ድርሻውን ወስዶ “የተረፈ ካለ” የሚለው የመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግርን ኹሉም ድርሻውን ቢወስድ ከአስሉ ሊጎድልም እንደሚችል ጠቋሚ መኾኑን ስለተረዱ እንደኾነ ይሰመርበት፡፡
♦ መልስ
ይህ ታሪክ በእርግጥም ቁርዓን የፈጣሪ ቃል አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም ድምሩ 116.6% ነውና። ከከሊፋው ጋር የነበሩት ሱሐባ የዐውሉን ህግ ሲመሰርቱ ምንም አይነት ቁርዓናዊ ድጋፍ አልነበራቸውም (4:12 4:176)
🚫 ይህ ጸሐፊ የመሐመድን ሀዲስ አሁን ካለው ጉዳያችን ጋር ሊያገናኘው መሞከሩ ሁኔታው እንዳልገባው ያሳያል። ምክንያቱም የነብዩ ሀዲስ ክፍፍል ተካሂዶ የተረፈ ካለ (ወይም ከ100% ካነሰ) የሚፈጸመውን ሂደት እየገለጸ ነው።
የኛ ጉዳይ ግን የንብረት መትረፍ አይደለም! የንብረት አከፋፈሉ ከንብረቱ #መብለጡ ነው። (ወይም ከ100% በላይ መሆኑ)
🚫 ስለዚህ የነብዩ ሀዲስ ዐውልን ለመመስረት በጭራሽ ምክንያት ሊሆን አይችልም!!!! አይጠቁመውምም
✒ እነሱ
ምናልባት እዚህ ጋር ታዲያ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) የጀመረው ነገር እንዴት የእምነቱ አካል ተደርጎ ይታሰባል የሚል ሌላ ውዥንብር ከተነሳ፣ ኢማሙ አህመድ በሙስነዳቸው ( ሐዲስ ቁጥር 127, 126) ላይ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሳቸውና ከሳቸው በኋላ የሚመጡት የቀጥተኛ መንገድ መሪ ኸሊፋዎችን ፈለግ እንድንከተል አሳስበዋል፣ በሌላ አባባል የኸሊፋዎቹ ፈለግ የሃይማኖቱ አካል እንደኾነ በግልጽ ተናግረዋል፡-
عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي، تمسكوا بها وعضوا عليها بالنواجذ
“ በኔና ከኔ በኋላ በሚመጡ ቀጥተኛውን መንገድ ጠቋሚና መሪ በኾኑት ኸሊፋዎች ፈለግ ላይ ጽኑ፤ያቺን ፈለግ አጥብቃችኹ ያዙ፣ በመንጋጋ ጥርሳችኹም ንክሱ አድርጋችኹ ያዙ”
♦ መልስ
አሁንም እነዚህ ወገኖች በቁርዓንና በሀዲሳቱ መካከል ግጭት እንዳለ በተግባር ስላሳዩን ልናመሰግናቸው እንወዳለን
ምክንያቱም እነሱ እየገፋበት ያለውን የ"ዐውል" ሂሳብ ከተከተልን የቁርዓኑ ትዕዛዝ ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም። ለምሳሌ
በቁርዓኑ መሰረት ሚስት ከ48,000 ድረሻ 1/8ኛ ትወርሳለች። 6,000 ማለት ነው። በዐውሉ ህግ ግን 1/9ኛ ይሆናል። 5,333.33 ማለት ነው
የከሊፋ ዑመርን አከፋፈል ከተጠቀምን ቀጥታ ከሱራ 18:27 ጋር እንላተማለን። ።
" ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ። #ለቃላቶቹ ለዋጭ #የላቸውም። ከእርሱ በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም። " ሱራ 18:27
ቁርዓን 1/8ኛ እያለ 1/9ኛ ማለት የሚያዘውን መለወጥ ማለት ነውና። ነብዩም ወደ እርሳቸው "ከወረደው" ዋሂ ጋር ተጋጩ ማለት ነው።
✒ እነሱ
ከዚህ ኹሉ ማስረጃ በኋላ “ዐውል” ቁርኣናዊ አይደለም በሚል ሙግት የሚጸኑ እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ እኛም የመጀመሪያዎቹን ቁርኣናዊ የውርስ ህግጋት መርሆዎችን ብቻ መሰረት አድረገን፡፡ ቁርኣን ኹሉም ወራሾች የሚደርሳቸው ክፍልፋይ ተደምሮ የግድ አንድ መምጣት አለበት አይልም፤ የእያንዳንዱ ወራሽ ድርሻ ሊወርሱ ከመጡ ወራሾች አኳያ የተመደበ ክፍልፋያዊ ዕጣ እንጂ፣ ከጠቅላላው ገንዘብ አኳያ የሚደርሳቸው ድርሻ አይደለም፤ የሚሉትን ኹለት መርሆዎች ይዘን “አስልን”ም “ዐውልንም” ሳንጠቀም ወገናችን ገልብጦ ያመጣቸውን ወራሾች እናካፍል
ጠቅላላ የሚወረስ ገንዘብ 48000 ብር
ሚስት (1/8)
አባት (1/6)
እናት (1/6)
3 ሴቶች (2/3)
የኹሉም ክፍልፋዮች ድምር (1/8 + 1/6+ 1/6+ 2/3) = 27/24 = 9/8
………………………….
