. ꧁
﷽ ꧂
. ╔═════ ❁✿❁ ══════╗
. 2⃣ ተውሂዱል~ኡሉሂያ
. ╚═════ ❁✿❁ ══════╝
2⃣ والنوع الثاني : توحيد الألوهية : وهو إفراد الله تعالى بأنواع العبادة التي شرعها من الصلاة والصيام والحج والزكاة والدعاء والنذر والنحر والرغبة والرجاء والخوف والخشية إلى آخر أنواع العبادة، فإفراد الله تعالى بها يسمى بتوحيد الألوهية، وهذا النوع هو المطلوب من الخلق.
2⃣ ተውሂዱል~ኡሉሂያ:- ማለት እሱም አላህ በአምላክነቱ ብቸኛ መሆኑን ማወቅና ማመን ነው።
ይህም ሊረጋገጥ የሚችለው አማኞች የሚሰሯቸውን መልካም ስራዎች ለምሳሌ፦ ሶላትን፤ ፆምን፤ ሐጅን፤ ፀሎት፤ ስለትን፤ ውዴታንና የመሳሰሉትን መልካም ስራዎች ሲያከናውኑ ፍጹም ለአላህ ብቻ አድርገው ሲሠሩ ብቻ ነው።
ከአላህ ሌላ ማንንም ሼይህም ይሁን ወልይ አንለምንም ምክንያቱም አላህ እንዲ ስላለን፦
🍃 { وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا } ( النساء :36)
“ አላህንም ተገዙ በእርሱም ምንንም አታጋሩ ” (አል-ኒሳእ፡ 36)
አላህ በሌላ አንቀፅ ላይም እንዲህ ይላል፡-
🍃 { وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لا إِلَهَ إِلا أَنَا فَاعْبُدُونِ }( الأنبياء :25) .
“ ከአንተ በፊት ማንኛውንም መልእክተኛ አላክንም እነሆ ከእኔ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም። ስለዚህ እኔን ብቻ ተገዙ የሚል መለኮታዊ ራዕይ ወደ እርሱ ያወረድን ቢሆን እንጂ ” (አል-አንቢያእ፡25)
አላህ እንዲህ ይላል፡-
🍃 وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ
ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ።
ከአላህ ሌላ በአምልኮ ጉዳይ ሌላ ማንንም መፍራት እንደሌለብን እንዲህ ይላል፦
🍃 ُفَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡
መመካት በአላህ ብቻ እንደሆነ፦
🍃 وَعَلَى اللَّهِ فَتَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
ምእመናንም እንደኾናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ» አሉ፡፡
እርዳታ እሱን ብቻ መጠየቅ እንዳለብን፦
🍃 إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
መጠበቅ ስንፈልግ በአላህ ብቻ እንጂ በሌላ በሸይሆች ይሁን በማንም መጠበቅ እንደሌለብን፦
🍃 قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ
በል በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡
ይህ የተውሂድ ክፍል የአላህ መልክተኞች ባጠቃላይ የተላኩበት ዋና አላማ ነው።ሁሉንም ነቢያቶች የዳዓዋቸው ዋና ተልዕኮ አምልኮን ባጠቃላይ ለአላህ ብቻ ማድረግ (ተውሂደል ኡሉሂያ)ነው።
ማስረጃው
🍃 وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوت
َ
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡
ይህ የተውሂድ ክፍል በእያንዳንዱ ነቢይ ዘመን ህዝቦች ሲያስተባብሉ የነበረው ይህ ነው።
ለምሳሌ፦በመልክተኛው ዘመን የነበሩ ሙሽሪኮች ነቢያችን የውሸት አማልክት ትታችሁ አንድ አላህ ብቻ አምልኩ ሲሉዋቸው፦
🍃 أَجَعَلَ الْآلِهَةَ إِلَٰهًا وَاحِدًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيْءٌ عُجَابٌ
«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው» አሉ፡፡በመልክተኛውም ተሳለቁ።አላህ በእየ ዘመናቱ ከላካቸው ነቢያቶች (ሷሊህ፤ኑህ፤ሁድ፤...)ጥርያቸው ይህ ላይ በከፍተኛ ትኩረት አድርገው ነበር፦
🍃 لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
«ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»እያሉ እያሰጠነቀቁ ነበር
ውድ አምባቢያን በዚህ ርዕስ ላይ አብዛኛው ማህበረሰባችን አቅጣጫ ስቶ በወልይ ስም፤ ለድንጋይ፤ ለጂን፤ ለዛፍ፤ ለዛር፤ ለቆሌ፤ ለአድባር፤ ለአብሬትዬ፤ ለቃጥባሬ፤ አብዶዬ እያለ ህዛባች ምንም ለማይጠቅሙ እና ለማይጎዱ አካላት ለአላህ ብቻ የሚገባው አምልኮ አሳልፎ ለሌሎች እየሰጠ በሽርክ ላይ እየተድበሰበሰ ይገኛል ትኩረት ልናደርግበት ይገባል።
ፓለቲከኞች ህዝባችን አምልኮት ከአላህ ውጭ እየሰጠ እያዩ በሂክማ ስም ተዋቸው ጊዜው አሁን አይደለም ተውሂድ ተውሂድ እያልክ ህዝቡ አታጨናንቀው የሚሉት ፓለቲከኛ እንጂ እውነት ለህዝቡ ያዘኑ እንዳይመስላችሁ ነቃ ልንል ይገባል።
🎟 እንደዚህ ከሆነ እንዴት ብቸኛና ቢጤ ከሌለው ከአሏህ ጋር ፍጡርን እናመሳስላለን?
o الدال على الخير كفاعله
. ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
👇 ምንጭ:-
👉🌐
https://t.me/Ibnu_Akil_Official_Channel/10🌼͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͡͡͡ ͜͜͜͡͡🌼