Goqa-ጎቃ (Ethio-news)


Гео и язык канала: не указан, Английский
Категория: не указана


All about Ethiopia!!!
ሁሌም ስለ ኢትዮጵያ እንዲሁም አለም-አቀፍ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበረሰባዊ ዜና ከትንተና ጋር።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, Английский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


#በሰሜን ጎጃም በድሮን ጥቃት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ

⚡️በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።

⚡️ጥቃቱ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ከወረዳው ዋና ከተማ ዱርቤቴ 40 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አርጌ (ዝብስት) በተባለች ታዳጊ ከተማ በተከታታይ ሦስት ጊዜ መፈጸሙን እማኞች እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።

‼️ጠዋት 1፡10 አካባቢ በከተማዋ ገበያ አካባቢ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ጤና ጣቢያ ላይ ጥቃቱ እንደተፈጸመ እማኝነታቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ “ከልጅ እስከ አዋቂ ያለቀበት” ነው ብለውታል።

Join us

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0




#Update

የ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት መመለስ እና የመጀመሪያ የቤት ስራቸው

⚡️ሚድል ኢስት ላይ; የእስሬእሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የእንኳን ደስ አሎት ምልክታቸውን መላካቸውን የድሮ ጠንከር ያለ ግንኙነታቸውን ከማደስ ባሻገር ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ተነጋግረዋል:: ታዲያ ይህ ልክ እንደነ ኢራን ላሉ ሃገራት ስጋታቸውን እየገለፁ ነው በአሜሪካ እስራኤል ላይ ባላት ምልከታ ማለት ነው:: ሃማስ ራሱ ይህ ለፍልስጤማዊያን ስጋት ነው ብሏል::

⚡️ራሺያ ና ዩክሬን; በትራምፕ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሰረት በራሺያ ላይ የጣልቃ ገብነትን ሳይሆን ለዩክሬን የሚሰጣትን እርዳታ ላይ ማቆምን ይከተላል ምንአልባትም ይህን አካሄድ ኮንግረሱ እስካልተቃወመ ድረስ:: የ Putin አጋር በመሆን የሚታወቀው #ዲሜትሪ ሜድቪድቭ እንዳስታወቀው የትራምፕ የቢዝነስ መር አስተሳሰብ ለራሺያ ይጠቅማል ሲል የዩክሬኑ መሪ ቭላድሚር ዜለንስኪ በበኩሉ ትራምፕ ለአለም ሰላም ሲባል ወራሪውን የራሺያን ሃይል መዋጋትን ማስቀጠል አለበት ብላል:: ትራምፕ በበኩሉ ነጩ ቤተመንግሥት በገባው በመጀመሪያው ቀን ጦርነቱን አስቆመዋለው ማለቱ አይረሳም::

⚡️ቻይናም የትራምፕ አልገምትም ባይነት በታይዋን ጉዳይ ላይ ስጋት ይፈጥርባታል ለዚህም ቤጂንግ ለመጪው ችግሮች ራሷን ያዘጋጀች
ትራምፕ ታይዋን ለአሜሪካ የደህንነት ዋስትና ክፍያ የመክፈል ግዴታ አልባት ሲል መናገሩ ይታወሳል አሁንም ይህን ነገር ያጠናክረዋል ሲሉ የውጭ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ

⚡️ስደተኞችን በተመለከተ ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆኖ በተመረጡበት እለት ከተናገረው መረዳት እንደሚቻለው በቅርቡ ብዙ ሚሊየን ህገወጥ ስደተኞችን ወደሃገራቸው እንመልሳለን ሲል ተናግሯል:: ታዲያ በቅርቡ mass deportation የሚያካሂድ መሆኑን ተናግሯል::

ለበለጠ መረጃ ይቀላቀሉን
@Goqaeth


#Update

ኔታንያሁ ጋላንትን ማባረሩ በሙሉ #እስራኤል ሰላማዊ ሰልፎችን አስነሳ!!!

⚡️"#እስራኤል አንድ አንድ ሃሳቦች ላይ ለመደራደር ፍቃደኛ አስከሆነች ድረስ ታጋቾችን ማስመለስ ይቻላል" የሚለው ጋላንት የጦርነቱን ማብቂያ ለናፈቁ #እስራኤላውያን የተስፋ ድምፅ ሆኖ ቆይቷል።

⚡️በዚህም ምክንያት መባረሩ ብዙሃኑን ያስቆጣ ውሳኔ ሲሆን ህዝቡ የጋላንትን መመለስ ከመጠየቅ አልፎ ኔታንያሁ ስልጣኑን አንዲለቅ አየጠየቀ ይገኛል::

⚡️ኔታንያሁ ለጋላንት መባረር አንደምክንያት ያቀረበው በመሪዎቹ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲ የተፈጠረው አለመተማመን ሲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በጦርነት ወቅት በመሪዎች መካከል መተማመን አንደሚያስፈልግም ተናግሯል ::

#እስራኤል #ጋላንት #ፖለስታይን #ኔታንያሁ

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#Update

ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቷን የጦር ሚንስቴር ዮአቭ ጋላንትን ከስራ አባረረ!!!

