ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


☞︎︎︎ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቻናል

ምን ፈልገው አጥተዋል❓
➪ ትምህርቶች
➪ የተለያዩ ጽሑፎች
➪ አጫጭር አስተማሪ ታሪክ
➪ መጣጥፎች
➪ ግጥም
➪ ወግ
➪ ይቀላቀሉ
👉 ለወዳጆ ይጋብዙ

አስተያየት ካሎት ግሩፑን ይቀላቀሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የስራበትን መንገድ ስታይ ስው ክቡርነው፤
የተፈጠረበትን አፈር ስታይ ስው ከንቱነው።"
ቅዱስ _ባስልዮስ


በፈተና የጸና ፣ በማጣቱ ያልተማረረ ፣ በቅድስና የከበረ ፣ አፉ ከምስጋና ያልተቋረጠ ፣ ሁለንተናውን ለእግዚአብሔር የሰጠ ፣ ሰይጣንን ድል የነሣ ፣ መምህረ ትዕግሥት ቅዱስ ኢዮብ።

[ የከበረች በረከቱ ትድረሰን ]


[ © ቀሲስ ጌትነት አይተነው ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖


በስመ አብ ወወልድ ወመንስፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
  እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
  
  እያቄም ወሃና ወለዱ ሰማየ፣
  ወሰማዮሙኒ አስረቀት ጸሐየ።

መንፈሳዊ ግጥም

👉ቅኔ_ልቀኝልሽ

ልጀምር መወድስ ልጀምር ምስጋና፣
ታስበሽ ለኖርሽው በእግዚአብሔር ሕሊና።
ቀዳሚዊው አዳም ከእግዚአብሔር
ተጣልቶ፣
         ወረደ ወደ ምድር አንቺን አነግቦ።
ወለድሽለትና ዳግማዊውን አዳም፣
አውጥተሽ ከአሮንቃ አኖርሽው በለምለም።
             የአቤል ደግነት የሴት ቸርነቱ፣
             አንቺ ነሽ ምስጢሩ ለላሜህ እረፍቱ።
ንፂህት መስታወት የፍጥረታት መልክ፣
ከርከቤደል ነሽ ወላድተ አምላክ።
             አንቺ የኖህ ርግብ የማቱሳላ ዕድሜ፣
             እፀ ሳቤቃችን ልቀኝልሽ ቅኔ።
የሰሎሞን አትሮንስ የኤልሳ ማሰሮ
ፍጹም ላይመለስ  ጠፋልን እሮሮ።
       ይጠለሉብሻል የሰው ልጅ ከወጀብ
         ከጎፈር እንጨት ኖህ በሰራው መርከብ፣
ኖህ ከነልጆቹ ከንፍር ወጣና፣
ሀሴት አደረገ በልቡ ተፅናና፣
ድንቅ ምልክት በሰማይ አየና።
          የሕይወት መናን የያዘች ደመና፣
          አመተ ምህረት ሊገባ ሲል ገና፣
          ብቅ አለች በምስራቅ ጥምን ልታረካ።
የዘላለም ምግብ የያዘች ደመና፣
ሰማይን ወለዱ ኢያቄም ወሐና።
       አማናዊ ዝናብ ከድንግል ዘነበ፣
       የደረቀችን ነፍስ በፍቅሩ አጠገበ።
በኃጢያት ለሚኖር በድቅድቅ ጨለማ፣
ድህነት ተጀመረ ምስራች ተሰማ፣
መጣ የድኅነት ድምፅ ከላይ ከራማ።
           ኃያላን መላእክት የሚያጫውቱሽ፣
           ምድራዊ ጎረምሶች የማይጎበኙሽ፣
            የሕይወቴ ምስጢር  ድንግል ልዩ ነሽ።
    የሰው ልጅ በሙሉ በኃጢያት ሲኖር፣
    መጣችለትና ታቦተ ዘዶር፣
     አውጥታ አኖረችው በገነት ምድር።
ከሰው ልጅ ራቀ ጥንተ አብሶ ጠፋ፤
ንፂህት በሆነችው በማክሰኞ እርሻ።
          የምድር አርያም በሕይወቷ አብባ፣
          ተራራው እፅዋቱ ሆኑልን እንጀራ።
ከአርያም ይልቅ ይረዝማል ስፋቱ፣
ማሕፀነ ድንግል የአምላክ ዙፋኑ።
      እናትም ድንግልም ሙሉ በክልኤ፣
      ይደንቃል ግሩም ነው ልቀኝልሽ ቅኔ።
ተነግሮ አያበቃም አምላክ የሰራልሽ፣
ድንግል ሁነሽ ሳለ እንደት ህፃን ወለድሽ።
            ሰሜኑን ደቡቡን ምሥራቅ ምዕራቡን
          ፈለገ አሻተተ አምላክ ማደርያውን
በረዶና እሳት አንድ ላይ ወረዱ፣
ስጋና መለኮት በድንግል አንድ ሆኑ።
             ሱራፌል ኪሩቤል ይሸፋፈናሉ፣
             በእሳተ መለኮት እንዳይቃጠሉ።
ይህን ሁሉ አይተው እነ አባ ጊዮርጊስ፣
እነ ቅዱስ ኤፍሬም ቅኔ ቢቀኙልሽ፣
እረ በምን በምን እንመስልሽ ቢሉሽ፣
ተቃጥለው ነደው ነው በእናትነት ፍቅርሽ።
                   የአብ ሙሽራ የወልድ ወላድቱ፣
                   የመንፈስ ቅዱስ ፅርሐ ቤቱ፣
                   ቅኔ ልቀኝልሽ እንደ ሊቃውንቱ።

