮስ ወልድ ከአብ የተወለደ ነው ብሎ ቢያምንም ክርስቶስ ዘላለማዊ መሆኑን መግለጹ ይህ ልደት ዘላለማዊ ልደት እንደሆነ አማላካች ነው [6]። ይህ አመክንዮ /ሎቱ ስብሐት/ ወልድ ፍጡር ነው የሚለው አስተምህሮ ለአግናጥዮስ እንግዳ እንደሆነ ከማሳየቱ በላይ በክርስቶስ ዘላለማዊነት ዙሪያ ከቅዱስ አትናቴዎስ ጋር የተስማማ አስተምህሮ እንዳለው ያመለክታል።

ይቀጥላል ...

             አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

         ✍ በዲ/ን ዘአትናቴዎስ የተጻፈ

https://t.me/ZeathanAmharic

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

1). Epistle To Symrnaeans , 1

2). Epistle To Magnesians , 6

3). Epistle To Polycarp , 6

4). Epistle To Magnesian , 7

5). “ ... Since Ignatius has already  told us that Jesus Christ was “with the Father before the ages” (6:1), we bring that information with us when we read the subsequent statements about Jesus Christ’s coming forth from the Father (7:2) or the  Word’s coming forth from silence (8:2) ... ” Learning Christ : Ignatius of Antioch & The Mystery Of Redemption By Gregory Vall , pp. 270

6). “As the only son, he not only came forth from the one father ; he also remained with the one and returned to the one.This was an eternal coming forth , for the son was ‘before all ages with the father and appeared at the end time.”
The Apostolic Christology of Ignatius of Antioch : The Road to Chalcedon By Thomas G.Weinandy , pp.75


ለዚህም ይመስላል ቅዱስ ሄሬኔዎስ በእንተ ስብከተ ሐዋርያት 5 ላይ “ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።”(ኤፌ 4:6) የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ ቃል በመጥቀስ ለሦስቱም አካላት አውሎ አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ መሆናቸውን የገለጸው [6] ፤ እንዲህ ሲል :-

“የእርሱ ሐዋርያ ጳውሎስም ' ከሁሉ በላይ የሆነ በሁሉም የሚሠራ ፣ በሁሉም የሚኖር የሁሉም አባት አንድ አምላክ አለ’ ሲል ተናገረ። ከሁሉ በላይ አብ ነው ፣ በሁሉም የሚሠራ ደግሞ ወልድ ነው አብ በእርሱ ሁሉን ነገር ፈጥሯልና እንዲሁም በሁሉ የሚኖር አባ እያለ የሚጮኸው ፣ ሰውንም በአምላክ መልክ የሰራው መንፈስ ነው።”

በመጨረሻም ከላይ በሰፊው እንደዳሰስነው ቅዱስ ሄሬናዎስ ዘኤዶም አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ ያልተፈጠረ እና ዘላለማዊ የሆነ መለኮታዊ ባሕርይ አላቸው ብሎ እያመነ ፣ እንዲሁም ሦስቱም አካላት አንድ አምላክ ናቸው ብሎ እየመሰከረ እንዴት ከኒቂያ ጉባኤ ጋር የተስማማ ነገረ ሥላሴ አላስተማረም ማለት እንችላለን ? የሚለውን ጥያቄ ለህሊና ትቼ ለአሁን ጽሑፌን እዚህ ጋር እቋጫለሁ።

ይቀጥላል ...


            አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና !

         ✍ በዲ/ን ዘአትናቴዎስ የተጻፈ

https://t.me/ZeathanAmharic


🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

1). Early Christian Doctrines by J.N.D Kelly , pp.104

2). Irenaeus On The Trinity by Jackson Lashier , pp.205

3). Irenaeus of Lyons and the theology of the holy spirit by Anthony Briggman , pp.38-41

4). Against Heresies 2.25.3

5). Against Heresies 5.12.2

6). Irenaeus’s Trinitarian Theology by Michel René Barnes , pp.98


ነገረ ሥላሴ በቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘኤዶም ድርሳናት (ክፍል 1)

በክርስቶስ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው።

በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደተ ክርስቶስ ከግኖስቲክ መናፍቃን ጋር አንገት ለአንገት በመተናነቅ የሐሰት ትምህርታቸውን ያጋለጡ ፣ የክርስትና እውነትነት የገለጡ አበው ሲወሱ ስሙ ቀድሞ ይነሳል - የፓሊካርፐስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘኤዶም።

የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ዐቃቤ እምነት ፣ የክርስቶስ ሙሽራ ሰማዕት የሆነው ቅዱስ ሄሬኔዎስ በዘመናዊ የነገረ አበው ጥናት የእርሱ መሆናቸው የታመኑ ሁለት ድርሳናት ያሉት ሲሆን እነርሱም “በእንተ መናፍቃን - Against Heresies” እና “On The Apostolic Preaching - በእንተ ስብከተ ሐዋርያት” ይሰኛሉ።

