Alexo Tech


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


አላማችን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ እዉቀቶችን ማድረስ እና ተጠቃሚ ማድረግ ነው።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች
አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-
1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡
2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡
3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
6. 2 ደቂቃ ቢያቆይዎት ነው፤ ነገር ግን ይሄን መረጃ ሼር ብታደርጉት የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል፡፡ አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡


🔱በስልካችን ቪዲዮዎችን በማቀናበር ፕሮፊሽናል ኤዲተር መሆን እንችላለን?መልሱ አዎ ነው!
🎦ቪዲዮንኤዲት ለማድረግ የግድ ኮምፒውተር መጠቀም አይኖርቦትም!ዘመን አፈራሽ የሆነው ስልክዎ ከኮምፒውተር ባልተናነሰ መልኩ ቪዲዮዎችን ለማቀናበር አንዲያደርጉ ያስችሎታል!እኛም ለቪዲዮ ኤዲቲንግ ያገለግላሉ ያልናቸውን 8 አፖችን ይዘን ቀርበናል!
1️⃣FilmoraGoበብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተወደደ አስደናቂ የAndroid ቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው!የመቁረጥ (Trim/Cut)ገጽታዎችን መቀየር፣ሙዚቃን ወዘተ...የመሳሰሉት ዋና ዋና ተግባራት በቀላሉ በዚህ መተግበሪያ ሊያከናወኑ ይችላሉ!
:
2️⃣VideoShowብዙ ሽልማቶችን የተቀበለ አስደናቂ መተግበሪያ ሲሆን PlayStore ውስጥ ከሚገኙ ነፃ ምርጥ የቪዲዮ መተግበሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው!ለአጠቃቀም ቀላል ነው!
🛃ከዋናዋና ተግባራቶቹ ውስጥ ፊልተሮችን፣ሙዚቃዎችን እና የድምፅ ውጤቶችን በመጨመር ወይም በቀጥታ ስርጭት ጊዜ ቪዲዮዎን መቆጣጠር፣ማስዋብ ይችላሉ!
3️⃣PowerDirectorለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የጊዜ መስመር ያለው ገራሚ የቪዲዮ ኤዲተር ነው!በቸኮሉ ጊዜ አልያም ፈጣን ግዜያዊ (ቋሚ)ቪዲዮዎችን በሰአታት ውስጥ ለመስራት ግሩም የሆነ አማራጭ ነው!
4️⃣KineMasterከኃይለኛ ባህሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ ከተሰራ በይነ-ገጽ ጋር በመጣመር #KineMaster ለAndroid ተስማሚ የቪዲዮ አርት ኤዲቲንግ መሣሪያ ነው!የተለያዩ የሚዲያ ፋይሎችን በቀላሉ ለማስመጣት የ ❝Copy Paste❞ አገልግሎትን መጠቀም ይችላሉ!ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለመፍጠር የKineMaster ኤዲቲንግ ሂደት ላይ በይበልጥ ተመራጭ ነው!የተለያዩ የሽግግር ዓይነቶችን መጨመር ወይም የጽሁፎችን ወይም የትርጉም ጽሑፎችን (ብሎግ)ማስገባት ይችላሉ!ብቻ ይሄ መተግበሪያ የግድ ስልክዎ ላይ ሊኖር ይገባል!የኤዲቲንግ ፍላጎት ካላችሁ!
:
5️⃣Quikእጅግ በጣም ገራሚ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ሌላው ብልጥ መንገድ ነው!ፈጣን እና ነፃ ነው የራሳቹን ታሪክ በQuik ለማድረግ የራስዎን ተወዳጅ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮ ይምረጡ!ሌላው #ለQuik ይተውት!በጣም ጥሩው ነገር ደግሞ የቪዲዮ ፈጠራ ችሎታዎን ማሳደግ መቻሉ ነው!ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ ቪዲዮዎችን #Crop ማድረግ፣ማሳመሪያዎችን፣ጽሑፎችን መጨመር እና ቪዲዮዎችን ከሙዚቃ ጋር ለማመሳሰል ፈጣን የሆነ አማራጭ ነው!
6️⃣VivaVideoብዙ አስደናቂ ባህሪዎች አሉት!መተግበሪያው በቀጥታ በስልክዎ ፕሮፌሽናል የሚመስሉ ቪዲዮዎችን እንዲፈጥሩ ለማገዝ የታሰበ ነው!ከተለጣፊዎች እስከ ተንቀሣቃሽ ክሊፖች እና የትርጉም ጽሑፎች ከሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተስማሚ ፊልተሮች መምረጥ ይችላሉ!በውስጡ ዘገምተኛ (#SlowMotion)ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ስሪት እና የተንሸራታች ማሳያ #SlideshowMaker አለው!
7️⃣FuniMateVideo Editor በቀላሉ አዝናኝ ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይረዳል!የዕለት ተዕለት ኑሮዎን በቀጥታ ወደ ፈጠራ ቪዲዮዎች ለመለወጥ እና የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የማጋሪያ አማራጮች አሉት!አጭር ቪዲዮዎችን #ኤዲት ለማድረግ የታቀዱ የላቁ አማራጮች አሉት!
:
8️⃣Magistoመደበኛ የቪዲዮ ኤዲቲንግ ተሞክሮ ለሌላቸው ምርጥ የቪዲዮ ኤዲቲንግ መተግበሪያ ነው!ብዙ ጥረት ሳያደርጉ ምርጥ ቪዲዮን ለመስራት እንዲረዳዎ የቪዲዮ ክሊፕ ፎቶግራፎችን ሙዚቃን ጽሑፎችን (የቪዲዮውጤቶችን)እና የቪዲዮ ማጣሪያዎችን ይይዛል

