👉 የዘጠኙ ቀን ፆም
↪️ አላህ ለባሮቹ ከቸረው ከሰጠው በረከት ውስጥ አንዱ በዙል ሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ ዐስር ቀኖች ውስጥ ያደረገው አምሳያ የሌለው ምንዳና ቱሩፋት ነው። እነዚህን ቀኖች አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦
عن ابن عباس– رضي الله عنهما –قال:- قال رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم:-
"مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهَا أَحَبُّ إِلَى اللهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ" يَعْنِي أَيَّامَ الْعَشْرِ، قَالُوا :- يَا رَسُولَ اللهِ، وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ قَالَ:- "وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ".
أخرجه أبو داود وابن ماجه وغيرهما.
"ከእነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነበት አንድም ቀን የለም (የዙል ሒጃ ዐስሩ ቀኖች) አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን? አሉዋቸው። በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን, ምናልባት አንድ ሰው ነፍሱንና ገንዘቡን ይዞ ወጥቶ በምንም ነገር ካልተመለሰ እንጂ"
➲ ይህ ሐዲስ መልካም ስራ የቱ እንደሆነ አልገደበም የትኛውም አይነት መልካም ስራ ያካትታል። ይሄኛው መልካም ስራ እዚህ ውስጥ አይገባም የሚል ሰው ማስረጃ ይጠየቃል ካላመጣ ተራ ወሬ ነው የሚሆነው። በእነዚህ ቀናቶች መፆም ከመልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው። እያንዳንዱ ቀን ራሱ የቻለ ስለሆነ አንድ ላይ መፆም አይፈቀድም ማለትም ከልብ ወለድ መናገር ነው የሚሆነው።
➧ ነብዩን አስመልክቶ እናታችን ሐፍሳ ይፆሙ ነበር ስትል እናታችን ዓኢሻ ደግሞ ፆመው አያውቁም ትላለች ዑለሞች በዚህ ዙሪያ የተለያየ ማስማሚያ (ማስታረቂያ) አቅርበዋል። ነገር ግን የሳቸው መፆምም ይሁን አለመፆም ንግግራቸውን አይፃረርም። አልፆሙም ቢባል እንኳን መፆም አይቻልም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ለኡማቸው የሚጠቅመውን በቃላቸው አረጋግጠዋልና, አብዛኛዎች የፍቅህ ሊቃውንቶች መፆሙ ሱና ነው ይላሉ። የዘመናችን ትላልቅ ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሰይሚንንና ፈውዛን የመሳሰሉ መፆሙ ከመልካም ስራ መሆኑን አረጋግጠዋል። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በየአመቱ ንትርክ መፍጠርና አማኞችን ግራ ማጋባት አያስገልግም።
አላህ ለምልካም ስራ ያግራን።
Copy