Wku muslim student(former freshman studentds)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана



Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ይህን ሙሃደራ ሁላችንም እናዳምጠውና እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ
ባረከላሁ ፊኩም!!!




የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


📍 አል-ኢማም ኸሊል ቢን አሕመድ አልፈራሒዲ'ይ :

«.. አንድ ሰው ያለ ጓደኛ ልክ ግራ እንደሌለው ቀኝ እጅ ነው .. »


«..ጓደኛን ማበላሸት ጠላትን ከማስተካከል የበለጠ ይከብዳል እንዴ ? »

ተብለው ሲጠየቁ :

«አዎ .. ልክ ልብስን መቅደድ አስተካክሎ ከመስፋት የበለጠ ቀላል እንደሆነው ! ».. አሉት።
፡፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አብዛኛውን ግዜ እውነተኛ ሷሒብን ማግኘት ከባድ ከመሆኑ ጋር ሌላ በጣም ከባድ የሆነው ነገር እንዘነጋለን ። እሱም እውነተኛ ሷሒብ መሆን ነው ! ብንሆን ኖሮ እናገኝ ነበር ።

አላህ እውነተኞች ያድርገን
ኮፒ


🟢ከሞት በኋላ ያለው ጉድ  እንደይዘነጋ።

ድንገት መከሰቱ አይቀሬ ነው።


👉የቀብር ጥያቄና መልስ

👉የቀብር ፀጋ አሊያም ቅጣት

👉ከሞት መነሳት

👉ሂሳብና ምርመራ

👉የነቢያት ተከታይ ሱኒዮች በነቢያቸው እጅ የሚጠጡትና ሙኻሊፎችና የፊትና ሰዎች የሚገፈተሩበት አጓጊው ሀውድ

👉ሁሉም የስራ ውጤቱን መገናኘቱ

👉የአላህ መምጣት

👉የአላህ በግልፅ መታየት

👉እጅግ ከባድና አስፈሪው እለተ ቂያመህ

👉ታላቋ ጀነትና አስፈሪዋ ጀሃነም

👉ሙተቆች  በጀነት ድግስ ሲንበሻበሹ

👉ሙጅሪሞች ወደ ጀሃነም ቃጠሎ ሲወረወሩ

👉የጀሃነምን ቅጣት የሚቀምሱ ወንጀለኛ ሙስሊሞች

👉ሸፋዐህ (ምልጃ) ለሚገባቸው ብቻ መኖሩ

🤲 አላህ ያለቅጣትና የለ ውርደት በጀነቱ ይሰብስበን።

📚القصيدة النونية للقحطاني
المؤلف: أبو عبد الله محمد بن صالح القحطاني،الأندلسي المالكي (ت ٣٧٨هـ)

📚ከኑኒየህ አልቀህጣኒይ ግጥም የተወሰደ


ከኳስ ምን አተረፈክ?
▬▬▬▬▬▬▬▬

ዝነኛው ተጨዋች ከሆነ ሞዴልህ፣
በፀጉር አቆራረጥ የልብስ ስታይልህ፣
የዝውውር ዜና አሰላለፋቸው፣
የነሱ አፓርታሞ የደሞወዝ ጣራቸው፣
ማንስ አሸነፈ ጎሉን ማን አገባው፣
ማን ቀይ ካርድ አየ ዋንጫውን ማን በላው፣
ስል አሰልጣኛቸው መረጃ መጎርጎር፣
ተጫዋች መሸምደድ በስማቸው ዝርዝር፣
የትኛው ከተማ መቼ ተወለደ፣
የማልያ ቁጥሩን ሳይቀር ሸመደደ።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥

💥💥💥💥💥💥💥💥💥
ግን...
የዚያን ውድ ነብይ የትውልድ ቦታቸው፣
የእናት አባቱን ስም እንዲሁም አያታቸው፣
በኢስላም ፍና ላይ ያኖሩት አሻራ፣
የትግል ታሪካቸውን ያኖሩትን አደራ፣
ምንስ ከለከሉን ምንስ አዘውናል፣
በሳቸው መንገድጋስ መቼ ተዋውቀናል፣
የፀጉር አቆራረጥ አለባበሳቸው፣
አበላል አጠጣጥ ከነ አተኛኛቸው፣
የሀጅ አደራረግ አሰጋገዳቸው፣
የአቀማመጥ አደብ ስነምግባራቸው፣
ስለነገው ህይወት ስለ አኼራችን፣
መች ለማወቅ ጓጓን አሳስቦን ጉዳችን፣
ስለ ሽርክ ጣጣ ስለ ተውሂድ ጥቅም፣
መች አውቅን ቢድአን የኮተቱን ጥርቅም፣
ዋናውኮ አላማ የተፈጠርክበት፣
ልትገዛው ነበር እርሱን በብቸኝነት።

