ከ ቀደምቶች ንግግር🔊


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


💡በዚህ ቴክኖሎጂ በያይነቱ በበዛበት ዘመን የገሩለትን አጋጣሚዎች በመጠቀም ትንሽ ትልቅ ሳይል በጎ ነገሮችን ለማስተላለፍ ወኔ ያጣ ሰው መለስ ብሎ እራሱን ቢመረምር ሳይሻለው አይቀርም። ወደ አላህ መጣራት ትልቅ ክብር ነው‼
•••━════✿═════━•••
🔊«ወንድምህ አቡ ሱፍያን[ሑሴን አል_በናን]
○ለ አስተያየት እና ሀሳበዎ በ @Abu_Sufiyan_bot ያድርሱኝ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


★ዕድሜው ገፋ፣
★አጥንቱ ደከመ፣
★ፀጉሩ በሽበት ተንቀለቀለ፣
★ሚስቱም መሃን ነበረች።
እንዲህም ሆኖ ዘከርያ ከአምላኩ ተስፋ አልቆረጠም ።
'አንተን ለምኜማ ዕድለቢስ አልሆንም። ልጅ ስጠኝ፣ ብቻዬን አታስቀረኝ ...' አለ።
የማይሆን በሚመስል ጉዳይ ላይ ዱዓ አደረገ።
አብዝቶ ተማፀነ፣ ያ ረብ! አለ።
★ፈጣሪው ሰማው፣
★ዱዓው ምላሽ አገኘ፣
★በየሕያ ተበሰረ።

ኢማን ሲኖር፣ የቂን ሲኖር... ሁሉም ነገር ቅርብ ነው።
ትዳር፣ ልጅ፣ ሀብት፣ ... ለአላህ ሲነግሩት እሩቅ አይደለም ።
እንዴት ያ ረብ! ማለት ያቅታችኋል!?
ኢማናችሁ ከልብ ይሁን። የቂናችሁ ከፍ ይበል። እሱ ተለምኖ የከለከለው የለም።

ችግራችሁ ሁሉ ተፈቶ ይደር
ያ ረብ!


@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


أخي المسلم لا تتبع النفس والهوى فمن اتبٍع الهوى هوى في الهاوية والعياذ بالله من ذلك ولا سيما أن وسائل النظر إلى النساء بشهوة كثرت فترى الكثير من الشباب يمضي زهرة شبابه في النظر المحرّم إلى هذه وإلى هذه على الفضائيات والانترنت والخلوي السللر ونحوها وينسى أن الله تعالى مطّلع عليه لا تخفى عليه خافية.


አላህ ይጠብቅልን ...‼

🔸ቃላቶቻቸው እንደ ልብስ ሁሉ የጠቀሙን ብዙ ወዳጆች አሉን!!
✔️ሲበርደን ያለብሱናል፣
✔️ሲከፋን ያፅናኑናል፣
✔️ሲደዉሉልን ደህንነት ይሰማናል
✔️ነገሮች ሲቀየሩብን አይቀየሩብንም፣
✔️ሁኔታዎች ሲለወጡብን አይለወጡብንም፣
✔️ስናጣም ሆነ ስንቸገር አይርቁንም፣
✔️ግራ ሲገባን ሕይወታችንን መስመር ለማስያዝ ይጨነቁልናል፣
✔️መንገድ ጨልሞብን እያዩ ፊትለፊታችን ብርሃን እንደሆነ ለማሳመን ይከራከሩናል።
✔️እኛ ተስፋ ቆርጠን እነርሱ እንዳንወድቅ ይገፉናል፣

@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


🔸" ﻭﻟﻴﺲ ﺍﻟﺬﻛﺮ ﻛﺎﻷﻧﺜﻰ"
🔹“ወንድም ልጁ እንደ ሴት ልጁ አደለም»

