የቀዳሚው ሙፍቲ'ል ፊትነህ ነገር…—————
ክፍል_② [ከአላማዎቹ በከፊል]
—————
ክፍል አንድን በሚከተለው ሊንክ ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/IbnShifa/23602ኛ, ያለ በቂ እውቀት እራሱን አጉልቶ የማውጣት አላማ!!ይህ ደግሞ "እዩኝ እዩኝ" ማለት "ደብቁኝ ደብቁኝ" ማለትን እንደሚያስከትል አለመገንዘብም ይመስላል።
حبُّ الظهور يقسيم الظهور"ታዋቂነትን መውደድ ወገብን ይሰብራል"ይሁን እንጂ የስልጣን ጥማት ያሳበደው አካል እንዲህ ያለውን ነገር ቆም ብሎ የሚያስተውልበት ጊዜ የለውም።
ይህ እራሱን የማጉላት ተግባሩ ለመጀመሪያው አላማው የሚረዳው አላማ ነው። እንደሚታወቀው ስልጣን ፈላጊና ፖለቲከኛ የሆነ ሰው ከመሬት ተነስቶ አይደለም ወንበር ላይ የሚቀመጠውና ፈላጭ ቆራጭ፣ አዛዥ ነዛዥ የሚሆነው። ሰዎች ዘንድ በተለያየ መንገድ እውቅና ካተረፈ በኋላ ነውና ለዚህ አላማው ደግሞ አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም ብቅ ብቅ እያለ እራሱን መልካም አሳቢ በማስመሰል ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል። ያው ሰይጣንም እራሱን መልካም አሳቢ በማስመሰል አይደል አባታችንን አደምንና ባለ ቤቱን ያሳሳታቸው።
በተለያዩ አጋጣሚዎች ያለ አቅሙ ከመሻይኾች በፊት ቀደም ቀደም በማለት የተሳሳተ የእራሱን ብይን በመስጠት ጎልቶ መውጣት ይፈልጋል!።
በዚህም "
ወላእ እና በራእን" ይመሰርትበታል። ያለ በቂ እውቀት ብይን ከመስጠቱ ባሻገር ሌላው ከባዱ አደጋ ይህ "
ወላእ እና በራእን" መመስረቱ ነው።
የሰጠውን ብይን ትክክል እንዳልሆነ በመጥቀስ የሚኮንን እና እንዲታረም የሚጠይቅን አካል በሰለፊያ ጀመዓ ላይ ልክ እንደ አጥፊና ከሌሎች የጥመት ቡድኖች ጋር ስውር ትስስር እንዳለው አድርጎ በማቅረብ ከዙሪያው ያሉ ሰለፊይ ወንድሞችና ዱዓቶች በጥርጣሬ ዓይን እንዲመለከቱት የተለያዩ ውኃ የማይቋጥሩ አቃቂሮችን አጋኖ ለማሳየት እየሞከረ እንዲጠነቀቁት ያደርጋል። ከተሳካለትም ከሠለፊያ ጎዳና ውጪ እንዲደረግና ከጥመት ቡድኖች ነው ተብሎ እንዲፈረጅለት ያለ የሌለ አቅሙን ሁሉ ይጠቀማል። ይህ ሌላኛው በሰለፊያው ጀመዓ ውስጥ በተለያየ መንገድ ሊያባላና ብሎም ጀመዓውን ሊበታትን ዘርግቶት የነበረው የከሸፈው የፊትናው ሙፍቲ ሰንሰለት ነው።
