ልሳል👩🎨
የብእሬ ሚስጢር የመኖሬ ህዋ
የቅኔዬ ፍቺ የነፍሴ መንታዋ
ትመስለኝ ነበረ
የሀሳቤ ገዢ ለነብሴ ደራሹ
ለራሴ ትራሱ ሁሌ ምትመጣልኝ ባመሻሹ
የሀሳቤ መቆሚያ
ለችግሬ ሁሉ ጠያቂ መላሹ
ይመስለኝ ነበረ
የዐለም ዉስጠቷ በአንተ ተመስሎ
መኖሬን ያናረ
ይመስለኝ ነበረ
የቃልህ እስትንፋስ በድኑን ገላዬን
አንደ እግዜር እስትንፋስ ለህይወት የነዘረ
የግራ ጎኔ አጥንት ለአጥንቶችህ ግጣም
ለአንተ በቻ ጎኔ ለአንተ የተፈጠረ
ይመስለኝ ነበረ
አይንህ ለኔ ብቻ
እኔ ያንተን መመልከቻ
ከንፈርህስ ብትል
ዎስጥህ ያቃተውን ያወጣው ይመስል
ተስሎልህ ነበር ከዛ ከፊትህ ላይ
አንተ አለኸኝ ብዬ ሌላ ሰዉ እንዳላይ
ነፍስህስ ብትሆን የነፍሴ መረቧ
መኖሬን የሳለች ሞቴን በህይወት ክባ
ይህ ሁሉ ሳለ ግን
ባዶ ማንነትህ በደም ስሬ ገብቶ
ባልኖርክበት ስዬ አንግሼህ ነበረ
ባለመኖርህ ጥግ
ባልኖርክበት ዐለም ውስጤ እየሰከረ
ይህ ሰዐሊዉ ልቤ
በሌለህበት ደርዝ ስዕሉ ሰመረ
ታዲያ ..
አለመኖር መጥቶ አንተን ካልገበረ
ዳግም እስቲ..
ልሳል ነፍሴን ክንፍ አውጥታ
ከአርያም ከዐምላክ መንደር ከላይ ወጥታ
አንተና አካልህን ለኔ አስጠርታ
እንድትኖር ከዐለም ተርታ
የእኛን መንደር ቤትን ሰርታ::
@Be_nayas
@flawsome_poetry
የብእሬ ሚስጢር የመኖሬ ህዋ
የቅኔዬ ፍቺ የነፍሴ መንታዋ
ትመስለኝ ነበረ
የሀሳቤ ገዢ ለነብሴ ደራሹ
ለራሴ ትራሱ ሁሌ ምትመጣልኝ ባመሻሹ
የሀሳቤ መቆሚያ
ለችግሬ ሁሉ ጠያቂ መላሹ
ይመስለኝ ነበረ
የዐለም ዉስጠቷ በአንተ ተመስሎ
መኖሬን ያናረ
ይመስለኝ ነበረ
የቃልህ እስትንፋስ በድኑን ገላዬን
አንደ እግዜር እስትንፋስ ለህይወት የነዘረ
የግራ ጎኔ አጥንት ለአጥንቶችህ ግጣም
ለአንተ በቻ ጎኔ ለአንተ የተፈጠረ
ይመስለኝ ነበረ
አይንህ ለኔ ብቻ
እኔ ያንተን መመልከቻ
ከንፈርህስ ብትል
ዎስጥህ ያቃተውን ያወጣው ይመስል
ተስሎልህ ነበር ከዛ ከፊትህ ላይ
አንተ አለኸኝ ብዬ ሌላ ሰዉ እንዳላይ
ነፍስህስ ብትሆን የነፍሴ መረቧ
መኖሬን የሳለች ሞቴን በህይወት ክባ
ይህ ሁሉ ሳለ ግን
ባዶ ማንነትህ በደም ስሬ ገብቶ
ባልኖርክበት ስዬ አንግሼህ ነበረ
ባለመኖርህ ጥግ
ባልኖርክበት ዐለም ውስጤ እየሰከረ
ይህ ሰዐሊዉ ልቤ
በሌለህበት ደርዝ ስዕሉ ሰመረ
ታዲያ ..
አለመኖር መጥቶ አንተን ካልገበረ
ዳግም እስቲ..
ልሳል ነፍሴን ክንፍ አውጥታ
ከአርያም ከዐምላክ መንደር ከላይ ወጥታ
አንተና አካልህን ለኔ አስጠርታ
እንድትኖር ከዐለም ተርታ
የእኛን መንደር ቤትን ሰርታ::
@Be_nayas
@flawsome_poetry