Hasen Injamo


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በየእለቱ ለሚሰግደው ሶላት የረካአ ቁጥር ማለትም ዒሻ/አሱር/ዙህርን አራት, መግሪብን ሦስት እና ሱብህ ሁለት ረካአ የሚያመለክት ይቅርና ,, የሚሰገዱ ግዴታ ሶላቶች አምስት አውቃት ይሁን ሦስት አውቃት ከቁርአን መረጃ የሌለው ጃሂል ስለመውሊድ ሊከራከርህ ይመጣል::

እስቲ አምስቱንም አውቃት ሶላት ቦታቸውን ከቁርአን አምጣ ብትለው ፍጥጥ ይላል:: እና ወንድሜ መውሊድ ላይ እንዲህ ለክርክር የበረታኸው ሲሰግዱ አይተህ ነው እንዴ የሰገድከው? ረካአቸውንማ አታስቸግረው::

የመውሊድ እኮ ከዚህ በላይ ፍጥጥ ብሎ በግልጽ ቁርአን ውስጥ ቁጭ ብሏል:: ጠዋት ፖስቼልሀለሁ:: ከፈለግክም እጨምርልሀለሁ::
በቁርአን የነቢያችንን ﷺ ስም አራቴ ነው የምታገኘው:: ከ124ሺህ የነቢያችን ﷺ ሶሀቦች ውስጥ የአንድ ሰው ስም ብቻ ነው በግልጽ "ዘይድ" ተብሎ የተጠቀሰው:: ቁርአን ለዓለም ሁሉ መመሪያ እንጂ የዓረብ ታሪክ መተረኪያ አይደለም:: ስትቆፍር ብትኖር አትጨርሰውም:: ክርክር ተውና የምትፈልገውን ጥያቄ መልስ እዚያ ፈልግ::


በአላህ ችሮታ በእዝነቱ ነብይ ሙሐመድ ﷺ መወለድ ምእመናን ይደሰቱ::


መውሊድን አለማክበር
ፖለቲካዊና ዘረኝነት ነው
================
ነቢያችን ﷺ ካለፉ ከ20 ዓመታት በሗላ ጀምሮ ከ90 ዓመታት በላይ የቀድሞ ፈታኞቻቸው ማለትም ነቢያችንን ﷺ ሲያሳድዱ የነበሩ ጎሳዎችና ቤተሰቦች (ኡመዊዮች) ሙስሊሙን አስተዳድረዋል:: እነዚህ ነቢያችን ﷺ ነብይ መሆናቸውን በትክክል ቢረዱም የእነርሱ ጎሳ ንግሥና ከናካቴው እንደሚነጠቅ ሰግተው ነው:: ሙአዚኑ ቢላል (ረዲየሏሁ ዓንሁ) የሰለመው በባርነት ኡመያ ቤት ሲሠራ ይህንን ምስክርነት ሰምቶ ነው:: ሙሐመድ ﷺ ልክ መሆኑን አውቃችሁ ዘረኝነት ነው እንዴ የከለከላችሁ ብሎ ነቢያችንን ﷺ ፍለጋ ወጣ::

ከኡመዊዮቹ የሰለሙት ጥቂት ናቸው:: የተቀሩት ግን በፈተና ጀምረው በፈተና ቀጥለዋል:: ነቢያችን ﷺ እንዳለፉ ግን ዳግም ክህደቱ አገረሸ:: በዚህ ወቅት የነቢያችንን ﷺ ስም የሚነሳው ለፖለቲካ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውን ግን ገድለው ጨርሰው በወቅቱ ታሞ ከሞት በተርፈ በአንድ ሕጻን በኩል ነው ዘራቸው የተቀጠለው:: በዚህ ወቅት እንኳንስ መውሊድ ይቅርና መወለዳቸውም ባይኖር ይመርጡ ነበር::

ዘጠና ምናምን ዓመታት የቆየው የኡመዊዮቹ ስርወመንግሥት አብቅቶ እስከአለፈው 100 ዓመት ድረስ መውሊድ ሲከበር ቆይቷል:: ሆኖም ግን የዚህ አስተዳደር ተጻራሪ የሆነና የእንግሊዝ ድቅል የመጣ ጊዜ በነቢዩ ﷺ ቤተሰቦች ላይ ልክ እንደ ቀድሞ ኡመዊዮቹ ዘመን ፈተና ተደቀነባቸው:: በየሀገራቱ ተበታትነው እና አብዛኛዎቹ እራሳቸውን ደብቀው ይኖራሉ:: ይህንን የይሁድ (ስዑድ) አረቢያ ፖለቲካ ያላወቁ ሰዎች ግን መውሊድን መቃወም አይሁድን እና ኩፍርን ከመቃወም በላይ ወጥረው ይከራከራሉ:: መረጃ ቢመጣ እንኳ አያምኑም::

ለመውሊድ መረጃ ከሁለቱ ዒዶች በላይ ለመውሊድ አለው::

ከቁርአን
🕋
يٰۤاَيُّهَا النَّاسُ قَدۡ جَآءَتۡكُمۡ مَّوۡعِظَةٌ مِّنۡ رَّبِّكُمۡ وَشِفَآءٌ لِّمَا فِى الصُّدُوۡرِۙ وَهُدًى وَّرَحۡمَةٌ لِّـلۡمُؤۡمِنِيۡنَ‏
قُلۡ بِفَضۡلِ اللّٰهِ وَبِرَحۡمَتِهٖ فَبِذٰلِكَ فَلۡيَـفۡرَحُوۡا ؕ هُوَ خَيۡرٌ مِّمَّا يَجۡمَعُوۡنَ

እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡
«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ (ቁርአን ሱረቱል ዩኑስ 10:57-58)🕋

ሺፋእ, ፈድል እና ራህማ وَشِفَآءٌ, بِفَضۡلِ اللّٰهِ وَبِرَحۡمَتِه ምንድን ናቸው ብለን ቁርአን ብንፈትሽ በቁርአን አልፎ ነቢያችን ﷺ ጋር ያደርሰናል:: ይህንን ማብራሪያ ለመደርደር መጽሐፍ እንጂ ፌስቡክ አይመችም:: እኔ አይደለሁም የምደረድረው:: የቀደምት እውቅ እና በርካታ የቁርአን ተንታኞች ናቸው የደረደሩዋቸው:: ይህንን ትንታኔ የተቃወመው አንድ የይሁድ (ስዑድ) ዓረቢያ ሸይኽ ነው::

ከሀዲስ አንድ
ሶሂህ ሙስሊም 1162
قَالَ وَسُئِلَ عَنْ صَوْمِ يَوْمِ الاِثْنَيْنِ قَالَ ‏"‏ ذَاكَ يَوْمٌ وُلِدْتُ فِيهِ وَيَوْمٌ بُعِثْتُ أَوْ أُنْزِلَ عَلَىَّ فِيهِ ‏"‏
ሰኞ ቀን የምፆመው የተወለድኩበት, ነብይ የተደረግሁበት እና ቁርአን ለእኔ የወረደበት እለት ስለሆነ ነው::

عَنْ أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ، رضى الله عنه أَنَّرَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سُئِلَ عَنْ صَوْمِ الاِثْنَيْنِ فَقَالَ ‏ "‏ فِيهِ وُلِدْتُ وَفِيهِ أُنْزِلَ عَلَىَّ ‏"‏
የሰኞ ፆም የተወለድኩበት እና ወደኔ የተወረደበት ነው::

ተመሳሳይ ሀዲሶች በሌሎች የሀዲስ ጥራዞች ሞልተውላችሗል::
=========

መውሊድን ማክበር የተቃወሙ የይሁድ (ስዑድ) ዓረቢያ ሸይኾች ሲሆኑ ከእነርሱም አንድ ወይም ሁለት ናቸው:: ዓላማውም ፖለቲካዊ እንጂ ሀይማኖታዊ አይደለም:: ምክንያቱም ስዑዶች የነቢዩ ﷺ ቤተሰቦችን ገልብጠው ሥልጣን ስለያዙ ,, ለሥልጣናቸው ተቀናቃኝ የሚሆን ስብስብም ይሁን አስተሳሰብ ማውደም አለባቸው:: የነቢዩን ﷺ ቤተሰቦችን ጥሉ ብለውማ አይናገሩም:: ምናቸው ሞኝ ነው:: መውሊዳቸውን ማምከን እንጂ:: ይህንን በማድረጋቸው ብቻ የነቢያችን ﷺ ቤተሰቦችን ስም ማንሳት የሚያስነውር ደረጃ ተደርሷል::

ቤተሰቦቻቸው ማለት ከቁርአን ቀጥሎ እንደ መረጃ ውርስ እንደሆኑ በሀዲሳቸው አለ:: ቁርአን አህሉል በይት እና ሀዲሳቸው የመረጃ ምንጭ ናቸው:: አህሉል በይት ማለት ዘካ (ግብር) አይበሉም:: የሚለውን ሀዲስ የሰማን ስንቶቻችን እንሆን? ኢራን ይህንን ስለምታቀነቅን የአህሉል በይት ወዳጅ ትመስል ይሆናል:: የእርሷም ፖለቲካዊ ነው::

መውሊድ ማክበር የተወደደ ብቻ ሳይሆን አጅር (ምንዳ) እንደሚያስገኝም ጭምር የተነተኑ ጉምቱ የቁርአን ሙፈሲሮች መኖራቸው ቂርአት ሰፈር የደረሰ ያውቀዋል:: ለዚያም ነው የሀገራችን የዒልም (እውቀት) የላይኛው እርከን ላይ የደረሱ ሰዎች በሀድራ ውስጥ እራሳቸውን እስኪስቱ ድረስ በነቢ ﷺ ፍቅር የሚሰምጡት::

የሚቃወሙት ግን መስጂድ ከመጡ ወይም ቂርአት ከጀመሩ ወራት ያስቆጠሩት ለምን ሆኑ? ብላችሁ እራሳችሁን መጠየቅ ነው:


የፈለገ ይታነቅ😆
===========
(አላህ በነቢዩ ﷺ ላይ ቀልድ የለውም)
እልቅናችን እና ክብደታችን የሚለካው እንዲሁም ድላችን የሚመጣው ለነቢያችን ﷺ ባለን ፍቅር ልክ ነው:: ቁርአን ነቢዩ ﷺ በነበሩ ወቅት ይወርድ ነበር:: ሲያልፉ ተቋረጠ:: የሙስሊሞች አንድነት ነቢዩ ﷺ በነበሩ ወቅት ነበር:: ሲሄዱ ግን ሄደ:: የነቢ ﷺ ፍቅር እና ክብር ሙስሊሞች መካከል የነበረ ጊዜ ድል እና ክብር ሙስሊሞች ዘንድ ነበር::