♦️ሴት ልጅ በሕይወት ዘመኗ በተለያዩ አካላዊና፣ ሆርሞናዊ ሂደቶች ዉስጥ ታልፋለች፡፡ ለምሳሌ በወር አበባ፣ በእርግዝና፣ በወሊድ፣ በማጥባት፣ በወር አበባ መቋረጥ ወቅት ….  ከባባድ የሆርሞን ለውጦች የሚታዩባቸው ጊዜያቶች ናቸዉና በባህሪዋም ላይ ለውጥ ቢታይ የሚገርም አይሆንም፡፡ እነኚህን ጊዜያት በተለይ የሕይወት አጋራቸው የሆኑ ወንዶች በሚገባ ማስተዋል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ማስተዋል ከሴት ልጅ አንፃር ለሚወስዱት እርምጃ ምክንያታዊና ትክክለኞች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ ብትነጫነጭ፣ ብትቆጣ፣ ብትበሳጭ፣ ሆድ ቢብሳት፣ ቢደብራት … ምን አባቷ! ብሎ ከመቆጣት  ይልቅ ምን ሆና ነው!? ብሎ ጠጋ ብሎ ነገሩን መመርመሩ ሳይሻል አይቀርም፡፡

@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


«ቀደምቶች እና መውሊድ» ②
ሸይኽ ሙቅቢል ስለ መውሊድ ምን አሉ⁉️

‏قال الشيخ مقبل الوادعي رحمه الله :
المولدُ النبوي يُعتبر بدعة ما أنزل اللهُ بها من سلطان، لم تكن على عهد النبي ﷺ ،
ولا على عهدِ أبي بكر ولا عهد عمر ولا عثمان وهكذا،
ما أنشأه إلا العُبَيْديون الذين يُعتَبَرُون أكفر من اليهود والنصارى.

📚[إجابة السائل (273)]

✵أبـو سـفـيان
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan

@AbuSufiyan_Albenan


«ቀደምቶች እና መውሊድ» ①

ኢማሙ ሸውካኒ መውሊድን አስመልክተው ምን አሉ‼
◉ الإمَامُ الشَّوكَانِي - رَحِمهُ اللَّه -.

❖« المَولِد لَم أجِدُّ إلى الآن دَلِيلاً يَدُلُ عَلَى ثُبوتِهِ مِنَ كِتَابٍ ، ولا سُنَّةٍ ، ولا إجمَاعٍ ، ولا قِيَّاسٍ ، ولا إستِدلَالٍ ،

بَل أجمَعَ المُسلِمُون أنَّهُ لَم يُوجَد فِي عَصرِ خَير القُرونِ ، ولا الَّذِينَ يَلونَهُم ، ولا الَّذِينَ يَلونَهُم ».

[ الفَتحُ الرَبَّانِي || ٢ / ١٠٨٨ ]

✵أبـو سـفـيان

https://t.me/AbuSufiyan_Albenan

@AbuSufiyan_Albenan


📌 የምንወደው ሰው ሲታመም
ፈተና ነው እንላለን
⇨ የማንወደው ሰው ሲሆን ደግሞ
ቅጣት ነው እንላለን
⇨ የምንወደው ሰው ሙሲባ ሲነካው
ጥሩ ስለሆነ ነው እንላለን
⇨ የማንወደው ሰው ሲሆን ደግሞ
በዳይ ስለሆነ ነው እንላለን ...
♻️ስሜትህን እየተከተልክ የአላህን ቀደር
ልክ እንደሚያውቅ ሰው አትከፋፍል ።
@AbuSufiyan_Albenan
 ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈
@AbuSufiyan_Albenan


