⛔️~ ዑዝር ቢል'ጀህል ~(ክፍል 2)
በትልቁ ሽርክ ላይ ባለማወቅ ዑዝር አይሰጥም የሚሉ አካሎች በብዛት የሸይኽ ፈውዛንን አንዳንድ አሻሚ የሆኑ የድምፅ ሪከርዶችን ሲያራግቡ እናያለን።
እነዚህ ሰዎች ከዚህም በማለፍ ዑዝር አለ የሚሉትን በኢርጃእ እንደዚሁም ከሑጃ በኋላ ደግሞ በኩፍር የገለፃሉ ይላሉ።
ይህንን ቅንጣት ያማያሻማ የሸይኽ ፈውዛንን ንግግር ሲሰሙ እሳቸውንም ሙርጅእ እና ካፊር ይሉ ይሆን !? ወይስ የነሱ ቃዒዳ የሚሰራው አንዳንድ አካሎች ላይ ብቻ ይሆን !?
🔖 سؤل الشيخ -حفظه الله-
📌السؤال : أحسن الله إليكم صاحب الفضيلة، ما الفرق بين الوصف بالكفر والحكم على المعين بالكفر والاعتقاد بكفر المعين؟
📌جواب الشيخ -حفظه الله : أما الحكم بالكفر على الأعمال، كدعاء غير الله، والذبح لغير الله، والاستغاثة بغير الله، والاستهزاء بالدين، وسبة الدين،
هذا كفر بالإجماع بلا شك، لكن الشخص الذى يصدر منه هذا، هذا يتأمل فيه، فإن كان جاهلا أو أو متأولا أو مقلدا
فيدرأ عنه الكفر حتى يبين له، فيبين له الحق، لأنه عنده شبهة، أو عنده جهل، أو عنده ...، ما يتسرع بإطلاق الكفر عليه،
حتى تقام عليه الحجة، فإذا أقيمت عليه الحجة واستمر على ما هو عليه يحكم عليه بالكفر، لأنه ليس له عذر، نعم،"
ሸይኹ ተጠየቁ ፦
ጥያቄ ፦ "እንዲሁ በክህደት ከመግለፅ እና በተለየ አካል ላይ በክህደት ከመፍረድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው"?
መልስ ፦ {{ በተግባሮች ላይ የሚሰጥ ፍርድ ለምሳሌ ከአሏህ ዉጭ መጣራት ፤ ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ማረድ ፤ በጭንቅ ጊዜ ከአሏህ ውጭ ካለ አካል እርዳታን መጠየቅ ፤ በሀይማኖት ማላገጥ እና ሀይማኖትን መስደብ ይህ ያለምንም ጥርጥር እና በኡለማዎች
ስምምነት ክህደት ነው።
ነገር ግን ይህ ተግባር የተገኘበት ሰው ሁኔታው ይታያል።
አላዋቂ (ጃሂል) ፤ ባጢሉ ሐቅ የመሰለው (ሙአዊል) ወይም ጭፍን ተከታይ (ሙቀሊድ) ከሆነ እስኪብራራለት እና ሐቁ እስኪገለፅለት ድረስ ክህደት ከእርሱ ይራቃል (ካፊር ተብሎ አይፈረድበትም)። ሐቅ ይብራራለታል። ምክኒያቱም እርሱ ዘንድ ብዥታ ወይም
መሀይምነት አለና።
ሑጃ (ማስረጃ) እስኪቆምበት ድረስ ክህደትን በዚህ አካል ላይ በማስፈር አይቻኮሉበትም። ማስረጃ ተቁሞበት ግን በዛው ክህደት ላይ ከዘወተረ በክህደት ይፈረድበታል። ምክኒያቱም
ዑዝር የለውምና።}}
https://t.me/AbU_ImRan_AlaSeriy