💥💥💥💥💥💥💥💥💥
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
እስኪ ምን አተረፍክ!!
  ▬▬▬▬▬▬▬
ከመስጅድ ተኳርፈህ አሏህን ከረሳህ፣
የመፈጠርህን ግቡን ከዘነጋህ፣
ከዒልም ማእድ ላይ ጠፍተህ ከሰነበትክ፣
አኼራን ረስተክ በኳስ ፍቅር ካበድክ፣
ሶላትን በወቅቱ መስገድን ከልክሎህ፣
ከፈረንጅ ተጨዋች ከሆነማ ውሎህ፣
ስለኳስ ምንነት ጠንቅቀህ ተረድተህ፣
የረሱልን ፈለግ ከተውከው ዘንግተህ፣

ከኳስ ምን አተረፍክ ከእንስሳት ውሎ፣
የኢስላም ትልቅ ፀጋ በአንተ ላይ ጎድሎ።


የጁምዓ ቀን ሱናዎች

❶ኛ ገላን መታጠብ።
➋ኛ ሽቶን መቀባባት እና መዋብ።
❸ኛ ሲዋክን መጠቀም።
❹ኛ የክት ልብስ መልበስ
❺ኛ በጊዜ መስጂድ መጓዝ።
❻ኛ በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ።
❼ኛ መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር
❽ኛ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ።
❾ኛ ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ።
❿ኛ ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ።
⓫ኛ ሰደቃን ማብዛት።
⓬ኛ ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት
⓭ኛ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ።
⓮ኛ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ።

   منقول


Репост из: WKU Muslim student ጀምዓ(አስ ሰለፊይ)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ለወንድማችን ሑሴን እና ለእህት ሰሚራ ማሻአላህ ተባረከላህ እንኳን ለዚህ አበቃቹህ አልፍ ወአልፍ መብሩክ ብለናል።
                   🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
                  🌷ትዳራቹ ያማረ     🌷
                  🌷ፍቅራቹ የሰመረ   🌷
                  🌷ኑሮአቹ የከበረ     🌷
                  🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
አላህ ያድርግላችሁ!

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
 🌹ባረከሏሁ ለኩማ         🌹
 🌹ወባረከ አለይኩማ       🌹
 🌹ወጀመዓ በይነኩማ      🌹
  🌹   ፊኸይር                 🌹
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ألف مبروك
 ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች (ሰለፍያ) ጀመዓ https://t.me/WKUMuslimstudent


👉 የዘጠኙ ቀን ፆም

↪️ አላህ ለባሮቹ ከቸረው ከሰጠው በረከት ውስጥ አንዱ በዙል ሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ ዐስር ቀኖች ውስጥ ያደረገው አምሳያ የሌለው ምንዳና ቱሩፋት ነውእነዚህን ቀኖች አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦

عن ابن عباس– رضي الله عنهما –قال:- قال رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم:-
"مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهَا أَحَبُّ إِلَى اللهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ" يَعْنِي أَيَّامَ الْعَشْرِ، قَالُوا :- يَا رَسُولَ اللهِ، وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ قَالَ:- "وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ".
أخرجه أبو داود وابن ماجه وغيرهما.

"ከእነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነበት አንድም ቀን የለም (የዙል ሒጃ ዐስሩ ቀኖች) አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን?  አሉዋቸው። በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን, ምናልባት አንድ ሰው ነፍሱንና ገንዘቡን ይዞ ወጥቶ በምንም ነገር ካልተመለሰ እንጂ"

ይህ ሐዲስ መልካም ስራ የቱ እንደሆነ አልገደበም የትኛውም አይነት መልካም ስራ ያካትታል። ይሄኛው መልካም ስራ እዚህ ውስጥ አይገባም የሚል ሰው ማስረጃ ይጠየቃል ካላመጣ ተራ ወሬ ነው የሚሆነው። በእነዚህ ቀናቶች መፆም ከመልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው። እያንዳንዱ ቀን ራሱ የቻለ ስለሆነ አንድ ላይ መፆም አይፈቀድም ማለትም ከልብ ወለድ መናገር ነው የሚሆነው።
  
