" ዓብዱረህማን ዑመር"


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


#ሀቅን_ትተህ ሠውን የምትከተል ከሆንክ አልቆልሀል ዘወር በልልኝ! በአሏህ ፈቃድ "እስላማውይ ትምህርቶች፣ግጥሞች
የሚለቀቁበት #የቴሌግራም_ቻናል ይቀላቀሉ ለሌሎችም ይጋብዙ
👇
t.me/Abdurhman_oumer
اتقي ربك فإن لم تكن تراه فإنه يراك

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አድስ ወሳኝ እና ጣፋጭ ደዕዋ

👌 በሰለፎች መንገድ እንጓዝ

🎤 በ ኡስታዝ ሱልጣን

ክፍል አንድ

👍 ወራቤ ዳሩል ሂጅረተይን መስጂድ የተደረገ ሙሓደራ

ወሳኝ ለግዜያችን አስፈላጊ ሙሓደራ ስለሆነ ለዑማው እንዲዳረስ ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም

ኡስታዙን በፊትም በአካል አውቀዋለሁ በሱና በተውሂድ ጠንካራና በጣም ጣፋጭ አንደበት ያለው ከሸይኽ አብደል ሀሚድ አንጋፋ ደረሶች ውስጥ አንዱ ነው

ማሻ አላህ ድምፁ ከሸይኽ አብዱል ዓዚዝ አረይስ ጋር ይመሳሰላል!

መንሀጅም አንደበትም ሲያምር ደስ ይላል እያጣጣማችሁ ስሙት

✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2133


ለወንድም ኸድር አህመድ አል ኬሚሴና ለመሰሎቹ አድርሷት

ባለፈው ኮሞቦልቻ ሸይኸ አቡ ዘር በመጡበት ሰዓት በጣም አሰተማሪና ገሳጭ ትምህርት ሰጥተው ስለነበር ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ያነን ትምህርት አቅጣጫውን ለማስቀየር

ለሱና እየታገሉ ያሉ ወጣቶችን በሌሉበት ሲወነጅል፦
ወጣቶች ልክ በራሳቸው ተነሳሽነት ሰዎችን ሙብተዲዕ እያሉ እንደሆነ አስመስሎ ሲያቀርብ

በድፍን በዛ መልክ በጣም ከወነጃላቸው በሇላ

ነገር ግን በዝርዝር ያነሳው ነጥብ ወጣቶች ሠዎችን ሙብተዲዕ ሱንይ ማለታቸውን ሳይሆን

ጭራሽ ዝም እንዲሉ የሚኮረኩም ነበር
ይህ ደግሞ ድሮ ኢኽዋኖች ጥፋታቸው እንዳይነገርባቸው በጊዜው ጠንካራ የነበሩ ተማሪዎችን (እነ ሳዳት ከማልን) ዝም ለማስባል ሲጠሩ የነበሩበት አካሄድ ነበር

ዛሬም ኸድር አህመድ ባለችው ሸቀጥ ሰዎችን ዝቅ የሚያደርግበት አጋጣሚ አድርጎ ይዞታል

በጣም አሳዛኙ በርካታ ሰዎች
በዚህ የተሳሳተ አካሄድ በጭፍን ሲከተሉት ይስተዋላሉ

ለማንኛውም ይሄን አስተማሪ የሆነ ሸይኽ ረቢዕን በቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን መልስ ላኩለት
👇

السؤال :
بعض الناس يبالغون في إسكات المحذرين من المبتدعة، ويقولون: إن هذا عمل العلماء؟

قال الشيخ ربيع حفظه الله :
على كل حال هؤلاء غلوا في إسكات طالب العلم، غلوا جداً، وكلام فيه إرهاب وإلقام الشباب أحجاراً في أفواههم ليمنعوهم قول الحق في أهل البدع.
بالغوا في هذه الأشياء، الآن في مسائل خفية، أنت طالب العلم لا تتكلم فيها بغير علم، وهناك أمور واضحة جلية، وجوب الصلاة وجوب الصيام وجوب الزكاة وجوب الحج تحريم الاستغاثة تحريم التوسل هذه الأمور واضحة يتكلم فيها العالم وطالب العلم وهناك أمور خفية تحتاج إلى اجتهاد، هذه توكل إلى العلماء، أما كل شيء !

طيب ابن باز وابن عثيمين والألباني وغيرهم من العلماء المعتبرين لا يذهبون إلى أوربا وأمريكا، يكفيهم هناك طلاب العلم ، يتكلمون في حدود ما يعلمون، أما النوازل فلا بد أن يسألوا عنها العلماء عن طريق الوسائل المتاحة اليوم، فكل واحد يبلّغ الذي عنده، إذا سألوك في أمور تخفى عليك فقل:والله هذه خفية وتحتاج إلى علماء أكبر مني، أنا أسأل.

