ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ ከዚህ በኋላ አይገደዱም ተባለ!!
ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ እንደነበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ አስታውሰዋል።
ይህም የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲኖር በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ እንደነበር እና አሁን ግን ግዳጁ እንደተሳ አክለው ተናግረዋል።
@etstocks