🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»🎀


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


🎀ውስጧ በዐቂዳ፣ በሱና የጠራ🎀
በሀያእ በእውቀት፣ልቧ የጎመራ
በሠለፎች መንገድ፣ እምነቷን ተያዘች
አማኟ እህቴ እሷማ ውድ ነች!!!!!!
↪️ለማንኛውም ጥቆማ እና አስተያየት
👉@Kidmyaletewhid_t👌 ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


◼️ከሶላት በኋላ የሚባለው ተክቢራ፦
🔹ከሱና ሶላት በኋላ ማለት ይቻላል⁉️
🔹ሴቷ እቤቷ ሰግዳ ማለት ትችላለች⁉️
🔹ከዚክር በፊት ወይስ ኋላ ሚባለው⁉️
🔹ወንድ ልጅ ብቻው ቢሰግድ ይላል⁉️
🔹የተወሰነ የቁጥር ገደብ አለውን⁉️


↪️ወሳኝ ጥያቄዎች ተዳሰውበታል

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ


الإكثار في يوم عرفة من: (لا إله إلا ﷲ وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير)

الشيخ ‎عبدالرزاق البدر حفظه الله
https://t.me/https_Asselfya


انتبهوا إلى أمر غاية في الأهمية في الدعاء ..

الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله


በዐረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
« خير الدعاء دعاء يوم عرفة , وخير ما قلت أنا والنبيون من قبلي : لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ. »

‘ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋህ ዕለት የሚደረግ ዱዓ ነው፡፡ እኔና ከኔ በፊት የሚደረግ ዱዓ ነው፡፡ እኔና ከኔ በፊት የነበሩ ነብያት ከተናገሯቸው ሁሉ በላጩ ፡-
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ የርሱ ነው፡፡ ’


💥አዲስ ሙሐደራ💥
〰〰〰〰〰〰〰

↪️ሙሐደራው የያዛቸው ነጥቦች

🔹የዐረፍን ቀን መፆም ያለው ጥቅም...
🔹የዒድ አዳቦች
🔹ከዒድጋ ለተያዙ ጥያቄዎች መልስ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

https://t.me/https_Asselfya


📌♻️ አቅሙ የቻለና ኡዝር የሌለው ነገ ቢፃም ኸይር ነው። ምክንያቱም ያለፈውንና የሚመጣውን የሁለት አመት ወንጀል የመማሪያ ሰበብ ነውና። ነገር ግን መፃም ያሰባችሁ ወንድም እህቶች ግን
🔺 በቀልባችሁ እንደምትፃሙ ማሰብና
🔺 ሌሊት ተነስታችሁ ስሁር መብላትን እንዳትረሱ ብዙ ሰው ግን በነዚህ ነገር ላይ ይዘናጋል።

 📌قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : تَسَحَّرُوا فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً  رواه البخاري (1923) ، ومسلم (1095)

📌قال النبي صلى الله عليه وسلم :  فصل ما بين صيامنا وصيام أهل اكتاب أكلة السحور

https://t.me/https_Asselfya


የአረፋ ቀን ትሩፋቶች
〰〰〰〰〰〰〰〰

◾️የአረፋ ቀን መለያዎች
◾️የአረፋ ቀን ያለው ብልጫ
◾️ቀኑን መፃም ያለው አጅር


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw


ሴት ልጅ ወደ ሐጅ ስትሄድ መንገድ ላይ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ቢያጋጥማት መንገዷን ትቀጥላለችን?
||
||
➫ይህ በኢህራም ወቅት ከሆነ ያጋጠማት ልክ እንደ ሌላዋ ጦሀራ ሴት ኢህራም ታደርጋለች ምክንያቱም የኢህራም መጀመር ጦሀራ መስፈርት አይደረግለትም! ሙግኒ ጥራዝ 3 ገፅ 293_294 ላይ እንድህ ይላል፦ የዚህ መታጠብ ተገቢ ነው ምክንያቱም የሐጂ ስርዓት ስለሆነ የወር አበባና የወሊድ ደም ባለቤት ሴት ላይ የጠነከረ ነው ይህን አስመልክቶ የሚከተለው ሀድስ መጥቷል!
ጃቢር ረድየላሁ አንሁ እንድህ ይላሉ፦
"ዙል ሑለይፋ ስንደርስ አስማዕ ቢንት ኡመይስ ሙሐመድ ኢብኑ አቡበክርን ወለደች ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለባት ወደ አሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ ላከች!
ነአሏህ መልዕክተኛም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንድህ አሏት፦"ታጠቢና በጨርቅ አስረሽ ኢህራም አድርጊ።"(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
||
||
➫ከኢብኑ አባስ ረድየላሁ አንሁማ በተዘገቡት ሀድስ ነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ፦

➫የወር አበባ ያለች ሴት እና የወሊድ ደም ያለባቸው ሴቶች ወደ ኢሕራም ቦታ በመጡ ጊዜ ይታጠቡና ኢሕራም ያደርጋሉ ከዚያም በካዕባ ዙሪያ መዞር ሲቀር ሁሉንም የሐጅ ተግባራት ይፈፅማሉ!! (አቡ ዳውድ ዘግቦታል)

➫ዓኢሻ ረድየላሁ አንሀ የወር አበባ ላይ ስለነበረች ነብያችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ለሐጅ ኢሕራም ለማድረግ እንድትታጠብ አዘዋታል!