أما الأمور الواضحة فبينها بشرط أن تكون عالماً بها وبأدلتها، لا تتكلم بجهل، إذا كان-حتى والأمور واضحة- ما عندك أدلة لا تتكلم بها، إذا كانت الأمور واضحة وعندك فيها أدلة تتكلم وتبين، هناك أمور معلومة من الدين بالضرورة يتكلم فيها طلاب العلم ، يعني مثل الاستغاثة بغير الله من الأمور الواضحة﴿مَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ﴾﴿وَلَا تَدْعُ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنْفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ﴾
إلى آخره ، عنده أدلة يبين؛ رأى شيعياً رأى صوفياً يطوف بقبر، يستغيث، يذبح، ينذر، هل يقول: أنا أتوقف عن بيان هذا الباطل والتحذير منه، وأنتظر حتى يأتي أحد كبار العلماء ليقوم بهذا الواجب؟
أقول:إن هؤلاء يريدون أن يسكتوا الشباب السلفي خاصة، لأن أكثر الناس إنكاراً للمنكر ووقوفاً في وجه الباطل هم الشباب السلفي.رأيتم؟!
هؤلاء السياسيون يتعاطفون مع الراوفض، مع الخوارج، مع أهل البدع كلهم، لا يريدون أن تجرح مشاعرهم، فيأتون بمثل هذا الكلام يقولون:
-ما يتكلم به إلا العلماء!.
-حتى الأطفال يتكلمون؟!
-حتى الذي ما يحسن الفاتحة يتكلم!.
ويبالغون في تشويه الشباب السلفي! كل هذا محاماة [عن] أهل البدع، وصد عن سبيل الله، وإرهاب للشباب السلفي الذي يتصدى للدعوة إلى الله والأمر بالمعروف والنهي عن المنكر.

ونحن نقول للشباب السلفي:
أنتم يا إخوتاه لا تتكلموا بغير علم، القضايا الواضحة عندكم التي عندكم فيها أدلة تكلموا فيها، والأشياء الخفية لا يجوز لكم أن تخوضوا فيها، نقول لهم هذا، ثم نقول:ادعوا إلى الله، كل واحد يدعو بقدر ما عنده من العلم، يقول رسول الله صلى الله عليه وسلم:((بلغوا عني ولو آية))(1)

(1) / أخرجه البخاري في " أحاديث الأنبياء" حديث (3461)، وأحمد في "مسنده" (159/2)، والترمذي في "جامعه٦" حديث( 2669).
المصدر : ( من كتاب عون الباري ببيان شرح السنة للإمام البربهاري / لفضيلة الشيخ العلامة ربيع بن هادي عمير المدخلي -حفظه الله- / الجزء الأول، الصفحة 423 )


بسم الله وبعد :

الحق احق ان يتبع
እውነትን ሊከተሉት ይገባል !!
=============================
የተከበራቹ የሰለፈ ሳሊሕ መንሀጅ ተከታይ የሆናችሁ እህት ወንድሞቼ በመጀመራ እኔንም እናንተንም አለሀን በመፍራት እመክራለው ከዚህም በመቀጠል ወደ ↓↓↓↓↓↓↓↓
•••••••••••••• ነሲሓ •••••••••••••
ምናልባት ነሲሓን በ1000 እናሻግር ሊላቹህ መስሏቹህ ግራ እንዳትጋቡ

የኔ (ነሲሓ) ለመላው ሙስልሞች በተለይ የሰለፈ ሷልህ መንሀጅ ተከታይ ለሆናችሁ በሙሉ ይሆናል (በተለይ የሰለፈ ሳልህ መንጅ ተከታዮች) ያልኩበት ምክንያት ሁሉም ሙስሊም የሚከተለው መንሀጅ 1 ስላልሆነ ነው ለዛም ነው ተላላቅ ዑለማዖች ሁሉም ሰለፍይ ሙስልም ነው ነገር ግን ሁሉም ሙስልም ሰለፍይ አይደለም የሚሉት ወደ ነሲሓዬ ሲመለስ ሁላችንም እንደ ምናውቀው ባሁን ሰዐት ፊትናዎች ከሌላ ግዜ በተለየ መልኩ እያገረሹ መተዋል ከፊትናዎች አንዱ ና ዋነኛው ( ለሐቅ ሳይሆን ለግለ ሰብ ወገንተኛ መሆኑ ነው) በዲናችን ከዚህ በላይ ፊትና ዬለም ለማለት ወደኋላ አልልም ምክንያቱም ሀቅን ትተን ለግለ ሰብ ከወገንን ያ ሰው አለህ አያድርገዉና ቢከፍርም ከሱ ጋ ለመሆን ወደኋላ አንልም በገሀድ ከብዙዎች እንደ ምናስተውለው ነገር ግን የሰለፎችን ፈለግ መከተል ከፈለግን ሰዎችን በሐቅ እንመዝን እንጂ ሐቅን በሰዎች መመዘን ዬለብንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አንሁን!። ምክንያቱም የታዘዝነው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድንከተል አይደለም። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውረናል እንጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልነው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ እኛም አብረነው ገደል እንዲንገባ ምክንያት ይሆነናል ጭፍን ተከታይ አኒሁን።

ندور مع الدليل حيث دار ، ولا نتعصب للرجال ، ولا ننحاز لأحد إلا للحق
- التوسل أنواعه وأحكامه 48 -
ታላቁ የሀዲስ ምሁር አልባኒይ (ረሒመሁላህ) ትክለኛ ማረጃ በዞረበት አብረን እንሽከረከራለን ለግለ ሰብ ወገንተኛ አንሆንም ለማንም አንጎተትም ለሐቅ እንጂ (📚 አልተወሱሉ አንዋዑሁ ወአሕካሙህ 48 📚)
ቆም ብለን እናስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውረን!። ነገ አላህ ፊት ወዳጆቻችን ጠላታችን ሊሆኑብን ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል

الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ (سورة الزجرف 67)
«ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ናቸው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67
ወገኖቼ በተከታይ ብዛት ልንታለል አይገባም ቀደምት ኡለማዖች የመጥፎዎች ብዛት አይግረምህ እንደዚሁም የጡሩዎች ማነስ አያሳስብህ ይሉ ነበር ኣንዴ ኡመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) የሆነ ሰው መንገድ ላይ ስሄዱ
اللهم اجعلني من عبادك القليل
አለህ ሆይ ከትንሽ በሪያዎችህ አድርገኝ ብሎ ዱዓ ስያደርግ ሰምተው አንተ ይህን ዱዓ ኬት ነው ያመጣሀው ብለው ጠየቁት እሱም
إن الله يقول في كتابه العزيز: (وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ)[ سبأ: 13]
አለህ አሸናፊ በሆነው መፅሓፉ እንድህ ይላል ከባሮቼ አመስጋኞቹ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሰበዕ 13
ከዛም ኡመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሁሉም ሰው ከኔ በተሻለ መልኩ ይገነዘባል ብለው ማልቀስ ጀመሩ ይህ ማለት ከቁርዓኑ እንደ ምንረዳው ብዙዎች ሐቅን እንደ ማይከተሉ ብዙዎች ከሐቅ ያራቁ መሆኑን ነው
ወገንተኝነት አያጥቃን፣ ለሐቅ ብቻ እንወግን! ሐቅ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረን እኛም ሆንን የምንወደው ዳዒ አለያም ከጎናችን ያሉ ወዳጆቻችን መንገድ ስህተት ከሆነ ወደ ሐቅ ለመመለስ አናንገራግር የተነገረን እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑረን። ምክንያቱም ወገንተኛ የምንሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው ﷺ በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው ﷺ እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ እንሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሐቁ ካልተገለጠልን ደግሞ እስኪገለጥልን ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነን በአደብ እንፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግነው ኢን ሻ አላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይናል
አለህ ሐቅን ሐቅ መሆኑን ይግለፅልን የምንከተለዉም ያድርገን
ባጢልን በጥል መሆኑን ይግለፅልን የምንሪቀዉም ያድርገን ።

✍ ወንድማቹህ ሙሰፋ ኢብኑ ጀማል ከሳንኩራ 1443 ጁማደል አኺር 15

ከይቅርታ ጋር ወንድማችን ቻናል የለውምና በሠው ፁሁፍ የራሴቻናል ሞክሬው ባላውቅም👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/2001


ይህ የቴሌግራም ቻናል የታላቁ ሸይኽ የሸይኽ አብዱል ሀሚድ ያሲን የልጃቸው ቻናል ነው።
አላህ ያሳደግላቸው በርሳቸው ቦታ የሚተካ ለሱና ታጋይ ለተቃራኒው ለቢድዓና ለባለቤቶቹ ደግሞ የማይበገር ያድርገው
ጠቃሚ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች ይለቀቅበታል ተቀላቀሉ
👇
@abdulhalimibnushayk
@abdulhalimibnushayk
@abdulhalimibnushayk


👆👆👆👆👆
ትላንትና ዛሬ አቋምህ አንድ አይነት ሁኖ ስታገኘው
የሌለ በመደሰት ታላቁና ብቸኛ አምላክህን አላህን ታመሰግናለህ አልሀምዱ ሊላህ

እንደ አጋጣሚ ቻናሌን ስፈትሽ
የዛሬ ሁለት አመት የፃፍኳትን አንድት ፁሁፉ ሳገኛት ግርም አለኝ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/658
👆
በትክክለኛ መርህ ተደግፈህ ስትናገር ንግግርህ የመጭውን ነገር ትንቢት የተናገርክ ይመስልብሃል! እኛ ሳናስበው የሆነ ነገርን እንናገራል እንጅ የመጭውን ሁሉ የሚያውቀው ታላቁ አምላካችን አላህ ብቻ ነው።

ጠንቋዩ ሁሉኮ አንድ ቀን እንደ አጋጣሚ የተናገረው ሲከሰት ነው ዘላለም ሰው የሚያጠምበት አዑዙ ቢላህ

እና የዛኔ ጠንካራ የነበሩ፡ሰዎች ዛሬ ተገልብጠው ሳይ! የኔ ነገር በጣም አስፈራኝ ዋናው የመጨረሻችን ነገር ነውና በራሳችን ላይ ከመገለባበጥ መፍራት አለብን

✍ አብዱረህማን ዑመር


ሀይማኖታቸው እና በዓላቸው
ከሰላም ጋር ያለው እርቀት!!
➖➖
➖➖➖➖➖➖➖

አዋጅ ስማ! ዛሬ በክርስቲያኖች የጥምቀት በዓል ምክንያት ደሴ አረብ ገንዳ መንስጅ በጥይት ተመታ!

አል ሀምዱ ሊላህ
ለአላህ ምስጋና የተገባው ነው።
ሰላም ወደ ነገሰበት እስልምና ሀይማኖት የመራን ለሆነው ጌታ!!

