Barreeffamni kun bu'a qabeessa namni Amaariffa dandeessan dubbisaa
*************
መጅሊስ በሀጅ መሀመድ ሳኒ አመራርነት ከተመሰረተ እና የ ሙነዘማ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በሗላ ኡለሞች ለሶሰት ተከፈሉ። አንደኛው ቡድን የወጣቶች እንቅስቃሴ ሊወገዝ እንደሚገባ እና ከዲን የወጣ እንቅስቃሴ ነው ተብሎ እንዲፈረጅ የሚፈልጉ ዑለሞች ያሉበት ሲሆን (ሀጅ ኡመር እና ሀጅ አብድልቃድር ይገኙበታል) ሁለተኛው የኡለሞች ክፍል ደግሞ ወጣትነት እና ችኩልነት እንጂ መስመሩ ከዲን የወጣ አይደለም ልንቃወመው አይገባም የሚሉ ኡለሞች ናቸው። ሀጅ መሀመድ ሳኒ ፣ሼኽ አብድልራህማን ሸሪፍ፣ ሀጅ ዙመካን ፣ሀጅ ሙስጠፋ፣ ሼኽ መሀመድ ራፊዕ (ሙሀዲስ) ሀጅ ሙሳ ኪክያ እና ሌሎችም ታላላቅ አሊሞች ይህንን ሀሳብ ደግፈው ሁለቱን ለማስማማት ጥረት በማድረግ በሁለቱም ወገን ችግሮችን አስተናግደዋል። ሙስሊሙን የሚከፋፍል እና ለብዙ ችግር የሚዳርግ ብዙ በላእም መልሰዋል።
ሶስተኛው የኡለማእ ክፍል የሙነዘማ እንቅስቃሴ ትክክል ነው ብሎ በማመን ፊት አውራሪ ሆኖ የተንቀሳቀሰው እና ጠንካራ የነበረው ክፍል ነው። ሀጅ መሀመድ ወሌ፣ሼኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ እና ሌሎችም እዚህ ውሥጥ የሚካተቱ ናቸው።
በዚህ መሀከል ሁለቱን ለማስተሳሰረወ እና በጋራ ሆነው ኡማውን ለመኻደም እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ከነበሩት ውሰወጥ ዋነኛ የነበሩት ሀጅ መሀመድ ሳኒ ህልፈት ተከሰተ። መሀከል ላይ የነበረው ክፍል ላይ የሳቸው መሞት ከፍተኛ ክፍተት ፈጠረ።
ሼኽ አብድልራህማን ላይ የነበረው ጫናም ይበልጥ በረታ።
በወቅቱ የነበረው ልዮነት የጀመአ እና የብሄር ነበር ። ሰሜኑ አካባቢ የነበሩ ኡለሞችም ሆኑ ከሼኽ አብድልራህማን ጋር በብሄር ይገናኙ የነበሩት የሀደሬ ማህበረሰብ ዘርን መሰረት አድርገው ያነሷቸው የነበሩ ትችቶች እና በኡለሞች መካከል የፈጠረው ክፍተት ጥሩ አልነበረም።
በተለይ ሀጅ መሀመድ ሳኒ እና ሼኽ አብድልራህማን መስፈርታቸው ከብሄርም ከቡድንም ወጥቶ እውቀት እና ታማኝነትን ብቻ ያደረገ መሆኑ በሌሎች አወንዲወገዙ አድርገዋል።
ሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀጅ ዙመካንን እና ሀጅ ሙስጠፋን ምናልባት በብሄር ከሚቀርቧቸው በላይ ማቅረባቸው እና ቦታ መስጠታቸው በግልፅ ትችት እንዲቀርብባቸው አድረጓቸዋል። በወዙ ሰዎችም ሀጅ መሀመድ ሳኒ ለዚህ ትችት ይሰጡት የነበረ ታላቅነታቸውን የሚያስመሰክሩ ምላሾቻቸውን ይናገራሉ።