ፖለቲከኞች > ያሉ ጊዜ የሰዎችም የዓረቦችም ክብር ወደቀ:: በሁለቱም ዓለም እያሉ ድል ከነቢያች ﷺ ጋር ነው:: እሳቸውን ያዝ ታሸንፋለህ:: ሞተዋል ብለህ ተዋቸው:: ትዋረዳለህ:: ይህንን አላምንም ካልክ በሲባጎ መታነቅ ትችላለህ::

🕋
مَنۡ كَانَ يَظُنُّ اَنۡ لَّنۡ يَّـنۡصُرَهُ اللّٰهُ فِى الدُّنۡيَا وَالۡاٰخِرَةِ فَلۡيَمۡدُدۡ بِسَبَبٍ اِلَى السَّمَآءِ ثُمَّ لۡيَـقۡطَعۡ فَلۡيَنۡظُرۡ هَلۡ يُذۡهِبَنَّ كَيۡدُهٗ مَا يَغِيۡظُ‏
አላህ (መልክተኛውን) በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አይረዳውም ብሎ የሚያስብ ሰው ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋ፡፡ ከዚያም (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ፡፡ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግድለት እንደሆነም ይመልከት፡፡ ቁርአን 22:15🕋


የነቢያችን ﷺ ኑር (ብርሀን) የተቀላቀለበት ገላ በሌሊት ጭለማ ያበራል:: ቢሰግድ ቢጦም እንኳ የእሳቸው ኑር ከሌለው ፊቱ እንደ እንስሳ ፊት ክስክስ ያለ ነው:: ምሳሌው ለዘለዓለሙ የሚያበራ, የማያበራና የተቃጠለ አምፖል ማለት ነው::

የተለየነው እኮ በጦም በጠሎት ሳይሆን በነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ነው:: ብዙ ሶለዋትና ብዙ ሱጁድ ለሸክላው ገላችን መብራት ነው:: መስመሩ በምላስና በልብ መካከል ነው:: አላህ ከፈጠራቸው ርቀቶች ሁሉ ከምላስ እስከ ልብ ያለው ርቀት ይበልጣል ይባላል:: የአማኝ ልብ የአላህ ቤት ነው ይላል ሀዲስ:: እርሱን መስበር ካእባ ከመስበር ይልቃል::

ካስተዋልነው የልባችን ቅርጽ የተንጠልጣይ አምፖል ቅርጽ ነው:: እያንዳንዱ የልብ ውዝዋዜ በዚክር ነው:: ልባችን ድቤ እየመታ "አሏህ, አሏህ, አሏህ, አሏህ, አሏህ" ይላል:: ከምላሳችን እስከ ልባችን (አምፖላችን) ድረስ ያለውን ረጅም መስመር በዚክር በሶለዋት እንዘርጋው:: ሁሌ እድሳት ይፈልጋል:: ኬብሎቹን ካጸዳንለት እና ከሸይጧን ሽፍታ ከጠበቅንለት አምፖሉ ይበራል:: ፊታችን ወገግ ይላል:: ስለዚህ በነቢያችን ﷺ ኑር ፊታችንን እናኒር!

አሏሁመ ሶሊ ዓላ ሙሐመድ ወዓላ አሊሰዪዲና ሙሐመድ ﷺ


ፈቃደኛ ሰዎች አግዙኝ
ደመወዝ ከአላህ ብቻ ፈልጋችሁ ካልሆነ
ግን አትምጡ:: ደመወዝ አኼራ ላይ ተሳሰቡ
============================
በአላህ ፈቃድና እገዛ በፋይናንስ ላይ ከፍተኛ ጥያቄ, ውይይት, ክርክርና ብዥታ መፍጠር ተችሏል:: አልሀምዱሊላህ:: (በቴሌቪዥን ለምን ማቅረብ እንዳልተፈለገ አሁን ይገባችሗል)

አሁን ደግሞ መልስ እና መላሽ ማዘጋጀት ነው:: በግሌ ጀምሬው ኮረና አስቆመኝ:: ይህም በግል የሚሠራ ስለነበር ነው:: ምክንያቱም መጅሊሱ ላይ በስንት ልፋት የተቋቋመው እና 26 አባላት ያለው የዑለማ መማክርት almost ፈርሷል ማለት ይቻላል:: ብዙ ነገር ያቀል የነበረውን ጉባዔ ምሁራን ተብዬ ቦርዶች በተኑብን:: ብሔርተኞችና ጥቅመኞች ዋኙበት:: አንዳንዶች ድግሞ ዱንያ አታለለቻቸውና ወደ ባንክ "የትርፍ ነፃ" መስኮት ተቀጠሩ:: ስለዚህ ዳግም መንደር ለመንደር ኢማሞችና ዑለሞች ፍለጋና "ተሽኪል" ውስጥ ገባሁ:: ምክንያቱም ስለወለድ ያላቸው አመለካከት Traditional ነው:: "ወለድ ሀራም ነው እናትን ከመገናኘት ይከፋል" እያሉ ማስቦካካት ማንም አያቅተውም:: ወለድ እኮ እንኳን ኃይማኖት ያለው ይቅርና ኮሚዩኒስትም ሀራም መሆኑ ያውቃል:: የምንፈልገው ይህንን አይደለም:: የባንክ ብድር ሀራም ነው ወይ? ስትላቸው ወይ ይሸሹሀል, ወይ አስደንግጠው ይሸኙሀል ወይ "የምትበላው አጣህ ወይ?" ይሉሀል:: ጥያቄህ ግን እርሱ አይደለም:: የምትበላው ብታጣ እዚያ ምን ወሰደህ?