ስለሙ ሰላም ትሆናላችሁ የሚባለውኮ አንዱ ለዚህም ሲባል ነው።

ክርስቲያኖችን አትፍረዱባችው
ይሄን እዲል አላገኙምናኮ ነው!
👇
አላህ እንዲህ ይላል
يَهْدِي بِهِ اللَّهُ مَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَهُ سُبُلَ السَّلَامِ وَيُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِهِ وَيَهْدِيهِمْ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
, ትርጉም
{{አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል፡፡ በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፡፡ ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል፡፡}}]
[ ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 16 ]


አዎ! ክርስቲያኖችንም ሆኑ በአጠቃላይ ከእስምና ውጭ ያሉ አካላቶችን እንኳን መስጅድ በጥይት መምታት ቀርቶ ሌላም የሰሩትን ቢሰሩ አትፍረዱባቸው
ምክንያቱም ይሄን አያውቁምና ነው
👇
አላህ እንዲህ ይላል
۞ لَهُمْ دَارُ السَّلَامِ عِندَ رَبِّهِمْ ۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
, ትርጉም፦
{{ (አማኞች) ለእነርሱ ከጌታቸው ዘንድ የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡}}
[ ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 127 ]

ነገ ጀነት (ገነት) መግባት እንዳለለት የሚያውቅ አንድ አማኝ የሆነ ሠው፦
አሰካሪ መጠጡን ጠጣጥቶ ሞቅ ሲለውና በበዓሉ ምክንያት በርካታ ሰዎች ተሰብስበው ሲመለከት አጉል ተደናፍቶ ቤት መስጅድ ለማቃጠል አይሯሯጥም።


አዎ! ከእስልም ሀይማኖት ውጭ ያሉ አካላቶችን በፍፁም አትፍረዱባቸው
ምክንያቱም ይሄ ታላቅ አምላክ መኖሩን ስለማያውቁ ነውና!
👇
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَىٰ دَارِ السَّلَامِ وَيَهْدِي مَن يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
. ትርጉም
{{አላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡}}
[ ሱረቱ ዩኑስ - 25 ]


ግን ይህ ከመሆኑም ጋር የእስልምና ሀይማኖት የሰላም ሀይማኖት ነውና አንደፈለግን እንጫዎትበት ባትሉ ጥሩ ነው።

ሀገሪቱን የምታስተዳዲሩ የመንግሥት አካላቶች ምነው በየ ወቅቱ በሙስሊሞች የአምልኮ ቦታዎች (መስጅዶች) ላይ ጥቃት ሲደርስ እናንተም ቁማችሁ እያያችሁ ነውን? ወይስ ወደ የት እልም ብላችሁ ጠፍታችሁ ነው?? እነዚህ አክራሪና አሸባሪ ክርስቲያኖችኮ ወቅት እየጠበቁ ጥቃት ሲያደርሱ በሚስጥር ከእናንተ ፈቃድ የተሰጡ ነውኮ ሚመስሉት! እባካችሁ ሌላው ባያሳስባችሁም (የግዛት) እድሜያችሁ እንዲጨምር ብላችሁ እንኳ ከጥፋት ብትቆጠቡና አጥፊዎችን እጃቸውን ብትይዙ መልካም ነው። ያዙ!

ስንት ጊዜ ደግመን ደጋግመን እንናገራለን! እስልምናን በመንካት ትልቅ ወንጀል ውስጥ አትግቡ ምክንያቱም
👇
አላህ እንዲህ ይላል

أَوْ يُوبِقْهُنَّ بِمَا كَسَبُوا وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ

' ትርጉም
{{ (አላህ) በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት ያጠፋቸዋል፡፡ (ያውም) ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡ }}
[ ሱረቱ አል-ሹራ - 34 ]


✍አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2126


👆👆👆
#በቀድሞዎችና
በአዲሶቹ ሙመይዓዎች ላይ የተሰጠ መልስ

🎙 በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ደሴ (አላህ ይጠብቀው)

🌐 https://t.me/shakirsultan




የተብራራ መልስ
, በድፍኑ ለሚከስ

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ለማያውቅህ ንገር እኛ አንሰማህም
ታውቆህ እንደሁ ግጥሙ ቤት አልመታልህም
ከጫፍ ቃላቱ እንጅ ማዓና የለውም
ከአንተ ባህሪ ጋር አላጣጣምከውም
እንዳንተ ጭፍን ሰው በጭራሽ አላውቅም
🦚
ባትመለስ እንኳ አስታውስህ እንዲትፈዝ
ሩጫህ ቢሆንም ብዙ ሰው ለመያዝ
ተዓሱብ አውሮህ ምንም ብትደነዝዝ
ባይገበህ ልንገርህ ስማኝ አንተ ደነዝ
🦚
ባንድ ስንታገል ስንሻገር ያን ወንዝ
ኢኽዋን ሙመይዑን ባንድ ልናዎግዝ
ቁሙ ቁሙ ብሎ ሲጣራ ያ ኡስታዝ
አንተ ያኔ ከዳህ አቋም እንደመያዝ
ሀራ ሌላ አውርተህ ኮምቦልቻ መሰረዝ
ሙሪድ ካላስባለ ምንዲን ነው ይሄ ኬዝ
ከዛ በኀላማ ምንህን እንያዝ
ወጣት ተረጋጋ እያልክ መሟዘዝ
በሽታ ሲጋባህ የሙሪድነት መርዝ
ለአላህ ብለን ጣልንህ እንዳለቀበት ጓዝ
🦚
ከፊሉ ውድቅ ነው ሌላው ያነሳሃው
ልንገርህ እውነቱን ምንም ዋጋ የለው
እውርነትህን ነው ገልፀህ ያሳየኸው
🦚
እንኝህ መሪዎችህ ህዝብ ቢያቃቸውም
ጭፍን ተከታዮች በብዛት ቢያፈሩም
ሚዲያ አግንኗቸው በጣም ቢደነፉም
🦚
ኪታብ በማስቀራት ብዙ አሉ የለፉ
ሰው የማያውቃቸው ያን ሁሉ ሲገፉ
ትልልቅ ደረሶች አንፀው ያፋፉ 100%
ዛሬም ብቅ ብለው ብዙ ለፈለፉ
በሀቅ መለፍለፍ ቢያስብላቸው ከፉ
ወጥርው ይዘዋል አንገትም አልደፉ
ለኮሜን ጋጋታ ቅንጣት ሳይከፉ

🦚
ያነማ ኡስታዝህ?