°°°°°°°° እሺ ልበለው⁉️°°°°°°°

🌐ለጋብቻ በመጠያየቅ ዓለም ስንት ዓይነት ሰው ያጋጥምሻል መሰለሽ ...፡፡
ስለራሱ ብቻ የሚያወራሽ ላንች ምንም ዓይነት ዕድል የማይሠጥ ወንድ ያጋጥምሻል፣
አንዳንዱ ደግሞ ተስማምታችሁና ተግባብታችሁ ጨርሣችሁ እቤቱ ሳትደርሺ ግማሽ መንገድ ላይ ይተዉሻል፣
አንዳንዱ ቁምነገር ጀምሮ በነጋታው ከቶዉኑ እንደማያውቅሽ ይሆናል፣
አንዳንዱ ታንሰኛለች፣ ሌላው ደግሞ ትበልጠኛለች ብሎ ይሸሻል፣
አንዳንዱ ንብረትሽን እንደማታካፍይው ሲያውቅ ያኮርፋል፣
አንዳንዱ እንደ ሕፃን ልጅ በርሽን አንኳኩቶ ይሮጣል፣
ሌላው ይሁንታሽን ካወቀ በኋላ ይደበቃል፣
አንዳንዱ ደግሞ ዝምብሎ ዙርያሽን ይዞራል፣
አንዳንዱ ደግሞ ከየት መጣ ሳትይዉ ያንች ልሁን ብሎ ድርቅ ይላል፡፡

♻️አልጨረስኩም፤.... ስለደከመኝ ተውኩት፡፡
ስለዚህ እህቴ በአሁኑ ሰአት
ትዳር የተመሸገ ምሽግ ሲሆን
⇨ በውስጧ የሌለው መግባት ይፈልጋል
⇨ ውስጧ ያለው ደግሞ መውጣት ይፈልጋል
እናማ አጣርተሽ፣አጢነሽ፣አዳምጠሽ፣ዛዙረሽ ግቢበት ያ ኡኽታህ‼ ምክሩ ላንተም የሆናል የኔ ቢጤው ላጤ ወንድሜ…!!

https://t.me/AbuSufiyan_Albenan
 ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
@AbuSufiyan_Albenan


👀~~~~~~ዓይንናስ በሉኝ~~~~~~👁

✂️ሰዎች በተለምዶ አላህ የሠጣቸዉን ፀጋ መሠረት አድርገው አንዱ በሌላው መቀናናቱ የተለመደ ነው፡፡ በሃይ ስኩልም ሆነ በዩኒቨርስቲ ሰነፍ በተማሪ በጎበዙ ይቀናል ሌላው ቀርቶ በዒልም ቦታ ላይ ደረሳው በደረሳው ጧሊበል ዒልሙ በጡላበል ዒልሙ ሊቀና ሁሉ ይችላል፡፡ ደሃ ሰው ሀብታሙን ሰው ይመቀኛል፡፡ መልከጥፉዋ ሴት በቆንጆዋ ትናደዳለች ትቃጠላለች፣ በመሥሪያ ቤት የማይወደደው በሚወደደው ይቀናል፣ ከፍ ሲልም ይመቀኛል፡፡
.
🔖ምቀኝነት ከሚታይባቸው ቦታዎች መካከል የትምህርት ማዕከላት ይጥቀሳሉ፡፡ ከምቀኝነት ዉጤቶች መካከል ደግሞ ዐይን/ሒስድ እና ድግምት ዋንኞቹ ናቸው፡፡

📊ይህም ብዙ ግዜየ ሚከሰተው በዚያ ግለሰብ አንድን ነገር የሚያይ ሰው ይደነቃል፤ በአድናቆትም ሳያበቃ መጥፎ ነገር ያስባል፤ ምቀኝነትና ክፉ ነገር ይመጣበታል፡፡ ያ መጥፎ እይታ አደገኛ ቀስት ነው ሰዉን ይወጋል፣ ህመም ላይም ይጥላል፡፡ ለዚህም ነው አንድን አስደናቂ ስታዩ ሱብሓነላህ! ማሻአላህ ! በማለት በአላህ አፈጣጠር ተደነቁ፣ አላህንም አወድሱ የሚባለው፡፡