እና እያወቁት ግን በግል ይፈራሉ:: 26ቱ ዑለማ ሥራ ላይ ሆኖ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፈትዋ ተሰጥቶ ምእመኑ ከቆፈን ይወጣ ነበር:: እዚህ ጋር በአንድ ሰው የሚሠራ ሥራ አይደለም:: ገንዘብ, ጉልበት, ቀናነት እና ሙሉ ለሙሉ ሊላሂ ማለት ይፈልጋል:: ወሏሂ አቅሜን የተፈታተነ ደረጃ ደርሷል::

በኢስላም ስም ምእመኑን የባሰ ዋርጣ ውስጥ የሚከቱና በአንድ ረድፍ ለጥቃት የሚያሰልፉ ሙስሊም ጥቅመኞች በቀኝ, በሀገር ሀብት የተቋቋሙ, ሰፊ መሠረት ያላቸውና በባለሥልጣናት ጭምር የሚደገፉ 16 ግዙፍ ባንኮች በግራ ሆነው ነው ትግሉ:: እዚህ ጋር ሁለት ወይም ሦስት ብንሆን እኮ እነዚህ ሁሉ ኢምንት ነበሩ:: ዕውነት ሲመጣ ብክለት ይወገዳልና:: አብረኸው የምትቀራ አንድ ሰው እንኳ እንዴት ይጠፋል?
=========
ምሳሌ:- ቀጣይ ሥራ ምን መሰላችሁ? ጥያቄውን ወደ ኢማሞች, ዑለሞችና ፉቀሐዎች በየአድራሻቸው ማድረስ ነው:: ምክንያቱም የጋራ ጽሕፈት ቤት የላቸውም:: ጥያቄ ተፈጥሮ የለ? መላሽ ማዘጋጀት ነው:: የእኔ ምላሽ በቂ አይደለም:: ሕዝቡም አይፈረድበትም:: ሲወለድ ጀምሮ የሚያውቀው የተሳሳተውን ነውና::


የብዙ ትዳር መፍረስና ልጅ አለመውለድ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ኢብሊስ (ሸይጧን) ነው:: ከምንገምተው በላይ ሲህር (ድግምት) እየተደረገ ነው:: ሩቅያ (ሩቃእ) ቤቶች ጭራሽ ንግድ አድርገውት ሸይጧን ያዟዙራሉ:: ከሸይጧኑ ጋር አብረው ድርጅት ይከፍታሉ:: "ሸይጧን ይመስገን ሥራ ጥሩ ነው" የሚሉ ይመስለኛል:: አላህ በሸይጧንና በእነርሱ ላይ በላእ ያውርድ::

መውለድ ያልቻላችሁ የማኅፀን ኦፕሬሽን ባታሰሩ ይመከራል:: ቀድማችሁ ታማኝ ሸይኾች ጋር ሩቅያ አስቀሩ (ድግምቱን አስከሽፉ):: አላህ ልጅ ይረዝቃችሁ::

ድንገተኛ የጸባይ ለውጦች ወይ ሲህር ነው ወይ የሸይጧን ጉትጎታ ነውና ትዳራችሁን ከሸይጧን ጠብቁ::


ፍሬንዴ ታዲዮስ ሁሴን ኪሮስ መኪና መግዛት ቢፈልግና ኢስላማዊ ባንክ ቢሄድ መጀመሪያ ለዋስትና የቤት ካርታ ሊኖረው ይገባል:: ከዚያ ታዲዮስ መኪናውን ከሙሀመድ ዓለዊ ሙደሲር መደብር ይስማማና ስምምነቱን ባንክ ይዞ ይሄዳል:: ኢስላማዊ ባንክ ,, ሊብሬውን በባንኩ ስም ያሰራና ለሙሀመድ ዓለዊ ይከፍላል:: ባንኩ መልሶ ለታዲዮስ ሁሴን በዓመት 9% ሪብህ አትርፎ በዱቤ ይሸጥለታል:: ታዲዮስ የባንክ መኪና ይነዳል:: ታዲዮስ በሦስት ዓመት ለመክፈል ከተስማማ 9% x3 = 27% ለባንኩ ትርፍ ይከፍላል:: በአምስት ዓመት ከሆነ 45% ሪብህ መክፈል ግዴታ ይገባል:: በተባለው ጊዜ ካልከፈለ 5% መቀጫ ይጨመርበታል:: ሙሉ ከፍሎ ሲጨርስ ሊብሬ በስሙ ይሠራለታል:: (ብዙ ጊዜ ይህንን ይዘሉትና ሊብሬ ቀድሞ በስምህ ይሠራና ግን ባንክ ይቀመጣል:: 90% የዓለም ኢስላማዊ ባንኮች የሚሠሩበት የሚሉት ይህንን ነው:: አሠራሩ ይህ ካልሆነ እኔ ልቀጣ:: ሙራባሀ ፊቅህ ውስጥ እንኳ አታገኙትም::

ከወለድ ጋር ልዩነቱ ስትላቸው
- የኢስላማዊው 9% ሲሆን ያኛው 16% መሆኑ (ድንቄም😆 ወንድሜ እኩል ናቸው)
- የኢስላማዊው መኪና ሲገዛልህ ያኛው ብር ወስደህ እራስህ ትገዛለህ (እና የቱ ይሻላል? አሃሃሃሃ)
- 5% ቅጣት ለNGO ይሰጣል (ለማንኛው NGO?)
============

የኢስላማዊው ጉዳት
- ታክስ ሦስቴ ትከፍላለህ:: ወይም ታጣለህ: ከታክስ ሕግ ጋር ይጋጫል
- ለቀሪው ብድር መኪናው ተሽጦ ባያወጣ ባንኩ ቤትህን ሽጦ ዕዳውን ይወስዳል::
- ብር ወስደህ እራስህ መወሰን አትችልም:: በባንኩ ውሳኔ ነው የምትኖረው

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብትሄዱ የኢስላማዊው ብድር አለ:: መደበኛው ግን አታገኙም:: ምክንያቱም መደበኛው ርካሽ ነው::

መልካም ብድ ርርርርርር!


