የግጥም ህይወት


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


የተለያዩ የግጥም ስራዎች የሚቀርቡበት ፣ የታላላቅ ገጣሚያን ችሎታ የሚታይበት ፣ የጀማሪና እውቅና የሌላቸው ሰዎች ጥበብ የሚለካበት የፍቅር ቻናል ነው።
( የግጥም ህይወት )

ኑ። የግጥምን ጥበብ እስከ ጥግ እናስመለክቶታለን። ከ እናንተ የሚጠበቀው ቻናሉን ጆይን በማለት ለወዳጅ ፣ ለጓደኛ ፣ ለዘመድ ሼር ማድረግ ብቻ ነው።
https://t.me/yegtmhywet

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


​​​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚. 💚
💛 ╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥ 💛
❤️ ❤🇪🇹


ደርሶ እየጠቆረ
ደርሶ እየዳመነ ይህ የክረምት ሰማይ
ናፍቆት እያዘነበ በምስኪን ነፍሱ ላይ፤
በሴቃ እየሞላ
በአሳር እያሰቃየ ትዝታ ግምግምታው፤
ብትት የሚያደርገው
ድንግጥ የሚያሰኘው ምስሉ እና ብልጭታው፤
ቦግ እልም እያለ
ሽው ጥፍት እያለ ፍቅሩን ቀስቅሶበት፤
ሌት ቀን የሚያስነባው ሚሞላው በጭንቀት፤
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ማለዳም ምሽትም
ፀሀይም ጨረቃ ኮኮብም ቢወጣ፤
በተስፋ ብርሀኖች
በምኞት መንገዶች ትዝታ እየመጣ፤
ወደፊት እንዳይሄድ
ወደ ኃላ ስቦ ወደ ኃላ ወስዶ፤
ዛሬውን እንዳይኖር
አሁንን እንዳያይ በትናንት ቀፍድዶ፥
አሳሩን ሚያበላው!
ስቃዩን ሚያሳየው!
ይህ የእግዚየር ሰማይ
ጠላቱ የሆነ አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ዛፉ ሳር ቅጠሉ ድምፅ እየፈጠረ፤
ተፈጥሮው በሙሉ ስንኝ እየቋጠረ፤
ከአእዋፍ የሚዋሀድ ዜማ እየቀመረ፤
በሄደበት ሁሉ እየተከተለ
በትዝታ ቅኝት እያንጎራጐረ
ትዝ ወደ'ሚለው ድምፅ
ነፍስያውን ወስዶ ስላም እየነሳ፣
በሀሳብ እየዋዠቀ በአካል እንዲሳሳ፤
ሰማዩ መሬቱ፣
ሁሉ ዘፍጥረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
በዛች ጠባብ ቤቱ
ብቸኝት ሰፍቶት ውቂያኖስ ሁኖበት፤
ምስኪን ጀልባ ልቡን
ናፍቆት ማእበሉ ትዝታ አናውጦበት፤
ላለመውደቅ ሚቀዝፍ፣
ላለመስመጥ ሚጥር ፤
በነፍስ ግቢ ውጪ በጭንቀት ሚጣጥር፤
የገዛ ንብረቱ፣
የሆነ ጠላቱ!
አንድ ወንድ ታውቂያለሽ?
ምናልባት ምናልባት
በህልም አለም ውስጥ
ተከስቶ ካየሽው
ወይ በእብደት ዓለም ውስጥ
ዙሪያ ካገኘሽው
ያ ወንድኮ እኔ ነኝ !
ያ ወንድ "አዳምሽ" የፍጥረትሽ ፍንጩ
አንቺን ሲጠብቅ የደረቀ ምንጩ።