እንኳን 9 ፣10 ሽ አመትም ቢያስተምር
ከሱፍይ ጠበቃ ከቆመ ከሱ ጋር
ከጀይላኒ ጫጩት ከነ-ኢልያስ ስር
በይነ ሰለፍይን ብሎ ሲመሰክር
አኽላቁ ሲያስጠላ በቲክቶክ ሲደከር
ከሴት ከዎንዱ ጋር መላፋት ሲጀምር
🦚
ነፍሱን አበላሽቶ ለሌሎችም ሲተርፍ
ምን ላድርገው ታዲያ ሙመይዕ ሲደግፍ?
ጭፍን በመከተል በኀላው ልንከርፈፍ?
እኔ አልገባበትም ራስህ ተንከርፈፍ
ኑረድን አረቢ ተው አትደናፈፍ
🦚
መረጃ አምጡ ብለህ የምትጠይቀው
ቢመጣ ቢመጣ ፍፁም ለማጠግበው
ዶቄትኮ አይደለም በኬሻ ምትሞላው
ህፃን ልጅ ይመስል ጢጦህ አደረከው
እንደገና ናና በጥሞና አንበብው
, 👇
👉 https://t.me/Abdurhman_oumer/1895

, 👇
👉 https://t.me/Abdurhman_oumer/1901

, 👇
👉 https://t.me/Abdurhman_oumer/1995
🦚
እስኪ ልጠይቅህ መረጃ ምንዲን ነው?
መረጃ ሚባለው አንተን መደገፍ ነው?
ወይስ ያንን ኡስታዝ ፅናት የተሳነው
ለተጣላው ሁሉ መረጃ ሚጭረው
ትናንት በነዛ ላይ ዛሬ በሌላኛው
ሲጣላ ሲጣላ ትግሉ ለበቀል ነው
ወላሂ አልዋሸንም እውነቱ ይሄው ነው።

🦚
ሰው ተነካ ብለህ ጅስምህ አይቀደድ
ለሰው በመዎገን አትጩህ አትበድ
ለአላህ ሸሪዓ ለሱ ብቻ ፍረድ
አዎ! ተዓሱብን ትተኸው ተራመድ

✍አብዱረህማን ዑመር


አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ውዶቼ ሆይ፦
አንድ በጭፍን ሙሪድነቱና በጭፍን አራጋቢነቱ እንዲሁም ቃላት እየመረጠና እየቀመረ ሲፈልግ ስለ ዘሩ ሲፈልግ
ስለ ጎጡ ሲፈልግ ሰለ ተራራውና ስለ ሸለቆው ሲፈልግ ስለ ውንዱ ስለ ሴቱ በቃ ምን ልበላችሁ የማያልቅ ዛዛታና ተረት ተረት የሚደሰኩር የተከታይ ብዛት እጅጉን የሚያሳስበው አንድ ሚዲያ ያገነነው ልጅ፦

በአቋማቸው በፀኑና ለኢኽዋን ፣ለሙመይ፣ ለአህባሽ ፣ለሀጃዊራ ያልተበገሩ ሰለፍዮችን በደፈናው ተችቶ ግጥም ቢጤ¡ ለቋል
ምን ማለት ነው? .እንደኛ ካልተንሸራተቱ ነው? ቅናት ነው?
አዑዙ ቢለህ!

ስለዚህም ልክ የሚያስገባ የተብራራ የሆነ ምላሽ ልስጠው እንደ? በሉ?
እሽ ኢንሻ አላህ ገባ ገባ በሉማ!

t.me/Abdurhman_oumer


ውቢቷ የአል ኢስላህ መድረሳ እንደባለፈው ዛሬም ልትደግመን ነው መስለኝ

🦚
👇
ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂወበረካቱ
ኢንሻ አላህ
የፊታችን እሁድ በቀን 15/5/2014
የዳዕዋ ፕሮግራም ስላለ እርሶናወዳጅ ዘመድዎ እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል
ተጋባዥ እንግዶች

1 ኡሥታዝ አቡ አብዱራህማን አብድልቋድር ኢብን ሐሰን(ሀፊዘሁሏህ) ከታላቁ ሸይኽ አብደል ሀሚድ አንጋፋ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ነው

2 ኡስታዝ ሻኪር ኢብን ሱልጣን(ሀፊዘሁላህ)
ሌላም ተጋባዥ እንግዳ ይኖረናል
ሰዓት ጠዋት 2:30
ቦታ ፉሪ አል ኢስላህ መድረሳ ፖሊስ ክበብ ፊትለፊት ኑሪሜዳ ባጃጅ መጨረሻ
ማሳሰቢያ መጠቀም ያለብን እንድንጠቀም በጊዜ እንገኝ

ወደ ውቢቷ መድረሳ ግሩፕ ለመቀላቀል
👇
https://t.me/medresetulislah
https://t.me/medresetulislah

.


ገናን አከበርክ ወይ?