ቅዱሱ ለነበረበት ዘመን ተስማሚ የሆኑ የነገረ መለኮት እና የፍልስፍና ቃላትን በመጠቀም ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሥላሴን አስተምሮ ያለፈ ቢሆንም ተንባላት እና ነጠላ አሃዳዊ መናፍቃን የሥላሴ አስተምህሮ ከኒቂያ ጉባኤ በፊት አይታወቅም ፣ ቅድመ ኒቂያ የሚገኙ አበውም አላስተማሩትም የሚለው ቅጥፈታቸው በአጥንቱ እንዳይቀር ከቅዱስ ሄሬኔዎስ ጽሑፎች በመጥቀስ ሥጋ ለማልበስ ይሞክራሉ።

ስለሆነም በዚህ በክፍል በክፍል በምጽፈው መጣጥፍ በሙሐመዳውያን ለሚቀርቡ ሙግቶች ምላሽ  ከመስጠት ይልቅ ቅዱሱ በዘመኑ የሚገኙ የሥነ መለኮት ቃላት እና ሀረጋትን በመጠቀም ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሥላሴን ለማስተማሩ አዎንታዊ ማስረጃ የማቀርብ ይሆናል - መልካም ንባብ !

የቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘኤዶም ድርሳናትን ያጠኑ ሊቃውንት እንዳመለከቱት ቅዱሱ ስለ አምላክ የጻፈው ከሁለት መንገድ ወይንም ከሁለት አቅጣጫ በመነሳት ነው ፤ የመጀመሪያው ከአምላክ በራሱ (Trinity ad intra - God in Himself) አንጻር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አምላክ ከፍጥረቱ ጋር ካለው ግንኙነት ወይንም ውጫዊ/አፍአዊ ግብር አንጻር ነው።[1]

በዚህም ስለ ቅዱስ ሄሬኔዎስ የነገረ ሥላሴ አስተምህሮ ለማጥናት ስንነሳ ሁሉቱን መንገዶች ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነውና ቅዱሱ ስለ ቅድስት ሥላሴ ያሰፈረውን  “አንድም ሦስትም የሆነው አምላክ በራሱ - The Triune God in himself” እና “ቅድስት ሥላሴ ከአፍአዊ ግብር ጋር በተገናኘ - The Triune God in Relation to The Economy” በማለት ለሁለት ከፍለን የምንመለከት ይሆናል።[2]

አንድም ሦስትም የሆነው አምላክ በራሱ

የቅዱስ ሄሬኔዎስ ጽሑፎች ላይ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት በቅዱሱ እሳቤ ውስጥ የ «ፈጣሪ - ፍጥረት ክፍፍል» በጉልህ እንደሚስተዋል አመልክተዋል [3]፤ ማለትም ለሄሬኔዎስ ሁለት ምድብ (Category) ያለ ሲሆን ይኸውም አንደኛው የፈጣሪ ሌላኛው ደግሞ የፍጥረት ነው።

ቅዱሱ ለዚህ ክፍፍል መነሻ እና መድረሻ አድርጎ የሚያቀርበው ፍጡር የሚያድግ ፣ የሚጨምር እና የሚጎለብት ሲሆን ፈጣሪ ግን ማደግ የማያሻው ፍጹም መሆኑን ነው። ለአብነት ያህል በበእንተ መናፍቃን 4.11.2 ላይ የጻፈውን እንመልከት  :-

“በተጨማሪም አምላክ በዚህ ከሰዎች ይለያል፣ ይህም አምላክ ፈጣሬ ሲሆን ሰው ግን የተፈጠረ ነው። የሚፈጥረው ሁልጊዜ አንድ ነው የተፈጠረው ግን መጀመሪያ እና መካከለኝነትን ፣ ማደግ እና መጎለበትን ሊቀበል ይገባዋል። ዳግመኛም አምላክ ጥቅምን ይሰጣል ሰው ጥቅምን ይቀበላል። አምላክ በሁሉ ነገር ፍጹም ሲሆን ከራሱ ጋርም የተካከለ እና አንድ ነው ... ሰው ግን ወደ አምላክ ዘንድ ያድጋል ፣ መጨመርንም ይቀበላል።”

ታዲያ በዚህ የ «ፈጣሪ - ፍጥረት ክፍፍል» ውስጥ ቅዱስ ሄሬናዎስ ዘኤዶም ወልድ እና መንፈስ ቅዱስን /ሎቱ ስብሐት/ እም አልቦ ከተፈጠሩ ፍጥረታት ዘንድ ሳይሆን ዘላለማዊ እና ያልተፈጠረ ከሆነው ከአብ ዘንድ በማኖር እነርሱም ዘላለማዊ እና ያልተፈጠሩ መሆናቸውን መስክሯል።