ጸሃፊ Abu

ከተመቻችሁ እስኪ ጆይን በሉልኝ

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


🔩🔩🔩 ርዕስ ፦ መደቀርያው ላልቶ፤
ቢመቸኝ ቢደላኝ ፤ ተድላዬ ቢሰምር፣
ቀመሩ ቢቃና ፤ ቢታደለኝ መኖር፣
ሁሉን አሳክቼ ፤ የምታቱን ክምር፣
ስዕሌን አድምቄ ፤ እኖር ነበር የምር።
የድልድዩን ቀመር ፤ የሚሰስት ሞልቶ፣
ችለክ ብትራመድ ፤ ጎሽሞ ጎትቶ፣
እንዲ ይወቅስሀል ፤ ስህተትን አጉልቶ፣
ችግርን በዝርዝር ፤ ያለ መፍትሄ ሰቶ።
ግድ የለም ይቻላል!
አትይ የኋላህን ፤ ማን አለ የሰራ፣
ባለፈው ታሪኩ ፤ ነገውን የገራ፣
ምንም ቢከብድ ፤ ቢመስልህ ተራራ፣
ስፍናን አትሻ ፤ ለሱም አትራራ፣
ገፊን አትመልከት ፤ ተሞግቶ ሚራራ፣
አሜን ይሁን ባይ ፤ ሚቀበል አደራ፣
ግራ ቀኝ ቢታይ ፤ ነውኮ አዋራ!
ጆሮህን አታድል ፤ ገደብ ለሚያወራ፣
በራዕይ ተራመድ ፤ በራስህም ኩራ።

ገጣሚ ናርዶስ✍

ከተመቻችሁ ብቻ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


🙎🙎🗣🗣 ርዕስ ፦ መርገጫሽ አይብዛ

ስልክሽ ተጨናንቆ ፤ ኮቴሽ ከፈጠነ፣
ካለሽበት ስፍራ ፤ ዝናሽ ከገነነ፣
ቀጠሮ በዝቶብሽ ፤ ካስባለሽ ለነገ....!
አጥብቀሽ ፍሪ ፤ መልህቅሽ ቀጠነ።
የሄዋንን ክብር ፤ እንደቀልድ ጥለሽ፣
ስሙን አሳምረሽ ፤ ላተራምስ ብለሽ፣
ከዚህ እስከዛ ፤ ጉልቻ በዝቶብሽ፣
በማስመሰል ማቀቅ ፤ ፍቅርን አቃለሽ፣
መገኛሽ ብዛቱ ፤ አራዳነት መስሎሽ።
ሀብታምና ደሀ ፤ ቆንጆ በከርታታ፣
ለሁሉም ቅርብ ፤ ከመጣ ከባታ፣
ጉዳትን አታቂ ፤ ይተካል ባፍታ፣
መቶ የሚሄደው ፤ አይበልብሽ ፈታ።
አዳሙም አያርግሽ ፤ ስህቱን ማረምያ፣
ባጣ ቆይ ፤ ስሜቱን ማቆያ፣
ለሄዋኑ እፎይታ ፤ እልፍን ማረምያ፣
ድልድይ አትሁኚ ፤ ለመጣው ማለፍያ።

በናርዶስ ተፃፈ✍

ከተመቻችሁ ብቻ ጆይን በማለት ቤተሰብ ሁኑን

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ሰላም ፣ ሰላም ፣ ውድ የግጥም ህይወት ይቻናልና የግሩፕ አባላቶች በሙሉ። እንኳን ለደብረታቦር የቡሄ በአል በሰላም ፣ በጤና በፍቅር አደረሳችሁ። ባእሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ።

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


"የናፈቀ ሰው ሃቅ"