                
"ልደትሽ ልደታችን ነው!"                 
       
    ገጣሚ፦   ዲ/ን ኃይለ ማርያም

በማርያም ሼር link በማድረግ ያስተላልፉ
https://t.me/yetewahedofera


የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄድ ጀመሯል !

" ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያናችን እንደ ቤተክርስቲያን ፣ ሕዝባችንም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡

በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል ፤ የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል፡፡ "


[ ቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬


የአምላኬ እናት ዛሬ ተወለደች ሁሉም ሰምቶ ደስ ይበለው || መምህር ዘበነ ለማ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የአምላኬ እናት ዛሬ ተወለደች ሁሉም ሰምቶ ደስ ይበለው || መምህር ዘበነ ለማ


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ መግለጫ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተሰጥቷል። ቅዱስነታቸው በትግራይና በኦሮሚያ ስለተፈጠሩ ችግሮች ምልዓተ ጉባኤው ይወያያል ብለዋል። እንደ ሕዝብ ለደረሰብን ችግር እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልህ መሆን አለብን ሲሉ አሳስበዋል። አሁን እየታየ ያለው ግጭት እንዲቆምም አሳስበዋል።
ሙሉ መግለጫውን ከላይ አያይዘናል።

ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/yetewahedofera




ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እየሰጠ ነው። ይጠብቁን።


_ቅዱስ ሲኖዶስ መልሶ ቢያጤነው_
25ቱ የባለፈው ሕገወጥ ተሿሚዎች በአሁኑ ሲኖዶስ እንኳንስ ለኤጲስ ቆጶስነት ሊታጩ የነበረ ክህነታቸውም ተሽሮ በምእመንነት እንዲኖሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ሊወያይበት ይገባል። እነ አባ ሳዊሮስ የተመለሱበት መንገድ ክርስቲያናዊ አይደለም። የቤተክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ካስቀመጠው የቀኖና አካሄድ ይልቅ በዐቢይ አሕመድና በሽመልስ አብዲሳ አማካኝነት በተስማማነው ስምምነት ነበር የሚለው። የአሁኑ ሲኖዶስ ጉዳዩን እንደገና በቀኖና ለክቶ እነ አባ ሳዊሮስን እና 25ቱን የሹመት ጥመኞች ወደአቶነታቸው ቢመልሳቸው መልካም ነው። በእነርሱ ምክንያት ምእመናን ተገድለዋል፣ አካላቸው ጎድሏል። በእነርሱ ፊት ለመቆም አያፍሩምን!? ንስሓ አልገቡም። ቢጸጸቱና ይቅርታ ቢጠይቁንኳ በምእመንነት ይኖራሉ እንጂ ከሹመታቸው ተሽረው እንደሚቀሩ የሚከተሉት የሐዋርያት ሲኖዶሶች ይገልጻሉ።