ኡመተ ኦሮሞ ኡመተ ታላቅ ሕዝብ ለጥንቃቄ ያህል

Guyyoota 2 Qofa (06/02/2013) ! Nootii isa duraanii qarshii kuma dhibba tokkoo hanga miiliyoona tokkoo fi kuma dhibba shanii (Qar. 100,000 hanga 1,500,000) maallaqa dheedhii (callaa) harkaa qabduu? Bultii lama keessatti Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaatti jijjiirradhaa! Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa Jijjiirama Guddaaf Kan Onnate!

ከኑማ


የሚሊዮኖች ብሮች ዕውቀት በነፃ (ከ16+ በላይ)
===============================
የወለድ ነፃ ባንኮች ወይም መስኮቶች ጥቅማቸው ምንድን ነው?

(ሀ)
- ከደሀ በነፃ የቁጠባ ገንዘብ ያገኛሉ:: 7% ወለድ መክፈል ሲገባቸው ለራሳቸው ሲያዞሩት እጥፍ (14%) ትርፍ ይሆናል:: ደሀው ግን በብሩ ሀብታሞች ሠርተውበት ድህነቱን ይዞ ይኖራል::

(ለ)
ከደሀ የሰበሰቡት ገንዘብ የዋስትና ማስያዣ ላለው ብቻ በ"ሙራባሀ" በአማካይ 9% ወለድ (ትርፍ ይሉታል) ያበድራሉ:: ይህኛው ከ16.22% ወለድ ጋር እኩል ነው:: ካልኩሌሽኑን ብዙ ጊዜ አስረድቻችሗለሁ:: ከ80% እስከ 90% የዓለም የኢስላማዊ ባንኮች አሠራር "ሙራባሀ" ነው:: ትርፍ ጨምሮ መሸጥ እንደማለት ነው::

በምሳሌ ሲገለጽ የመደበኛው ባንክ ብድ ር ማለት ልጅ ለመውለድ ሴትህን ከፊት በኩል ጉማዬ ማስጨፈር ሲሆን ኢስላማዊ የሚሉት ከሗላ በኩል ማለት ነው:: የፖዚሽን ምርጫው የእናንተ ነው:: "ባንኩኩም ሀርሱን ለኩም (ባንኮቻችሁ እርሻዎቻችሁ ናቸው)" ይለዋል ሪቻርድ ኒክሰን!

ሲጠቃለል ቆጣቢ በነጻ ያስቀመጠውን ባንክ ዓረቢኛ ቃላት ጨምሮ ለባለማስያዣ በአማካይ በ9% ሪብህ (ወለድ) ያበድረዋል:: 9% ሪብህ ከ16.22% ወለድ ጋር እኩል ነው:: ያተርፋል ሳይሆን ይዘርፋል:: በኢስላማዊ የተበደረ ቢያንስ ሦስት ጊዜ ታክስ አድቫንቴጅ ያጣል::


በድል ላይ ድል - ለእኔ
==============
ግልጽ ስድብ ለብቻዬ ስለምጎነጭ ድልም ላይ ለእኔ ማለቱ አይክፋችሁ:: ከከፋችሁ ደግሞ በጂማ በኩል አድርጋችሁ ወደ ከፋ!

ባንኮች ከወለድ ነፃ ብለው እስ-ላሙን ደህና አለቡት:: ምንም ፋኢዳ እንደሌለው ሄዶ አይቶት "ሀሰኖ አንተ ነበርክ ልክ" ማለት ጀመረ::

አሁን ደግሞ እነዘምዘም ባንክ ሲመጡ ሌሎች ንግድ ባንኮች ከወለድ ነፃ ብለው በስፋት ለማበደር እንቅስቃሴ ጀምረዋል:: አሁንም ትሰሙኝ እንደሆን አገኘሁ ብላችሁ አትበደሩ::

- ገንዘባችሁን በዓረብኛ ቃላት ሸንግለው በነፃ ወሰዱ
- ሞኙ, አሸባሪና አክራሪውን ለይተው በአንድ ቅርጫት ከተቱ
- ከዚያ አሁን ንብረታችሁን በነፃ ለመውሰድ አሰፍስፈዋል::
- ወዳችሁና ፈቅዳችሁ ከገባችሁላቸው በሗላ ማንም አያስጥላችሁም:: (ወደሽ ከተደፋሽ ቢ*** አይክፋሽ)::

============
የኢስላም የሚባሉ ባንኮች አሪፍ መናጆ ወይም ማጇኮሚያ ናቸው:: እና እኔ እንደሆን እየቆያችሁ "ሀሰኖ ልክ ነህ, ሀሱዬ እንዳልከው" የምትሉበት ዋዜማ ላይ ነኝ:: ልክ ሆኜ ከምትበሉ ተመችቶአችሁ ብሳሳት ደስ ይለኛል:: ከሁሉ ይበልጥ ግን ብንግባባ ይመቸኛል::


ዑለሞችን ስታገኙ የምትጠይቁዋቸው ሌላ ተጨማሪ ፈንጅ ጥያቄ

በወረቀት ገንዘብ ዘካ አለ? ካለ ኒሷቡ (Floor value መነሻ ዋጋ) ስንት ነው?

