ኸይር መሥራትና መናገር ባንችል እንኳ ዝም ማለት መቻል አለብን። ዝምታም በራሱ ኸይር ነው። ያኔ በትንሳዔ የሥራ መዝገባችን ሲቀርብ በድንጋጤ «
ይህ ምን አይነት ጉደኛ መጽሐፍ ነው ትንሿንም ትልቋንም ልቅም አድርጎ የያዘብን ምንድን ነው? የምንልበት ቀን ሳይመጣ ቀድመን
ትርፍ ቃላችንን መቀነስ ኸይር ነው። ከእኛ ጋር ያሉት መዝጋቢ መላእክት ዝም ካላልን በቀር ቃላችንን ለመጻፍ አንዲት ሰከንድ አይደክሙም።
❝ ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡❞ (ሱረቱ ቃፍ 17-18)
አቡ ሑረይራ(ረዓ) እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው
መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል»። «በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው ጎረቤቱን በምንም አያስቸግር፣ እንግዳውንም ያክብር»። (ቡኻሪ 6475)
t.me/IbnuHashm