Репост из: Isaiah 48 Apologetics
♦ የቁርዓን ግልጽ ስህተት (መልስ)
ባለፈው ጽሑፋችን በቁርዓን ወስጥ። የሚገኘውን ስህተት አሳይተን ነበር። ስህተቱ በውርስ ክፍፍል ውስጥ የውራሾች የውርስ ልክ ከሀብቱ መብለጡ ነው
ለዚህ ስህተት መልስ እንሰጣለን ብለው ብለው ብዕራቸውን ያነሱ ሙስሊም ወገኖች አሉ። ቀጥለን እንደምንመለከተው እነዚህ ወገኖች በቁርዓን ውስጥ ለሚገኘው ለዚህ ስህተት እልባት ከመስጠት ይልቅ ለቁርዓኑ external የሆነ የራሳቸውን mathematical እልባት ነው የሰጡት
ይህ እነሱ ከቁርዓኑ ጸሐፊ ይልቅ የሂሳብ እውቀት እንዳላቸው ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ የለውም። ምክንያቱም ስህተቱ አልተወገደምና፥ ቁርዓናዊ እልባትም አልተሰጠውም
እስቲ የነሱን መልስ እንመልከተው
ሰውዮው ሲሞት ትቶት የሄደው የገንዘብ መጠን 48000፣ ለውርስ የቀረቡት የቤተሰብ አባላት ደግሞ እንደሚከተሉት ናቸው፡-
1. ሚስት
2. ሦስት ሴት ልጆች
3. እናትና አባት
...
ከወንዶች ውርስ አኳያ መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “ ውርሶችን ለሚገባቸው አካላት አድርሱ፤ የተረፈ ካለ (ለመውረስ ከመጡት ወንዶች መካከል) በውርስ የበላይ ለኾነው ስጡ”
♦ መልስ
ይህ ከኛ ነጥብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። የተረፈ ንብረት ካለ ባል መውረስ ይችላል የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ጥያቄ አልተነሳበትም
✒ እነርሱ
አኹን ወደ ማከፋፈሉ እንግባና ያሉትን ሕግጋት እንይ፡-
አስል 24
ሚስት (1/8) = 3
3 ሴቶች (2/3) = 16
እናት (1/6) = 4
አባት (1/6) እና የተረፈ ካለ = 4
ለእነዚህ ክፍልፋይ ቁጥሮች አካፋይ ኾኖ በጋራ የሚያገለግለው ቁጥር 24 ነው፡፡ይህንን በውረስ ሳይንስ “አስል” እንለዋለን፡፡ ይህ ማለት የሚወረሰው ንብረት ለ24 ይካፈላል ማለት ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን የእያንዳንዱን ሰው ድርሻ ከጠቅላላው 24 ላይ እያነሳን እናካፍል፡፡ ከላይ ሰንጠረዢ ላይ እንደምናየው ሚስት 3 እጅ (ከ24 ላይ1/8 ኛውን ስናነሳ ማለት ነው)፤ ሴቶቹ 16 እጅ፣ እናት 4 እጅ፤ አባትም 4 እጅ ይደርሳቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህንን ድርሻቸውን ስንደምር 24 ሳይኾን 27 ይመጣል፡፡
♦ መልስ
ዋናው ነጥብ ይህ ነው። ቁርዓኑ የቤተሰቤ አባላቱ እንዲከፋፈሉ ያዘዘበት ልክ ከሀብቱ በላይ መሆኑ ነው። ይህ አይነቱ አሰራር በየትኛውም ውል ተቀባይነት የለውም
1/8 + 2/3 + 1/6 + 1/6 = 112.5%
ክፍፍሉ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ነው። ማለትም ይህ ትዕዛዝ በየትኛውም መልኩ ባለበት አቋምና ልክ ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም
✒ እነሱ
ቁርአን ተሳስቷል ብለው የደመደሙ አካላት እዚህ ድረስ መጥተው ከዚያም ምን መደረግ እንዳለበት ሳያውቁ በቀጥታ በክፍልፋዩ የሚወረሰውን 48,000 ብር አባዙና 54,000 ብር ላይ ደረሱ
...
