Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ይሄ ቆሻሻ ቅጠል ወገናችን ላይ ያደረሰው ግፍ አንድና ሁለት አይደለም።
① የስንቶችን ዐቂዳ አፈር ድሜ አብልቷል።
② ስንቱን ባለትዳር አባልቷል።
③ የስንቱን ጤና አናግቷል።
④ የስንቱን ኢኮኖሚ አድቅቋል።
⑤ የስንቱን ወጣት ህይወት አጥፍቷል።
⑥ በዐረብ ሃገር በሰው ቤት የሚዳክሩ የስንቱን ወገኖቻችንን ላብ ከንቱ አስቀርቷል።
⑦ ስንት መስራት፣ ስንት መድረስ የሚችሉ ጀግኖቻችንን ወኔያቸውን አፍስሷል።
ጫት:–
* ወኔው የላሸቀ፣
* አእምሮው የዛገ፣
* ነገን ቀርቶ ዛሬን የማያስብ፣
* ይሉኝታ ቢስ፣
* አጉል ጀብደኛ፣
* "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" የሚል አህያዊ መርህ የሚያራምድ፣
* ለቤተሰብም፣ ለወገንም፣ ለሃገርም ሸክም የሆነ ከንቱ ፍጡር ነው የሚያፈራው።
ጫት የስንቶችን አእምሮ ነክቷል። አማኑኤል ሆስፒታል ለዚህ ምስክር ነው። በየሰፈሩ ግማሽ እብድ ግማሽ ጤነኛ የሆነውን ወፈፌ ቤቱ ይቁጠረው። ስንቶች አሉ በዐረብ ሃገር ያሉ ልጆቻቸው፣ ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው ብር እንዲልኩላቸው እየወተወቱ ተዘፍዝፈው ቅጠል የሚያኝኩ። በስንት መከራ የተገኘን ገንዘብ፣ ሽንት ቤት ጠርገው፣ በእሳት ተለምጥጠው፣ ክፉ ደጉን አይተው፣ ነጭ ላብ አፍስሰው፣ ህይወታቸውን ቤዛ አድርገው የሚያገኟትን ገንዘብ ስጋነት ይዟቸው፣ የቤተሰብ ህይወት አስጨንቋቸው ሲልኩ በማመስገን፣ ለቁም ነገር በማዋል ፋንታ እንደ ዋዛ ቁጭ ብለው ይህን ቆሻሻ ቅጠል በውድ ገዝተው ሲያደቁበት ስታዩ ጫት ምን ያክል ለልጅ፣ ለእህት፣ ለወንድም፣… መቆርቆርን፣ ርህራሄን እንደሚገድል ታያላችሁ። ምን ያክል ይሉኝታ ቢስ ፍጡር እንደሚያደርግ ትረዳላችሁ። ምን ያክል የወገንን ላብ ቀርቶ ደም ለመጠጣት የማይመለስ አውሬ ፍጡር እንደሚያፈራ ትመለከታላችሁ።
ጌታዬ ሆይ! ይህንን መርዝ ከአገሬ አጥፋው። ወገናችንን ልብ ስጠው። ኣሚን።