🎙አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2117


ኡስታዝህ ዲንህ የሆነብህ

🎙አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2116




↪️አድስ ሙሀደራ
➖➖➖➖➖➖

♦️የሙሀደራው ርዕስ
➫➫➫➫➫➫➫➫

4️⃣ ዒልምን መደበቅ ያለው አደጋ በሚል ርዕስ የተደረገ ምርጥ ሙሀደራ ።

✅ ባለፈው ኮቦልቻ ላይ ከቀረቡት ሙሀደራዎች በአካል ለመገኘት ላልቻችሁ ሁሉ

🎙በሸይኽ አቡዘር ሀሰን"አቡ ጦለሀ"(ሀፊዘሁሏህ)

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha


#ተውሒድና_ሱና_በዚች_ሀገራችን !
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የሠው ህልውናው የመኖር ሚስጥሩ
የመጣበት ምክንያ የፍጥረት ጅምሩ
ፈክቶ ማሸብረቂያው መዋቢየው ማማሩ
የነገሮች ሁሉ ተውሒድ ነው ማገሩ
ሌላ"ም ነገር አለ የተውሒድ አጥሩ
በሱና ያብባል ያፈራል በጥሩ
#ተውሒድ
#ሱና
ሁለቱ አይለዩም በአንድ ካልተጠሩ

እነዚህ ሁለቱን አለ ሚያጠፋቸው
ከባድ ሰደድ እስት ባንዴ ሚበላቸው
ከል-ካይ ካላገኘ ቶሎ የሚያጠፋው
ጨርሶ ይበላል የለም የሚያስቀረው
ይሄም ሰደድ እሳት ሽርክ ቢድዓ ነው
የኢስላምን ካዝና አቃጥሎ ሚያዎድመው
ጥቂትም ሳያሥቀር አመድ የሚያደርገው

ሥለዚህ ወዳጄ ተነስና ዝመት
ምንም ሳትሰለች ለዲንህ ልፋለት
እንቅልፉን ተውና ተራመድ በንቃት
ጠላቶች ተባብረው ዲንህን ሲወሩት
ሽርክን እየዘሩ ተውሒድን ሲያከሥሙት
ቢድዓን ኮትኩተው ሱናውን ሲነቅሉት
ዝም ችላ አትበል ታች አትንሸራተት
በቭዠታ አትውደቅ አያታልህ ቃላት

አንበጣው መጣልህ ዲንህን ሊወረው
በእውቀቱ ማይሰራ ዓሊም የተባለው
በልቶ እንዳልበላ ሠው እውቀቱ የጠፋው
ይሄው መጣ ዛሬ ሱናውን ሊገድለው
ወጣቱን ሠብስቦ ሱፍይ ሊያደርገው
በደንብ ቆፍሮ ተውሒድን ሊቀብረው
አህባሸ አሻዒራን በምድር ሊዘራው

በዶክተር ነጋደ ይህን ብልሹ ሠው
ሙመይዑ መጣ ተዝኪያ ሊሠጠው
እያለ ዘፈነ ጥሩ ኪታብ አለው
አየ ጉድ ሚስኪኑ በጣም አሳዛኝ ነው
ለሠው መመሥከሩ የራሱ ሳያንሠው
በሰላሳ ምክር ሀገር የገደለው
ደሊል በማጣመም ብዙ ያሞኘ ነው

ተውሒድህ የት አለ እስኪ አንተም ንገረኝ
ትናንት የጮህክለት ዛሬ ናና አሳየኝ
በትላንቱ ትግልህ ፍፁም አታታለኝ

የት አለ ተውሒድህ ከቶ አንተ ሰው ምን ሆንክ
አህባሹ ሱፍዩ ዶሪህ ቀብር ሲያመልክ
ዶክተር ጀይላን መጥቶ ወደነሱ ሲሰብክ
ኢልያስ አህመድ ለሱ ሲያደከድክ
በአጭበርባሪ ቃላት ሞኞችን ሲማርክ
አንተም መጣህና ለሱ ተምበረከክ
ተውሒድሕ መጥፋቱን አሁንም አላወክ
እንደት"ሥ አይጣፋ አይል ዲቅቅ እምሽክ
የዘር ሀረግህን ከአህባሽ ካደረክ
በኢልያስ በኩል ከዶክተር ከደረስክ
ዶክተር ተቀብሎ ወደ አህባሽ መድረክ

#በግልፅ_ይግባህ?
~~~~~~~~~~~
አንተ ለሙመይዕ እገዛ ከሰጠህ
ሙመይዕ ለኢኽዋን ሲታገል እያየህ
ከዚህስ በኀላ ያሰፈራል በአላህ

ኢኽዋን ለሡፍዮች ወርቅ ዋንጫ ሲያዘጋጅ
መልካም ፀባየ"ኞች እያለ ሊያ-ደራጅ
አሻዒራን ሱንይ አድርጎ ሊፈርጅ
ሽርክን በመሬት ላይ አስፋፍቶ ሊያቀናጅ
ባገሪቱ ሊጥል የቢድዓውን ፈንጅ
ወጣቱ እንዲወድቅ በዑመር ገነቴ እጅ
በጡሃ እንድመራ በአኗሩ አሰጋጅ
መጽሓፍ እንድያነብ ሂዶ ከ -ሀስን ታጅ
እንዲህ እንድሆን ነው ዶክተሩ የሚቃጅ
በሽርክ በቢድዓ ሁሉም እንዲባጅጅ

#አይሳካለትም_ኢንሻ_አሏህ!
~~~~~~~~~~~~~~~~
ይቺ ሀገራችን ሞልቷታል ዑለማ
ዲኑን ጠባቂዎች በገጠር ከተማ
ስማቸውን በመርዝ ቢቀባው ጠማማ
በውሽት አሉ ቧልታ ቢዞር ቢያስተማማ
የትም አያደርሠው ይወድቃል ከጫማ
በምኞት ይቀራል አፉም እንደገማ