@ethiotechforall


ኮምፒዩተር
... ...
ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።
ኮምፒዩተር
ታሪክ
ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው።
የኮምፒዩተር ዐይነቶች
ሜን ፍሪም
ሱፐር ኮምፒዩተር
ዎርክ ስቴሽን
ማይክሮ ኮምፒዩተር-(ዴስክቶፕ፣ ላፕቶፕ፣ ፓልምቶፕ)
ሚኒ ኮምፒዩተር
ዋና የኮምፒየተር ዐይነቶች እንደሚከተለው ነው፦
የኮምፕዩተር ክፍሎች
የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ሞኒተር (የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል)
ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡
14 ኢንች 15 ኢንች እያልን ስንናገር አለካኩ ከምስል ማሳያው አንድ ጥግ እስከ ሌላኛው ጥግ ያለውን ርቀት በመለካት ነው፡፡(ስዕሉን ይመልከቱ፡፡)
በፊት የነበሩት የላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ሬሾ (ርዝመት ሲካፈል ለወርድ) 4በ3(በትክክል ሲጻፍ 4:3 ይሆናል) ነበር፡፡
አሁን ደግሞ የቲያትር ሞድ የሚባለው ባለ 16፡9 ሬሾ ወይም ዋይድ ስክሪን (widescreen) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡
2.ማዘርቦርድ(እናት ሰሌዳ)(ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት)
3.ሲፒዩ(የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡)
4.ሜሞሪ(ማስታወሻ)(የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠንበት የምንሰራበት)
ሜሞሪ(ማስታወሻ) በባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡
ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡
5.ኤክስፓንሽ ስሎት
6.የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረቢያ (power supply)
7.የሲዲ ማሰሪያ (cd drive)
8.ሀርድ ዲስክ (የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ)
9. መሎጊያ (ማውስ )
10.የፊደል ገበታ (ኪቦርድ)
ዊኪፒዲያ ላይ ያለውን ምስል ከቁጥሩ ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡
ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ
ታዋቂ ዋና ዋና የኮምፕዩተር አምራቾች
ታዋቂ የኮምፕዩተር አምራቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳዱን የኮምፕዩተር ክፍል(ዕቃዎች)ይሠራሉ ማለት አይደለም፡፡
1.አይቢኤም[IBM](አሁን እንኳ የፒሲ ክፍሉን እ.ኤ.አ. በ2004 ለቻይናው ሊኖቮ ሸጦታል)፡፡ አሁን ሜን ፍሬም[Main Frame] ኮምፒዩተር ነው በብዛት የሚያመርቱት/የሚሠሩት፡፡
ድረ ገጽ---[ http://www.ibm.com የአይቢኤም ድረ ገጽ ]
2.ዴል[Dell]
ድረ ገጽ---[ http://www.dell.com የዴል ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የዴል ወኪል አልታ ኮምፒዩተር ነው፡ ፡አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ኔጃት ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
3.ኤሰር[Acer]
ድረ ገጽ---[ http://www.acer.com የኤሰር ድረ ገጽ]
በኢትዮጵያ የኤሰር ወኪል ኔጃት ኮምፒዩተር ነው፡፡ አድራሻቸው ቦሌ መንገድ ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት አልታ ኮምፒዩተር ያለበት ፎቅ ላይ ነው፡፡
4.ቶሺባ [Toshiba]
ድረ ገጽ---[ http://www.toshiba.com የቶሺባ ድረ ገጽ]
5. አፕል [Apple]
ድረ ገጽ---[ http://www.apple.com የአፕል ድረ ገጽ]
6.ኤችፒ[HP]
ድረ ገጽ---[ http://www.hp.comድ የኤችፒ[ድረ ገጽ]
ኮምፕዩተሮችና የዓለም ፊደላት
የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።

@ethiotechforall


ከናተ የሚጠበቀው
በዚህ ሊንክ

https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i475170065

ገብታችሁ ቦቱን Start ትሉታላችሁ ከዛ #Join የሚለውን ተጭናችሁ ቻናሉን ከተቀላቀላችሁ በሗላ ለጓደኞቻችሁ invite ማድረግ ነው።




በInbox አይሰራም ያላችሁኝ
እኔ በስልኬ የተሞላልኝ ካርድ ይከው
👇👇👇👇


Join the group
@ethiotech_discussion


በስልኮ ኢንተርኔት ጠቀሙ ብዙ ብር እየቆረጠብዎ ተቸግረዋል?
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

እንግዴዉ በስልኮ ላይ የ ሚከተሉትን ማስተካከያዎች በማድረግ መቀነስ ይችላሉ።

1.መጀመሪያ የስልኮን በመክፈት Setting -> Connection ( Wireless and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን በደረጃ ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ሳይታዩ አፕሊኬሽኑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ይነግረናል፤ ከታች ደግሞ Limit background process የሚል አማራጭ አለ። ከእሱም ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል እንችላለን። ወደ ሗላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ የሚወስድብንን ብር መቀነስ እንችላለን። በተጨማሪም ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል።
አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting -> Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ።
2.በተጨማሪም Setting -> Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ለHuawei ስልኮች Data usage
ለመግባት፣ Setting -> wireless & Networks -> more.. -> Data Usage ->
Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ

3.Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል።

4.Setting -> Developer option (About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።
Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት
የሚከተለውን ያድርጉ። Setting -> About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል።

5.የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት።
ለዚህም Setting ->About phone (device) -> Software update ገብተን Auto update የሚለው
የተመረጠ ከሆነ [√] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።