ይህ ሁሉ ትችት ባለበት ከሀጅ መሀመድ ሳኒ ህልፈት በሗላ ሼኽ አብድልራህማን ሸሪፍ ሀጅ ሙስጠፋን የሀጅ ዙ መካና ምክትል እንዲሆኑ ማድረጉ ከትችቶቹ በላይ ሆኖ መርህን ለማክበር እና ኢስላማዊ ሚዛኑን ለማስጠበቅ ያደረገውን የሚያሳይ ቢሆንም ትችቱን እና ውጥረቱን ግን አብዝቶበት ነበር።
በጊዜው መንግስት መሀከል ላይ ያሉትንም ሆነ ሙነዘማ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ሰዎችን መምታት እንዳለበት በመወሰኑ ወሀቢያ እያለ የሚያወግዘውን ወገን በማቅረብ እና የሁለቱን ልዮነት በሁለቱም ወገን ያሉ አካላት እንዲያጦዙት በማድረግ ግጭት እንዲከሰተ አደረገ።
በዚህም ሁለቱን በማስማማትም ሆነ ለኡማው ትልቅ ቁም ነገር ሊሰራ ይችል የነበረው መሀከል ላይ የነበረው የኡለማእ ክፍልም ሆነ አብዛኛውን ወጣት ማቀፍ ችሎ ትልቅ ተስፋ የነበረውን ስብስብ በተኖ ሙስሊሙን ወደተነሳበት ደረጃ መለሰው።
ከግጭቱ በፊት ጫና ይፈጥር የነበረው የሱፊ ቡድን የወጣቱ እንቅስቃሴ ከዲን የወጣ እና የተሳሳተ እንደሆነ እንዲፈረጅ ግፊት ሲያደርግ የተወሰኑ ኡለሞች ተመርጠው የወጣቶችን ዳእዋ ቁጭ ብለው በማዳመጥ ስህተት ካለ ወይም ከዲን መስመር የወጣ ከሆነ እንዲያሳውቁ ተደረገ።
ሀጅ ዙመካእና ሌሎችም ነበሩ። የሚያስተምሩት ቁርኣንና ሀዲስ መሆኑን እና ከዲን የወጣ እንዳልሆነ በመናገራቸው በመስጂድ ውስጥ ዳእዋ እንዳያደርጉ ለማድረግ የተሞከረው ሳይሳካ ቀረ።
ከግጭቱ በሗላ ግን
መጅሊስ ውስጥ መሀከል ላይ የነበረውንም ሆነ ወሀቢያን ማጥፋት የሚፈልጉ ሰዎች የተሻለ አቅም እያገኙ መጡ። የሀጅ መሀመድ ሳኒን መሀከል ላይ ሆኖ ኡማውን አንድ የማድረግ ሌጋሲን ለማስቀጥል ፍላጎት የነበረው ቡድን ይገለል እና ጫና ይደረግበት ጀመረ።
ቀጥሎም ከመጅሊስ ውጭ ይቀነቀን የነበረው ወሀቢን የመፈረጅ እና ሱፊያን የማንገስ እንቅስቃሴ በዋናው ተቋም ይቀነቀን ጀመር።
ከመንግስት ጭምር በቀጥታ በሚሰጥ ትእዛዝ እና አቅጣጫ እንዲሁም እገዛ መሰረት መጅሊስ ጠርዝ ነክቶ በየ ኡለማው ቤት ፍተሻ ተካሂዶ እነሱ ስህተት ናቸው የወሃቢያ ናቸው የሚሉትን ኪታብ የማቃጠል እንቅስቃሴ እንደሚጀምሩ ኡለሞችን ሰብስበው ነገሯቸው።
በዚህ ወቅት ኡለሞች ላይ ተፈጥሮ የነበረው ሀዘን መሪር ነበር።
ሀጅ ሙስጠፋ ይህ ወሳኔ በሰሙበት ቀን በድንጋጤ ታመዉ ቤት መጥተውም ኪታብ የሚቃጠልበት ዘመን ላይ ደረስን በማለት ኪታባቸው እንዲሸፈንላቸው ጠየቁ ። ከዛን ቀን ጀምሮም ለተወሰኑ ወራት ከታመሙ በሗላም በዛው ህመም ህይወታቸው አለፈ። ረሂመሁላህ።
ከህልፈታቸውም በሗላ በጊዜው መጅሊስ ላይ የነበሩ አመራሮች ወሃቢያን አላወገዙም እና ሞታቸው በዜና መተላለፍ የለበትም ብለው ከለከሉ።
