እነሱ ለጥፋት ሲፈነጩ ተመልካች አትሁን። የማህበራዊ ሚዲያ ዳዕዋ ለስንቶች ሂዳያ ሰበብ እንደሆነ በተግባር እያየነው ነው። የስንቱ ሴረኞች ተንኮል በመጋለጡ ስንቱ ተርፏል። ዛሬን አጥብቀህ ከሰራህ የሚሰድብህ፣ የሚረግምህ አካል ነገ ይቅርታ ይጠይቅሃል። ህዝብህ ላይ አትፍረድ። ለዘመናት የጥፋት ኃይሎች እግር ከወርች ጠፍረው ይዘውታል። በትንሽ ጥረት የተንኮል ድራቸው ሲበጣጠስ እያየን ነው። ለዚህ ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያዎች ደዕዋ ሚና ቀላል አይደለም። ስለዚህ እነዚህን መገናኛዎች አጥፊዎች ለጥፋት ሲያውሏቸው አንተ ኸይር ለማሰራጨት ተንኮልን ለማክሸፍ በሚገባ ተጠቀማቸው።
ሕዝባችንን አንድየው ከጥፋት ይጠብቀው፣ በተውሒድና በሱንናህ ላይ ይሰብስበን፣ መንገድ የሳቱ ወገኖቻችንንም ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ ወደ መንገዱ ይመልሳቸው። ኣሚን።
ሕዝባችንን አንድየው ከጥፋት ይጠብቀው፣ በተውሒድና በሱንናህ ላይ ይሰብስበን፣ መንገድ የሳቱ ወገኖቻችንንም ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ ወደ መንገዱ ይመልሳቸው። ኣሚን።