በኢስላም ውርስ ሕግ ንብረቱን ማከፋፈል ከመጀመራችን በፊት፣ “አስሉን” ለኹሉም ባለመበት ካከፋፈልን በኋላ የድርሻዎቹ ድምር ከ”አስሉ” እኩል ካልኾነ “ዐውል” የሚባል ሌላ ሒሳብ ውስጥ እንገባለን፡፡ ለምሳሌ እዚህ ጋር የኹሉንም ድርሻ (ሰህም) ስንደምር ሚስት (3) + ሴቶች (16) + አባት (4) + እናት (4) = 27 ይመጣል፡፡ ይህ ደግመ ከአስሉ (24) ይበልጣል፡፡ ስለዚህ “ዐውል” ስናደርገው አስሉ 24 መኾኑ ይቀርና 27 ይኾናል፡፡ ይህ ማለት ጠቅላላ ንብረቱ ለ24 መካፈሉ ይቀርና ለ27 ይከፋፈላል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የምናደርገው በመጀመሪያው አስል (24) የደረሳቸውን ድርሻ(ሰህም) በ”ዐውሉ” ማካፈል ይኾናል፡-
ሚስት (3/27)፣ ሴቶች (16/27)፣ አባት (4/27)፣ እናት (4/27)
ይህ አዲሱ የዐውል ክፍልፋይ ኹሉም ወራሾች መጀመሪያ ከሚኖራቸው ድርሻ ዝቅ ብለው ያለምንም ሒሳባዊ ስህተት የሚካፈሉበት ሒደት ነው፡፡ ለምሳሌ ሚስትን በመጀመሪያው አስል (24) እናካፍላት ብንል ይደርሳት የነበረው 3/24 ነበር፡፡ ይህ ማለት ጠቅላላ ንበረቱ 24 ቦታ ተከፋፍሎ ለሚስት 3/24 ወይም 1/8 ው ይደርሳት ነበር ማለት ነው፡፡ በዐውል ሒሳብ ግን ከመጀመሪያው ዝቅ ብላ 3/27 ወይም 1/9 እንድትወርስ ይደረጋል፡፡
♦ መልስ
እነዚህ ወገኖች ቁርዓን በእርግጥም የፈጣሪ ቃል እንዳልሆነ ስላረጋገጡልን ልናመሰግናቸው እንወዳለን።
ምክኒያቱም እነሱ ይህንን ችግር ይፈታልናል ብለው የተጠቀሙት ዘዴ በዛሬው ዘመን proration ተብሎ የሚታወቀው የሂሳብ ዘዴ ነው።
ይህ ዘዴ በክፍፍል መጠን ውስጥ ስህተት ሲኖር፥ የወራሾችን ቅደም ተከተል ባላፋለሰ መልኩ፥ ratioን በጠበቀ መልኩ የሚደረግ ማስተካከያ ነው
"ዐውል" የተሰኘው "ሌላ ሂሳብ" ቁርዓናዊ ድጋፍ የሌለው ዘዴ ነው። እነዚህ ወገኖች ይህንን ዘዴ መጠቀማቸው በእርግጥም ቁርዓን በክፍፍል ሂደቱ ውስጥ በሂሳብ እንደተሳሳተ አሳይተውናል። ባይሳሳትማ proration ባልተጠቀሙ ነበር
በእነሱ መሰረት የንብረት ክፍፍሉ በ24 መካፈሉ ቀርቶ በ27 ከተካፈለ የወራሾቹ የውረስ መጠን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ ከቁርዓኑ ጋር በቀጥታ ያላትመናል
ለምሳሌ
ሚስት በቁርዓኑ መሰረት (ሱራ 4:12) ባሏ ከተወው 1/8ኛ ንብረትን ትወርሳለች። እነሱ በተጠቀሙት ዐውል/proration ግን ውርሷ ወደ 1/9ኛ ዝቅ ይላል
ማለትም፦ 48,000 x 1/9 = 5333.333
በቁርዓኑ መሰረት ግን ሚስት መውረስ የነበረባት 6,000 ነበር!!!
🚫 አላህ በዘላለማዊ ቃሉ ሚስት 1/8ኛ መውረስ አለባት ሲል እነዚህ ወገኖች ግን 1/9ኛ ነው ብለዋል!
ሌሎቹም የቤተሰቦቹ አባላት እንዲሁ ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል። ነገር ግን ቁርዓኑ ከደነገገው ጋር የሚላተም ነው። ምክንያቱም የነሱ የውርስ መጠን ቁርዓኑ ካዘዘው ያንሳልና
ቀርዓን እነሱ
- አባት 1/6 (0.1666) - አባት 4/27 (0.1481)
- ሴቶች ልጆች 2/3 (0.666) - ሴቶች ልጆች 16/27 (0.5925)
ሌላው አስገራሚው ነጥብ " የድርሻዎቹ ድምር ከ"አስሉ" እኩል #ካልኾነ.." ማለታቸው ነው። ይህ ጸሐፊ በቁርዓኑ ክፍፍል ሂደት ውስጥ እኩል ሊመጣ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል አድሮጎ እየተናገረ ነው
ቅሉ ግን የትኛውንም የገንዘብ መጠን በቁርዓኑ የክፍፍል ሂደት ብንከፋፍለው #ሁሌም ይበልጣል። የማይበልጥበት ጊዜ ሊኖር አይችልም
▶ ከዚህ ችግር መውጫ ብቸኛው መንገድ ቁርዓኑ ያዘዘውን የክፍፍል ልክ ጠብቆ ንብረቱ ከወራሾቹ ልክ እንዳይበልጥ ማድረግ ነው።
እንጂ የቁርዓኑን ቃል ሽሮ የራስን የሂሳብ እውቀት ማስመስከር አይገባም። ምክንያቱም በዚህ የሂሳብ ዘዴ ንብረቱን ማከፋፈል ማለት ቁርዓኑን በላጲስ አጥፍቶ የራስን ቃል እንመጻፍ ነውና
✒እነሱ
አኹን “ክርስቶስን” እንድንቀበል የጠሩን ወገኖች ኢስላም ምን ያህል ጥልቅ እምነትና ሳይንሳዊ እንደኾነ የተረዱ ይመስለኛል፡፡ ቀጥለን እኛም እስኪ እናንተው ያነሳችኋቸው ሰዎች 48000 ብር ለመውረስ ቢመጡ ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ እንዴት እንደምታከፋፍሏቸው አሳዩን ብለን እንጠይቃለን፡፡
♦ መልስ
እኛ ከዚህ ምልልስ የተረዳነው ቁርዓን በሰዎች የሂሳብ እውቀት ተዳኝቶ ቃሉ የሚሻር ስሁት መጽሐፍ መሆኑን ነው
እናንተ የቁርዓኑን ክፍፍል ስላልተቀበላችሁ ያልተጻፈ ክፍፍል በራሳችሁ የሂሳብ እውቀት መሰረታችሁ። ይህ በእርግጥም የኛን ነጥብ ያጠነክርልናል
አሁንም ጥሪያችን አንድ ነው። እናንተ በራሳችሁ እውቀት edit አድርጋችሁ እንኳ ከመቃረን ያላተረፋችሁት መጽሐፍ አያዋጣችሁም