«★ቀውሌ ለኤቲስቶች
አምላክ የለም ባዮች
ከሞት ኋላ ህይወት በሚክዱ ሰዎች።★»
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ጎህንም ፈልቃቂ ሁሉኑም አዋቂ፣
ከሞት ኋላ ህይወት በማኖር አድማቂ፣
ደካማን የሰው ልጅ መልካም አሳዋቂ፣
ልጀምር በስሙ በአላሁ ጥበብ ሆኜ ተደናቂ፣
እንደው ጥበቡማ ቢቆጠር ቢቆጠር አይደለም አላቂ፣
ይሄው ፈጥሮ አኑሯል የፍጥረት እላቂ፣
ፈጣሪ አለ እንዴ?? እያለ ጠያቂ፣
ከሞት ኋላ ህይወት ይህን አላዋቂ፣
ከራስ የተጣላ ሀሳበ ድቃቂ፣
በሰይጣን ምሽግ ውስጥ ሄዶ ተደባቂ፣
ረብ የለሽ እውቀትን ያዋቂ አላዋቂ፤
ዒልመል ከላም ብሎ፣
ተስፈንጥሮ ወቶ ከብልሎ ከብልሎ፣
እውቀት መስሎት ሄዶ ከሰይጣን ተዳብሎ፣
ምላስ ከልቡ ጋር አልስማማ ብሎ፣
ይሄው ተቀመጠው አቅሉንም ጥሎ።
ለዚህ አይነቱ ሰው በቋንቋው ልንገረው፣
ሳይሻል አይቀርም ምሳሌ ብሰጠው፣
የአላህ ፍቃድሆኖ ቀጥዬ ልፅፍ ነው፤
ምሳሌን መስጠቱ የረሱሉ ሱና፣
እኔም ተከትዬ የታላቁን ፋና፣
ይሄው ልጀምር ነው ምሳሌ አረኩና።
ከዕለታት በአንዱ ..............
ሁለት መንትያዎች ባንድ ላይ ተፀንሰው፣
አንደኛው ላንደኛው እንዲህ ሲል ጠየቀው፣
«ከማፀን ስንወጣ ህይወት አለ ብለህ፣
ትንሽ ታስባለህ ቅንጣትን ታምናለህ??»
ብሎ ሲጠይቀው፣
2ኛው ደግሞ እጅጉን ደነቀው፣
እንዴታ ............................
«በአፍህ ተትቶ በትብትህ ምትበላው፣
በቶሎ ጠንክረህ በፍጥነት ምታድገው፣
ለውጨኛው ዓለም ትበቃ ዘንድ ነው።»
አንደኛው ተገርሞ እጅጉኑ ሳቀ፣
በወንድሙ ቃል እየተሳለቀ፤
ህይወት ከዚህ ወዳ‼?፣
ኧረ አስገረምከኝ በሳቄ ልፈንዳ፤
ሁለተኛው ደግሞ ቀጠል አረገና፣
ሀሳቡን ቀጠለ እንዲህ በጥሞና፣
«ምንአልባት በእግር እንሄድም ይሆናል፣
ምግብንም በአፍ መብላትም ይገኛል፣
አሁን ማንረዳው እልፍ አእላፍ ይኖራል።»
ሁለተኛውም ልጅ ልክ እንዲህ እያለ፣
የመጀመሪያው ልጅ በቁጣ ቱግ አለ፣
ከዚያም እንዲህ አለ፣
«ኧረ የቀን ቅዠት ጭራሹኑ ማበድ፣
በእግር መራመድ?‼ እህል በአፍ መስደድ?‼፣
ጭራሽ ማይታሰብ ለጭንቅላት ሚከብድ።»
ይሄማ እብደት ነው ብሎ እያጣጣለ፣
ታጋሽ ወንድሙ ግን መናገር ቀጠለ፣
«ተረጋጋ ወንድም እንዲህ አይደለ፣»
ብሎ እያባበለው እየነገረው ሳለ፣
የመጀመሪያው ልጅ እንዲህ እንዲህ አለ፤
«አይዋጥልኝም! ይሄ ምታወራው፣
ልቀበልህና እሺ እንደምትለው፣
ከመሀፀን ውጪ ህይወት እዚያም ካለም፣
ወቶ የመጣ ሰው ለምን አናገኝም¡?
Because ከዚህ ውጪ ህይወት ሚባል የለም፣
ለዚህ ነው ምንኖረው ወዴትም አንሄድም።»
አሁን እንደገና በተራ በተራ፣
ሁለተኛው ደግሞ እንዲህ ሲል አብራራ፤
«እርግጥ ነው እንዳልከው አቅም ባይኖረንም፣
ከወጣንም ኋላ ጉልበት ቢከዳንም፤
እናታችን አለች ከኛ ትሆናለች፣
መጥፎ እንዳይመጣ ትጠብቀናለች፤»
የመጀመሪያው ልጅ የተንቀለቀለው፣
አሁንም በመሀል እንዲህ ሲል አቆመው፣
«እናት‼‼?????»