6.GPS መዝጋት

7.ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል።

8.Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት።

9.Opera Mini የምንጠቀም ከሆነ Opera Setting ውስጥ Image quality የሚለውን Low quality ማድረግ። ይሄም ኦፔራ ፈጣን እንዲሆን እና ብዙ ገንዘብ እንዳይቆርጥ ያደርጋል።

10.ቴሌግራም ሲጠቀሙ auto download የሚለዉን uncheck ማድረግ
Go to ቴሌግራም Setting->Data Usage->auto download የ ለሚለውን uncheck ያድርጉ።
ይህ በቴሌግራም እኛ ያልፈለግናቸዉ fileች በራሱ እንዳያወርድ ያደርገዋል።

ጠቃሚ ሆኖ ከገኙት ለጓደኛዎ ሸር ያድ ርጉ ።
@AlexoTech


📍 መረጃ ቴክኖሎጂ 📍

"የሳይበር ጥቃት በማን ይፈጸማል? ምንስ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?" -

#በዝነኛው_የቴድ_ቶክ_የዲስኩር_መድረክ_ላይ_ፓብሎስ ቆሟል።

የኮምፒውተር ምስጢር እንዴት ሰብሮ እንደሚገባ እያስረዳ ነው። እርሱ ራሱ የኮምፒውተር መረብ ሰርሳሪ ነበር።

በአዳራሹ የታደሙ ሰዎች ስልኮቻቸውን እንዲያወጡ አዘዘ። የግማሹን ታዳሚ የስልክ መክፈቻ የምስጢር ቁጥር ለራሳቸው መልሶ ነገራቸው።

ሌሎች ተመልካቾች ደግሞ ክሬዲት ካርዳቸውን ይዘው ወደ መድረክ እንዲመጡ አደረገ። የባንክ ክሬዲት ካርድ የምስጢር ቁጥራቸውን በዚያው መድረክ አጋልጦ ሰጣቸው።

#እንበልና…" አለ ፓብሎስ፣ "…እንበልና ያረፍኩበት ሆቴል ከጎኔ የተከራየው ሰው በቴሌቪዥን ምን እየተመለከተ እንደሆነ ልሰልለው ብፈልግ ያ ለእኔ ቀላል ነው…።"

"ጎረቤቴ በቴሌቪዥን የወሲብ ፊልም እየተመለከተ ይሆን? ወይስ የዲዝኒ ፊልሞችን…? ከፈለኩ ደግሞ ጎረቤቴ አልጋው ላይ ተጋድሞ የሚመለከተውን ቻናል ከክፍሌ ሳልወጣ ልቀይርበት እችላለሁ።"

#ተመልካቹ_በዚህ_ልጅ_ድርጊት_ተደነቀ።

ይህ ልጅ ድርጊቱን የሚፈጽመው እንዲሁ ለጀብዱ ነው። ሁሉም የሳይበር ጥቃቶች ግን ለጀብዱ ብቻ አይፈጸሙም።

የመረጃ መረብ ጥቃት ምን ያህል ያሳስባል? መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ።

በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው።

አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል።

ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች አንድ አየር መንገድ መረጃዎቹ ቢጠለፉበት የአውሮፕላኖች መከስከስን ጨምሮ መላ ተግባሩ ሊስተጓጎል ይችላል። በዚህም በቀናት ውስጥ ቢሊዮኖችን ሊያሳጣው ይችላል።

አንድ አገር የመብራት ኃይል አቅራቢ ድርጅቱ በመረጃ ቦርቧሪዎች ቢገረሰስበት አገር በድቅድቅ ጨለማ ልትዋጥ ትችላለች።

ባንኮች በመረጃ ጠላፊዎች መረጃቸው ቢታወክ አለኝ የሚሉት ገንዘብ፣ ሰበሰብነው የሚሉት አዱኛ ሁሉ በአንድ ጀንበር እንደ ጉም ሊተንባቸው ይችላል።

ይህን ሁሉ ተአምር የሚሰሩት መረጃ ጠላፊዎች እነማን ናቸው? በቀድሞ ጊዜ መረጃ ጠላፊዎች ገና ሮጠው ያልጠገቡ ጎረምሶች ነበሩ።

ድርጊቱን የሚፈጽሙትም ድርጊቱን መፈጸም እንደሚችሉ ለማረጋገጥና እርካታን ለማግኘት ብቻ ነበር። ልክ ቤት ውስጥ የተበላሸ ቴፕ ፈታትቶ መገጣጠም እንደሚያስደስተው ሰው፤ ልክ የተጣለ ኮምፒውተር አንስቶ ዳግም ሕይወት መዝራት እንደሚያስደስተው ልጅ…ነገሩ ጌም ነው! ጨዋታ ነው!