ዘካ ለማውጣት የሚባልበት "ኒሷብ" ይፈልጋል:: የዘካ አርካን ነው::

ምሳሌ: ግመል በቁጥር
-ከ5-9 ግመል ላለው ሰው አንድ ፍየል ወይም በግ
- ከ10-25 ግመል ላለው ሁለት ፍየል ወይም በግ
- ከ61-70 ግመል ላለው አምስት ዓመት ያለፋት ሴት ግመል ወዘተ

ወርቅ
20 ሚስቃል (ዲናር) ካለፈ,, ከ40 ዲናር አንድ ዲናር ይወጣል:: ሀያው ዲናር 85 ግራም ይመጣል::

ፊያት (የወረቀት ገንዘብስ?)
ከዚህ ያህል ብር ይህን ያህል የሚባል የለውም:: ምንም ዓይነት የቁርአን ወይም የሀዲስ ወይም የፊቅሕ ፍንጭ አላገኘሁም:: ፈተናውም እዚህ ጋር ነው:: በተለምዶ የሆነ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በወርቅ አዙራችሁ ክፈሉ ብሏል:: ለምን በስንዴ ኒሷብ አናነጻጽርም? ለምን በግመል ኒሷብ አንቀይስም? ለምን በወርቅ ተነጻጸረ? 😆😆


ከመቶ ብር እንነሳ? ወይስ ከሺህ? ወይስ ከሚሊዮን? ወይስ ከዶላር? ወይስ ከክሮነር? ወይስ ከየን? ወይስ ከናቅፋ?

መልሱ:- በአጭሩ ለመነሻ የወረቀት ገንዘብ እና ወለድ FIAT MONEY AND INTEREST ላይ አለላችሁ:: ይህ ርዕስ ብቻ ኃይለኛ ሪሰርች ይጠይቃል::


ባንክ ከወለድ ነፃ ሲያበድር ጥቅሙ ምንድነው?

መልስ:- በወለድ ከሚያበድረው እጥፍ ድርብ ወለድ ያገኛል::

መደበኛው ላይ ባንክ ወለድ ካገኘ ,, ከወለድ ነፃው ላይ ግን "አድአፈል ሙዷአፋ (እጥፍ ድርብ) ወለድ" ያገኛል::

ካልኩሌሽን ውስጥ አልገባም::
ክርስቲያኖች በከፈቱት ባንክ ለክርስቲያን ወንድማቸው በወለድ ለሙስሊሙ ግን በነፃ እንዴት ሊያበድሩ ቻሉ ብሎ የሚያስብ ጭንቅላት ያጣ ሰው ጋር ክርክር አያስፈልግም:: በደንብ ከተወገረ በሗላ "ሀሰኖ አንተ ልክ ነበርክ" ብሎ እስኪመጣ መጠበቅ ነው:: ሴቶቹም "ሀሱዬ ልክ ነበርክ እኮ" ብለው ይመጣሉ:: አህለን ወሳህለን! ግን ከአራት እንዳታልፉ::


የጉራጌ ፈላስፋ ሲናገር
በጣም ተምረህ ደሀ ከሆንክ የተማርከው ደሀ መሆኛ ትምህርት ቤት ነው:: በጣም ለፍተህ ከደኸየህ የሠራኸው የአህያ ድርሻ ነው:: ( ጉሪስጣጣሊስ )


ኢስላማዊ ባንኮች በስድሳ ዓመታት ውስጥ ለባንኪንግ ኢንደስትሪ ያበረከቱት አስተዋጽዖ
የሚሉ የዓረቢኛ ቃላት ብቻ ነው:: ከመደበኛው በብዙ እጥፍ ይብሳሉ:: ቢራን ብጹእ ወቅዱስ ጊዮርጊስ ብትለው ማስከሩ ይቀራል?

ከአስር ዓመታት በፊት "እኛም አለን ሙዚቃ ለዓለም የሚበቃ" የሚል ዘፈን ትዝ ብሎኝ በክርስቲያኖች እና ይህንን ቃላት በማያውቁ ሙስሊሞች እፎክር ነበር:: ምክንያቱም የምንሰማው ነገር ገራሚ ነው:: ውጮች ልክ ሳይሆኑ አይቀሩም የሚል ባዶ "ወህም" እንጂ መጽሐፍም አላነበብኩም:: ባንኩም ላይ አልሠራሁም:: ከዚያ ምንጫቸውን እና ምንነታቸውን የገባኝና ፕራክቲካል አሠራራቸው ያየሁ ጊዜ ግን ጂን እንደወጣለት ሰው አንዘፍዝፎ ለቀኝኝ:: ብዙ ጉጉ ሰው ሲለቀውና Factory setting ሲመለስ አየሁ::

በኢስላም ስም "አላህን የሚፈሩና ወለድን የሚጠየፉ ሰዎችን ማታለል" ዘገነነኝ:: ድህነቴን መረጥኩ:: በበረባሶ ብሄድ አይደንቀኝም:: ግን የሀላል ሀብት መንገዱ ቀላል ነው:: ለሸሪዓ ቅርቡ መንገድ "አርተፊሺያል ኢስላማዊ" አይደለም::