                             ።
አንድ ኤጲስ ቆጶስ ባጠፋው ጥፋት ምክንያት ከተወገዘ በኋላ ከውግዘቱ እስኪመለስ ምንም ዓይነት የክህነት ሥራ መሥራት የለበትም። ከሠራ ግን የሚከተሉት ቀኖናት እስከመጨረሻው እንዲሻር ያዝዛሉ። (እነ አባ ሳዊሮስ ከተወገዙ በኋላ የክህነት ሥራ ሲሠሩ እንደነበርና የጵጵስና ልብስም እንዳላወለቁ እናውቃለን)። ትእዛዝ ፲፯:- በታወቀ ኃጢአት ምክንያት በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስም ቢኖር ቄስም ቢኖርና ከተሻረ በኋላ ከመሻሩ በፊት በክህነቱ ይሠራ የነበረውን ሥራ ሲሠራ ቢገኝ ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን ይራቅ። ሥርዓተ ጽዮን ቁጥር ፳፯:- በታወቀ በደል በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖርና ቀድሞ በተሰጠው ሥልጣን ለመሥራት ቢደፋፈር እስከዘለዓለሙ ድረስ ከቤተክርስቲያን ይሻር። አብጥሊስ ፳፯:- ባደረገው በደል ከቤተክርስቲያን ያስወጡት ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ከተሻረ በኋላ ከመሻሩ በፊት ይሠራው የነበረውን የክህነት ሥራ ሲሠራ ቢገኝ እስከመጨረሻው ከቤተክርስቲያን ይሰናበት። ቀሌምንጦስ ቀኖና ፳፯:- ባደረሰው በደል ምክንያት ሥልጣኑ ተይዞ ከቤተክርስቲያን የተባረረ ኤጲስ ቆጶስ ከተወገዘ በኋላ ውግዘቱን አቃሎ በክህነት ቢያገለግል እስከመጨረሻው ከቤተክርስቲያን ይሰናበት።
                               ።
ቤተክርስቲያን የወንበዴ ዋሻ መሆን የለባትም።
©በትረ ማርያም አበባው
https://t.me/yetewahedofera


በዚህ ወቅት ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን መሾም በቤተ ክርስቲያን ላይ ተጨማሪ መከራ መጫን ነው። በዚህ ወቅት ቤተ ክርስቲያን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ናት።
ምእመናንን እየተገደሉ ነው።
አብያተ ክርስቲያናት እየፈረሱ ነው።
ካህናት እየታረዱ ነው።
አብነት ትምህርት ቤቶች እየደረቁ ነው።
አህጉረ ስብከት በባእድ እጅ ተይዘዋል።
ቤተ ክርስቲያን በፖለቲከኞች እጅ ሥር ናት።
ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያን ፈተና ጉዳይ ሊመክር ይገባዋል እንጂ ለፖለቲከኞች ደስታ ሲባል ሕግ መተላለፍ የለበትም።
የግንቦቱን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እቃወማለሁ!

ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/yetewahedofera






ከመፈንቅለ ሲኖዶሱ ይልቅ የግንቦቱ ሹመት የከፋ ነው!