በኋላ ላይ ነው ነገሩ የቢዝነስ ቅርጽ እየያዘ የመጣው። ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ተሰባስበው የአንድን ድርጅት ምስጢር መቦርበር ጀመሩ።

ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ያሉ አደገኛ ወጣቶች ተሰባስበው ትልቅ ድርጅት መመስረት ያዙ። የሰው መረጃን በመቦርቦር የጀመሩት ሱስ መረጃ ቦርቧሪዎችን አድኖ ወደመያዝ ተሸጋገረ።

ይህ በጎረምሳነቱ ኪስ አውላቂ የነበረ ነውጠኛ በጎልማሳነቱ ጠብ የማያጣው መሸታ ቤት ደንብ አስከባሪ (ጋርድ) ሲሆን ማለት ነው።

በዚህ ሂደት የጸረ ጥቃት ተከላካይ ኩባንያዎች መመስረት ያዙ።

ይህ ነገር እያደገ ሄደና አገራት ጦርነት የሚከፍቱት የእግረኛ ጦር በመላክ፣ ታንክ በመንዳትና ሚሳይል በማስወንጨፍ መሆኑ እየቀረ የሳይበር ውጊያ ውስጥ ገቡ።

'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? አሜሪካ ለተፈፀመባት የሳይበር ጥቃት ሰሜን ኮሪያን ከሰሰች

ምናልባት በመጪዎቹ ዘመናት "የድሮ ሰዎች ድንበር ድረስ ሄደው ይዋጉ ነበር" ተብሎ የታሪክ መጽሐፍ ይጻፍ ይሆናል፣ ለዚህ ትውልድ።

በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠሩትን ጥቃቶች ገታ አድርገን የመረጃ መረብ ደኅንነት ጥሰቶች በአገራት ደረጃ እንዴት ነው የሚፈጸሙት፣ ለምንድነው የሚፈጸሙት፣ ምን ያህል አሳሳቢ ናቸው የሚለውን እንመልከት።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ መሠረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ሙከራ እንዳደረጉባትና እንዳከሸፈችው ገልጸ ነበር።

ምንም እንኳን የተፈጸመባት ጥቃት ኢእተዮጵያ እንደላችው ቀላል ባይሆንም ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬን ተመሳሳይ ክስ በሩሲያ ላይ አቅርባ ነበር።

ይህ በታሪክ ትልቁ የመረጃ መረብ ጥቃት ነበር የተባለለትን የዩክሬንን ክስተት ዛሬ መልሰን ብንዳስስ ከወቅቱ ጋር ስሜት የሚሰጥ ጉዳይ ይሆናል ብለን ተስፋ አደረግን።

ዩክሬንን በእንብርክክ ያስኬዳት ጥቃት ሰኔ፣ 2009 ዓ.ም ጠዋት።

ኦሌዳር ቪያንኮ በዩክሬን የጸረ ሳይበር ጥቃት ኩባንያ ባለቤት ነው።

አስቤዛ ለመገዛዛት ወደ ሱፐርማርኬት እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ። የዩክሬን ትልቁ ቴሌኮሚኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ናቸው የደወሉት።

"ቪያንኮ! ጉድ ሆነናል ቶሎ ድረስ" አሉት።

ብዙም አልደነቀውም። ምክንያቱም ሳይበር ጥቃት በዩክሬን በሽበሽ ነዋ።

እሺ እመጣለሁ ብሎ ሕይወቱን ቀጠለ። አስቤዛውን ገዛዝቶ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ነዳጅ ማደያ ገብቶ ነዳጅ ቀዳ። ሒሳብ ሊከፍል ክሬዲት ካርዱን ሲጠቀም ግን ካርዱ አይሠራም። ደነገጠ።

በዚያው ቅጽበት በዩክሬን ግዙፍ ኩባንያዎች ወደእርሱ እየደወሉ ነበር። የሁሉም ጥሪ "እባክህን ቶሎ ድረስ፤ ጉድ ሆነናል" የሚል ነበር።

ለካንስ ያን ዕለት ማለዳ የደረሰው ጥቃት የሁልጊዜው አይነት አልነበረም። ጥቃቱ ከዩክሬን ተነስቶ 60 አገራትን ያዳረሰ ስለነበር "አንደኛው (የሳይበር) የዓለም ጦርነት" ብለው የሚጠሩት አልታጡም።

ዓለም በታሪኳ እንደዚያ ዓይነት ጥቃት ከዚያ ቀደም በጭራሽ ደርሶባት አያውቅም።

ይህ ከመሆኑ ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የሳይበር ጥቃት መረጃዎችን በመለዋወጥ የሚታወቁትና አምስቱ ዓይኖች (The five Eyes) በሚል የሚታወቁት እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ "ሩሲያ አደገኛ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች" ብለው ፍርሃታቸውን ገልጠው ነበር።

#የፈሩት_ደረሰ።

ለመሆኑ ሳይበር ጥቃት ሲደርስ ምንድነው የሚሆነው? ሚስተር ቪያንኮ ያን ቀን ክሬዲት ካርዱ አልሰራ ሲለው መኪናውን ባለችበት አቁሞ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ካፌ ገብቶ ላፕቶፑን አውጥቶ ወደ ሥራ ገባ። ጥቃቱን ሊዋጋ፣ አንድ ላፕቶፕ ይዞ መሸገ፤ ካፌ ውስጥ።

ወዲያውኑ በየአቅጣጫው ከሚገኙ የጸረ ሳይበር ጥቃት ተከላካይ ጓዶቹ ጋር መነጋገር ጀመረ። እርሱ እንደ ጄኔራል፣ እነርሱ እንደ እግረኛ ሠራዊት ጦርነት ጀመሩ። የሁሉም ጦር መሳሪያ ደግሞ ላፕቶፕ ነው።

"ወዲያውኑ ይህ ጥቃት እንደተለመደው ተራ ጥቃት እንዳልሆነ አወቅን" ይላል ቪያንኮ።

#እንዴት_አወቀ?

