"ባንዲራችን ከእነ ክብሯ ናፍቃን ነበር" የታች ጋይንት ሕዝብ
የአማራ ፋኖ በጎንደር ገብርዬ ክፍለ ጦር የደመራ እና የመስቀል በዓልን አርብ ገበያ ላይ ከህዝብ ጋር በድምቀት አክብሯል።
በበዓሉ አከቤበር ላይ የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥና የአማራ ፋኖ በጎንደር ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ ኮሎኔል አዲሱ ደባልቄ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል።
ኮሎኔል አዲሱ በመልእክታቸው፤ "ዛሬ እያጣጣምን ያለውን ነጻነትና ደስታ ዘላቂና ሙሉ ለማድረግ መላው ህዝብ በብልጽግና አገዛዝ ላይ ሊነሳበትና ከፋኖ ጎን ሊቆም ይገባል" ብለዋል።
በበዓሉ የታደሙት የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ "ልጆቻችን ስላጎናጸፋችሁን ነጻነትና ደስታ እናመሰግናችኋለን። በእናንተ ተጋድሎ የናፈቀንን ሙሉ ባለ ግርማ ባንዲራችንን አሳያችሁን። ባንዲራችን ናፍቃን ነበር" በማለት ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ አክለውም፤ "ይህን ድል ማጽናትና መላ የአማራ ህዝብ ከዚህ ጨፍጫፊ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲወጣ ሁላችንም ከፋኖ ጎን ልንሰለፍ ይገባናል" ሲሉ መናገራቸውን የአማራ ፋኖ በጎንደር የገብርዬ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጂነር ደመወዝ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።
@ኢትዮ 251