ስለዚህ አህባቦቼ! አማኝ ሁሌም ራሱን መፈተሽና መገምገም አለብት፡፡ ዙርያዉን ምሽጉን ማጠናከር አለበት፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ብርቱና የተጋ መሆን አለበት፡፡ ጠልፈው ሊጥሉት የከበቡት ጠላቶቹ በርካታ ናቸውና፡፡ ለጥቃት ላለመጋለጥ ሶላቱን በአግባቡ የሚሰግድ፣ ከወንጀል የሚርቅ፣ ሲያጠፋ ቶሎ የሚመለስ፣ በኃጢኣት የማይዘወትር፣ የአላህን ክልከላና ትዕዛዙን የመጠበቅ ሁኔታው ከፍ ያለ መሆን አለበት፡፡ ሴቶች በተለይ ተንኮሉ በነርሱ ላይ ይበዛልና መሳነፍ የለባቸዉም፡፡ ብርቱና የማይሸነፉ መሆን አለባቸው፡፡ በእምነታቸው የማይጠራጠሩ፣ ሒጃባቸዉን አስተካክለው የሚለብሱ፣ ንፅህናቸዉን የሚጠብቁና በተቻለ መጠን በዉዱእ የሚንቀሳቀሱ መሆን አለባቸው፡፡
በዚህ መልኩ ራሣችንን በመጠበቅ ቀዳዳዎች ካልደፈንን የሸይጣን መጫወቻ ነው የምንሆነው፡፡ በዐይነናስ፣ በመተትና በድግምት የተነሳ ብዙ ተማሪዎች ከመንገድ ቀርተዋል፤ ከዓላማቸውም ተሰናክለዋል፡፡

« አላህ በዐይንናስ እየተሰቃዮ ያሉ እህትና ወንድሞቻችንን ዓፊያቸውን ይመልስላቸው እኛንም ከስኬት የሚያሰናክሉንን የጁንም ሆነ የሰው ሸረኛ ያንሳልን

✍ ~~~አቡ ሱፍያን~~~
@AbuSufiyan_Albenan
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan


የሸይጧን ሚስት

አንድ ዘው ወደ ታላቁ ታቢዕይ ሊቅ ወደ ኢማሙ ሻዕቢይ ዘንድ በመምጣት «የሸይጧን ሚስት ማን ትባላለች?» በማለት ጠየቃቸው፤ እርሳቸውም “ይቅርታ! ያ ሰርግ ላይ አልተገኘሁም” በማለት ምላሽ ሰጡት።

@AbuSufiyan_Albenan

https://t.me/AbuSufiyan_Albenan


ሪዝቅ ገንዘብ ወይም የእለት ጉርስ ብቻ አይደለም። በመልካም ነገር የሚያስታውሱን ወንድሞችና እህቶችም አላህ ከረዘቀን ነገሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

ስናገኛቸው ገንዘብ ከሚያስጨብጡን በላይ ምክር የሚለግሱንና በአላህ የሚያስታዉሱን ናቸው ይበልጥ ለኛ ጠቃሚዎች።

@AbuSufiyan_Albenan


📌አንዳንዶች በዉስጥ በ"ቦት" እየመጡ ዛሬ ጠፋህ ፃፍ እንጂ …ምን ሁነህ ነው ጠህፋ እኮ ምናምን… ብለውኛል… በቅድሚያ ቻናሌን ይህን ያክል ለመከታተላቹህ እጁጉኑ ሞራል ሁኖኛል (አላህ ኢኽላስን ይስጠኝና_) እናማ አንዳንድ ግዜ የማልፅፈው ያው…
እኔም እኮ
ሰው ነኝና አንዳንዴ ይደክመኛል፣
አንዳንዴም ሀሳብም ይጠፋብኛል፣
አንዳንዴም
ሁኔታዬም ደስ ሳይለኝ ሲቀር እጄ ለመፃፍ እንቢ ይለኛል።
የምፅፈውማ ለራሴው ጥቅም ነው፣
ስደክም ለመበርታት
ሳጠፋ ለመቶበት፣
ስወድቅ ለመነሳት፣
ስረሳ ለማስታወስ፣
በኢማን ሳረጅ ለመታደስ ነው ወዳጆቼ‼

@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


🚫ስልክህ በእጁህ ላይ ነው ማንም አያይህም…

‏جوالك بيدك، لا أحد يراك، خال من البشر، كل شيء تستطيع الوصول إليه.. كل هذه الأشياء، في بواطنها اختبار، وفي سجيتها امتحان، وفي ذاتها حساب، وعليها معرفة الجواب: (لِيَعلَمَ اللهُ مَن يَخافُهُ بِالغَيبِ) ! فاتقِ الله.