ምክንያቱም ውስብስብ ነው፤ ምክንያቱም ሌሎች ጥቃቶች አንድ መሥሪያ ቤትን ነው ኢላማ የሚያደርጉት። ይህኛው ግን ያስተረፈው ነገር የለም።

ከትልልቅ የኤሌክትሪክ አመንጪ ድርጅቶች ጀምሮ ትንንሽ የሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች ድረስ መዋቅራቸውን አውኮት ነበር።

ባንኮች አልቀሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን አልተረፈ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ፍርድ ቤቶች…ዝርዝሩ የትየለሌ ነው።

ሰው ሰራሽ ልህቀት፦ ከመፃኢ የዓለም ፈተናዎች አንዱ! ሌሎቹስ? እንዲህ ዓይነት ጥቃት በተራ የመረጃ ቦርቧሪዎች የሚፈጸም ሊሆን እንደማይችል ሚስተር ቪያንኮም ያውቃል፣ ሰይጣንም ያውቃል…አጥቂም ያውቃል…ተጠቂም ያውቃል።

ምንጭ :- ቢቢሲ


Online ገንዘብ መስራት ለምትፈልጉ ሁሉ።

በነገራችን ላይ እውነተኛ ነው።

Step 1⃣ ይከንን ሊንክ ተጫኑ

👇👇

https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i475170065

ቦቱን Start ያድርጉት

Step 2⃣

ከዛ join የሚል ይመጣል
Join የሚለውን ተጭናችሁ
Ask Anything Ethiopia
ቻናል ተቀላቀሉ

Step 3⃣ Ask Anything Bot

ላይ ሌላ ሰው #invite ማድረጊያ #link ይላክላችሗል
ሊንኩን ኮፒ በማድረግ ወይም #Share
የሚለውን በመጫን ሌላ ሰው ወደ ቻናሉ እንዲገባ ማድረግ አለባችሁ።

አንድ ሰው ወደ ቻናሉ ሲገባላችሁ 50 ሳንቲም ታገኛላችሁ።

30 ሰው ስትጋብዙ 15 ብር ማውጣት ትችላላችሁ።

ገንዘቡን በስልካቻሁ ወይም በባንክ ማስላክ ትችላላችሁ።

Step 4⃣ ገንዘቡን ለማውጣት እዛው እቦቱ ላይ Cash Out የሚለውን ስትጫኑት

በሞባይል ካርድ ወይም በባንክ ብሎ ያስመርጣችሗል
በ ሞባይል ካርድ የሚለውን ስትጯኑ ብሩ በስልካችሁ ላይ ይላክላችሗል።

ልብ በሉ ብሩ የሚከፈለው 30 ሰው በናተ ሊንክ ወደ ቻናሉ ሲገባ ነው

ሞክሩት እውነተኛ ነው።


ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

@ethiotechforall


እነዚህን አጫጭር ኮዶች ያውቋቸዋል❓❔❓

1.) GOOGLE : Global Organization
Of Oriented Group Language Of Earth .
2.) YAHOO : Yet Another Hierarchical
Officious Oracle .
3.) WINDOW : Wide Interactive
Network Development for Office
work Solution
4.) COMPUTER : Common Oriented
Machine Particularly United and used
under Technical and Educational
Research.
5.) VIRUS : Vital Information
Resources Under Siege .
6.) UMTS : Universal Mobile
Telecommunications System .
7.) AMOLED: Active-matrix organic
light-emitting diode
8.) OLED : Organic light-emitting
diode
9.) IMEI: International Mobile
Equipment Identity .
10.) ESN: Electronic Serial Number .
11.) UPS: uninterrupted power supply .
12). HDMI: High-Definition
Multimedia Interface
13.) VPN: virtual private network
14.) APN: Access Point Name
15.) SIM: Subscriber Identity
Module
16.) LED: Light emitting diode.
17.) DLNA: Digital Living Network
Alliance
18.) RAM: Random access memory.
19.) ROM: Read only memory.
20) VGA: Video Graphics Array
21) QVGA: Quarter Video Graphics
Array
22) WVGA: Wide video graphics
array.
23) WXGA: Wide screen Extended
Graphics Array
24) USB: Universal serial Bus
25) WLAN: Wireless Local Area
Network
26.) PPI: Pixels Per Inch
27.) LCD: Liquid Crystal Display.
28.) HSDPA: High speed down-link
packet access.
29.) HSUPA: High-Speed Uplink
Packet Access
30.) HSPA: High Speed Packet
Access
31.) GPRS: General Packet Radio
Service
32.) EDGE: Enhanced Data Rates for
Global Evolution
33.)NFC: Near field communication
34.) OTG: on-the-go
35.) S-LCD: Super Liquid Crystal
Display
36.) O.S: Operating system.
37.) SNS: Social network service
38.) H.S: HOTSPOT
39.) P.O.I: point of interest
40.)GPS: Global Positioning System
41.)DVD: Digital Video Disk / digital
versatile disc
42.)DTP: Desk top publishing.
43.) DNSE: Digital natural sound
engine .
44.) OVI: Ohio Video Intranet
45.)CDMA: Code Division Multiple
Access
46.) WCDMA: Wide-band Code
Division
Multiple Access
47.)GSM: Global System for Mobile
Communications
48.)WI-FI: Wireless Fidelity
49.) DIVX: Digital internet video
access.
50.) .APK: authenticated public key.
51.) J2ME: java 2 micro edition
53.) DELL: Digital electronic link
library.
54.)ACER: Acquisition Collaboration
ExperimentationReflection
55.)RSS: Really simple syndication
56.) TFT: thin film transistor
57.) AMR: Adaptive Multi- Rate
58.) MPEG: moving pictures experts
group
59.)IVRS: Interactive Voice Response
System
60.) HP: Hewlett Packard

@ethiotechforall


DV 2022 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2022 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ ጥቅምት ሀሙስ 07/2020 ጀምሮ ህዳር 10/2020 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2022 Program: Online Registration
DV-2022 Program: The online registration period for the DV-2022 Program begins on Wednesday, October 7, 2020 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 10, 2020 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2022 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2022 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2022 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም
መልካም እድል ይመኝላቹሀል
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ


የተበላሸ ወይም ኮራብት ያደረገ ሚሞሪ ካርድ ወይም ፍላሽ ዲስክ
እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል እነዚህን እስቴፓች ይጠቀሙ።
#ያስተዉሉ : በተበላሸዉ ወይም ኮራብት ባደረገው ሚሞሪ ካርዱ ውስጥ የነበሩት ፋይሎች
መጥፋታቸው የማይቀር ነገር ነው!
Step1: ሚሞሪ ካርዱን የኮምፒውተሮ USB port ላይ ይሰኩት።
Step2: ከዛም my computer ውስጥ ገብተው ኮምፒውተሩ ሚሞሪ ካርዱን እንዳነበበው ቼክ ያድርጉ።
Step3: ከዛም Start በተኑን በመጫን cmd ብለው በመፃፍ Enterን ይጫኑ።
Step4: ከዛም Command prompt ውስጥ ብለው DISKPART ይፃፋና Okን ይጫኑ።
Step5: ከዛም list disk there ብለው ይፃፋና የሚቀርቡ አማራጮችን ይዩ።
Step6: ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ ሚሞሪ ካርዱን ከነ ቁጥሩ ያገኛሉ።
Step7: ከዛም select disk (disk_number) ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።
Step8: ከዛም clear ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።
Step9: ከዛም create partition primary ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።
Step10: ከዛም active ብለው ይፃፋና Enter ይጫኑ።
Step11: ከዛም format fs=fat32 ብለው
ይፃፋና Enter ይጫኑ።
Step12: ከዛም ኮምፒውተሩ ሚሞሪ ካርዱን ፎርማት ያደርገዋል።


ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከExternal Hard Disk በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን ከዛስ የደበቅነውን ፎልደርና ፋይል እንዴት እናወጣዋለን?
ምሳሌ: "Documents" የሚል ፎልደር Local Disk C. ቢኖር
✅ Step 1: ከአንድ ላይ Windows key ና R key ይጫኑ ከዛም Run dialog box ይመጣ cmd ብለው ይጻፉና OK ይጫኑ Command Prompt ይመጣላችኋል.
✅ Step 2: ይህንን ይጻፉ attrib +s +h c:\documents ላይ ከዛም Enter ይጫኑ .
አሁን documents የሚለው ፎልደር ከነበረበት ቦታ ይጠፋል ማለት ነው። ይህ ማለት ሙሉበሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም ተደበቀ እንጅ።
_/_//_/___________
-----ሌላ አማራጭ------
ለምሳሌ ከፍላሽ ዲስክ ወይም ከሀርድዲስክ ያለን መረጃ ለመደበቅ ለምሳሌ ፍላሹ Removable dusk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን ኢተርን እንጫናለን ይህ ማለት ወደ ፍላሽ ዲስክ ገባን ማለት ነው ከፍላሹ ውስጥ documents የሚል ፎደር ቢኖርና መደበቅ ብንፈልግ
✅ attrib +s +h documents ብለን እንጽፋለን ከዛም ኢንተርን እንጫናለን አሁ documents የሚለው ፎልደር ይደበቃል ማለት ነው።
ከፍላሽ ዲስካችን የደበቅነውን documents የሚለውን እንደገና ለማውጣት ብንፈልግ
✅ attrib –s –h documents ጽፈን ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ይመለሳል ማለት ነው ከዚህ ላይ የናንተ folder ስም የተለየ ከሆነ documents የሚለውን ብቻ ነው የምትቀይሩት ማለት ነው። ለምሳሌ my secret file የሚል ፎልደር ካላችሁ በ " ማስገባት አለባችሁ ይህም ማለት
✅ ለመደበቅ attrib +s +h "my secret file"
✅ ከተደበቀበት ለማውጣት attrib –s –h "my secret file" የፎልደሩ ስም ከአንድ በላይ word ከሆነ የግድ በ" " ማስገባት አለባችሁ።
_/_//_/___________
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!


ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን በምን አይነት መንገድ ነው ማሳረፍ የሚኖርብን?
--------------
ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ
መንቀራፈፍ ይጀምራል።
በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም
ማሳረፍ ያስፈልጋል።
ኮምፒውተራችን “ተርን ኦፍ”፣ “ስሊፕ” አልያም “ሀይበርኔት” በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ
ማድረግ እንችላለን።
ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው።
እናም ከዚህ በታች ስለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች እና ጉዳቶች
በዝርዝር እንመለከታለን።
“ስሊፕ”
በቀደሙ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ “ስታንድ ባይ”
የሚል ስያሜ የነበረው “ስሊፕ” የኮምፒውተራችን የሀይል ፍጆታ የሚቀንስ ነው።
ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል።
የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ
ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ስራ በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል።
ይሁን እንጂ ስሊፕ ማድረግ ከሸት ዳውን እና ሃይበርኔት የበለጠ ሀይል ይወስዳል። በመሀል
የሀይል መቋረጥ ከተከሰተም ሴቭ ሳናደርግ የተውናቸው ስራዎች ሊጠፉ ይችላሉ።
በመሆኑም ኮምፒውተራችን “ስሊፕ” ከማድረጋችን በፊት የተጀመሩ ስራዎችን ሴቭ
ማድረግ ተገቢ ነው።
“ሸት ዳውን”
ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው “ሸት ዳውን” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም
ነው።
በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል፤ የራም (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል፤
በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም።
በ”ሸት ዳውን” የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም።
ይሁንና ኮምፒውተራችን በድጋሚ ስንከፍት ዘለግ ያለ ጊዜ (ከ“ስሊፕ” አንፃር) ይወስዳል።
“ሀይበርኔት”
ይህ አማራጭ ደግሞ በ”ስሊፕ” እና በ”ሸት ዳውን” መሀል የሚገኝ ነው።
“ሀይበርኔት” ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን
ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ።
ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን፥
ከ“ስሊፕ” አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ነገር ግን ስሊፕ ያደረግነውን ኮምፒውተር
ስንከፍት ከሚወስደው ጊዜ ዘግየት የማለት ባህሪ አለው።
በሀይበርኔትም ሆነ “ሸት ዳውን” ኮምፒውተራችን ስናጠፋ እና ስንከፍት የምንጠቀመው
ሀይል ተመሳሳይ ነው።
ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ “ሀይበርኔት” ተመራጭ ነው።
መቼ ነው “ስሊፕ”፣ “ሸት ዳውን” ወይም “ሀይበርኔት ማድረግ የሚኖርብን?
በቀን ውስጥ ለተከታታይ ስአታት ኮምፒውተራችንን የምንጠቀምበት ከሆነ ሙሉ በሙሉ
ማጥፋት (ሸት ዳውን) አይጠበቅብንም።
ይሁን እንጂ በቀን ውስጥ ለአንድ ስአት አልያም ለሁለት ስአት የምንጠቀም ከሆነ ሙሉ
በሙሉ ቢጠፋ መልካም ነው።
“ስሊፕ”
ካቆምንበት በአጭር ጊዜ ተመልሰን ስራችንን ለመቀጠል “ስሊፕ” ተመራጭ ነው።
“ስሊፕ” ስናደርግ ኮምፒውተራችን በፈለግነው ቅፅበት ዝግጁ ይሆናል።
“ሸት ዳውን”
ለስአታት አልያም ለቀናት ኮምፒውተራችን እንዲያርፍ ስንፈልግ ደግሞ “ሸት ዳውን”
ማድረጋችን መዘንጋት የለብንም።
በርካታ ሰዎች የዘጉት ኮምፒውተር በፍጥነት እንዲከፈት በማሰብ “ሸት ዳውን” ከማድረግ
ይልቅ “ሀይበርኔት”ን ይመርጣሉ።
ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች እና ሶፍትዌሮች ከ”ሀይበርኔት” መልስ ተግባራቸውን
በአግባቡ ማከናወን ሊሳናቸው ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም “ሸት ዳውን”
ማድረጉ ተመራጭ ነው።
“ሀይበርኔት”
ከ“ስሊፕ” ይልቅ “ሀይበርኔት” ሀይል በመቆጠብ ረገድ የተሻለ ነው።
ረዘም ላለ ስአታት የጀመርነውን ስራ ማቋረጥ ከፈለግን “ሀይበርኔት” ማድረግ ይመከራል። ለምሳሌ ለእንቅፍል ወደ መኝታ ክፍላችን ስናመራ።
“ሀይበርኔት” የኤሌክትሪክ ሀይልን እና የኮምፒውተር ባትሪን ሀይል ለመቆጠብ ይረዳል።
ነገር ግን ሀይበርኔት ያደረግነውን ኮምፒውተር ስንከፍት ጥቂት ጊዜ ይወስዳል።
በአጠቃላይ ኮምፒውተራችን እንደምንጠቀምበት አግባብ የእረፍት ጊዜ እነዲኖረው ከላይ
የጠቀስናቸውን ማሳረፊያዎች መጠቀም ይገባል።


Genzeb yemegega bot nw
Channalu join adregachihu share sitaderge birr tagegalachihu
👇

https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i475170065


ከኮምፒውተር፣ ከፍላሽ፣ ከExternal Hard Disk በፎልደር ውስጥ ያለን ፋይል እንዴት መደበቅ እንችላለን ከዛስ የደበቅነውን ፎልደርና ፋይል እንዴት እናወጣዋለን?
ምሳሌ: "Documents" የሚል ፎልደር Local Disk C. ቢኖር
✅ Step 1: ከአንድ ላይ Windows key ና R key ይጫኑ ከዛም Run dialog box ይመጣ cmd ብለው ይጻፉና OK ይጫኑ Command Prompt ይመጣላችኋል.
✅ Step 2: ይህንን ይጻፉ attrib +s +h c:\documents ላይ ከዛም Enter ይጫኑ .
አሁን documents የሚለው ፎልደር ከነበረበት ቦታ ይጠፋል ማለት ነው። ይህ ማለት ሙሉበሙሉ ጠፍቷል ማለት አይደለም ተደበቀ እንጅ።
_____/_//_/___________
-----ሌላ አማራጭ------
ለምሳሌ ከፍላሽ ዲስክ ወይም ከሀርድዲስክ ያለን መረጃ ለመደበቅ ለምሳሌ ፍላሹ Removable dusk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን ኢተርን እንጫናለን ይህ ማለት ወደ ፍላሽ ዲስክ ገባን ማለት ነው ከፍላሹ ውስጥ documents የሚል ፎደር ቢኖርና መደበቅ ብንፈልግ
✅ attrib +s +h documents ብለን እንጽፋለን ከዛም ኢንተርን እንጫናለን አሁ documents የሚለው ፎልደር ይደበቃል ማለት ነው።
ከፍላሽ ዲስካችን የደበቅነውን documents የሚለውን እንደገና ለማውጣት ብንፈልግ
✅ attrib –s –h documents ጽፈን ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ይመለሳል ማለት ነው ከዚህ ላይ የናንተ folder ስም የተለየ ከሆነ documents የሚለውን ብቻ ነው የምትቀይሩት ማለት ነው። ለምሳሌ my secret file የሚል ፎልደር ካላችሁ በ " ማስገባት አለባችሁ ይህም ማለት
✅ ለመደበቅ attrib +s +h "my secret file"
✅ ከተደበቀበት ለማውጣት attrib –s –h "my secret file" የፎልደሩ ስም ከአንድ በላይ word ከሆነ የግድ በ" " ማስገባት አለባችሁ።
_____/_//_/___________
አንዳንድ ጊዜ በፍላሽ ዲስክ የያዝነው መረጃ ይደበቅብናል። ከተደበቀበት ሁሉንም ፎልደሮችና ፋይሎችን ለማውጣት ስንፈልግ ከይ በጠቀስኩት አግባብ ለምሳሌ ፍላሽ ዲስካችን Removable Disk(F) ቢሆን ከኮማንድ ፕሮምፕቱ ላይ F: ብለን እንጫንና attrib -s -h /s /d ብለን እንጽግና ኢንተርን እንጫናለን ከዛም ሁሉም የተደበቀው ፋይል ሁሉ ይወጣልናል ማለት ነው። ሞክሩትና እዩት!


