Репост из: Isaiah 48 Apologetics
♦ ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ መበረዙን ያሳያልን? (ክፍል 3)
ባለፉት ሁለት ክፍላት ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ እንደሌለበት ከእስላማዊ ምንጮች መረጃ በመጥቀስ ለማሳየት ሞክረን ነበር
ዛሬም በጌታ ፈቃድ በዚህ ክፍል ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶችን ለማሳየት እንሞክራለን።
🚫 በፊት ለማለት እንደሞከርነው፥ ቁርአን ከስር መሰረቱ የሚቃረኑትን መጻሕፍት ነው እንደ ፈጣሪ ቃል ያጸደቀው። ይህ መሆኑ በመረጃ ከተረጋገጠ፥ ቁርአን የፈጣሪ ቃል አለመሆኑ ይረጋገጣል።
" ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡ "
▶ ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ምክንያት፦
1. በሱራ 5:43 አይሁዶች ኦሪት ስላላቸው ወደ መሐመድ መምጣት እንደሌለባቸው አላህ መናገሩ
በሱራ 5:43 ላይ አይሁዶች ለዳኝነት ወደ መሐመድ መጥተው ሳለ፥ አላህ የመለሰላቸውን መልስ እንመለከታለን። እርሱም፥ ኦሪቱ ስላላቸው ወደ አንተ መምጣት አያስፈልጋቸውም ነው
" እነርሱም ዘንድ ተውራት እያለች በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ስትሆን እንዴት ያስፈርዱሃል? ከዚያም ከዚህ በኋላ እንዴት ይሸሻሉ! እነዚያም በፍጹም ምእመናን አይደሉም። " ሱራ 5:43
▶ ኦሪት መበረዙን አላህ በ2:79 ተናግሮ ቢሆን ኖሮ፥ ለምን እሱ ስላላቸው ወደ አንተ ይመጣሉ አለ? "ከመጨረሻው" "ነብይ" ይልቅ የተበረዘው መጽሐፍ ዋጋ በለጠ? ነገር ግን 2:79 ተበርዟል ስለማይል አላህ እንዲህ አለ
🚫 5:43ን በይበልጥ አስፈላጊ የሚያደርገው ደግሞ 2:79 "ወረደ" ከተባለ ከብዙ አመታት በኋላ "የወረደ" ነው መባሉ ነው። ታዲያ አላህ ቀድሞ ተበርዟል ብሎ ተናግሮ ከአመታት በኋላ በዚያ "በተበረዘው" ዳኙ አለ? ሊሆን የማይችል ነገር ነው
2. በሱራ 5:68 ለመጽሐፉ ሰዎች ከኦሪትና ከወንጌል በቀር መቆሚያ የላቸውም ብሎ አላህ መናገሩ
በ5:68 አላህ ለመጽሐፉ ሰዎች ከኦሪት እና ከወንጌል በቀር መቆሚያ እንደሌላቸው ይናገራል
" እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትንና ኢንጅልን፣ ከጌታችሁም ወደናንተ የተወረደውን እስከምታቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም በላቸው፤ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው ቁርአን ከነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክሕደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል፤ በከሐዲያን ሕዝቦችም ላይ አትዘን። " ሱራ 5:68
▶ አይገርምም! የኦሪትን እና የወንጌልን መለኮታዊ ምንጭነት እንዲህ ከሚናገር መጽሐፍ ውስጥ ተበርዘዋል የሚል ጽንሰ ሀሳብ መፈለግ? ኦሪት ከተበረዘ ለምን አላህ ከእሱ በቀር መቆሚያ የላችሁም አለ? ለምን በተበረዘ መጽሐፍ ቁሙ ይለናል?