መፈንቅለ ሲኖዶሱ ሕገ ወጥነቱ የታወቀ በመሆኑ በምእመናን ሰማዕትነት፣ በእውነተኛ አባቶች ጸሎት እና ጥበብ ከንቱ ሆኖ ቀርቷል። ይህ መፈንቅለ ሲኖዶስ ቅርጹን ቀይሮ በሕጋዊ ሹመት ስም እየመጣ ነው።
የግንቦቱ ሹመት ሕገ ወጥ ግለሰቦች በሕጋዊነት ስም የሚሾሙበት፣ የቤተ ክርስቲያን ልዕልና እውነተኛ ባልናቸው አባቶች የሚጎድፍበት፣ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ያለበት መሆኑን በሚገባ አረጋግጠናል።
በዚህ ሹመት ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እስከ ዳንኤል ክብረት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ናቸው። የኦሮሚያ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች፣ የወንጌላውያን እና የብልጽግና ወንጌል አራማጆች ፊታውራሪ ናቸው። ጎጠኞችና ፖለቲከኞች ተሿሚዎች ናቸው።
ሕገ ወጥ ጳጳሳት ከኦሮሚያ ተነሥተው ትግራይ ድረስ በመሄድ ካኮረፉ አባቶች ጋር ጥምረት ፈጥረዋል። ተሿሚ ግለሰቦች ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ጋብቻ ፈጽመዋል። የሲኖዶሱ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከጠሚ ዐቢይ እና ከዳንኤል ክብረት ጋር እጅ እና ጓንት ሆነዋል።
ትናንት በመግለጫ ያነቡ መነኮሳት፣ በዓደባባይ ሕገ ወጡን ቡድን ያወገዙ ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል።
እየሆነ ያለው ሁሉ ከባድ ድራማ ነው። ደራሲው እና ተዋናዮቹ ተናበዋል። ዳይሬክተሩ ስኬት ላይ ነው። ተመልካቹ ግራ ተጋብቷል።
ግራ ያጋባን ድራማ እስከሚከሽፍ ድረስ ዝም አንልም!

ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/yetewahedofera


የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በእያንዳንዳችን እጅ ነው!

ሥርዐት ጠብቀን የምንማጸናቸው አባቶች ድምጻችንን ለመስማት የተዘጋጁ አይመስሉም። ከሚሞቱላቸው ልጆቻቸው ይልቅ ማዕበል የሚያናውጠውን የፖለቲካ ትርፍ ለማዳመጥ ጆሯቸውን አዘንብለዋል። ከገዳማውያን ይልቅ ብሔርተኞችን ተቀብለዋል። ከዋልድባ እስከ ማኅበረ ሥላሴ፣ ከጣና ቂርቆስ እስከ ደብረ ሊባኖስ የተማጸኑ ድምጾች ቦታ አጥተዋል። አባቶች የጀመሩት ኢቀኖናዊ አካሄድ ቤተ ክርስቲያንን የሚደፋፈር ቅጽሯን የሚያፈርስ ነው። ከነዮዲት፣ ከነግራኝ እና ከውጭ ጠላቶች ጥፋት ቀጥሎ የሚመጣው ቀኖናዊ ጥሰት በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ የታሪካችን ጠባሳ ሆኗል።
ምንም እንኳን መፍትሔው እየከረረ እና እየጠነከረ ቢሄድም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ይህንን ሕገ ወጥ ሹመት መከላከላችንን እንቀጥላለን። ተቃውሟችንን እና ድምፃችንን ንቀው ፖለቲካዊ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በሚያካሂዱ አካላት ግን እጃችን መጠንከሩ ልባችንም መጨከኑ የግድ ነው። ቤተ ክርስቲያን በውጭ ኃይሎች ስትደፈር ከሞትን በውስጥ ፖለቲከኞች መሠረቷ ሲናጋ ዝም እንል ዘንድ አይገባንምና። ቤተ ክርስቲያን በሁላችን እጅ ናት እና አጥብቀን እንያዛት።

ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/yetewahedofera


               †               

ሆደ-ሰፊነት ትርጉም ያለው በግል ጉዳይ እንጂ !

🔔

ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያን እና እግዚአብሔር ለወገኖቹ የደለደለውን ርስት የሚመሩ ጳጳሳትና የመንግሥት መሪዎች የግል ንብረታቸው አስመስለው "በሆደ ሰፊነትና ታጋሽነት" ስም እረኝነታቸውን ያለ አግባብ መጠቀሙን ፈጽሞ እንዲያቆሙ ሊነገራቸው ይገባል።

ሆደ-ሰፊነት ትርጉም ያለው በግል ጉዳይ እንጂ በአገርና በቤተክርስቲያን ኃላፊነት ወስደው ያለ ቦታው የሚነገር  የግል ምቾትና ድሎት ፣ ሥልጣንና ዋስትና ማስጠበቂያ አይሁን ! 