ይህን ሴራውን ብዙ የጥመት ቡድኖች በተለይ ሙመይዓዎች፣ ኢኽዋኖች፣ ሙመይዐቱል ጁደድና ሀዳዲያዎች… "ተግባራዊ ይደረጋል፣ ይሳካለታል" ብለው በጉጉት ጠብቀውት የነበረ፣ ነገር ግን በአላህ ጥበብ ከዚያም በተለያዩ በሳል በሆኑ መሻይኾችና ሴረኛውን ሴራውን በማክሸፍ ረገድ አጥፈውት መሄድ በሚችሉ ወንድሞች የረቀቀ አካሄድ ሊከሽፍ ችሏል። ይህ ስግብግብ ጥማተኛ ከያዘው አላማ ውጭ እንዲህ ያለው ነገር ፈፅሞ አያሳስበውም። የተንኮለኞችን ተንኮል መላሽ የሆነው አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا ۞ وَأَكِيدُ كَيْدًا «
እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡» [አጥ-ጧሪቅ 15-16]
:
ሙመይዐቱል ጁዱድ እንደምትቀጥፈው ሰለፊይ መሻይኾች ዘንድ የቃዒዳ ሙስና ቢኖር ኖሮ ይህ ሰው ያለ በቂ ማስረጃና ያለ ጥፋታቸው ንፁህ ሰለፊዮችን ሙብተዲዕ እንዲባሉ ያደረገውን ጥረት በተቀበሉት ነበር። በዚህ ሰው አመካኝነት በሰለፊያው ጀመዓ ላይ ጥላሸት የመቀባት ጥረታችሁና ተስፋችሁም በአላህ ፈቃድ ተሟጦ ማብቂያው ላይ ደርሷል። የሱንና ዑለማዎች ጀርህና ተዕዲል የሚያደርጉት እንዲህ ያሉ ማንነታቸውን ደብቀው፣ የተለያየ አላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በነገሯቸው ነገር ተንተርሰው ሳይሆን አስፈላጊውን ማስረጃና መስፈርት ካሟሉ በኋላና የኸበሩን ትክክለኛነት ካረጋገጡ በኋላ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮማ ገና ዑለማዎች የራሳቸውን ጥናት ሳያደርጉና ብይን ሳይሰጡባቸው በፊት እናንተም ቀደም ብላችሁ (አላማችሁን አላህ ያውቀዋል) በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ የሙብተዲዕነት ብይን እንዲሰጡባቸው ያደረጋችሁት ጉትጎታ በጊዜው በተሳካላችሁ ነበር። ዑለማዎች የራሳቸውን ጥናት ካደረጉና የእናንተው በወቅቱ የተናገራችሁት ኸበር ትክክል ሆኖ ካገኙት በኋላ የተብራራ ጀርህ በማድረግ ከሱንና ያፈነገጡ መሆናቸውን ግልፅ አደረጉ። እናንተ ደግሞ በተቃራኒው ሄዳችሁ ከራሳቸው ተጨመራችሁ። "
ጀርህና ተዕዲል" በቦታውና መስፈርቱን ባሟላ መልኩ ከቀደምቶችም የመጣ፣ ተተኪዎችም የተገበሩት፣ ወደፊትም አይቀሪና የሚቀጥል ነው።
:
ታላቁ ዓሊም ኢማሙ ሸውካኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“
የዚህ ህዝብ ቀደምትና ተተኪዎች፣ የሀዲስ ዘጋቢዎችንም ሆነ በሰዎች ደም፣ ንበረትና ክብር ላይ በሚመሰክሩ አካላት ላይ ጀርህ ማድረግ የሚገባውን ጀርህ ከማድረግ፣ ተዕዲል የሚገባውን ደግሞ ከመዐደል አልተወገዱም። ይህ ባይሆን ኖሮ ንፁህ በሆነችው ሱንና ላይ ውሸታሞች በተጫወቱባት ነበር። መልካሙ ከመጥፎው በተደበላለቀ ነበር፣ ትክክለኛው ከባጢሉ የትኛው እንደሆነ ባልተለየ ነበር፣ ውድቅ የሚደረገው ከሚፀናው ባልተለየ ነበር፣ ደካማው ከጠንካራው ባልተለየ ነበር…፣ ምክንያቱም ውሸታሞች በመልእክተኛው ﷺ ላይ ከመዋሸት አልተወገዱም።” [አል-ፈትሁ ረባኒይ ሚን ፈታዋ አል-ኢማም አሽ-ሸውካኒይ 11/583]