⚡️ከድሮም ቢሆን እምብዛም ያልነበሩት ሁለቱ መሪዎች የነበራቸው ሸካራ ግንኙነት በስተመጨረሻ አብቅቷል። ቤንያሚን አና ጋላንት ከሚለያዩበት ነጥቦች መሃል ዋነኛው ቤንያሚን የሃማስ መደምሰስ ላይ ሲያተኩር ጋላንት ደግሞ በቅድምያ የታጋቾቹ መመለስ ላይ መሰራት አለበት ብሎ ያምናል።

⚡️በተጨማሪም ጋላንት #እስራኤል በመስከረም 27ቱ ለደረሰባት ጥቃት ያን ያህል ተጋላጭ ያደርጋት የመረጃ፣ የወታደር አንዲሁም የጥበቃ ድክመት ላይ ምርመራ ይካሄድ ሲል ቤንያሚን ግን አሁን ለዛ ጊዜው አይደለም ይላል።

⚡️ከዚህ በፊትም በየካቲት 2016 ከሥራው ተባሮ የነበረው ዮአቭ ጋላንት የእስራኤል ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ወደ ስልጣኑ ይመለስ ባለው መሰረት መመለሱ ይታወሳል።

#እስራኤል #ፖለስታይን #ኔታንያሁ
https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#update

ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ አህመድ ለአሜሪካው 47ኛ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አሎት መልክታቸውን አስተላልፈዋል

⚡️የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ጄ ትራምፕ በሰፊ ልዩነት ተቀናቃኙን ካማላ ሀሪስን ከረቱ ቡሃላ ከመላው አለም የእንካን ደስ አሎት መልክት አየተበረከተላቸው ይገኛል

⚡️በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ከነ ባለቤታቸው እንኳን ደስ አሎት ምልክታቸውን ልከዋል

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#Update

አሸናፊው ዶንልድ ትራምፕ አሁን ላይ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንታዊ ንግግራቸውን እያደረጉ ነው!!!

ተፎካካሪው የነበረችው ካምላ ሀሪስ እስካሁን ድረስ  ስለደረሰባት ሽንፈት ሆነም ስለአዱሱ ፕሬዝዳንት ምንም አልተናገረችም።

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#update

ዶናልድ ትራምፕ ዊስኮነስን ላይ በማሸነፋቸው ከ270 ድምፅ በላይ ማለፋቸው ተረጋግጧል::

⚡️ዶናልድ ትራምፕ 2016 ዙር ምርጫ በማሸነፍ ለ4 አመት ማገልገላቸው ይታወሳል ቢሆንም በ 2020 ላይ በ ጆይ ባይደን ተሸንፈው ከነጩ ቤተ መንግሥት መባባረራቻው ይታወሳል ይህው ዛሬ ከ 4 አመታት ቆይታ ቡሃላ የዴሞክራቷ እጩ ካማላ በማሸነፍ የፕለቲካ come back አድርጓል ይህም በታሪክ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት በመሆን በ አሜሪካ ታሪክ ላይ መስፈር ችለዋል::

⚡️በተጨማሪም የኤል ሳልቫዶሩ መሪ የእንኳን አደረሶት መልክት በመላክ የመጀመሪያው መሆን ችለዋል

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#Update

47ተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ መሆናቸው ተረጋግጧል!!!

ምርጫውን ከሚያስፈልገዉ 270 ድምጾች 267ቱን በማግኘት አሸንፏል!!!!

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


ዶናልድ ጄ ትራምፕ 47 ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን በfox news ተረጋግጧል ከተከታያቸው ካማላ ሀሪስ በሰፊ ርቅት ሲመሩ የነበሩት የሪፐብሊካኑ እጩ ትራምፕ አሁን ላይ ለሁለትኛ ጊዜ አሜሪካን እንደሚመሩ ተረጋግጧል

መረጃው የ fox news ነው

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


ነገሮች እያበቁ ይመስላሉ ሪፐብሊካን እጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ 247 ለ 210 እየመሩ ሲሆን አስፈላጊ በሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በከፍተኛ ብልጫ እየመሩ ነው