ይህ በቤተክህነትና በቤተመንግሥት እየተለመደና ሕዝብ እያስጠፋ ያለው አካሄድ የወንጀልና ኃጢአት መደበቂያ ፣ ከኃላፊነት መሸሺያ እየሆነ  መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን በነፍስም በሥጋም እየተቀበልን ለምንገኘው መከራ ፣ ስደትና ሞት ዋና መንስዔ እንደሆነ አምናለሁ።

ምእመን ነኝና ስለቤተክርስቲያን ፣ እንዲሁም ዜጋ ነኝና ስለ አገር ፣ መሪዎች ይመለከተኛል።

መሪነት ኃላፊነት እንጂ ድሎት ፣ ምቾትና ዝና መገንቢያ ከይደለም። ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ መኳንንትና ሚኒስትሮች የመናገር ፣ የመጠየቅና የመቆጣት መብቴ ሙሉ ነው። ሌላውም እንደዚሁ።

እንወያይ። ለሚመለከታቸው ሁሉ መልእክት እንላክ። መስማት ይማሩ ፣ ይለማመዱ !!

[ መ/ር ፋንታሁን ዋቄ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬


"ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት በሚጀመረው የርክበ ካህናት የሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ዋና ዋና መልእክቶቻቸውን አስቀምጠውበታል ብዬ የማስበው አንቀጽ የሚከተለው ነው።

"...በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር፣ የመምከርና የማስታረቅ ኃላፊነት የእኛ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ዛሬ የተሰበሰብነው የተሰጠን አምላካዊ ተልእኮ ምን ያህል በተግባር አከናውነናል? ምን ሰርተናል? ምንስ ይቀረናል? ተልእኮአችንን ለመፈጸም በምናደርገው ጉዞስ ምን ችግር አጋጠመን? ችግሩን ለመፍታትስ ምን እናድርግ? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች በማንሣት በዝርዝርና በጥልቀት በማየት ተልእኮአችንን በኣግባቡ ለመወጣት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናም ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የረክበ ካህናት ዓቢይ ጉባኤ እንዲደረግ ያዘዘበት ዋና ምክንያት ይህንን እንድናደርግ ነው፡፡

ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያናችን እንደ ቤተክርስቲያን፣ ሕዝባችንም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡

በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፤ የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!
ጌታችን፡- “እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ” ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል፡፡በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡

በተለይም በትግራይና በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል፡፡ በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል፡፡

እኛ ያጐደልነው፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፡፡ ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም፡፡የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡"

በዚህ የቅዱስነታቸው መልእክት ውስጥ ያልተዳሰሰ መሠረታዊ ነገር ባይኖርም ችግሮቹ ስለሚፈቱበት መንገድ ካቀረቧቸው የመፍትሔ ሀሳቦች መካከል ሁለቱ ትኩረቴን ስበውታል። አንደኛው በኦሮሚያ እና በትግራይ ቤተ ክህነቶች የሚነሡት ጥያቄዎች ከቤተ ክህነቱ አልፈው የሕዝብ ጭምር ስለሆኑ መፍትሔ መስጠት አለብን የሚለው ነው። ሁለተኛው ደግሞ መፍትሔው "የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱን እና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄያቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፣ ጉዳታቸውንም መክፈል ይገባናል" የሚለው ነው።
ጥያቄ መቀበል እና ጉዳት መካፈል የሚሉት እንኳን ለልጆቿ ለማንም ብታደርገው የሚጠቅማት እንደሆነ አምናለሁ። እኔን የቸገረኝ ግን ቀኖና በመጣስ ፖለቲካዊ መብት ተደርጎ የሚቀርብ ጥያቄ ሃይማኖቱን እና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ እንቀበለው የሚለው እንዴት እንደሚታረቅ ነው። እውነቱን ለመናገር የእኛ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓመት የገጠማት ሁኔታ ፍርስርሷ እንዲወጣ የታቀደበት ይመስላል። አንዳንዶች በተንኮል እንደሚያስቡት እና ሞኞች እንደሚያደርጉት እንድትፈርስ ሳይሆን የተንኮለኞች ምክር እና የሞኞች ድርጊት ፍርስርሱ ወጥቶ ቤተ ክርስቲያን የምትነሣበት እንዲሆን ጠባቂዋ ክርስቶስ በቸርነቱ ያድርገው።


🔔

የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም [2015] ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል !

በቤተ ክርስቲያናችን በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚካሔዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የሆነው የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤም ከዛሬ ጀምሮ ጉባኤውን የሚያከናውን ይሆናል።

[ TMC ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️
🏆 ግንቦት_3

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ ❖

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሦስት በዚች ቀን ጌታ ከመረጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ያሶን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን በሰበከ ጊዜ ብዙ መከራዎችን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተቀበለ ድንቆች ተአምራትንም አደረገ በሃምሳኛው ቀን ከሐዋርያት ጋራ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏልና።

ትውልዱም ከጠርሴስ አገር ነው ከጠርሴስም ሰዎች አስቀድሞ አመነ ሐዋርያ ጳውሎስም ከተጠራና ከአመነ በኋላ በብዙ አገሮች ተከትሎ በወንጌል ትምህርት አገለገለው በተሰሎንቄ ከተማም ከጳውሎስ ጋራ ይዘው በመጐተት ከተሰሎንቄ ገዢ ዘንድ አቀረቡአቸው።

ከዚህም በኋላ በጠርሴስ አገር ቅዱስ ጳውሎስ ኤጲስቆጶስነት ሾመው የወልደ እግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን በመልካም አጠባበቅ በቅንነት ጠበቀ። ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ከአጸናቸውና በጎ ምግባርን ከአስተማራቸው በኋላ ከዚያ ወደ ምዕራብ አገር ሒዶ በውስጥዋ የከበረ ወንጌልን አስተማረ። ስሟ ኮራኮራስ ወደምትባል ደሴትም ደርሶ በውስጧ ወንጌልን ሰበከ እግዚአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው በዲያቆናት አለቃ በሰማዕታትም መጀመሪያ በከበረ ሐዋርያ እስጢፋኖስ ስም በውስጧ ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው።

የዚያች አገር ገዥም በአወቀ ጊዜ ይዞ ከእሥር ቤት አስገባው በዚያም ሰባት ወንበዴዎችን አግኝቶ ሃይማኖትን አስተማራቸው በክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው። ከዚያም በኋላ በመኮንኑ ፊት ቁመው እኛ ክርስቲያን ነን በክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ዝፍትና ዲን በተመላ ምጣድ ውስጥ አግብቶ አቃጠላቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶንን ከእሥር ቤት አውጥቶ ብዙ አሠቃየው ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። የንጉሡም ልጅ ከቤቷ መስኮት ሁና አይታ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነች ልብሶቿንና ጌጦቿን አውጥታ ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠችና ከዚያም በሐዋርያው በያሶን አምላክ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ታመነች አባቷም ሰምቶ እንዲአሥሩዋት አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ። በጢስም አፍነው አሠቃዩዋት ደግመውም አራቈቷትና አባቷ በፍላፃ ነደፋት ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶንን ወደ ደሴት ሰደደው በደሴትም ውስጥ ያሠቃየው ዘንድ መኰንኑ ከሠራዊቱ ጋራ አብሮ በመርከብ ተሳፈረ እግዚአብሔርም ከሠራዊቱ ጋራ በባሕር አሠጠመው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶን ወንጌልን እያስተማረ ብዙ ዘመናት ኖረ። ሁለተኛም ሌላ መኰንን ተሾመ ቅዱስ ያሶንንም ይዞ በምጣድም ውስጥ ድኝና ዝፍት ሰም መልቶ ነበልባሉ ወደ ላይ እስቲወጣ ድረስ ከበታቹ አነደደ ቅዱስ ያሶንንም በውስጡ ጨመረው። የክብር ባለቤት ጌታችንም አዳነው ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም መኰንኑም ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተሰቡ ሁሉ ከሀገር ሰዎች ሁሉ ጋራ አመነ። ሁሉንም አጥምቆ የከበረ የወንጌልን ሕግና ትእዛዝ አስተማራቸው አብያተ ክርስቲያንም ሠራላቸው በውስጣቸውም ብዙ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ብሩህ በሆነ ገድሉ ጌታችንን ደስ ካሰኘውና ካገለገለው በኋላ በበጎ ሽምግልና አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