...
ከህሊና አልጋየ
ናፍቆትሽን አባብሎ-ማስተኛት ይከብዳል፣
ምክኒያቱም
እንደ ዓመለኛ ልጅ
በሾሉ ጥፍሮቹ -ነፍስ ይጨመድዳል።
ናፍቆትሽ!
ትዝታሽ!
ገላየን ገረፈው-ልቤን አደቀቀኝ፣
ትላንት ላይ ሁኖ
ከህይወት ጓዳየ-ዛሬየን ሰረቀኝ።
እናም...
ገዘፍሽ፣
ፈረጠምሽ፣
በናፍቆትሽ በኩል-የቀን ግብር በልተሽ፣
ግን ማን ነኝ ?
ግን ማን ነሽ?
ግዛቷ ሰፊ ነው
ከነፍሴ ጫፍ አልፎ-ከየት እስከ የትም፣
እውነት ከተወራ
አሁን የኔን አንች-አንችም አታውቂያትም።
...
ዘነበ-ሞላ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ስፅፍ ስለ መሄድ - ስፅፍ ስለ መምጣት
ስፅፍ ስለ "ካሳ" - ስፅፍ ስለ ቅጣት
ስቀኝ ስለ ሀገር - ስቀኝ ስለ ውበት
ራሴን ብረሳ - በራሴው አንደበት
ማን ይፈርዳል በኔ?
የሰው ልጅ ለራሱ
እንዴት ነው የሚፅፍ እንዴት ነው 'ሚቀኘው
የተፃፈለትን "ከላይ" ካላገኘው።

Abu

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ውስጥሽ አይነበብ ፤ ከጀርባ ነው ልብሽ
ስሜትሽ ማዕበል ፤ ስውር ነው ሀሳብሽ፡፡
ጨረቃ ስትደምቅ ፤ ትደበዝዢያለሽ
ሰማዩ ሲዳምን ፤ ታንፀባርቂያለሽ
አንቺ ግራ ገብቶሽ ፤ ግራ ታጋቢያለሽ
የሰውን አዕምሮ ፤ ትበጠብጪያለሽ
አትገቢኝም ውዴ!!………
ለምን በዚህ መጠን ፤ ታሰቃይኛለሽ..?

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ሊወዱሽ💞

ጠላ'ናት ይላሉ በሩቅ ተመልክተው
በወጠሩት ሸራ
በማይገልፅሽ ቀለም አደብዝዘው ስለው

ክፉ ናት ይላሉ ውስጥሽን ያላዩ
በራሳቸው ክፋት ነደው እየጋዩ
እውን ያላወቁሽ...
ጨረቃ ምስልሽን መመልከት ከብዷቸው
ዝለው ወድቀው ነበር በአንቺ ተመዝነው

ግን...እቴ..
ድሮ ያላወቁሽ ካንቺ ሲታደሙ
በክፋት የሳሉሽ በቁጭት ታመሙ
በሩቅ የሚጠሉሽ ወደዱሽ ሲቀርቡ
ከፍጥረታት ፍቅር አልፈው ከገደቡ::

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ልታከም በፍቅርሽ💞

እቺ የፍቅር ምንጭ የፍቅር መፍለቂያ
የፍቅር እመቤት የፍቅር መለኪያ
እያሉ ሲያወሩ ስላንቺ ሰምቼ
አንቺን እስካገኝሽ እላፊ ጓግቼ
ስላንቺ ሲነግሩኝ አላምን ስላቸው
ስላንቺ ሊነግሩኝ ቃላት አጠራቸው
እሷ እኮ ዶክተር ናት የፍቅር አካሚ
እንኳን ለወደዳት ለጠላት ተስማሚ
ብለው ሲናገሩኝ ስላንቺ ሰምቼ
ላይሽ ቸኮልኩና የት ነው ምትኖረው ብዬ ጠየኳቸው
ነገሩኝ እሩቅ ነው እመስሪያ ቤታቸው
በጣም ስንደፈደፍ ወደሷ ገስግሼ
ስለሷ ለማወቅ ተስፍዬን አንግሼ
በፍቅፘ ልታከም ወደሷ መጥቼ
ቢሮሽ ስር ደረስኩኝ ሳንባዬን አጥቼ
እንደምንምን ሆኜ እራሴን አርግቼ
ትንሽ አረፍ እንዳልኩ ቀጭ ቋ ቀጭ ቋ የሚል ድምጽ ሰምቼ
ፈጥኜ ተነሳው መድከሜን እረሳው ልክ እንደተነሳው
አይንሽን አይቼ
ታምሜ ቀረውኝ ልታከም መጥቼ::

Esmael

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


Re....