ሼር አድርጉት ይቀላቀላሉን

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


ትራምፕ የጆርጂያ የፔንስልቬኒያና የዊስኮሰን ድምፅ ካገኙ ያሸንፋሉ በሶስቱም ግዛት እየመሩ ነው

የጆርጂያ አሁናዊ ውጤት

ትራምፕ 98%
ሀሪስ 2%

የፔንስልቬኒያና አሁናዊ ውጤት

ትራምፕ 96%
ሀሪስ 4%

የዊስኮሰን አሁናዊ ውጤት

ትራምፕ 94%
ሀሪስ 6%

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


የአለምን ሁሉ ቀልብ የሳበው 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሁናዊ ውጤት

ትራምፕ 230
ሀሪስ 205

ትራምፕ የጆርጂያ የፔንስልቬኒያና የዊስኮሰን ድምፅ ካገኙ ያሸንፋሉ በሶስቱም ግዛት እየመሩ ነው

የሁነቱን እያንዳንዱ መረጃዎች ይከታተሉ 👇👇

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


በዛሬው እለት በሚልዬኖች የሚቆጠሩ #አሜሪካውያን የሚመርጧቸ አጬዎች ማን ናቸው??!!

⚡️የዴሞክራቶቹ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሀሪስ #ከጃሜካዊ አባቷ እና #ህነዳዊ እናቷ ኦክላንድ ውስጥ ስትወለድ የፖለቲካ ሙያዎን የጀመረችው የሳን ፍራንሲስኮ አቃቢ ህግ ከዛም ደግሞ #የካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ አቃቢ ህግ በመሆን ነው። ሀሪስ ለምርጫው መወዳደር የጀመረችው ጆ ባይደን እራሱን ከውድድሩ ሲያገል እሱን በመተካት ነው።

⚡️በዚህ ምርጫ የሀሪስ ጠነካራ ነጥብ "Roe vs Wade" ን ማስመለስ ከመሄኑ አንፃር የአብዛኛው ሴቶች ድምፅ ወደ እሷ እንደሚሄድ ይገመታል።

⚡️የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ የሪፖብሊካኖቹ እጬ ሲሆን #ኒውዬርክ ተወልዶ ያደገ የኢኮኖሚክስ ምሩቅ ነው። ትራምፕ "The Apprentice" በተባለው የራሱ የሪያሊቲ ፊልም ተዋናይ እና የሪልስቴት ባለቤት ነው። ትራምፕ ለምርጫ ሲወዳደር ይህ ሶስተኛው ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያውን 2016 ምርጫ አሸንፎ ለአራት አመት ከመራ ቡኋላ በሁለተኛው የ2020 ምርጫ በጆ ባይደን ተሸንፏል።

⚡️በዚህ ምርጫ የትራምፕ ጠንካራ ነጥብ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አስተካክላለሁ ማለቱ ነው።

እርሶስ ምርጫውን ማን የሚያሸንፍ ይመስሎታል?

#ምርጫ2024  #አሜሪካ

ተቀላቀሉን!! ሼር አድርጉት!!
https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#የአሜሪካን ምርጫ ፖሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለዶናልድ ትራምፕ እያደሉ መሆናቸው ተነገረ!

⚡️ነገ መሪዎቻቸውን በይፋ የሚመርጡት አሜሪካውያን የቅድመ ምርጫ ፖሎች ትራምፕ በጥቂት ነጥቦች መብለጡን እያሳዩ መሆናቸውን ሚዲያዎች ያሳያሉ
ካማላ ሀሪስ በሚሺጋን ትኩረቷን ስታረግ ትራምፕ ደግሞ ባንፃሩ ፔንሲልቬንያ ኖርዝ ካሮሊና እና ጆርጂያ ላይ አተኩሯል

⚡️አንገት ላንገት ትንቅንቅ በታየበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የትራምፕ ማሸነፍ የማይቀር ቢመስልም የካማላ አልገመት ባይነት ነገሩን ለመገመት አዳግቶታል

እርሶስ ማን የሚያሸንፍ ይመስሎታል

#ምርጫ2024 #አሜሪካ
ተቀላቀሉን ሼር አድርጉት

https://t.me/+b9wXeMwslWU3MTU0


#Update

ዶናልድ ትራምፕ እና ካምላ ሀሪስ በወሳኝ ግዛቶች የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ነው

⚡️በትራምፕ እና ካምላ መካከል ያለው እጅግ ተቀራራቢ የሆነው የድምፅ ልዩነት አሁን ላይ ካምላ ሀሪስን በ0.9% ብልጫ አስቀምጧታል። አሁን ላይ ሁለቱም እጭዎች የመዝጊያ ንግግራቸውን እንደ ፔንስልቬንያ፣ ሚሽጋን እና ኖርዝ ካሮላይና ያሉ ቁልፍ ግዛቶች ላይ እያደረጉ ነው።

⚡️የምርጫ ጣቢያዋች ነገ ማታ የሚዘጉ ቢሆንም እንዲህ አይነት ተቀራራቢ የድምፅ ልዩነት ሲኖር የድምፅ ቆጠራው ተጨማሪ ቀናትን ሊወስድ ይችላል።

#አሜሪካ #ምርጫ

@Goqaeth



Показано 17 последних публикаций.