➧ ነብዩን አስመልክቶ እናታችን ሐፍሳ ይፆሙ ነበር ስትል እናታችን ዓኢሻ ደግሞ ፆመው አያውቁም ትላለች ዑለሞች በዚህ ዙሪያ የተለያየ ማስማሚያ (ማስታረቂያ) አቅርበዋል። ነገር ግን የሳቸው መፆምም ይሁን አለመፆም ንግግራቸውን አይፃረርም። አልፆሙም ቢባል እንኳን መፆም አይቻልም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ለኡማቸው የሚጠቅመውን በቃላቸው አረጋግጠዋልና,  አብዛኛዎች የፍቅህ ሊቃውንቶች መፆሙ ሱና ነው ይላሉ። የዘመናችን ትላልቅ ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሰይሚንንና ፈውዛን የመሳሰሉ መፆሙ ከመልካም ስራ መሆኑን አረጋግጠዋል። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በየአመቱ ንትርክ መፍጠርና አማኞችን ግራ ማጋባት አያስገልግም።
አላህ ለምልካም ስራ ያግራን።


Copy






#. የጁምአ ቀን በላጭነት እና ሱናዎቹ❗️❗️


#በሷም አባታችን አደም የተፈጠረበት ቀን ነው።
#በስዋም ከጀነት የተባረረባት ቀን ነው።
#በስዋም ቂያማ ምትቆምባት ቀን ነው።
      #አይሁዶች ጁሙአ ቀን ሲሰጣቸው እምቢ ብለው ቅዳሜን መረጡ
    #ነሳራዎች እሁድን መረጡ
   አላህ ይህ የተከበረች ቀን ስጦታ ጁማአን ለኔ ኡመት ሰጣቸው ብለዋል ( ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
      #የጁመዓ ቀን ሱናዎች
✅ገላን መታጠብ!
✅ንፁህ ልብስ መልበስ
✅ሽቶ መቀባባት(ለወንድ ልጅ)
✅በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ
✅ሱረቱ ከህፍን መቅራት
✅ሁጥባን በጥሞና ማዳመጥ
    🛑ልብ እንበል ጀመዓ  ቀን በነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰላዋት ማብዛት ይወደዳል።
   (በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርዳል።)
🛑#(በኔ ላይ ሰላዋት አውርዱ የትም ቦታ ብትሆኑ ሰላታቸሁ ይደርሰኛል!)የትም መሄድ አይጠበቅብንም

    🛑ማስጠንቀቂያ ኢማሙ ሁጥባ ከጀመረ በኋላ
#ማውራት
#በሰው ትከሻ እየተረማመዱ መሄድ
#ጨዎታ ሌሎች ያልተገቡ ነገሮች መስራት ጁመዓን ያበላሻል (የጁመዓ አጅርን ይቀንሳል)


    🌷🌷🌷ጁመዓ ቀን ቶሎ ወደ መስጂድ ከመሄድ  የሚገኙ ትሩፋቶች🌷🌷
መጀመሪያ ወቅት መስጂድ የገባ

✅1# ወቅት የገባ የግመል ሰደቃ አንዳረገ
✅2 # ወቅት የገባ የሙክት ሰደቃ እንዳደረገ
✅3# ወቅት የገባ የዶሮ
✅4 # ወቅት የገባ እንቁላል እንደሰጠ ይቆጠርለታል።

#✅.ሱረቱል ከህፍ መቅራት
🔴 የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንህ ብለዋል
((ጁመአ ቀን ሱረቱል ከኸፍን የቀራ ሰው በሁለቱ ጁማአዎች መካከል አላህ ብርሃን ያደርግለታል))

# ልክ ኢማሙ ሁጥባ ሲጀምር መዝጋቢ
መላአክቶች መዝገባቸውን ዘግተው ሁጥባው ለማድመጥ ይጣዳሉ ከዛን ስአት ጀምሮ ሰደቃው ይጠናቀቃል ማለት ነው
🛑✅(ጁመዓ ቀን አንዲት ስዓት አለች ዱአዕ ሙስተጃብ ሙስተጃብ ምትሆንባት ) እና በዱዓም መበርታት
  🛑ልብ እንበል ሸርጡን የተሟላለት ተቀባይነት ያለው ጁማዓ ከሳምንት አስከ ሳምንት የተሰራን ጥቃቅን ወንጀል ያስምራል!!!!አላህ የጁመዓን አጅር ከሚያገኙት ያድርገን
   ✍️ابو لقمان اسلفي