ሾልኮ ቀለበቱ ፤ ከእጄ የወደቀው
ወሰዳት ብላችሁ ፤ ስትነግሩኝ እኮ ነው
እንዴት ትሞታለች…? ቤቴን ማን ያድምቀው…?
እንዲህ ይጨክናል… ሰው በሚወደው ሰው…?
ግራ ጎኔ ሞልቶ…ክፍተቴ ተከድኖ… ደስታዬ ሳከብር
አምላክ ምን ነክቶት ነው…? ፤ እንዴት ይቀጣኛል
…ከሞት ጋር በማበር፡፡
ይሁን እስቲ ተውት ፤ ሽንፈቴን ልዋጠው
በእግዜር እጅ ሲገባ ፤ ማንም ደካማ ነው
ግን ስታበጃጇት...
ሳጥን አትስሩላት ፤ ለእሷ አይገባትም
ከፈኗም ጨርቅ አይሁን ፤ አዎ አይመጥናትም
ይልቅ ቶሎ በሉ ፤ ቆዳዬን ግፈፉት
በዛ ጠቅልላችሁ ፤ በድኗን ከፍኑት
ከዛም ጉድጓድ ሳይሆን ፤ ልቤ ውስጥ ቅበሯት
አፈር እንዳይነካት ፤ ምስጡ እንዳይበላት
……….. እዛ ነው ሚሻላት
የራሷ ነኝ እኔ ….አካሌም ቤቷ ነው…..
ልቤ ዉስጥ አስተኟት እንዳይቀዘቅዛት።

የግጥም ፍላጎት ካላችሁ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


🥰🥰 የኔታ ነህ ለኔ 🥰🥰


ያ ሸንጋይ ምላስህ ቅቤ የሚያቀልጠው
ፎርጅድ ማንነትህ ከላይ የሚታየው

መታወቂያው ሌላ ማሞው ሌላ ሆነህ
ያንቺ ነኝ ስትለኝ ልብህን ሸሽገህ

ሰው አማኙ ልቤ ለፍቅርህ ሲሸነፍ
ምስኪን ማንነቴ አንተን አምኖ ሲከንፍ

የታሻለ ስታይ አቁስለኸው ልቤን
ትተኸኝ ስትሄድ ንቀኸው መውደዴን

እጅጉን ብጎዳም ባንተ ምክንያት ያኔ
አመሰግናለሁ የኔታ ነህ ለኔ
ስለሰው ማንነት ያዘረፍከኝ ቅኔ

✍ ፅዮን

ከተመቻችሁ ጆይን በሉልኝ

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


«ለአንዲት ቅፅበት ብቻ»
(ደበበ ሰይፉ)
-
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ
እስቲ የማነው ጉልበት
የሰው የአማልክት
ሊሰጠኝ የሚችል የደቂቃ ዕረፍት ?
ከእውነት - ፍቅር - ውበት እማወጋበት ?
ለአንዲት ውብ ሙዚቃ ሀሳቤን ሰውቼ
ለአንዲት መልካም ቅኔ ባርነት ገብቼ
ህሊናዬን፤ ቀልቤን፤ አካሌን ሰጥቼ፤
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ !
የአምሮዬ መርከብ ከማዕበል አምልጣ
ከሕይወት ስንክሣር አምርራ ፈርጥጣ
በዕፁብ - ውበት ቅኝት እጅግ ተመስጣ
ሌላው ሌላው ነገር ባፍንጫዬ ይውጣ!!
.
የጥበብ አፍቃሪያን ብቻ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ዛር ያለባት ሃገር ማጉራት የለመደች፣
በነጋ በጠባ "ደም አምጡ" ትላለች።
ይሄን ያየ ልጇም
ተነድፎ በክፋት ታሞ በከንቱነት፣
ይገብርላታል
የመንትያውን ነፍስ የወንድሙን አንገት።
ያው... አንካሳ ዘመን
ያው... ጉድፋም ትውልድ
ፍቅሩ የይስሙላ አካሂያዱ የግድ፣
ነውር ነው አያውቅም
በሃዘኑ ሲያሾፍ በሞቱ ሲቀልድ።
ወ....ግ...ድ!!!
ብራ ይሁን እና
የምስራቃችን በር የአድማሱ ገመገም፣
በቃችሁ ይበለን
በሃገሬ መሬት
በሃበሻ ሰማይ ላይ ሞት አይደጋገም።