«ኧረ ተው አንተ ልጅ እናት ትለኛለህ?፣
በእናትም መኖር ከልብህ ታምናለህ?፤
እሺ እውነት ካለች፣
ለምን አናያትም አሁንስ የታለች?፤»
ይህንን ሲሰማ ልክ እንዳዳመጠ፣
ሁለተኛውም ልጅ ሰብሩ ተሟጠጠ፤
«እውነት በእናት መኖር አንተስ ትክዳለህ፣
እሷን ተንተርሰህ እሷን ተደግፈህ፣
ምትበላውን ምግብ ከሷ ዘንድ አግኝተህ፣
እንዴት አታስብም?እንዴት ትክዳለህ?፤
በመሀፀን መኖር በደንብ ካስተዋልከው፣
በጥሞና ሆነህ እጅጉን ካጤንከው፤
የእናትን መኖር ትገነዘባለህ፣
የእዝነት ድምፇንም ትናፍቃታለህ፣
ፊቷንም ማየቱን እጅግ ትመኛለህ፤»
ይህንን አለና ክርክሩን ቋጨው፣
የወንድሙንም አፍ በዚህ አሰያዘው።
ስለዚህ ሰዎች ሆይ እጅጉኑ ንቁ፣
ይቺ ዓለም ማህፀን ናት ይህንን እወቁ፣
ለመጪው ዓለም መዝራት መሰነቁ፣
ይሄ ነው ጥቅሟ ይህንን እወቁ፤
ደግሞ ላሰበው ላስተነተነው ሰው፣
እዚህ ላይ ያስገኘው አንድ አላህ ብቻ ነው፣
ከዚህ ሰፋ አድርጎ በደንቡ ላሰበው፣
የሞትን እለታ ከጠባቡ ወተን ሰፊ ነው ምንሄደው
ደግሞ የዛን ለታ ከጭንቅ የምድንው፣
በቁርዓን በሱና ህይወትን ስኒዝ ነው።
✍በተማሪ ዓድናን ኸይሩ
✔ከሱቡለ ሰላም ጀመዓ ዳዕዋና እውቀት ዘርፍ።
ه ١٠/٩/١٤٤٠
03/05/2020 G.c
አምላክ የለም ባዮች
ከሞት ኋላ ህይወት በሚክዱ ሰዎች።★»
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ጎህንም ፈልቃቂ ሁሉኑም አዋቂ፣
ከሞት ኋላ ህይወት በማኖር አድማቂ፣
ደካማን የሰው ልጅ መልካም አሳዋቂ፣
ልጀምር በስሙ በአላሁ ጥበብ ሆኜ ተደናቂ፣
እንደው ጥበቡማ ቢቆጠር ቢቆጠር አይደለም አላቂ፣
ይሄው ፈጥሮ አኑሯል የፍጥረት እላቂ፣
ፈጣሪ አለ እንዴ?? እያለ ጠያቂ፣
ከሞት ኋላ ህይወት ይህን አላዋቂ፣
ከራስ የተጣላ ሀሳበ ድቃቂ፣
በሰይጣን ምሽግ ውስጥ ሄዶ ተደባቂ፣
ረብ የለሽ እውቀትን ያዋቂ አላዋቂ፤
ዒልመል ከላም ብሎ፣
ተስፈንጥሮ ወቶ ከብልሎ ከብልሎ፣
እውቀት መስሎት ሄዶ ከሰይጣን ተዳብሎ፣
ምላስ ከልቡ ጋር አልስማማ ብሎ፣
ይሄው ተቀመጠው አቅሉንም ጥሎ።
ለዚህ አይነቱ ሰው በቋንቋው ልንገረው፣
ሳይሻል አይቀርም ምሳሌ ብሰጠው፣
የአላህ ፍቃድሆኖ ቀጥዬ ልፅፍ ነው፤
ምሳሌን መስጠቱ የረሱሉ ሱና፣
እኔም ተከትዬ የታላቁን ፋና፣
ይሄው ልጀምር ነው ምሳሌ አረኩና።
ከዕለታት በአንዱ ..............
ሁለት መንትያዎች ባንድ ላይ ተፀንሰው፣
አንደኛው ላንደኛው እንዲህ ሲል ጠየቀው፣
«ከማፀን ስንወጣ ህይወት አለ ብለህ፣
ትንሽ ታስባለህ ቅንጣትን ታምናለህ??»
ብሎ ሲጠይቀው፣
2ኛው ደግሞ እጅጉን ደነቀው፣
እንዴታ ............................