[የደረሰበት ይገባውና ያመሰግነኛል]::


ስለባንክ ወለድ ፈትዋ ስታነቡ ዘመኑን እና የአርጊዩመንት መሠረቱን እዩት::
August 15/1971 ማለት ወርቅ እየተቀመጠ ፊያት (ወረቀት) ሲታተም የነበረበትን አሠራር በዓለም አቀፍ ደረጃ የቀረበት, አዲስ የገንዘብና የዓለም አወቃቀር የታወጀበት, ከካሽ ቤዝ ወደ ክሬዲት ቤዝ የተኬደበት ቀን ነው:: ይህንን ቀን የሚያውቁት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው:: ፈትዋ ከመስጠትህ በፊት ቢያንስ ይህንን እጅግ ወሳኝና ታሪካዊ ቀን ማወቅ አለብህ:: በሰጠሀቸው ፈትዋዎች ሁሉ ታፍራለህ:: የአገር ኪታብ ቀርተናል ብለው ተወጣጥረው ለክርክር ሲመጡ ይህኛውን ጠጠር ስስብባቸው ይፈርሳሉ:: ይበተናሉ::
(ለበለጠ መረጃ Nixon Shock ብለህ ጎልጉል)


ዛሬ አንድ ባንክ ሄድኩና ስለብድር ሁኔታ ስጠይቀው > አለኝ::

አሁን ላይ ከባንክ መቶ ሚሊዮን መበደር ቀልድ ሆኗል:: ለዚህ ለአንድ ሰው ብቻ 5,000 ብር የሚቆጥቡ 20 ሺህ ደሀዎች ያስፈልጋሉ:: ከወለድ ነፃ አስቀማጭማ አይገኙም:: አሪፍ ጠቦት ናቸው:: እንዲህ ያለ ጅል በሰው ልጅ ታሪክ ተፈጥሮ አያውቅም:: ባሪያ መሆናቸውን እንኳ የማያውቁ ናቸው::

ምንም ዓይነት "ኢስላማዊ" የሚባል ባንክ ቢመጣ እንኳ ደሀ ይቆጥባል:: ድህነቱን ይቀጥላል:: ሀብታም ይበደረዋል:: በሀብት ላይ ሀብት ይጨምራል:: ለደሀው ምንም የሚሰጥ ትርፍ አይኖረውም:: ምክንያቱም አይተዋወቁም:: ባንኩም በኢስላም ስም አታሎ "ማሙሽዬ ሚሚዬ እዚህ አስቀምጡ" ይሏቸዋል::


ዘምዘም ልክ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በኤዚቢሽን ማዕከል አዳራሽ ሲፈርስ ያልኩትን እራሱኑ "Commercial Banking ከፍተዋል:: እዚህ ቦታ ለመድረስ 10 ዓመት ይፈጅባችሗል ይላል አስተያየቴ:: ቪዲዮ ካላችሁ እዩት::

እና እኔ የምደግፈው ይህንን ነው:: የሆነ የነቃ ሰው መካከላቸው አለ ማለት ነው:: ለመግባባት የግድ 10 ዓመት መጠበቅ የለብንም::


ስለብሔር እና ኢስላም ያለኝ አቋም
ብሔሬ ጉራጌ ነው:: ብሔሩም, ቋንቋውም እኔም የአላህ ነን:: ከዚህ ውስጥ እኔ የፈጠርኩት የለም:: እኔም የማጠፋው አይኖርም:: በመሆኑም ልበልና ወደ ምሳሌ ልሂድ
የእስልምና መጻሕፍት ከዓረብኛ ወደ ጉራጊኛና ኦሮሚኛ መተርጎም ቢያስፈልግ እኔ ገንዘቤንም, ጉልበቴንም, ዕውቀቴንም ለኦሮምኛ ትርጉም አውላለሁ:: ምክንያቱም ጉራጌዎች እስከ ገጠር ድረስ ዓማርኛ ያነባሉ, ይናገራሉ:: የዓማርኛ ሥራዎች በብዛት አሉ:: ኦሮሚያ ላይ ግን ከቆዳ ስፋቱና የሕቡ ቁጥር አኳያ ብዙ ሰው ዓማርኛን አያነብም:: ስለዚህ ኢስላም መዳረስ ስላለበት ቅድሚያ ለኦሮምኛ እሰጣለሁ:: በጉራጊኛ መተርጎም አስፈላጊ ቢሆንም ቅሉ በዚህ ምሳሌ መሠረት ግን የማስቀድመው የኦሮምኛውን ነው:: ይህ ጽኑ እምነቴ ነው::


ሙስሊሙን ማነው የካደው? (መንሁወ ኻኢን?)
===============================
በዚህ በአስ ዓመት ውስጥ የሚገራርሙ ክህደቶችን አይተናል:: ውሸት ነግሦ ዕውነት ኮስሶ, ሙፍቲ ተዋርዶ ጃሂል ተወዶ, ሐቀኛ ተነውሮ ነውረኛ ተከብሮ, ሙእሚንን ሙናፊቅ ሙናፊቅን የጀነት በር አሳላፊ ተደርጎ ተቀላቅሏል:: ስም እየጠሩ ፎቶ እየለጠፉ ሲያነውሩ ጂሀድ ,, በደፈናው ስንከላከል ክፍፍል, ያለሙያ የገባው አፈቀላጤ ሲታመን በሙያው መሠረት የሚጓዘው ሲወቀስ ብዙ ጉድ አይተናል:: > እንደተባለው::