ይህ የኢማሙ ሸውካኒይ ንግግር ምንኛ ያማረና የዚህን ጊዜ የ"
ጀርህና ተዕዲልን" ጉዳይ ተጨባጭ የሚዳስስ ነው። በተለይ በዚህን ጊዜ ሙመይዓዎች የቢድዐ ባለቤቶችን ወገብ የሚሰብረው "
ጀርህና ተዕዲል" መሆኑን ስለሚያውቁ ለማጣጣል የተለያየ እርስ በርሱ የሚገጫጭ ንግግር እየተናገሩ ይዳክራሉ። ሲፈልጉ "ጀርህና ተዕዲል በዚህ ዘመን የለም" ይላሉ፣ ሲላቸው ደግሞ "ጀርህና ተዕዲል እንደ አገሌ አይነት ሰው ነው እንዴ የሚያደርገው?…" ይላሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ "ጀርህና ተዕዲል የሚያደርጉ መሻይኾችን የቃዒዳ ሙስና አለባቸው" በማለት ሊያጣጥሉና ውድቅ ሊያደርጉ ይፍጨረጨራሉ። በቁጭታችሁ ሙቱ! ጀርህና ተዕዲል ቀድሞውኑ የነበረ ወደፊትም የሚቀጥል ዲኑ የሚጠበቅበት አንዱ መሳሪያ ነው።
3ኛ, የእራሱን የሆነ የተለየ ቡድን የመመስረት አላማ!!ከላይ በ2ኛነት የተቀመጠው አላማ ይህን አላማ በእጅጉ ይረደዋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ያለ እውቅና ከመሬት ተነስቶ ቡድን መመስረትም ሆነ ማደራጀት አይችልም። ይህ ቡድን መመስረት ደግሞ ለመጀመሪያው አላማ ትልቁ መሳሪያና መዳረሻም ጭምር ነው። ቡድን ካደራጀ በኋላ ነገሩ አብቅቷል። ለምን ተነካ እያሉ እንደ ውሻ የሚጮሁ ጭፍን ሙሪዶችን መመልመል (ማሰልጠን) ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ይህን ካደረገ በኋላ የሸረሪት ድር ያህል እንኳን ጥንካሬ በሌለው ብዥታው "ሀላሉን ሀራም ነው፣ ሀራሙን ሀላል ነው…" እያለ፣ የተመቸውንና ከአላማው ጋር የሚገጥመውን ምንም ያህል ግድፈት ቢኖርበት "ሱኒይ ነው፣" ያልተመቸውንና ከአላማው ጋር የማይገጥመውን ምንም እንኳን ለሱና ታጋይ ቢሆንም "ሙብተዲዕ ነው…" እያለ ውዳቂ ህጎችን ሲደነግግ እንደ ገደል ማሚቱ ዝም ብለው ማስተጋባት ነው ስራቸው። በቃ! በፍቅሩ ታውሯል!! ልክ በሀዳዲያና በሙመይዓ ጭፍን ሙሪዶች እንደታዘብነው ብታናግራቸው አያናግሩህም፣ ልክ እንደ ፈረስ ጋሪ እንዲህ ያለውን አካል በጭፍን ተከትለው ወደ ፊት መጎተት ብቻ ይሆናል ስራቸው። ይህ የፊትናው ቀዳሚ ሙፍቲም የቡድን አደረጃጀት አላማው ላይ የተሳካለት ሲመስለው ጊዜ ለሱንናው ታጋይ የሆኑ ኡስታዞችንና ከፍ ሲልም ታላላቅ በቢድዐ ሰዎች ላይ የእግር እሳት የሆኑ መሻይኾችንም በነገር ወጋ ወጋ ማድረግ ጀምሮ ነበር። የአለማቱ ጌታ ግን የተንኮለኞችን ተንኮል አንኮታኳች ነውና