«በአፍህ ተትቶ በትብትህ ምትበላው፣
በቶሎ ጠንክረህ በፍጥነት ምታድገው፣
ለውጨኛው ዓለም ትበቃ ዘንድ ነው።»
አንደኛው ተገርሞ እጅጉኑ ሳቀ፣
በወንድሙ ቃል እየተሳለቀ፤
ህይወት ከዚህ ወዳ‼?፣
ኧረ አስገረምከኝ በሳቄ ልፈንዳ፤
ሁለተኛው ደግሞ ቀጠል አረገና፣
ሀሳቡን ቀጠለ እንዲህ በጥሞና፣
«ምንአልባት በእግር እንሄድም ይሆናል፣
ምግብንም በአፍ መብላትም ይገኛል፣
አሁን ማንረዳው እልፍ አእላፍ ይኖራል።»
ሁለተኛውም ልጅ ልክ እንዲህ እያለ፣
የመጀመሪያው ልጅ በቁጣ ቱግ አለ፣
ከዚያም እንዲህ አለ፣
«ኧረ የቀን ቅዠት ጭራሹኑ ማበድ፣
በእግር መራመድ?‼ እህል በአፍ መስደድ?‼፣
ጭራሽ ማይታሰብ ለጭንቅላት ሚከብድ።»
ይሄማ እብደት ነው ብሎ እያጣጣለ፣
ታጋሽ ወንድሙ ግን መናገር ቀጠለ፣
«ተረጋጋ ወንድም እንዲህ አይደለ፣»
ብሎ እያባበለው እየነገረው ሳለ፣
የመጀመሪያው ልጅ እንዲህ እንዲህ አለ፤
«አይዋጥልኝም! ይሄ ምታወራው፣
ልቀበልህና እሺ እንደምትለው፣
ከመሀፀን ውጪ ህይወት እዚያም ካለም፣
ወቶ የመጣ ሰው ለምን አናገኝም¡?
Because ከዚህ ውጪ ህይወት ሚባል የለም፣
ለዚህ ነው ምንኖረው ወዴትም አንሄድም።»
አሁን እንደገና በተራ በተራ፣
ሁለተኛው ደግሞ እንዲህ ሲል አብራራ፤
«እርግጥ ነው እንዳልከው አቅም ባይኖረንም፣
ከወጣንም ኋላ ጉልበት ቢከዳንም፤
እናታችን አለች ከኛ ትሆናለች፣
መጥፎ እንዳይመጣ ትጠብቀናለች፤»
የመጀመሪያው ልጅ የተንቀለቀለው፣
አሁንም በመሀል እንዲህ ሲል አቆመው፣
«እናት‼‼?????»
«ኧረ ተው አንተ ልጅ እናት ትለኛለህ?፣
በእናትም መኖር ከልብህ ታምናለህ?፤
እሺ እውነት ካለች፣
ለምን አናያትም አሁንስ የታለች?፤»
ይህንን ሲሰማ ልክ እንዳዳመጠ፣
ሁለተኛውም ልጅ ሰብሩ ተሟጠጠ፤
«እውነት በእናት መኖር አንተስ ትክዳለህ፣
እሷን ተንተርሰህ እሷን ተደግፈህ፣
ምትበላውን ምግብ ከሷ ዘንድ አግኝተህ፣
እንዴት አታስብም?እንዴት ትክዳለህ?፤
በመሀፀን መኖር በደንብ ካስተዋልከው፣
በጥሞና ሆነህ እጅጉን ካጤንከው፤
የእናትን መኖር ትገነዘባለህ፣
የእዝነት ድምፇንም ትናፍቃታለህ፣
ፊቷንም ማየቱን እጅግ ትመኛለህ፤»
ይህንን አለና ክርክሩን ቋጨው፣
የወንድሙንም አፍ በዚህ አሰያዘው።
ስለዚህ ሰዎች ሆይ እጅጉኑ ንቁ፣
ይቺ ዓለም ማህፀን ናት ይህንን እወቁ፣
ለመጪው ዓለም መዝራት መሰነቁ፣
ይሄ ነው ጥቅሟ ይህንን እወቁ፤
ደግሞ ላሰበው ላስተነተነው ሰው፣
እዚህ ላይ ያስገኘው አንድ አላህ ብቻ ነው፣
ከዚህ ሰፋ አድርጎ በደንቡ ላሰበው፣
የሞትን እለታ ከጠባቡ ወተን ሰፊ ነው ምንሄደው
ደግሞ የዛን ለታ ከጭንቅ የምድንው፣
በቁርዓን በሱና ህይወትን ስኒዝ ነው።
✍በተማሪ ዓድናን ኸይሩ
✔ከሱቡለ ሰላም ጀመዓ ዳዕዋና እውቀት ዘርፍ።
ه ١٠/٩/١٤٤٠
03/05/2020 G.c