🚫 ልክ እንደ 5:43 ሱራ 5:68ም "ወረደ" የተባለው 2:79 ከወረደ ከአመታት በኋላ ነው። ስለዚህ አላህ ቀድሞ ተበርዟል ባለው ነገር ነው ቁሙ የሚለው? ለዚህ ነው 2:79 ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት
3. በሱራ 5:44 አላህ አይሁዶች በኦሪት ካልዳኙ ከሐዲ ናቸው ማለቱ
ሱራ 2:79 ኦሪት ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ሌላው ምክንያት አላህ በ5:44 አይሁድ በእሱ ካልዳኙ ከሐዲ ናቸው በማለቱ ነው
" እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትሆን አወረድን፤ እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በነዚያ ይሁዳውያን በሆኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፤ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በሆኑት (ይፈርዳሉ)፤ ሰዎችንም አትፍሩ፤ ፍሩኝም፤ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፤ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ #ከሐዲዎች እነርሱ ናቸው። " ሱራ 5:44
▶ አላህ ከሚገባው በላይ ግልጽ ነው። ኦሪት የኔ ቃል ነው እያለ ነው። በ2:79 ላይ ኦሪት ተበርዟል ብሎ ከሆነ ለምን በእርሱ የማይዳኙ ሰዎች ከሐዲ ናቸው አለ? አላህ ብረዛን ይደግፋል ማለት ነው?
🚫 ይህኛውም አያ እንደ በፊተኞቹ 2:79 ከወረደ ከአመታት በኋላ ነው የወረደው። ስለዚህ አላህ በ2:79 ላይ ተበርዟል ብሎ መናገር አይቻልም። አልያም ለምን እንደዛ ካለ ከአመታት በኋላ በሱ ያልዳኘ ከሀዲ ነው አለ?
4. በሀዲሳቱ ውስጥ ኦሪት በመሐመድም ላይ ባለ ስልጣን ስለ ነበር
ሀዲሳቱን ስናጠና፥ መሐመድ ኦሪትን እንደ ንጹሁ የፈጣሪ ቃል ሲታዘዘው እንመለከታለን
A group of Jews came and invited the Messenger of Allah (ﷺ) to Quff. So he visited them in their school.
They said: AbulQasim, one of our men has committed fornication with a woman; so pronounce judgment upon them. They placed a cushion for the Messenger of Allah (ﷺ) who sat on it and said: Bring the Torah. It was then brought. He then withdrew the cushion from beneath him and placed the Torah on it saying: I #believed in thee and in Him Who revealed thee.
He then said: Bring me one who is learned among you. Then a young man was brought. The transmitter then mentioned the rest of the tradition of stoning similar to the one transmitted by Malik from Nafi'.
Sunan Abu Dawud 4449
▶ በዚህ ታሪክ መሐመድ ሁለት በዝሙት ሀጢአት የተያዙ ሰዎችን ሲዳኝ እንመለከታለን። ሲዳኝም ኦሪትን አስመጥቶ "ባንተና አንተን ባወረደህ አምናለሁ" በማለት በኦሪት እንደሚያምን ተናገረ። በሌላ ዘገባም (sunan abu dawud 4431) አመንዝራ እንዲገደል የሚያዘውን ጥቅስ ከቶራህ እንደጠቀሰ ይናገራል
መሐመድ ኦሪት ተበርዟል ብሎ ቢያምን ኖሮ ለምን በእሱ አምናለሁ አለ? በተበረዘ መጽሐፍ ነበር የሚያምነው? የሚያስፈጽመውስ በተበረዘ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ ትዕዛዝን ነው? ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነገር ነው
🚫 ምክንያቱም ይህ ታሪክ የተፈጸመው 2:79 "ከወረደ" ከአመታት በኋላ ነው። ያኔ ተበርዟል የሚል ዋህይ ቢወርድለት ኖሮ በኦሪት አምናለሁ ባላለ ነበር። ነገር ግን 2:79 ተበርዟል ስለማይል እንዲህ አለ
✒ በተጨማሪም ይህ ክስተት የኦሪትን መጠበቅ ያሳያል። ምክንያቱም ያኔ መሐመድ የጠቀሰው፥ አመንዝሮች እንዲገደሉ የሚያዘው ጥቅስ አሁን በኛ እጅ ባለው ኦሪት ውስጥ ይገኛል። (ዘሌ 20:10)
ይህ ያኔ በመሐመድ ዘመን የነበረው ኦሪትና አሁን በአይሁድ እና በኛ እጅ የሚገኘው ኦሪት አንድ ለመሆኑ መረጃ ነው።
▶ መደምደሚያ
ቁርአን ኦሪትና ወንጌል የፈጣሪ ቃል ለመሆናቸው በማያሻማ መልኩ ይናገራል። እነዚህ መጻሕፍት የፈጣሪ ቃል መሆናቸውን ከሚናገር መጽሐፍ ውስጥ "ተበርዟል" የሚል ጽንሰ ሀሳብ መፈለግ አይቻልም