“ማንም ቢሆን እነዚህ ለምርምር መንስኤ የሆኑ ነገሮችን መገኛ ካላወቀ ፣ ሰው ከአምላክ ያለ ገደብ እንደሚያንስ ይመስክር ፤ ይህም ጸጋን በከፊል የተቀበለ እና ከፈጠረው ጋር ተመሳሳይ ወይንም ዕኩል ያልሆነ መሆኑ ነው። በተጨማሪም እንደ አምላክ ያሉ ነገሮችን ሁሉ ልምድ ሊኖረው ወይንም እሳቤ ሊፈጥር አይችልም። ሆኖም በተመሳሳይ የተፈጠረው እና የፍጡረነትን ጅማሮ የተቀበለው ያልተፈጠረ እና ሁልጊዜ አንድ ከሆነው ከእርሱ ያንሳል ፤ በዚህም በዕወቅትና የነገሮችን መነሻ በመመርመር ከፈጠረው ከእርሱ ያንሳል - አንተ ሰው ሆይ ያልተፈጠርክ አይደለክምና እንደ ቃሉም ሁልጊዜ ከአምላክ ጋር አብረህ አልኖርክምና።” [4]

“ነገር ግን እስትንፋስ በፍጥረት ሁሉ ዘንድ ያለ እና የተፈጠረ ነገር መሆኑን አሳይቷል። የተፈጠረ ነገር ከፈጠረው የተለየ ነው ፣ በዚህም እስትንፋስ ጊዜያዊ ሲሆን መንፈስ ግን ዘላለማዊ ነው።” [5]

ቅዱሱ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከሥነ ፍጥረት ተለይተው እንደ አብ ያልተፈጠሩ እና ዘላለማዊ መሆናቸውን መግለጹ ሦስቱም አካላት አንድ ያልተፈጠረ እና ዘላለማዊ የሆነ መለኮታዊ ባሕርይ አላቸው ብሎ እንደሚያምን ያመለክታል ፤ ለዚህም ነው ሄሬኔዎስ አምላክ (Θεός , Deus) በሚለው ቃል እግዚአብሔር አብን ብቻ ሳይሆን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስንም ደጋግሞ መጥራቱ።

ለምሳሌ በበእንተ መናፍቃን 3.8.3 ላይ በ «ፈጣሪ - ፍጥረት ክፍፍል» እሳቤው በተቃኘ አገላለጽ ከፍጥረት ተለየተው አብ እና ወልድ በሚገባ አምላክ እና ጌታ ተብለው እንደሚጠሩ አመልክቷል ፤ እንዲህ ሲል :-

“ነገር ግን ማንኛውም ጅማሮ ያላቸው እና ሊፈርሱ የሚችሉ ፣ ለፈጠራቸው የሚገዙ እና በእርሱ ላይ የተንተራሱ ነገሮች ሁሉ - መጠነኛ የሆነ ነገሮችን የመለየት ዕውቀት ባላቸው ዘንድ እንኳ - በሁሉም ረገድ በተለየ ስም ሊጠሩ ይገባል ፤ በዚህም ሁሉን ነገር የፈጠረው እርሱ ብቻውን ከቃሉ ጋር አብሮ በሚገባ አምላክ እና ጌታ ተብሎ ይጠራል።”

ዳግመኛም በእንተ መናፍቃን 4.38.3 ላይ የሰው ልጅ ባልተፈጠረው አምላክ መልክ እና አርዓያ እንደተፈጠረ በመግለጽ ሦስቱም አካላት ያልተፈጠረ አምላክ መሆናቸውን ፍንትው እና ቁልጭ አድርጎ አመልክቷል።

“የተፈጠረ እና የተዋቀረ የሆነው ሰው የተፈጠረው ባልተፈጠረው አምላክ - ሁሉን በሚገባ አቅዶ ትዕዛዝን በሰጠው በአብ ፣ እነዚህን በፈጸመውና የመፍጠር ሥራን በሰራው በወልድ እንዲሁም የተፈጠረውን በሚያሳድገውና በሚያጎለብተው በመንፈስ - መልክ እና አርአያ ነው። ነገር ግን ሰው ቀን በቀን እያደገ ወደ ፍጽምና ከፍ ይላል ይህም ወዳልተፈጠረው መቅረብ ነው፤ ያልተፈጠረው ፍጹም ነውና እርሱም አምላክ ነው።

ቅዱስ ሄሬኔዎስ የሰው ልጅ ባልተፈጠረው አምላክ መልክ እና አርአያ እንደተፈጠረ ሲገለጽ አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስን ማንሳቱ ለእርሱ ያልተፈጠረው አምላክ አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ይህም አብ ብቻ ሳይሆን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስም ያልተፈጠረ እና ዘላለማዊ የሆነ መለኮታዊ ባሕርይ እንዳላቸውና በዚህም ከአብ ጋር አንድ አምላክ እንደሆኑ የሚያመለክት ነው።


ዌብሳይታችን በኢዲስ መልክ ስራ ጀምራለች 😁😁 ከዚህ በኋላ መጣጥፍ ምንለቀው እዚህ ላይ ብቻ ነው ፣ ስለዚህ አንብቡ አጋሩ አስነብቡ ...

https://www.sonsofathanasius.com/index.php/site/article_detail/11

2.6k 1 31 10 21
Показано 20 последних публикаций.

1 109

подписчиков
Статистика канала