👉 የነጃሺ ደብዳቤ
የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - መዲና ላይ ነገሮች ቦታ ቦታ ከያዙ በኀላ ለተለያዩ ነገስታት ወደ እስልምና እንዲገቡ ደብዳቤ ይፅፉ ነበር
ከእነዚህ የሳቸው ደብዳቤ ከደረሳቸው ነገስታቶች አንዱ የሀበሻው ንጉስ ነጃሺ ነበር
በስድስተኛው አመተ ሂጅሪያ
ዐምር ኢብኑ ኡመየተ አድዱመሪ የተባለ ሶሀብይን ደብዳቤ ሰጥተው ላኩት
ደብዳቤው እንዲህ ይላል :-
" በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
ከሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ ወደ ነጃሺ የሀበሻ ንጉስ , ከዚህ ቀጥሎ : እኔ ወዳንተ አላህን ያ ከርሱ በስተቀር ሌላ የሚመለክ የሌለ የሆነውን አመሰግናለሁ
ዒሳ የመርየም ልጅ ሲሆን ( አላህ ከፈጠራቸው )ሩኾች አንዱና የርሱ( ሁን ) የሚለው ቃሉ
ጥብቅና ንፁህ ወደ ሆነችው መርየም የላከውና በዚህም የፀነሰችው መሆኑን እመሰክራለሁ
ወደ አላህ አምልኮት እጠራሀለሁ እሱ ብቸኛ ሲሆን አጋር የሌለው እሱን በመታዘዝ ወደ መወዳጀት
እንድታምንብኝና ይዤው በመጣሁት እንድታምን እንድትከተለኝ
እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ አንተንና ተከታዮችህን ወደ እስልምና እጠራችዋለሁ
ተቀበሉ አድርሼያለሁ መክሬያለሁ መልእክቴ ሲደርስህ ተቀበል እንዳትኮራ
ሰላም ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ይሁን "
ይህ ደብዳቤ ወደ ነጃሺ ደርሶ ሲነበብ ከዙፋኑ ወርዶ ደብዳቤውን ተቀብሎ በአይኖቹ መካከል ለጠፈው
ከዚያም እንዲህ አለ በአላ እመሰክራለሁ እሱ ያ የኪታቡ ባልተቤቶች የሚጠባበቁት ነብይ ነው
ሙሳ በተውራት ላይ በአህያ የሚሄደው ብሎ ያበሰረውና ዒሳ በግመል የሚሄደው ብሎ ያበሰረው አንድ ነው
ከዚያም ነጃሺ የሚከተለውን ደብዳቤ ወደ ነብዩ ፃፈ
" በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
ከነጃሺ የሀበሻ ንጉስ ወደ ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ አስላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ያ ወደ እስልምና የመራኝ አላህ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም
ከዚህ በመቀጠል
የአላህ መልእክተኛ ሆይ ደብዳቤህ ደርሶኛል በውስጡ ስለ ዒሳ ያነሳኸው ሰማይና ምድርን በፈጠረው ጌታ እምላለሁ ዒሳ አንተ ካልከው በተምርና በሽፋኑ መካከል ያለው ልዩነት ያክል ልዩነት የለውም
ወደ እኛ የላከው መልእክት አውቀናል
አንተ አውነተኛ ነብይ መሆንህን እመሰክራለሁ በዚህም ቃል ገብቼልሃለሁ የአጎትህንም ልጅ ጃዕፋርን ቃል ገብቼለታለሁ በእጁም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ሰልሜያለሁ ወሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ "
ከዛም ነጃሺ ለዐምር እንዲህ አለው የሚታይ ነገር እንደ ሚሰማው አይደለም ወደርሱ መሄድ ብችል ኖሮ በሄድኩ ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን በሀበሻ ረዳቶቼ ትንሾች ናቸው ተከታዮች እስከማበዛና ልብ እስከማለሰልስ ታገሱኝ
ረሂመሁላሁ ራህመተን ዋሲዐን
አጥጢራዙል መንቁሽ እና ጀዋሂሩ ሀሳን እንዲሁም አስሲራ ነበዊያህ ሊብኒ ዳህላን
ኪታቦች የተወሰደ
http://t.me/bahruteka