@AbuSufiyan_Albenan



يـا فؤادي رحم الله الـهوى

‏كان صرحًا من خيالٍ فهوى

አንዳንድ ግጥሞች የሚያስተላልፉት መልዕክት 2_3 ኪታቡ አንብበን ማናገኛቸውን መልዕክት እናገኝባችዋለን‼

@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


ሳላገባ ዕድሜየ ገፋ…

📌ተማሪው እወድቅ ይሆናል ብሎ ሊወድቅ ይደርሳል፤
📌 ተመራቂው ሥራ አላገኝም ብሎ ይሸበራል፤
📌 አባት ልጆቼ በርሃብ ሊያልቁብኝ ነው ብሎ ይብሰለሰላል፣
📌 በዕድሜ የገፋው በሽታ ሊጥለኝ ነው ብሎ ይሰጋል፤
📌 ኮረዳዋ  ሳላገባ ዕድሜዬ ገፋ ብላ  ትጨነቃለች፤ ያ ኡኽታ አትጨነቂ…
📌 ወጣቱ ከምንም ሳልሆን ጊዜው ሄደ ብሎ ይደነግጣል፤
📌 እናት ልጄን ክፉ ያገኘዋል ብላ ትቆዝማለች፣
📌ነጋዴው እከስር ይሆናል ብሎ ይንቀጠቀጣል፣

✂️ኪሣራ፣ ዉድቀት፣ በሽታ፣ እንቅፋት፣ ሐዘን፣ ፍርሃት፣ ስጋት፣ ሽብር፣ ትካዜ  ከጥንት ጀምሮ የዚህ ዓለም መገለጫዎች ናቸው። ዱንያ አላህ ሲፈጥራት ቀድሞውኑ እንዲህ ናት።

ወዳጆቼ!
ነገሮች አላህ ካለው ልክ ላያልፉ
ማሰብ መጨነቅ ምንድነው ትርፉ??


@AbuSufiyan_Albenan
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan


⭕️ኢሚማ ሻፊዕይ እንድህ ይላሉ፦
ﻳﻘﻮﻝ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲ :
ﻣﻦ ﻳﻈﻦ ﺁﻧﻪ ﻳﺴﻠﻢ ﻣﻦ ﻛﻶﻡ ﺁﻟﻨﺂﺱ ﻓﻬﻮ ﻣﺠﻨﻮﻥ ﻗﺂﻟﻮﺁ ﻋﻦ ﺁﻟﻠّﻪ : ﺛﺂﻟﺚ ﺛﻶﺛﺔ ! ﻭﻗﺂﻟﻮﺁ ﻋﻦ ﻣﺤﻤﺪ : ﺳﺂﺣﺮ ﻭﻣﺠﻨﻮﻥ ! ﻓﻤﺂ ﻇﻨﻚ ﺑﻤﻦ ﻫﻮ ﺩﻭﻧﻬﻤﺂ ؟

«ከሰወች ንግግር(ወቀሳ) ነፃ እሆናለው ብሎ የሚያስብ ካለ ይህ ሰው እብድ ነው! (ምክኒያቱም) በአላህ ላይ”የአንድ ሶስተኛ ነው” አሉ፤ በነብያችን ሙሀመድ ላይ“ ደጋሚ እና እብድ” ናቸው አሉ። ከነሱ በታች በሆነው ላይ ታድያ(እንዴት ነፃ ይወጣሉ ብለህ) ትጠራጠራለህ!?