እንዴት የዮትዮብ ቻናል እንከፍታለን
*******************
*******************
በጉግል አካውንታችን የዩትዬብ ቪድዩችን ማየት #Like ማድረ እና ቻናሎንን #Subscribe ማድረግ እንችላለን ።
ነገር ግን #Video ለመጫን እና #play list ቪድዩችን ይትዮብ ላይ ለማስቀመጥ የዬትዬብ ቻናል ያስፈልጋል።

የዩትዬብ ቻናል ለመክፈት የሚያስፈልገው የኢሜል አድራሻ ብቻ ነው።

እንዴት የ ኢሜል አድራሻ እንከፍታለን የሚለውን እቻናላችን ላይ አለላችሁ ፈልጉት
የዬትዬብ ቻናል ለመክፈት ከታች ያሉትን እስቴፖች ተከተሉ
1.እስልካችሁ ወይም እኮምፒውተራችሁ ላይ #You tube ክፈቱ እና # Sign in አድርጉ።

እስልካችሁ ላይ የራሱ የዮትዮብ #App አለ እሱን ክፈቱት ወይም ይከንን ሊንክ
http://youtube.com/ ተጫኑ።
ከዛ ከላይ በስተ ቀኝ # Sign in የሚለውን ተጫኑ እና ኢሜላችሁን አስገቡ እና #Next በሉት።

2.ወደ ዬትዬብ #Account #Setting ውስጥ ግቡ እና ቻናላችሁን #Create አድርጉ።
የአካውንት ምልክቷን ተጫኑ (ከላይ በስተ ቀኝ በኩል ትገኛለች ) ከዛ Create a channel የሚለውን ተጫኑ

3. Create your channel
ከዛ ሁለት አማራጭ ይመጣላችሗል
1. Use your name ይከ የጐግ አካውንታችሁን ስም ተጠቅማችሁ የዬትዬብ ቻናል እንድትፈጥሩ ያደርጋል

2. Use a custome name ይከ ለዬትዬባችሁ ሌላ ስም እንድትሰጡ ያደርጋል ።ይከንኛውን አማራጭ #Select የሚለውን በመጫን ይምረጡ ።
ከዛ #Channel name የሚለው ላይ የቻናል ስም አስገቡ እና #Create የሚለውን ተጯኑ።
4.አሁን የዬትዬብ ቻናል ፈጥራችሗል።
የፈጠራችሁት ቻናል #Setting ላይ በመሄድ Profile photo #descriotion መስጠት ትችላላችሁ።

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
@ethiotechforall


ሞባይልዎ ላይ ችግር የሚያስከትሎ አፕልኬሽኖች የትኞቹ ናቸው?
********************************************************
1⃣.የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ

✅የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው።
አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ!

✅የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን "የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም" ይላል።

✅ የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም
ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ። የስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን "ናይት ሞድ" ወይም "ባትሪ ቆጥብ" የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት።

✅ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው።

2⃣.ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች

✅ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። "ክሊን ማስትር" የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው።

✅ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው "ክሊን ማስተር" የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል።

✅የሞባይል ስልክን ፀሐይ ላይ አለመተው
ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል።

✅• በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል?
ይህን ችግር እንቀርፋለን የሚሉ የስልክ መተግበሪያዎች ሐሰት ናቸው። መፍትሄም አያመጡም። እንዲያውም ትኩሳቱን ያብሱበታል። ስልክዎ በአዲስ መንፈስ እንዲሰራ ከፈለጉ አጥፍተው ያሳርፉት።

ለስልክዎ📲 ጠቅላላ ጤና የሚከተሉትን ያስታውሱ

✳️ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ምንነታቸው ከተረጋገጠላቸው ሁነኛ የስልክ መደብሮች ብቻ ያውርዱ። አፕል ስቶር እና ጉግል ስቶር የታወቁት ናቸው።

✳️ የፋይል ስማቸው በኤፒኬ ፊደል እንደሚጨርስ (.apk) ከሚታዩ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ

✳️ራሳቸውን ተአምራዊ ሥራ እንሠራለን እያሉ ከሚያሞካሹ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ

✳️ ስልክዎትን በየጊዜው "አፕዴት" በማድረግ ያድሱ

ቻናላችንን ለመቀላቀል
@ethiotechforall

Показано 20 последних публикаций.

795

подписчиков
Статистика канала