🏆 አርኬ
ሰላም ለከ ያሶን ረዳኡ
ለወልደ ማርያም ድንግል መጥበቤ ሕጻናት ስምዑ
ለጢገነ እሳት ወተይ ወዑይ ዘኢያሕመመከ ፍልሐተ ቅብዑ
ለወለተ ንጉሥ ሰላም ዘምስለ ፈያት ሰብዑ
እለ በእዴከ አምኑ ወጥምቀተ ነሥዑ

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ አባ ብሶይ ❖

በዚችም ቀን ዳግመኛ ከቤልጌት ሰዎች አባ ብሶይ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህንንም ቅዱስ በመናቅና በማቃለል ሰውነቱን በማጣመምና በመቆልመም አሠቃዩት የእግዚአብሔር መልአክ በእጁ አክሊል ይዞ አትፍራ ጽና እነሁ በእጄ ውስጥ አክሊል አለ አለው።
ደግሞም ብዙ አሰቃይተው ወደ እሳት ጨመሩት ተጋድሎውንም በዚህ ፈጸመ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

🏆 አርኬ
ሰላም ለአባ ብሶይ በላህበ ማኅቶት ዘውዕየ
እነዳ ገጹ ፍጹመ እስከ ተላጸየ በዝንቱ አክሊል ዘውስተ እዴየ
እኬልለከ መልአክ እንዘ ይብሎ አመ በርእሱ ወደየ
በዋዕየ እሳት ፈጸመ ገድሎ ሰናየ

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ ንግሥት ወለተ ማርያም ❖

ዳግመኛ በዚህ ቀን ኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቡርክት ወለተ ማርያም ትታሰባለች::

ወለተ ማርያም ማለት የደጉ አፄ ናኦድ ሚስት: የአፄ ልብነ ድንግልና የቅድስት ሮማነ ወርቅ እናት ናት:: በንግስትነት በቆየችባቸው ዘመናት (ከ1487-1500 ዓ/ም) የረሃብ ጊዜ በመሆኑ ብዙ ሕዝብ አልቆ ነበር::

ቡርክት ወለተ ማርያም ከጾምና ከጸሎት ባሻገር የተራቡትን በማብላት ብዙዎችን ታድጋለች:: የንጉሡን ቤተሰብ ወደ መልካም ክርስትና በመምራትም የተመሰገነች ነበረች:: በዚህ ቀንም አርፋ ተቀብራለች::

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ በዚችም ቀን ደግሞ የከበረ ቀሲስ አውሳብዮስና የሰማዕት ቅዱስ ሴም መታሰቢያቸው ነው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

❖ ግንቦት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያሶን ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት አንዱ)
2.አባ ብሶይ ሰማዕት
3.ቅዱስ አውሳብዮስ ቀሲስ
4.ቡርክት ወለተ ማርያም ንግሥት (የዐፄ ልብነ ድንግል እናት)

❖ ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3፡ ካህናት ዘካርያስ ወስምዖን
4፡ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5፡ አባ ዜና ማርቆስ
6፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
7፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
8፡ ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ

🏆 ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው ጌታ ሆይ! አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት:: እንዲህም አላቸው . . . እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችሁአለሁ:: የሚጐዳችሁም ምንም የለም:: ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ:: ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ::
🌹ሉቃ.10:17

🌹 ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🌹
🌹 ወለወላዲቱ ድንግ 🌹
🌹 ወለመስቀሉ ክቡር 🌹

🏆🏆🏆 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት


✝  ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።

   መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና #እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።
    
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

Показано 20 последних публикаций.

386

подписчиков
Статистика канала