⛓ / በፈተና ፊት መፅናት \ 🛡
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
✅:ዙለይኻ ሦስት ነገሮችን ያሟላች እመቤት ነበረች፡፡ ሃብት ፣ ዝና እና ማራኪ ዉበት፡፡ በዉበቷ በቀላሉ የሁሉንም ትኩረት ትስብ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ አንድ በአጠገቧ የሚኖር ወጣት ሰው ግን ስመለኖሯ ያስተዋለ አይመስልም፡፡ ነቢየላህ #ዩሱፍ ይባላል፡፡ በሷ ቤት አገልጋይ ሆኖ የሚኖረው። ዩሱፍ አይደለም ስለዉበቷ ሊደነቅ ቀርቶ ስለመፈጠሯም ትዝ ብሎት አያውቅም፡፡ እሷ ግን በዩሱፍ ፍቅር ክፉኛ ተይዛለች ፣ በዉበቱ ተማርካለች፡፡ እናም ለፍለጋው ቆረጠች፡፡ ስሜት ከተነሳሳ ይሉኝታ አያቆመዉም፡፡
🏮:ጉዳዩ ሲብስባት ነው መሰል አንድ ቀን እርሱ እቤት ዉስጥ እያለ የክፍሉን በር ዘጋች፡፡ በጥልቅ ፍላጎትም ተነሳስታ “ሀይተ ለክ” ና ተዘጋጅቼልሃለሁኝ!፡፡› አለችው፡፡ አላህ የማይወደዉን መጥፎ ነገር እንዲሠራ ጋበዘችው፡፡ በዚህ የትኛውንም እኔ ነኝ ያለ ጎረምሳ በሚያልፈሰፍስ ገጠመኝ ፊት ፣ በዚህ የወንድ ልጅን ቀልብ በሚያቀልጥ ክስተት ፊት ነቢየላህ ዩሱፍ ግን #ፀኑ፡፡ በአይሆንም ተጋፈጡ ፣ ወንጀልን እምቢኝ አሻፈረኝ አሉ፡፡ አላህ የሰጣቸዉን ብርታትና ኢማን ተጠቅመው ተቃወሙ፡፡ አላህ ብርታቱን ይስጠን፡፡
🔰:ወንድ ልጅ በህይወቱ ሊገጥመው ከሚችለው ፈተና ሁሉ ትልቁ ፈተና፣ በጣም ቆንጆ፣ ወጣት እና ሃብታም ሴት ጋብዛው፣ በዚያ ላይ ብቻውን ባለበት ሁኔታ “እምቢ” ማለቱ ነው ይላሉ #ዑለሞች፡፡
🖍:ስሜትን ከሚያንበረክክ ጎታች ኃይል ፊት በአላህ ጥበቃ ሥር ተጠልሎ “መዓዘሏህ!” (በአላህ እጠበቃለሁ!) ማለት የሚችል ስብዕና ያለው ሰው ምን ያህል ያሥቀናል በረቢ!፡፡
═════ •『 🩵 』• ═════
🩵:ወዳጆቼ! መልካም ሠርተን ያልተደሰትንበትና ዉስጣችን ያልረካበት ጊዜ የለም፡፡ መጥፎ ሠርተን ዉስጣችን ያልተረበሸበት ፣ ወደ ዉስጥ ያላነባንበት ጊዜ የለም፡፡ የአላህ ጥበቃ አይለየን፡፡ ዩሱፍ “መዓዘሏህ” አሉ፡፡ ወዲያውኑ ምንም ነገር ሊጥሰው የማይችል የአላህ ጥበቃ ሥር ሆኑ፡፡ “ሀይተለክ” “ወደ እኔ ና!” ስትለው “መዓዘሏህ!” እኔስ ወደ አላህ ተጠግቻለሁ” በማለት ወደ አምላካቸው ሸሹ፡፡ በዚህም ወንጀልን የሚያሸንፉበት ብርታት ተላበሱ፡፡
∬ አላህ በፈተና ፊት መቆም የምትችል ልብ ይስጠን ⨳
Copy