የወጣቱ እንቅስቃሴ ብሰለት የጎደለው፣ችኩል እና ቡድናዊነት ስሜትን ያራግብ የነበረ መሆኑ እንዳለ ሆኖ
የወሃቢያ ጥላቻ የነበረው ቡድንም ሌላ ጠርዝ እየነካ እና ሙስሊሙን የመክፈል ስራን ክፍተቱን እያባባሰ መጣ።
ያም ሆኖ በተለይም ከግጭቱ በሗላ ባሉ መጀመርያ አመታት በዋናነት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሆነው ይሾሙ የነበሩት በኡማው ዘ ንድ የተከበሩ እና ሚዛናዊ የነበሩ ናቸው።
መንግስት መጅሊስ ላይ ጫና የመፍጠር አቅሙ እየጨመረ በመምጣቱ እና ለኡማው ከልባቸው የሚቆረቆሩ ሰዎች በተመናመኑ ቁጥር መጅሊስ ከሱፍያውም ጭምር ተቀምቶ ለዲን ምንም አይነት ደንታ በሌላቸው ሰዎች እጅ ወደቀ። መጅሊስንም መንግስት ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረው።
የመጨረሻ ደረጃ የነበረው መንግስት መጅሊስ ውስጥ ደፍሮ እንዳይገባ ይጠብቁ የነበሩ ኡለሞች በሞትም በመገለልም ከተመናመኑ በሗላ ቀስ በቀስ አፍርሶ የጨረሰውን እና ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረውን መጅሊስ ለተደራጀ ቡድን አስረክቦ እና ሙሉ ድጋፍ ሰጥቶ ሙስሊሙን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ መምታት ነበር።
ይህንን የመረጠበት ምክንያት 3 ናቸው አንደኛ ከመጅሊስ አስወጥቶ እና ድርጅቱን መቶ አዳፍንኩት ያለው እንቅስቃሴ ድምፅ ሳያሰማ ሀገሪቷን ማዳረሱን መረዳቱ ሲሆን
ሁለተኛው መጅሊስ ያሉ ሰዎች ሆድ እንጂ ህሊናም ሆነ የቆሙለት ርእዮተ አለም.ስሌላቸው የመንግስትን እቅድ መንግስት በሚመኘው ልክ ማስፈጸም እና የሙስሊሙን እንቅስቃሴ መግታት አለመቻላቸው ነው።
ሶስተኛው ምክንያት መጅሊስን ብቻ መቆጣጠር መንግስት የሚፈልገውን ማሳካትም ሆነ እንቅስቃሴውን መግታት የማያስችል መሆኑን መረዳቱ ነው።
ሙስሊሙ መጅሊስን እርግፍ አድርጎ ትቶ መስጂድ ላይ እና ማህበር አቋቁሞ መንቀሳቀስ ላይ እንዲሁም በግል የሚያደርገው ጥረት ላይ በማተኮሩ ተቋሙን መቶ እንቅስቃሴውን መግታት አልተቻለም።
ስለዚህ በተመሳሳይ የተደራጀ እና አይዲዮሎጂ ይዞ የሚንቀሳቀስ ቡድን በማምጣት እና በማገዝ እንቅስቃሴዎችን መምታት የስከዛሬውን ክፍተት የሚያርም ስኬታማ ስትራቴጂ እንደሆነ ታመነ።
[27/05, 08:36] U Ahmad 1: በድምፃችን ይሰማ መሪ ቃልነት የተካሄደው ትግል መንግስት ከህዝበ ሙስሊሙ ቀምቶ ሙስሊሙን ለማጥቃት ፍቃደኛ ለሆኑ ሰዎች ያስረከበውን መጅሊስን በሀጅ መሀመድ ሳኒ ጊዜ ወደ ነበረበት ቁመና የማስመለስ ትግል ነው።
ኡለማኦቻችን መስርተውት በተቋሙ በኩ