🕊 ዛሬ ቀኑ 27 ቸሩ መድኃኔዓለም🙏🏻❤️
«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው። ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።
ምን ዓይነት ፍቅር ነው???🥹
ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለ እኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው። ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።
ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት። እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያደርጉትን አያውቁምና
አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር። ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን
በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል። ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን።"ሳይኖረን በክብር የሚያኖረን
የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ መድኃኔዓለም ነው። ቸሩ መድኃኔዓለም ጥበቃው ማዳኑ በረከቱ አይለየን በእውነት ♥
🌹
በቀኙ ያኑረን የዓለሙ ቤዛ🙏❤