ሸይኽ ሁሴን አሰልጢ መካ ያለው ዓሊም
የስልጤው ተወላጅ የሸሪዓው ኻዲም
ጥፋት ሲንሰራፋ አይቶ ዝም አይልም
ሀገሩን ለጅቦች አሳ-ልፎ አይሰጥም
ዘበኛ አድርጎታል አላህ አይሰስትም

የኮንሞልቻው ጀግና የሀዳድዮች ፀር
እንቅልፍ የሚያሳጣ የሙመይዓ አሳር
ተጠንቅቆ ቁሟል ሸይኻችን አቡዘር
ለሱና ይለፋል ቢሆንም ውጭ አገር

#ሸይኽ_ሀሰን_ገላው !
ሠው በማርጀት ሥበብ እንደ አላህ ሲመለክ
ሙፍቲ እየተባለ ከፍ ሲል ከመድክ
ተውሒድ መስበክ ባይችል እየዘረጋ ሽርክ
እንኳን ሀገር ሊጠቅም በጣም ሲዝረከረክ

ዲንን የሚገድል መ-ቼ በአህባሽ ሲያልቅ
ብዙ ሽማግሌ አለ- - -የኢኽዋን ሊቅ
ሽርክን ለማቃናት የማያርፍ ጥልቅልቅ
ሽማግሌ ሲሆን ሠው ሱናውን ሲለቅ
ተውበት እንደዚህ ነው እየው ልብ ሲደርቅ
ዶክተር በመባሉ በባዶ ሲደነቅ
እድሜው ሲረዝምለት ቢድዓ ሲያሟሙቅ

ሽማግሌም ብቻ አይደለም የሚያደርቅ
ወጣት ሁኖ ራሱ አለ ሚጥለቀለቅ
ከቢድይ ጋር በአንድ ሚባሽቅ
በሠላሳ ምክር ልብን የሚያደርቅ

ግን አልሀምዱ ሊላህ ጎበዝ ጠፍቶ አይጠፋም
አሉ ጀግና ጀግኖች በሽማግሌ ሥም
እንደ ሙፍቲ ዑመር ጉልበት የማያሰም
እንደ ዶክተር ጀይላን ለአህባሾች የማይቆም
ይልቅስ በትጋት ለድኑ የሚደክም
ሸርክና ቢድዓን በርትቶ ሚቃዎም

ጎናቸው ለቢድዓ ፍፁም ያላደላው
በአደብ የተሞላ ነገረ ሥራቸው
ደግሞም በአደብ ስም ለባጢል ያልቆመው
ታላቁ መካሪ አሉን #ሀሰን_ገላው

ከቶ ምን ልናገር በሸይኽ ሀሰን ገላው
ከመልካም ስራ ጋር እንድሜውን ያቆየው

በጣም ያስፈልጋል ጭራሽ በዚህ ዘመን
ፊትና በየ አቅጣቸው ሲከበን ዙሪያውን
ይህ ሠው ያስፈልጋል እንወቅ እውነቱን
ቀሥ ብሎ ይመክራል ብሎ ረጋ ሠከን
ወደታች ሳይዘቅጥ በጣምም ሳይፈጥን
እድል ነው ስጦታ እንዲህ ቢሟላልን


አሉን ትልቅ ዓሊም አገር የያወቃቸው
ተዓምር የታየ በደረሶቻቸው
ዒልማቸው ተባርኮ ለውጧል ብዙ ሠው
በሙብተዲዕ ሙሽሪክ የእግር እሳት ናቸው
ሸይኹ አብደል ሀሚድ ይባላል ሥማቸው
በነሱ ከተማርክ ቶሎ መለወጥ ነው
በሱና ከታሸ ትምህር እንደዚህ ነው
ዛሬ ሚያስፈልጉን እነኝህ ሸይኽ ናቸው
ከአልማዝም ከወርቅ እጅግ ውድ ናቸው
ተጠቃሚ ያርገን አላህ በእውቀታቸው

ሌላም አለ ጀግና የባህር ዳሩ አሰድ
አዎ! አምበሳ ነው ለሱና ለተውሒድ
የሱናን ብርሃን በፁሁፍ የሚያስኬድ
ለሥሜት ተከታይ የሆነ እንደ ወጥመድ
የማይበገረው ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ

ደግሞ እስኪ ሌላውን ላንሳው በቀጣዩ
ታላቅ ኡስታዛችን ጣፋጭ አሰተዋዩ
በለስላሳ አንደበት ታውቋል በፀባዩ
, በሽርክ በቢድዓ ኮሶ የሚደፋ
. ባለቤቶቹንም እንደ እከክ ያስከፋ
. ምንም ያልተዋቸው ከኀላ እየገፋ
. በህሩ ተካ ነው ኢኽዋንን ያስተፋ
ሙመይዓውንም ይዞታል በከፋ


እንደ ሰማይ መብረቅ ድንገት ብቅ ያለልን
አሥሮ የሚገርፈው ሽርክና ቢድዓን
በወኔ ይገልፃል ተውሒድና ሱናን
ምነው ድምፁ ራቀኝ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን


ሌላስ?
የሽርክ የቢድዓ በህሩ ሲማታ
አህባሹ ሱፍዩ ሲታገል ሊረታ
ኢኽዋን ሙመይዑ ሲሯሯጥ ሲያምታታ
አጉል ጠበቃቸው ሲያፈላልግ ቦታ
ቀስ ብሎ ሱንዩን በዘዴ ሊመታ
ከበር ቁሞበታል ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ