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

#ለእህቶች #ብቻ

ለዛሬ ሰኞ ማለትም 5/10/2015 የሴቶች የመትኑ ጀዘሪያ የተጅዊድ ደርስ final exam ይኖራችኋል
ሰዓት👉11:30
ቦታ 👉#ዓባስ_መስጂድ

ላልሰሙት አድርሱላቸው


☑️ አንድ ሰው የውመል ቂያማ ባነሳቸው ፎቶዎች ልክ ይቀጣል።

🎙الشيخ :- صالح الفوزان "حفظه الله "


ትውልድ አይወቅሰንም
በአላህ አንድነት-ስላመኑ ብቻ
ታቅፈው ዞረዋል-የስቃይ ስልቻ
በነብያት ትግል-በሶሀቦች ፅናት
ታስሮ ከመገረፍ-አንገት እስከመቅላት
በደል የማይገልፀው-ጭቆና አሳልፈው
ለሙስሊሙ ኡማ-በደም ታሪክ ፅፈው
ያቆሟት ኢስላምን-ያፀኑልን ለኛ
እንዴት ይደፈራል-በኩፋር ምቀኛ?!
አዎ በኛ ዘመን-በነብያት ፈለግ
ሙስሊሙ ሰው ፀንቷል
የአላህ ውዴታን-ከልቡ በማስረግ
ዛሬ በኛ ዘመን-በእስልምናችን
በኒቃባችን ላይ-ያውም በዘውዳችን
አ-ን-ደ-ራ-ደ-ር-ም ይሄ-ነው ቃላችን‼️
~በቅናት ገርጥቶ- ያበጠ ፊታቹ
በቅባት አይወዛም-ያውቀዋል ልባቹ~
እኛ ማለት እኮ......
በውድ ነብያችን-ሳንታይ ተናፍቀን
በሰው ልጆች እንቁ-ልብ ላይ ተወደን
ነብሳቸው ሰውተው-እልፍ አእላፍ ሶሀቦች
ኢስላም አፅንተዋል-ለዛሬ ሙስሊሞች!!

ይደፋታል እንጂ-ጠላትማ አንገቱ
ይቀምሳታል ፀፀት-የስራው ውጤቱ‼️
#አንሽመደመድም-በእናንተ ሴራ
ፀንቶዋል ልባችን-ቅንጣት አይፈራ
ብትቀቅሉት እንኳን-በጋን ዘይት ጥዳቹ
እ-ስ-ኪ-ለ-ያ-ይ ድረስ
አጥንትና ስጋው-ብታዩ ቆማቹ
ለሱ ግን ጀነት ነው-በአንድያ ነብሱ
ለዲኑ ተገሎ-ሳይሰስት ለራሱ
##እመኑ አዳምጡን....
አልፀናም ዲናችን-በዋዛ ፈዛዛ
አይረግፍ አቋማችን-እንደ ጠዋት ጤዛ
#አምነን ለብሰነዋል-ተውበንበታል
የጥንካሬን ጥግ-የምነታችን ሚስጥር አግኝተንበታል
ዛሬ በኛ ዘመን....
#በእናንተ ቅናት-ሂጃብ አናወልቅም
ክብራችን አንጥልም-ለማንም ልቅምቅም
ኢስላምን አዋርደን-ትውልድ አይወቅሰንም‼️
   ©copy©


Репост из: WKU Muslim student ጀምዓ(አስ ሰለፊይ)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

#ያለፈው ሳምንት ቆሞ የነበረው #ከሰኞ_እሮብ የነበረው ተከታታይ የከሽፉ ሹባሃት ኪታብ  የምትቀሩ ተማሪዎች ዛሬ የሚጀመር ይሆናል።