ክፍፍል
1️⃣ሙስሊሙን "አህባሽ/ፀረ-አህባሽ" ብለው በሁለት ሰነጠቁትና የቀወጠ ረብሻ ተነሳ:: (ረብሻውን የጠነሰሰውም እስከ 2007 ድረስ የመራውም ሕወሓት ነበር:: ዝርዝሩን በቀጣይ እመለስበታለሁ)
2️⃣ ከ2007 እስከ አሁን ኦህዴድ እና ፓስተሮች እየመሩት ነው:: የሚያስፈልግ ቦታ ላይ የኢስላም ስም ሲደመር ሂጃብ የለበሰች ዘማሪት እና ጺሙን ሒና የተቀባ ፓስተር ያቀርባሉ::

እላይ 1 ቁጥር ላይ ሕወሓት ሙስሊሙን በሴክት (አህባሽ/ፀረ-አህባሽ) ብሎ ሲከፍለው ,, ቁጥር 2 ላይ ደግሞ በዘር ተከፈለ:: ቁጥር 1 ላይ ኢሕአዴግ ውስጥ የነበሩ ሙስሊሞች በብዛት ሲባረሩ ቁጥር 2 ላይ ኦሕዴድ ውስጥ የነበሩት ተባረሩ:: በመጨረሻም አብረው ወይም ተሸውደው ሲያስፈጽሙ የነበሩት በሀጫሉ ግድያ ወቅት ሲታሰሩ ,, ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአርሲ ሻሸመኔ ግጭት ምክንያት ,, የሙስሊም አመራሮችን ከዞንና ከወረዳ አጸዱ::

==========

- ኦሕዴድ ይህንን ተልእኮ ሲያስፈጽሙ ለነበሩ (ጆከሮች) መኪና, ኮንዶሚኒየምና የቤት መሥሪያ ቦታ ሰጥቶ ሸኛቸው:: ለከፊሎቹ የማይረቡ ቦታዎች ላይ ቦርድ አድርገው አስገቡዋቸውና ተኮላሹ::
- ኡስታዞቹ ሌላውን ለሚስፈራራት ሲሻቸው ከባለሥልጣናት ሲላቸው ከወታደሮች ጋር ፎቶ እየተነሱ ይለጥፉ ገቡ:: ምስኪን!
- ለዘመናት በሸይኾቻችን ሲተዳደር የነበረውን መጅሊስ በብሔርና በመዝሀብ ከፍለው አናጭተው ሲያበቁ ከጎን ኦሮሚያና ወሎ ላይ ዋናውን መጅሊስ ክደው ፌክ መጅሊስ አቋቁመ ፌክ ሙፍቲ ሾሙ:: "መን ሁወ ኻኢን?"
- ገረፈን ካሉ ሕወሓት ጋር ዞረው ገጥመው ከዘረኛ ፖለቲከኛና ፓስተሮች ጋር ሆነው ሀገርን መረበሽ ውስጥ ገቡ::
- ታጋይ ነን የሚሉ ዱርዬዎች,, በሰበብ ባስባቡ የሙስሊሙን ኪስ እያጠቡ ከተረፋቸው ውስጥ ዲቃሎችን በመቅጠር ነውረኛ ሥራ ማሰራቱን ተያያዙት:: ሀገር ምድሩ የሚያከብራቸው ሙፍቲን መዝለፍ የለት ተለት ሥራ አደረጉ::
- ዑለሞቻቸው 26 አባላት ያሉት የዑለማ ኮሚቴን ትተው ባንክ ተቀጠሩ::
- ቦርዶቹ ከኡስታዞች ጋር በመተባበር ከዑለሞች ተገንጥለው የሀጅ ዘረፋ ውስጥ ተዘፈቁ
- በመጨረሻም ባለፈው ሳምንት መኪና ጥለው ፈረጠጡ:: መቸም አድብተው ይመለሱ ይሆናል::
============

-ሙስሊሙ ያለው አማራጭ በዑለሞቹ ስር መሆን ነው:: "አንድ እንሁን" ተብሎም ዑለሞቻችንን አዋርዶም ,, ታዲያ አንድነቱ ከኢብሊስ ጋር ካልሆነ ከማን ጋር ነው?

ወይ ከሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ ወይ ከእርጉሙ ኢብሊስ መሆን ምርጫው የእናንተ ነው::

-የሀገር ሰላም የሙስሊሙም ሰላም ነው:: ምክንያቱም ችግር ከመጣ በልጆቻችን, በቤተሰባችን, በነፍሳችን እና በንብረታችን ይመጣል:: ስለዚህ ይህ ከቅድሚያ አጀንዳዎች ነው::
- እስልምናችንን ለዘርም ለፖለቲካም መስዋዕት አናደርግም:: የፈለገ ወይ ለኢስላም ወይ ለዘር ይታገል:: የተመቸህ ረድፍ ላይ ተሰለፍ:: ሁለቱም ላይ ልሰለፍ ካልክ ትበለቀጣለህ::

ከፖለቲከኛ ጋር የሚያሴረውን ለኢስላም የሚሠራ ,, በንጹሕ ሕሊና በነፃ የሚሠራውን የሚያሴር አድርጎ መሳል ያበቃ ይመስለኛል:: ኻኢን ተለይቷል::

Показано 20 последних публикаций.

1 381

подписчиков
Статистика канала