ተውሒድ እና ሱና ባገር እንዲስፋፋ
ቭዠታን ጠቅላላ የሚጥል ባንካፋ
በትልቅ ጥረት ላይ ለሀቅ የሚለፋ
ሽርክና ቢድዓ ከሀገር እንዲጠፋ
በጣም ይታገላል ኡስታዝ ኢብኑ ሽፋ

አሁን ባልጠቅሳቸው ቢያጥሩኝ ሰዓታቶች
አሉ በየ ቦታው ሱናን ጠባቂዎች
ሰለቸኝ ሳይሉ በአቋም ፀኒዎች
ጭፍን ወገንተኞች ሳይሆኑ ደንባሮች
ለእውነት የሚጥሩ ሀቅ ፈላጊዎች
የጥመትን ጉዞ እልህ አሰጨራሾች
አቋም የሌለውን አሽቀንጥረው ጣይዎች
በአላህ እርዳታ ወደ ፊት ገሥጋሾች
በፅናት ተጉዘው ጀነት"ን ከጃይዎች
ኢንሻላህ

ወስላ ዓለይኩም

https://t.me/Abdurhman_oumer/2018


ሁርየቱል ኢዕቲቃድ (የእምነት ነፃነት) እያሉ ኢኽዋኖች የሚዘምሩለት የተበላሸ አካሄድ ይሄ ነው

በአላህ ፈቃድ በሰፊው በፁሁፍ እመለስበታለሁ

✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2111


ጭፍን ተከታዮች አላህን ፍሩ ጉዳዩ የዲን ጉዳይ ነው። በደመነፍስ ራሳችሁን ለጥፋት አታጋልጡ!
ወንድማችሁን ከወደዳችሁት ከጥፋቱ እንዲመለስ ተባበሩት
ብዙ የተሳሳታቸው ነገራቶችም እንዳሉ ታውቃላችሁ።

ካስፈለገም ከአሁን በፊት የተናገራቸውን የራሱን ድምፅ እያመጣን በቁርአን በሀዲስ መረጃ መልስ እንሰጣል
ታዲያ እስከዛ በትግስት ጠብቁ አትሞቱም
አንድ ሰው ሲነካ ከማበድ ታላቁ ሸሪዓ ሲገዘገዝ ትንሽ ብትከፉ ጥሩ ነበር

ድምፁን ቀነጫጭባችሁ የሚለው ደግሞ ታዲያ ሙሉው ሙሀዶራ ይቀረባል እንዴ? ይሄንማ ራሱስ እየሰራው የነበረ አይደለም እንደ?

ሲጀመር መልስ ለመስጠት ራሱ አለበት አይደል ይሄንም በግሉ ልኬለት አይቶታል ታድያ እናንተ ለምን በጭፍን ታረበርባላችሁ??

እኛ ወንድማችን ወደነበረበት መልካም አቋም እንድመለስ እንጅ በፍፁም ባዶ ጥላቻ አለመሆኑን አላህ ያውቀዋል

እናንተ ደግሞ እንኳን ተንሸራተተላችሁ እንጅ ደስታችሁ ነው እሱን በኮሜንት እያሳሳቃችሁ እያታለላችሁ ወስዳችሁ ድሮ በብርታት ሲቃዎቻቸው ከነበሩ ኢኽዋኖች ጉልበት ስር እንድወድቅ ነው እየሰራችሁ ያለው።

ሌላው ዋሽህ የምትሉት ነገር ደግሞ እናንተ ቆርጣችሁ ያመጣችሁበትና እኔ ያመጣሁት ሪከርዱ በፍፁም የተለያየ ነው
እኔ የዘመኑ በሸታ ከሚለው ከ 9 ደቂቃ ሪከርድ ነው
እናንተ ደግሞ ከ30 -45 ደቂቃ አካባቢ እያላችሁ ታጠቅ ከሚሉት ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ካደረገበት ነው ያመጣችሁት

ለምን ሳታረጋግጡ ትዞልሙኛላችሁ??

✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2105




ዓረበኛ መስማት ለምትችሉ
ወሳኝ የሆነች ትምህርት በተውሒድ ዙሪያ

🎙በታላቁ ሸይኽ ዱክቱር አብዱል ዓዚዝ ረይስ አረይስ (ሀፊዘሁላህ ወረዓህ)

ሸይኽ ወይም ዶክተር ማለት የሽርክ ባለቤቶችን ሱፍዮችንና አህባሾችን ለማቃናት ሌት ቀን የሚጥር ሳይሆን እንዲህ ፍርጥርጥ አድርጎ በመናገር ለዲኑ ዘብ የሚቆም ጀግና ነው።

መጨረሻ ላይ
(ሁርየቱል ኢዕቲቃድ) የእምነት ነፃነት የሚል አደገኛ መርህ አንገበው የሚሄዱትን የኢኽዋን አል ሙስሊሙን ቭዠታ ጠራርጎ ገደል የሚያስገባ ንግግር ሸይኹ ተናግረዋል።
ትላንት ጁሙዓ አድስ አበባ ቤተል አደባባዩ ካለው ተቅዋ መስጅ ኹጥባ ላይ የተበላሸና ህዝብ ገዳይ የሆነን ንግግር ለተናገረው ኸጢብ አድርሱለት
ይሄን ጨምሩና አድርሱለት
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/2027

🌿ተውሒድ ባለ አባቱ ከነቢ ሱና ጋር
🌿ሁለቱ በአንድ ላይ ተጩሆ ይነገር
🔥ሽርክና ቢድዓ ይሂድ ይጥፋ ከ
ሀገር


✍አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/2101

Показано 20 последних публикаций.

4 189

подписчиков
Статистика канала