⛓ / በፈተና ፊት መፅናት \ 🛡
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
✅:ዙለይኻ ሦስት ነገሮችን ያሟላች እመቤት ነበረች፡፡ ሃብት ፣ ዝና እና ማራኪ ዉበት፡፡ በዉበቷ በቀላሉ የሁሉንም ትኩረት ትስብ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ አንድ በአጠገቧ የሚኖር ወጣት ሰው ግን ስመለኖሯ ያስተዋለ አይመስልም፡፡ ነቢየላህ
#ዩሱፍ ይባላል፡፡  በሷ ቤት አገልጋይ ሆኖ የሚኖረው። ዩሱፍ አይደለም ስለዉበቷ ሊደነቅ ቀርቶ ስለመፈጠሯም ትዝ ብሎት አያውቅም፡፡ እሷ ግን በዩሱፍ ፍቅር ክፉኛ ተይዛለች ፣ በዉበቱ ተማርካለች፡፡ እናም ለፍለጋው ቆረጠች፡፡ ስሜት ከተነሳሳ ይሉኝታ አያቆመዉም፡፡
 
🏮:ጉዳዩ ሲብስባት ነው መሰል አንድ ቀን እርሱ እቤት ዉስጥ እያለ የክፍሉን በር ዘጋች፡፡ በጥልቅ ፍላጎትም ተነሳስታ  “ሀይተ ለክ” ና ተዘጋጅቼልሃለሁኝ!፡፡› አለችው፡፡ አላህ የማይወደዉን መጥፎ ነገር እንዲሠራ ጋበዘችው፡፡ በዚህ የትኛውንም እኔ ነኝ ያለ ጎረምሳ በሚያልፈሰፍስ ገጠመኝ ፊት ፣ በዚህ የወንድ ልጅን ቀልብ በሚያቀልጥ ክስተት ፊት ነቢየላህ ዩሱፍ ግን
#ፀኑ፡፡ በአይሆንም ተጋፈጡ ፣ ወንጀልን እምቢኝ አሻፈረኝ አሉ፡፡ አላህ የሰጣቸዉን ብርታትና ኢማን ተጠቅመው ተቃወሙ፡፡ አላህ ብርታቱን ይስጠን፡፡

🔰:ወንድ ልጅ በህይወቱ ሊገጥመው ከሚችለው ፈተና ሁሉ ትልቁ ፈተና፣ በጣም ቆንጆ፣ ወጣት እና ሃብታም ሴት ጋብዛው፣ በዚያ ላይ ብቻውን ባለበት ሁኔታ “እምቢ” ማለቱ ነው ይላሉ
#ዑለሞች፡፡

🖍:ስሜትን ከሚያንበረክክ ጎታች ኃይል ፊት በአላህ ጥበቃ ሥር ተጠልሎ “መዓዘሏህ!” (በአላህ እጠበቃለሁ!) ማለት የሚችል ስብዕና ያለው ሰው ምን ያህል ያሥቀናል በረቢ!፡፡

═════ •『 🩵 』• ═════

🩵:ወዳጆቼ! መልካም ሠርተን ያልተደሰትንበትና ዉስጣችን ያልረካበት ጊዜ የለም፡፡ መጥፎ ሠርተን ዉስጣችን ያልተረበሸበት ፣ ወደ ዉስጥ ያላነባንበት ጊዜ የለም፡፡ የአላህ ጥበቃ አይለየን፡፡ ዩሱፍ “መዓዘሏህ” አሉ፡፡ ወዲያውኑ ምንም ነገር ሊጥሰው የማይችል የአላህ ጥበቃ ሥር ሆኑ፡፡ “ሀይተለክ” “ወደ እኔ ና!” ስትለው “መዓዘሏህ!” እኔስ ወደ አላህ ተጠግቻለሁ” በማለት ወደ አምላካቸው ሸሹ፡፡ በዚህም ወንጀልን የሚያሸንፉበት ብርታት ተላበሱ፡፡

∬ አላህ በፈተና ፊት መቆም የምትችል ልብ ይስጠን ⨳

Copy


Репост из: WKU Muslim student ጀምዓ(አስ ሰለፊይ)
እህቶቻችን በኒቃባቸው ምክንያት ትምህርት ሊያቋርጡ ይቅርና በየትኛውም ቦታ ማሸማቀቅ ይቆማል ኢንሻአላህ በዱአ እንበርታ!




Репост из: WKU Muslim student ጀምዓ(አስ ሰለፊይ)
ኒቃብ_ሀይማኖታዊ_ድንጋጌ_ወይስ_የአረቦች_ባህል.pdf
1.3Мб
Share 'ኒቃብ_ሀይማኖታዊ_ድንጋጌ_ወይስ_የአረቦች_ባህል.pdf'

Показано 20 последних публикаций.

379

подписчиков
Статистика канала