#حديث عبد الله بن عمرو بن العاص رضي عنهما أن رسولﷺ قال له "أحب الصلاة إلي الله صلاة داود عليه السلام وأحب الصيام إلي الله صيام داود وكان ينام نصف الليل ويقوم ثلثه وينام سدسه ويصوم يوم ويفطر يوم"
➛ከአብዷላህ ኢብኑ አምር የተነሳው ሐዲስ የአለህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲ ኣሉት "ከሷላት ወደ አሏህ ይበልጥ የሚወደደው የዳዉድ ሷላት ነው።
ከፆምም ወደ አለህ ይበልጥ የተወደደው የዳዉድ ፆም ነው።
ግማሽ ለሊት ይተኛ ነበር ኣንድ ሶስተኛውን ይሰግድና ኣንድ ስድስተኛውን ይተኛ ነበር፤ ኣንድ ቀን ፆሞ ኣንድ ቀን ያፈጥር ነበር"
➣የአሰጋገዱን ሁኔታ ወደ ሰዓት ስናመጣው፦
ለሊቱ 12, ሳዓት ነው
የ12, ግማሽ 6 (12÷2=6) ስድስት ሰዓት ድረስ ይተኛል።
ኣንድ ሶስተኛውን ይሰግዳል
12÷3=4
አራት ሰዓት ይሰግዳል።
ስድስት ሰዓት ይተኛል አራት ሰዓት ይሰግዳል ስድስትና አራት አስር
ኣንድ ስድስተኛውን ይተኛል፦12÷6=2
ሁለት ሰዓት ይተኛል።
እስከ ስድስት ሰዓት ተኛ ከስድስት እስከ አስር ሰዓት ሰገደ ከአስር እስከ አስራ ሁለት አሁንም ተኛ ለሊቱ አበቃ።
(6+4+2=12)
https://t.me/abdulhalimibnushayk