መተከል🌑🌒😢😢 ኧረ በቃችሁ በለን የሰዉ ልጅ አንገት ከዶሮ አንገት የቀለለባት ሀገር...ከርመን መርዶ ብቻ...በሰዉ ደም ኪሱን የሚያደልብ..በሰዉ ደም የሚያተርፍ...በሰዉ ደም ኪሳራዉን የሚያሰላ ስግብግብ ተከበን ነፍሳችን ተጨማዳ ተኮማትራ አለቀች።....ግን ለምን...? ካልገደሉ ህይወት የለም...? እኛ ሀበሾች ግን መች ነዉ እንዲህ ሰይጣንን ማስናቅ የጀመርነዉ...?
የሚገርመኝ አሁንምኮ እንደሰኩራለን...አሁንምኮ ኢትዮጵያዬ የፍቅር ሀገር እንላለን...የቱ ጋር ነዉ ፍቅራችን...አብሮህ አንድ ማእድ ላይ የተመገበዉን ሰዉ..አንተ ትብስ ተባብለህ ኑረህ ቀን ሲመጣ ለማትረባ ክፍያ ተቀይረህበት ወንድምህን አጋድመህ እያረድከዉ ነዉ ፍቅር..? ቤተሰቡን መበተንህ ነዉ ፍቅር...ሚስቱን እና አንድያ ልጁን ደፍረህ ነዉ ፍቅር..? እዉነት በእራሳችን እንፈር ጭራቆች ሁነናል....ዲያቢሎስ ነዉ መሪያቸዉ የምንላቸዉ እነዛ ነጮች እንኳን የሰዉን ደም እንደኛ አያፈሱምኮ...አሁን ላይ ከእኛ የተሻለ ዲያቢሎስ የትም የለም...ዛር እና ዉቃቢያችን ከረም ይልና ደም እፈልጋለሁ ይለናል ከርመን እንገላለን ደም እንገብራለን።..

ሃሳቡ የተመቸው ቤተሰብ ይሁነን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


😘እራሴን ገድዬ😘

ሱሰኛ ብባልም ወይንም ዱርዬ
ፈልጌዉ አደለም ልንገርሽ ፍቅርዬ
በጫት በሲጋራ በአልኮል መነከሬ
እራሴን ገድዬ በቁም መቀበሬ
እማገኝሽ መሠሎኝ ነበር መጀመሬ
ተረድተሽ መዉደዴን አባክሽ ታደጊኝ
ከሱስ ተራ አዉጥተሽ ፍቅረኛሽ አድርጊኝ

✍ግጥም እርስትአብ //ፍፄ/

የተመቸው እስኪ ጆይን ይበላት
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ውዴ ታውቂዋለሽ ፤ ውስጤን አቁስለሻል
እየደጋገምሽም ፤ ልቤን አድምተሻል
ግና….
እንዴት ናችሁ ብሎ? ፤ ወዳጅ ሲጠይቀኝ
ቤተሰብ ጓደኛ ፤ ስላንቺ ሲያዋየኝ
ከንፈሬን ገልጬ ፤ ጥርሴን እያሳየሁ
ሰላም ነን እላለሁ ፤ ሁሉንም ዋሻለሁ
ወድጄ እንዳይመስለሽ ፤ ገበና መክተቴ
መዘንጠል አሞኝ ነው ፤ ጎኔን ከአካላቴ

ከ(😘😘😘)

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


" ንገሪኝ "
( በአምባዬ ጌታነህ )

