📍 መረጃ ቴክኖሎጂ 📍
"የሳይበር ጥቃት በማን ይፈጸማል? ምንስ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?" -
#በዝነኛው_የቴድ_ቶክ_የዲስኩር_መድረክ_ላይ_ፓብሎስ ቆሟል።
የኮምፒውተር ምስጢር እንዴት ሰብሮ እንደሚገባ እያስረዳ ነው። እርሱ ራሱ የኮምፒውተር መረብ ሰርሳሪ ነበር።
በአዳራሹ የታደሙ ሰዎች ስልኮቻቸውን እንዲያወጡ አዘዘ። የግማሹን ታዳሚ የስልክ መክፈቻ የምስጢር ቁጥር ለራሳቸው መልሶ ነገራቸው።
ሌሎች ተመልካቾች ደግሞ ክሬዲት ካርዳቸውን ይዘው ወደ መድረክ እንዲመጡ አደረገ። የባንክ ክሬዲት ካርድ የምስጢር ቁጥራቸውን በዚያው መድረክ አጋልጦ ሰጣቸው።
#እንበልና…" አለ ፓብሎስ፣ "…እንበልና ያረፍኩበት ሆቴል ከጎኔ የተከራየው ሰው በቴሌቪዥን ምን እየተመለከተ እንደሆነ ልሰልለው ብፈልግ ያ ለእኔ ቀላል ነው…።"
"ጎረቤቴ በቴሌቪዥን የወሲብ ፊልም እየተመለከተ ይሆን? ወይስ የዲዝኒ ፊልሞችን…? ከፈለኩ ደግሞ ጎረቤቴ አልጋው ላይ ተጋድሞ የሚመለከተውን ቻናል ከክፍሌ ሳልወጣ ልቀይርበት እችላለሁ።"
#ተመልካቹ_በዚህ_ልጅ_ድርጊት_ተደነቀ።
ይህ ልጅ ድርጊቱን የሚፈጽመው እንዲሁ ለጀብዱ ነው። ሁሉም የሳይበር ጥቃቶች ግን ለጀብዱ ብቻ አይፈጸሙም።
የመረጃ መረብ ጥቃት ምን ያህል ያሳስባል? መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ።
በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው።
አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል።
ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች አንድ አየር መንገድ መረጃዎቹ ቢጠለፉበት የአውሮፕላኖች መከስከስን ጨምሮ መላ ተግባሩ ሊስተጓጎል ይችላል። በዚህም በቀናት ውስጥ ቢሊዮኖችን ሊያሳጣው ይችላል።
አንድ አገር የመብራት ኃይል አቅራቢ ድርጅቱ በመረጃ ቦርቧሪዎች ቢገረሰስበት አገር በድቅድቅ ጨለማ ልትዋጥ ትችላለች።
ባንኮች በመረጃ ጠላፊዎች መረጃቸው ቢታወክ አለኝ የሚሉት ገንዘብ፣ ሰበሰብነው የሚሉት አዱኛ ሁሉ በአንድ ጀንበር እንደ ጉም ሊተንባቸው ይችላል።
ይህን ሁሉ ተአምር የሚሰሩት መረጃ ጠላፊዎች እነማን ናቸው? በቀድሞ ጊዜ መረጃ ጠላፊዎች ገና ሮጠው ያልጠገቡ ጎረምሶች ነበሩ።
ድርጊቱን የሚፈጽሙትም ድርጊቱን መፈጸም እንደሚችሉ ለማረጋገጥና እርካታን ለማግኘት ብቻ ነበር። ልክ ቤት ውስጥ የተበላሸ ቴፕ ፈታትቶ መገጣጠም እንደሚያስደስተው ሰው፤ ልክ የተጣለ ኮምፒውተር አንስቶ ዳግም ሕይወት መዝራት እንደሚያስደስተው ልጅ…ነገሩ ጌም ነው! ጨዋታ ነው!
