የተወሰኑ ቡድኖች ለቀደር የሚሰጡት ትንታኔ
✅ ቀደርን አስመልክቶ የተለያዩ አንጃዎች ከትክክለኛው መንገድ ባፈነገጠ ሁኔታ የተሳሳቱ ትርጉሞችን ሰጠዋል፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡-
1. ጀህምያ እና ጀብሪያ
እነዚህ ቡድኖች ባሪያው ተገዶ እንጅ በሚሰራው ስራ ምንም ዓይነት ምርጫ፣ ችሎታ፣ እቅድ እና ፍላጎት የለውም ይላሉ፡፡ የሰውን ልጅ ልክ በነፋስ እንደሚወዛወዝ ላባ ወይም ያለፍላጎቱ በነፋስ ሐይል እንደሚንቀሳቀስ የዛፍ ቅጠል ይመስሉታል፡፡ ይህ ከጀህምያ የሆኑ ጀብርያዎችና ሌሎችም የሚሉት ነው፡፡
2. ሙዕተዚላዎች [የጀህምያና የጀብሪያ ተቃራኒ የሆኑ ናቸው]
➧ ማንኛውም ሰው የአላህ ፍላጎት ሳይደበለቅ የራሱን ስራ የመፍጠር ችሎታ አለው ይላሉ፡፡ የባሪያው ስራ ከእራሱ ምርጫና ችሎታ ጋር እንጅ ከአላህ መሽአ ጋር ምንም አይነት ቁርኝት የለውም ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ወሰን በማለፍ ፡ አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ነገሮች ከተከሰቱ በኋላ እንጅ ቀድሞ አያውቀውም ይላሉ፡፡ ነገሮችን የሚያውቃቸው ባሪያው አሁን ስራውን እንዳስገኘው ነው ይላሉ፡፡ እነዚህ “አልቀደርየቱ አንኑፋት” በመባል የሚጠሩት የሙዕተዚላ ድንበር አላፊዎቸ ናቸው፡፡
↪️ የመጀመሪያው ቡድን ጀብሪያ ወይም ቀደርያ አንኑፋት በመባል ይጠራል፡፡ ይህ ቡድን ቀደርን ወይም የአላህን ውሳኔ ቢያጸድቁም በቀደር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ ከባሪያው ላይ ኢራዳን ወይም ፍላጎትን ያራቁታሉ፡፡ በዚህ አመለካከት ተቃራኒ ሁለተኛው የሙዕተዚላ ቡድን የአላህን መሽአ እና ኢራዳ ውድቅ በማድረግ የባሪያውን መሽአ በማጽደቅ ላይ ድንበር አልፈዋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ጠማማና ታላቅ ስህተትን የፈጸሙ ናቸው፡፡
✅ አህለሱና ወልጀማዓህ በኢማን፣ በቀደር ያላቸው መካከለኛ አቋም
ተገቢ የሆነ ጥላቻና ውግዘት ለቀደርዮች የአህለሱና ወልጀማዓህ መካከለኛ አቋም
➲ ለባሪያው ችሎታን፣ ምርጫን እና ኢራዳን ያጸድቃሉ፡፡ ይሁን እንጅ የባሪያው መሽአ፣ ችሎታ፣ ምርጫ እና ኢራዳ ለአላህ መሽአ፣ ችሎታ፣ ምርጫ እና ኢራዳ ተከታይ መሆኗን ያምናሉ፡፡ አንድ ሰው በአላህ ኢራዳ እና በእርሱ መሽአ ካልሆነ በቀር ስራን መስራት አይችልም፡፡
ቀደርያ ውግዘትና ጥላቻ ይገባቸዋል
ቀደርያ፡ ከአላህ ጋር ሁለት ፈጣሪዎችን በማረጋገጣቸው የዚህ ኡመት መጁስ በመባል ተጠርተዋል፡፡ እነዚህ ቡድኖች “ሁሉም ሰው ያለአላህ መሽአና ፍላጎት የራሱን ስራ ፈጥሮ መስራት ይችላል” ይላሉ፡፡
➪ በዚህ ታላቅ የኢማን መሰረት - የቀደር እምነት - ላይ ትክክለኛውን ጎዳና በመልቀቃቸውና ነገሮችን በማደባለቃቸው ከሐቅ ባለቤቶች ከፍተኛ የሆነ ውግዘት እና ጥላቻ ደርሶባቸዋል፡፡ በቀደር ማመን ከኢማን መሰረቶች ነው። በቀደር ማመን ከኢማን መሰረቶች አንዱ እንደሆነ በጅብሪል ሐዲስ ላይ ግልጽ ተደርጓል፡፡ ጅብሪል ነብዩን ﷺ ስለኢማን በጠየቃቸው ጊዜ የሚከተለውን ምላሽ ሰጠውታል፡-
"الإيمان أن تؤمن بالله ومالئكته وكتبه ورسله واليوم اآلخر وتؤمن بالقدر خيره
وشره"
“ኢማን በአላህ፣ በመላኢካዎች፣ በመጽሐፎች፣ በመልእክተኞች፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፤ መልካም ይሁን መጥፎ በአላህ ውሳኔ (የሚከናወን መሆኑን) ማመን”
(ቡኻሪ፡ 4499, ሙስሊም፡ 10)
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ
“እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡”
[ሱረት አል-ቀመር - 49]
የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"الحرص على ما ينفعك، واستعن بالله، فإن أصابك شيء فال تقل: لو أني فعلت كذا كان كذا ولكن قل قدر الله وما شاء فعل، فإن لو تفتح عمل الشيطان"
“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አንድ ነገር ከደረሰብህ “በዚህ መልኩ ብሰራው ኖሮ እንዲህ ይሆን ነበር፡፡” አትበል፤ ነገር ግን “አላህ የወሰነውና እርሱ የሻው ሆነ” በል፡፡ “ለው” (ይህ ቢሆን ኖሮ) የምትለው ቃል ለሰይጣን ተግባር (በር) ትከፍታለች፡፡”
ሙስሊም
➡️ በዚህ ዙሪያ የመጡ ግልጽ ሐዲሶች በርካታ ናቸው፡፡ ይህ የታወቀ መሰረት ነው፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው በዚህ ዙሪያ የአህለሱና ወልጀማዓ ዓቂዳ የሆነው ሐቅ በኪታብና በሱና መረጃዎች ተብራርቶ ግልጽ ሆኗል፡፡ ከዚህ መሰረት የተንሻፈፈ ከቁርኣንና ከሱና አፈንግጧል፡፡ መንሻፈፉን ያመጣው ከራሱ ነፍስ ወይም ከስሜቱ በኩል ያመጣው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከቁርኣንና ከሐዲስ መረጃዎች ለማፈንገጥ ሙከራ ያደረገ አካል ሁሉ ከጥፋት ላይ መውደቁ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
[ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 153]
#ጥቅል_የቀደምት_ደጋግ_የአላህ_ባሮች_ዓቂዳ ከሚለው ሪሳላህ የተቀነጨበ
https://t.me/AbuImranAselefy