ሀገሬ እናቴ እምዬ የምልሽ፣
ስምሽን አስር ጊዜ ጠርቼ ማልጠግብሽ፣
እንደው ለሰላምሽ
ከቶ እንደምን አለሽ!
እኔ እንዳለሁ አለሁ
ስግነት ገምዶኝ
ከገዳይሽ ጋራ ምግብ እየበላሁ።
ደግሞ ከሟች ድንኳን ለእዝን ተቀምጬ፣
በገዳይ ስግነት በሞተው ወንድሜ ቀብር ተረግጬ፣
በዘር ነህ እሳቤ በከፋፍለህ ሴራ፣
ግማሼ ሟች ሆኖ ግማሽ ገዳይ ጋራ
ሳልሞት ተከፍየ እንደ አባት ሰባራ በሄድኩት አፍሬ፣
ከገዳይ ጋ ስስቅ በሟቹ ሳለቅስ እኖራለሁ ሳልኖር በቁም ተቀብሬ።
እንደዛች ሴት ህይወት
"የገደለው ባልሽ፣
የሞተው ወንድምሽ፣
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ፣
ከቤትሽ አልወጣ"
እንደተባለላት
እኔም ጉዴ ሁሉ ጓድየ ጋ ሆኖ
መኖር እያስጠላኝ፣
ሞት እየናፈቀኝ፣
እንዳለሁ አለሁኝ።

:
እታተይ ሀገሬ፣
አንቺስ እንደምን ነሽ
ኑሮ እንዴት ይዞሻል፣
ትንሳኤሽ ርቆ ህዝቤን አፋጅቶታል።
ተስፋሽን ሚለኩስ የድል ችቦ ይዞ፣ አንድ ሰው ታጥቷል፣
የጎጥ ነፃ አውጭ እንጅ የአገር ነፃ አውጭ ጠፍቷል።
ንገሪኝ እማየ መቼ ነው 'ሚነጋው፣
ከጥላቻ ወተን በፍቅር ምንኖረው
ንገሪኝ እማየ
እየተራመደ በጥበብ መንገድሽ
ይሄንን የሚያደርግ ፦
ሞተው ከኖሩት ውጪ ሌላ ማን ልጅ አለሽ፣
ንግሪኝ እስኪ ቆይ
መቼ ነው አንድቀን?፣
ምንድን ነው ይነጋል?
በጎጥ ተጨራርሰን፣
ቀየሽ ባዶ ሲሆን?
ን.....ገ.....ሪ.....ኝ!


╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ህይወት ዝብርቅርቅ ነች
የቀለማት ውህደት
ጥዋት አረንጓዴ
ረፈድ ሲል ፅልመት
ሲመሻሽ ደማቅ
ሲጨልም ደብዛዛ
ዛሬ ቀጥ ስትል
ነገ ግን ጠምዛዛ
ሳምንት አስለቅሳ
ሳምንት የምታስቅ
አንድ ወር አስጨፍራ
አንድ ወር ምታማቅቅ
አሁን ተስፋ ሰጥታ
መልሳ ጭልምልም
ብሩህ ሆና ታይታ
ሳትቆይ ፍግምግም
ህይወት ዝብርቅርቅ ነች
ቋጠሮ የሌላት
የገጠመኝ ውህድ
ድብልቅልቅ ያለች ናት።

ከ(😔😔😔)

ከተመቻችሁና የግጥም ፍላጎት ካላችሁ ጆይን በማለት ቤተሰብ ይሁኑን

╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


በምናልባት ኑሮ


አይቦዝን አንቀልባው
አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ቢያድሩ
ሺሆች ተወለዱ
ይመሻል ይነጋል
ያው እንደልማዱ፤

መሬት ባህር ሆኖ፥ድሀን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ፥ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ፥በጡብ በብረት ደን
አየሁ ባደባባይ፥ሰው በሰው ሲታደን፤

ማን በገላገለኝ፥የጄን ሰዓት ሰብሮ
በምናልባት አገር፥በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ፥ማን ያቅዳል ደፍሮ።

በእውቀቱ ስዩም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥


ፈገግ በል አትበሉኝ፣ ባልስቅ ይሻለኛል፡
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው፣ ወንጀል ይከተኛል፡፡😉

#ጉረኛ_እኮ_ነኝ😜

እስኪ ከተመቻችሁ ጆይን በሉልኝ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥

Показано 20 последних публикаций.

567

подписчиков
Статистика канала