በኋላ ላይ ነው ነገሩ የቢዝነስ ቅርጽ እየያዘ የመጣው። ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ተሰባስበው የአንድን ድርጅት ምስጢር መቦርበር ጀመሩ።
ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ያሉ አደገኛ ወጣቶች ተሰባስበው ትልቅ ድርጅት መመስረት ያዙ። የሰው መረጃን በመቦርቦር የጀመሩት ሱስ መረጃ ቦርቧሪዎችን አድኖ ወደመያዝ ተሸጋገረ።
ይህ በጎረምሳነቱ ኪስ አውላቂ የነበረ ነውጠኛ በጎልማሳነቱ ጠብ የማያጣው መሸታ ቤት ደንብ አስከባሪ (ጋርድ) ሲሆን ማለት ነው።
በዚህ ሂደት የጸረ ጥቃት ተከላካይ ኩባንያዎች መመስረት ያዙ።
ይህ ነገር እያደገ ሄደና አገራት ጦርነት የሚከፍቱት የእግረኛ ጦር በመላክ፣ ታንክ በመንዳትና ሚሳይል በማስወንጨፍ መሆኑ እየቀረ የሳይበር ውጊያ ውስጥ ገቡ።
'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? አሜሪካ ለተፈፀመባት የሳይበር ጥቃት ሰሜን ኮሪያን ከሰሰች
ምናልባት በመጪዎቹ ዘመናት "የድሮ ሰዎች ድንበር ድረስ ሄደው ይዋጉ ነበር" ተብሎ የታሪክ መጽሐፍ ይጻፍ ይሆናል፣ ለዚህ ትውልድ።
በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠሩትን ጥቃቶች ገታ አድርገን የመረጃ መረብ ደኅንነት ጥሰቶች በአገራት ደረጃ እንዴት ነው የሚፈጸሙት፣ ለምንድነው የሚፈጸሙት፣ ምን ያህል አሳሳቢ ናቸው የሚለውን እንመልከት።
ሰሞኑን ኢትዮጵያ መሠረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ሙከራ እንዳደረጉባትና እንዳከሸፈችው ገልጸ ነበር።
ምንም እንኳን የተፈጸመባት ጥቃት ኢእተዮጵያ እንደላችው ቀላል ባይሆንም ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬን ተመሳሳይ ክስ በሩሲያ ላይ አቅርባ ነበር።
ይህ በታሪክ ትልቁ የመረጃ መረብ ጥቃት ነበር የተባለለትን የዩክሬንን ክስተት ዛሬ መልሰን ብንዳስስ ከወቅቱ ጋር ስሜት የሚሰጥ ጉዳይ ይሆናል ብለን ተስፋ አደረግን።
ዩክሬንን በእንብርክክ ያስኬዳት ጥቃት ሰኔ፣ 2009 ዓ.ም ጠዋት።
ኦሌዳር ቪያንኮ በዩክሬን የጸረ ሳይበር ጥቃት ኩባንያ ባለቤት ነው።
አስቤዛ ለመገዛዛት ወደ ሱፐርማርኬት እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ። የዩክሬን ትልቁ ቴሌኮሚኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ናቸው የደወሉት።
"ቪያንኮ! ጉድ ሆነናል ቶሎ ድረስ" አሉት።
ብዙም አልደነቀውም። ምክንያቱም ሳይበር ጥቃት በዩክሬን በሽበሽ ነዋ።
እሺ እመጣለሁ ብሎ ሕይወቱን ቀጠለ። አስቤዛውን ገዛዝቶ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ነዳጅ ማደያ ገብቶ ነዳጅ ቀዳ። ሒሳብ ሊከፍል ክሬዲት ካርዱን ሲጠቀም ግን ካርዱ አይሠራም። ደነገጠ።
በዚያው ቅጽበት በዩክሬን ግዙፍ ኩባንያዎች ወደእርሱ እየደወሉ ነበር። የሁሉም ጥሪ "እባክህን ቶሎ ድረስ፤ ጉድ ሆነናል" የሚል ነበር።
ለካንስ ያን ዕለት ማለዳ የደረሰው ጥቃት የሁልጊዜው አይነት አልነበረም። ጥቃቱ ከዩክሬን ተነስቶ 60 አገራትን ያዳረሰ ስለነበር "አንደኛው (የሳይበር) የዓለም ጦርነት" ብለው የሚጠሩት አልታጡም።
ዓለም በታሪኳ እንደዚያ ዓይነት ጥቃት ከዚያ ቀደም በጭራሽ ደርሶባት አያውቅም።
ይህ ከመሆኑ ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የሳይበር ጥቃት መረጃዎችን በመለዋወጥ የሚታወቁትና አምስቱ ዓይኖች (The five Eyes) በሚል የሚታወቁት እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ "ሩሲያ አደገኛ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች" ብለው ፍርሃታቸውን ገልጠው ነበር።
#የፈሩት_ደረሰ።
ለመሆኑ ሳይበር ጥቃት ሲደርስ ምንድነው የሚሆነው? ሚስተር ቪያንኮ ያን ቀን ክሬዲት ካርዱ አልሰራ ሲለው መኪናውን ባለችበት አቁሞ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ካፌ ገብቶ ላፕቶፑን አውጥቶ ወደ ሥራ ገባ። ጥቃቱን ሊዋጋ፣ አንድ ላፕቶፕ ይዞ መሸገ፤ ካፌ ውስጥ።
ወዲያውኑ በየአቅጣጫው ከሚገኙ የጸረ ሳይበር ጥቃት ተከላካይ ጓዶቹ ጋር መነጋገር ጀመረ። እርሱ እንደ ጄኔራል፣ እነርሱ እንደ እግረኛ ሠራዊት ጦርነት ጀመሩ። የሁሉም ጦር መሳሪያ ደግሞ ላፕቶፕ ነው።
"ወዲያውኑ ይህ ጥቃት እንደተለመደው ተራ ጥቃት እንዳልሆነ አወቅን" ይላል ቪያንኮ።
#እንዴት_አወቀ?
ምክንያቱም ውስብስብ ነው፤ ምክንያቱም ሌሎች ጥቃቶች አንድ መሥሪያ ቤትን ነው ኢላማ የሚያደርጉት። ይህኛው ግን ያስተረፈው ነገር የለም።
ከትልልቅ የኤሌክትሪክ አመንጪ ድርጅቶች ጀምሮ ትንንሽ የሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች ድረስ መዋቅራቸውን አውኮት ነበር።
ባንኮች አልቀሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን አልተረፈ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ፍርድ ቤቶች…ዝርዝሩ የትየለሌ ነው።
ሰው ሰራሽ ልህቀት፦ ከመፃኢ የዓለም ፈተናዎች አንዱ! ሌሎቹስ? እንዲህ ዓይነት ጥቃት በተራ የመረጃ ቦርቧሪዎች የሚፈጸም ሊሆን እንደማይችል ሚስተር ቪያንኮም ያውቃል፣ ሰይጣንም ያውቃል…አጥቂም ያውቃል…ተጠቂም ያውቃል።
ምንጭ :- ቢቢሲ