#ከቶ_በዚህ_ዘመን፣
#ፍቺን_ምን_አበዛው_!?
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ይከበር ነበረ፣ ትዳር ድሮ ድሮ፣
ለቤቱ ያስባል፣ ባል ሚስትም ጠንክሮ፣
ልፋት ሳያንሳቸው፣ ሁሉም ጥሮ ግሮ፣
ድምፅም አይሰማ፣ እንደ ዛሬ ሮሮ፣
======================
ትዳር ዛሬ ዘመን፣ ሁኗል የንግድ እቃ፣
መለወጥ መሸቀጥ፣ በሰዓት ደቂቃ፣
======================
በአንድ ቀን ትውውቅ፣ ተቻኩሎ መጋባት፣
በአንድ ቀን መጣላት፣ ደርሶ መለያየት፣
አክለፍልፎ ማግባት፣ አክለፍልፎ መፍታት፣
======================
ብዙ የለመደ ብዙ፣ የለመደች፣
ወንዱ ፀባይ የለው፣ ለትዳር አይመች፣
ሴቷ ኑሮ አይጥማት፣ እየተማረረች፣
======================
የራስን ጌጥ ትቶ፣ አሻግሮ ሰው ማየት፣
ጥሩ ሚስቱን ንቆ፣ መመኘት ሌላ ሴት፣
የባሏ ውለታ፣ መንምኖ እየታያት፣
የሌሎቹ ጎመን፣ ሥጋ መስሎ ታይቷት፣
======================
ሰው ሁኖ ሲፈጠር፣ ያገኘውን ጉዳይ፣
ደርሶ ዘገነናት፣ ከባሏ ላይ ሥታይ፣
ከኑር አልተሰራ፣ ይቺ ምን ትላለይ!?
======================
ሴት ልጅ በመሆኗ፣ ያለባት ጎደሎ፣
የሷ ችግር መስሎት፣ ቅቤ ልጥበስ ብሎ፣
ሚስቱን ያባርና፣ ይኖራል ኮብልሎ፣
======================
ሁለቱም ጠገቡ፣ በምኞት ማለሉ፣
ውሃ ቀጠነብን፣ ከሰል ጠቆረ አሉ፣
ውሃ ካልተነፋ፣ ትዳር"ን"ም ጠሉ፣
======================
ተገፍታም የገባች፣ የምንቸገረኟን፣
አመል የለሽ ማቱ፣ ገረጭራጫ ስኮን፣
ነግቶ ምታናድድ፣ የምታጨስ ባሏን፣
======================
ሳይፈልግ የገባ፣ ሲኖር ከወንዶችም፣
ለሴት ሸክም ሁኖ፣ የሚኖር ዘላለም፣
ይሄኔም ይዋጣል፣ ትዳር በፍች አለም፣
======================
ወይ አንዳንድ ሀሲድ፣ ምቀኛ ሆኗቸው፣
ማሻ አላህ ሳይል፣ ተስገብግቦ አይቷቸው፣
ተዋደው ቢኖሩም፣ ትዳር አምሮባቸው፣
የሚለዩም አሉ፣ ከሞቀው ቤታቸው፣
መቼም ዙሮ ዙሮ፣ ይሄው መፋታት ነው፣
ከቶ በዚህ ዘመን፣ ፍቺን ምን አበዛው!?
✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/3447
#ፍቺን_ምን_አበዛው_!?
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ይከበር ነበረ፣ ትዳር ድሮ ድሮ፣
ለቤቱ ያስባል፣ ባል ሚስትም ጠንክሮ፣
ልፋት ሳያንሳቸው፣ ሁሉም ጥሮ ግሮ፣
ድምፅም አይሰማ፣ እንደ ዛሬ ሮሮ፣
======================
ትዳር ዛሬ ዘመን፣ ሁኗል የንግድ እቃ፣
መለወጥ መሸቀጥ፣ በሰዓት ደቂቃ፣
======================
በአንድ ቀን ትውውቅ፣ ተቻኩሎ መጋባት፣
በአንድ ቀን መጣላት፣ ደርሶ መለያየት፣
አክለፍልፎ ማግባት፣ አክለፍልፎ መፍታት፣
======================
ብዙ የለመደ ብዙ፣ የለመደች፣
ወንዱ ፀባይ የለው፣ ለትዳር አይመች፣
ሴቷ ኑሮ አይጥማት፣ እየተማረረች፣
======================
የራስን ጌጥ ትቶ፣ አሻግሮ ሰው ማየት፣
ጥሩ ሚስቱን ንቆ፣ መመኘት ሌላ ሴት፣
የባሏ ውለታ፣ መንምኖ እየታያት፣
የሌሎቹ ጎመን፣ ሥጋ መስሎ ታይቷት፣
======================
ሰው ሁኖ ሲፈጠር፣ ያገኘውን ጉዳይ፣
ደርሶ ዘገነናት፣ ከባሏ ላይ ሥታይ፣
ከኑር አልተሰራ፣ ይቺ ምን ትላለይ!?
======================
ሴት ልጅ በመሆኗ፣ ያለባት ጎደሎ፣
የሷ ችግር መስሎት፣ ቅቤ ልጥበስ ብሎ፣
ሚስቱን ያባርና፣ ይኖራል ኮብልሎ፣
======================
ሁለቱም ጠገቡ፣ በምኞት ማለሉ፣
ውሃ ቀጠነብን፣ ከሰል ጠቆረ አሉ፣
ውሃ ካልተነፋ፣ ትዳር"ን"ም ጠሉ፣
======================
ተገፍታም የገባች፣ የምንቸገረኟን፣
አመል የለሽ ማቱ፣ ገረጭራጫ ስኮን፣
ነግቶ ምታናድድ፣ የምታጨስ ባሏን፣
======================
ሳይፈልግ የገባ፣ ሲኖር ከወንዶችም፣
ለሴት ሸክም ሁኖ፣ የሚኖር ዘላለም፣
ይሄኔም ይዋጣል፣ ትዳር በፍች አለም፣
======================
ወይ አንዳንድ ሀሲድ፣ ምቀኛ ሆኗቸው፣
ማሻ አላህ ሳይል፣ ተስገብግቦ አይቷቸው፣
ተዋደው ቢኖሩም፣ ትዳር አምሮባቸው፣
የሚለዩም አሉ፣ ከሞቀው ቤታቸው፣
መቼም ዙሮ ዙሮ፣ ይሄው መፋታት ነው፣
ከቶ በዚህ ዘመን፣ ፍቺን ምን አበዛው!?
✍ አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/3447