@AbuSufiyan_Albenan
@AbuSufiyan_Albenan


🚫 ልብ ላለው ሰው ልብን የሚያስፈራ የሆነ ንግግር

📝كلام يخيف القلب لمن كان له قلب💢

🔴 قــال العـلامة ابن عـثيمين رحمہ الله تعالـﮯ

«إذا رأيت وقتك يمضي وعمرك يذهب وأنت لم تنتج شيئا مفيداً
ولا نافعاً، ولم تجد بركةً في الوقت ، فاحذر أن يكون أدركك قوله تعالى: {ولا تطع من أغفلنا قلبه عن ذكرنا واتبع هواه وكان أمره فرطا}»

[تفسير سورة الكهف].

🔴قـال العـلامة ابن عثيمين رحمہ الله تعالـﮯ

« إن مـن أهـم أسـباب انحـراف ⁧الشـباب ⁩الفـراغ ⁩فالفـراغ داء قـتال للفكـر والعـقل والطاقـات، إذ النفـس لابـد لهـا مـن حـركة وعـمل، فـإذا كـانت فـارغة مـن ذلـك تبلـد الفـكر وثخـن العـقل وضـعفت حـركة النفـس واستـولت الـوساوس والأفـكار الـرديئة عـلى القـلب »

📚 |[من مشكلات الشباب (صـ 14)]|

🔴قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:

أنت الآن في مهلة:

اغتنم الوقت واجعل لنفسك حزبا من كتاب الله عز وجل
اجعل لنفسك وقتا للعمل الصالح
قم في آخر الليل ولو نصف ساعة قبل الفجر، ناج ربك، ادعه فإنه تعالى ينزل إلى السماء الدنيا فيقول: "من يدعوني فاستجيب له من يسألني فأعطيه من يستغفرني فأغفر له“

📝[]شرح الكافية الشافية4/380[]
•••━════✿═════━•••
@AbuSufiyan_Albenan

https://t.me/AbuSufiyan_Albenan


ለ ሰርጌ አልመጣም‼
__________________________
→ከደወለ እደዉላለሁ፣
→ከጠየቀኝ እጠይቀዋለሁ፣
→ስጦታ ከሰጠኝ እሰጠዋለሁ፣
→ሰርጌ ከመጣ ሰርጉ እሄዳለሁ፣
→ካበደረኝ አበድረዋለሁ፣

🔖አይሁን ከሰው ጋር ሕይወታችሁ።

ሰዎችን ለዉለታና ለጥቅም አትቅረቡ፣ የቆረጠን መቀጠል ፣ ለከለከለ መስጠት፣ ለበደለ ይቅር ማለት ...ኢስላማዊ አስተምህሮ ነው።

ከሰዎች ጋር በነፃ ከኖራችሁ ከአላህ ዘንድ ቆንጆ ሽልማት ታገኛላችሁ።

@AbuSufiyan_Albenan
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan


👌በአላህ እምላለሁ!፡፡ አንድ ቀን ዉስጥህን የሚያስደስት፤ ከደስታ ብዛትም የሚያስፈነድቅሽ ነገር ይመጣል፤ ይህን ስልህ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ዕውቀት ኖሮኝ አይደለም፤ ግና በአላህ በርግጠኝነት ስለማምን እና ስለምተማመን ብቻ ነው፤ እሱ ለባሮቹ አዛኝ ነው፡፡  

🔎ወዳጆቼ!
ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ!
ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ 

ኢንሻአላህ የጨለመው ይበራል ።
የጠፋዉም ይገኛል ።

https://t.me/AbuSufiyan_Albenan

@AbuSufiyan_Albenan


أكثِروا الصَّلاةَ على النَّبِي ﷺ يومَ الجمُعةِ…

በነብዩ ﷺ ላይ የጁሙዐ ቀን ሶለዋት ማዉረድን አብዙ!

@AbuSufiyan_Albenan
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan

Показано 20 последних публикаций.

361

подписчиков
Статистика канала