እያንዳንዱ ወራሽ ከጠቅላላው የክፍልፋዮች ድምር አንጻር በቁርአን መሰረት የተሰጠውን ድረሻ ወስደን ከሚወረሰው 48000 ብር አኳያ ስናሰላ፡-
ሚስት ( 1/8) (48000)/9/8 = (48000/8)( 8/9) = 5,333.3 ብር
አባት (1/6)(48000)/9/8 = (48000/6)(8/9) =7,111.1 ብር
እናት (1/6)(48000)/9/8 = (48000/6)(8/9) =7,111.1ብር
3 ሴቶች (2/3) (48000)/9/8 = (96000/3)(8/9) = 28,444.4 ብር
………………………………..
ጠቅላላ ድምር 47, 9999.94 ~ 48,000 ብር
………………………………….
ወዳጄ ይህ የስሌት መንገድ በሹብሀት ስድስት “አስል”ና “ዐውልን” ተጠቅመን ከሰራነው ጋር ተመሳሳይ ውጤት እንዳለው ልብ ይበሉ፡፡
♦ መልስ
ይህ ጸሐፊ ሒሳብ ባለማወቅ አሊያም ሆን ብሎ ያለምንም ጥያቄ የሚቀበሉትን ታዳሚዎችን እያጭበረበረ ነው። ምንም እንኳ "'ዐውልንም' ሳንጠቀም" ይበል እንጂ ቁርአን ያስቀመጠውን የአከፋፈል ሒደት ላይ ለክፍልፋይ ድምር(9/8) በማካፈል የሒሳብ ቁማር በመጫወት ወደ መጀመሪያው "ዐውል" አከፋፈል ሒደት ይወስደናል። ወይም ቁርአን የሰጠውን የእያንዳንዱን ክፍልፋይ ለእያንዳንዱ ክፍልፋይ ድምር ስናካፍል ፡ "ዐውል" የተሰኘው የተሻሻለ ውርስ አከፋፈል ይሰጠናል፡፡ "ነገር በምሳሌ ......." እንዲሉ አበው ፡ ምላሼን በምሳሌ ላስረዳ። ቁርአን ለአባት 1/6 እጅ ነበር ይህንን ለክፍልፋዩ ድምር(9/8) ስናካፍል ፡ ሙስሊሞች ለቁርአን እርምትነት ካስተዋወቁት "ዐውል" ጋር እኩል ይመጣል።
(1/6)/(9/8)=(1/6)*(8/9)=4/27 የ"ዐውልም" Ratio እኩል መሆኑን ይመለከቷል።
☞ሚስት፦(1/9) Or (3/27)
=(1/8)/(9/8)=(1/8)*(8/9)=(1/9) Or (3/27)
=(1/8)*(48,000)/(9/8)= (1/9)*48,000
=5,333.333 ብር
☞አባት፦(4/27)
=(1/6)/(9/8)=(1/6)*(8/9)=4/27
=(1/6)*48,000/(9/8)=(4/27)*48,000
=7,111.1111 ብር
☞እናት=(4/27)
=(1/6)/(9/8)=(1/6)*(8/9)=4/27
=(1/6)*48,000/(9/8)=(4/27)*48,000
=7,111.1111 ብር
☞3 ሴት ልጆች፦(16/27)
=(2/3)/(9/8)=(2/3)*(8/9)=[16/27]
=(2/3)*48,000/(9/8)=(16/27)*48,000
=28,444.444 ብር
ይህ እንግዲህ "ለምንና እንዴት?" የማይሉ ተከታዮችን የማታለል ሙከራ ነው። አልተሳካም እንጂ። ከዚህ እንደምንረዳው "ዐውልን" በሒሳባው መንገድ ገለጸ እንጂ ሌላ የቁርአኑን ስሕተት የሚያርም ቁርአናዊ የስሌት ሊያመጣ አልቻለም።
✒ እነሱ
ወገናችን ጀገን ብሎ “የትኛውም የገንዘብ መጠን በቁርአን የክፍፍል ሒደት ብንከፋፍለው ኹሌም ከአስሉ ይበልጣል፡፡ የማይበልጥበት ጊዜ ሊኖር አይችልም” በማለት “በካፒታል ሌተር” ኢስላማዊ የውርስ ሳይንስን እንደማያውቀውና ሐሳቡን ኹሉ እንደራሱ ኣላዋቂ ከኾኑ ጥራዝ ነጠቀኞች እንደቀዳ በአንደበቱ መስክሯልል፡፡ በቀደመው ጽሑፍም የሰፈረውንም ሐሳብ በቅጡ እንዳልተረዳ ነግሮናል፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ድርሻ ክፍልፋይ ደምረን ከአስሉ ከበለጠ፣ ወደ ዐውል እንገባለን ነው፤ የተባለው እንጂ ስለሚወረሰው ገንዘብ አልተወራም፡፡ ግን እስኪ በሚወረሰውም በክፍልፋዩም እንረዳቸውና፣ ክፍልፋዮች ተደምረው አንድ የሚመጡበትን ፣ከነ ድርሻ ገንዘባቸው ጋር በቀላል ምሳሌ በተግባር እንየው፡-
አንዲት ሴት 50 , 000 ብር ጥላ ሞተች እንበል፡፡ ባሏንና የእናትና አባት እህቷ ወራሽ ኾነው ቢመጡ፣ የውርስ ሂደቱ እንደሚከተለው ይኾናል፡-
ባል ( ½)፣ እህት (1/2)፤ “አስል” 2
ባል