➫የወር አበባ እና የወሊድ ደም ያለባቸው ሴቶች በዚህ ሁኔታ እያሉ መታጠባቸው ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ነው እንደዚሁም በሰወች ጋር ሲቀላቀሉ መጥፎ ጠረን እንዳይኖርና ነጃሳውን ለማስወገድ ነው!!
➫የወር አበባ የወሊድ ደም ሐጅ ከሀረሙ በኋላ ከሆነ የመጣው በኢሕራማቸው ላይ ምንም አይነት ችግር አያመጣም! #ሙሕሪም ሆነው በመቆየት ሐጅ ላይ የተከለከሉ መገሮችን ከመፈፀም ይቆጠባሉ ከወር አበባና ከወሊድ ደም ፀድተው እስኪታጠቡ ድረስ #በካዕባ_መዞር_አይችሉም!!
➫ከወር አበባ ወይም ከወሊድ ደም ሳይፀዱ የአረፋ ቀን ከደረሰ እና ኢሕራም ያደረጉት በሐጅ ከዚያም በኡምራ(ተመቱዕ) ከሆነ እሱን ትተው ሐጅ እና ኡምራን አንድ ላይ አድርገው (ቂራን) ያደርጉታል!!
#ለዚህም_ማስረጃ፦ በርካታ ሀድሶች ሲኖሩ ከነዛም መካከል ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሀድስ ነው!

➫ዓኢሻ ረድየላሁ አንሀ በዑምራ ኢሕራም አድርጋ የወር አበባ መጣባት እያለቀሰች እያለ ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ገቡ "ምንድነው የሚያስለቅስሽ? የወር አበባ ያየሽ ይመስላል" ሲሏት እርሷም "አዎ" አለቻቸው!

እሳቸውም "ይህ እኮ አሏህ የአደም ሴት ልጆችን የፈጠረበት የሆነ ነገር ነው በካዕባ መዞር ሲቀር ሓጃጆች የሚሰሩትን ሁሉ ስሪ" አሏት። (ቡኻሪና ሙስሊሞ ዘግበውታል)

#በዚሁ_ርዕስ_ይቀጥላል_ኢንሻ_አሏህ!
https://t.me/https_Asselfya


Репост из: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
የኡዱሕያ ህግጋቶች.pdf
2.3Мб
ተለቀቀ

አዲስ መፅሐፍ

"የኡዱሕያ ህግጋቶች"

በሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል‐ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ወደ አማረኛ የተመለሰ

በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq


👉 የዙል ሒጃ ዘጠነኛ ቀን ፆም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
የዙል ሒጃ ዘጠነኛ ቀን ፆምን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መለሱ : –
عنْ أَبي قتَادةَ – رضي الله عنه – ، قال َ: سئِل رسولُ اللَّهِ ﷺ : عَنْ صَوْمِ يوْمِ عَرَفَة َ؟ قَال َ: " يكفِّرُ السَّنَةَ المَاضِيةَ وَالبَاقِيَة "
َ رواه مسلمٌ
" ያለፈውን አመትና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል "
🔹 በአቡ ቀታዳ ተወርቶ ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል ።
አብዛኛዎች የረመዷን ቀዳእ እያለ ሱና ፆም መፆም አይቻልም የሚሉ ሊቃውንቶች የዙል ሒጃን ዘጠነኛ ቀን ይፈቅዳሉ ከፊሎቹ ዘጠኙንም ቀን ይፈቅዳሉ በመሆኑም ቀዷእ ያለባቸው እህቶችም ይህን ቀን መፆም ይችላሉ ። ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከሌለ በስተቀር የዚህን አይነት ምንዳ ማስመለጥ አይገባም ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን ።
https://t.me/https_Asselfya


💦 የማይመለከትሽን ተይ ‼️
〰〰〰〰〰〰〰〰

عن أبي هريرة – رضي الله عنه – قال፡- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم፡- "من حسن إسلام المرء تركه ما لا يعنيه"
رواه الترمذي بسند حسن

አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ ቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

"↪️የአንድ ሰው እስልምናው ከማማሩ ነው። የማይመለከተውን ነገር መተው‼️


::::::ቆንጆ ሴት ማለት :::::::::
〰〰〰〰〰〰〰
በዲኗ ጠንካራ የሆነች ፣በዲኗ ላይ የማትደራደር፣ ሁል ጊዜ #የአላህን እና #የመልእክተኛዉን ትእዛዝ ለማክበር የምትቻኮል፣

#አላህ ጋር በሚያቃርባት ነገር ሰው ምን ይለኛል ብላ የማትጨነቅ ‼️

💦በዲኗ በጥንካሬዋ በሲድቅነቷ፣ በአለባበሷ ከኡመተል ሙእሚኒን ጋር የምትመሳሰል፣ የምዕራባወያን ስልጣኔ የማያስደንቃት፣ በሱና የተዋበችዋ ፣ከቀልዷ ቁም ነገሯ የበዛ፣

ዲኗን ለመገንዘብ እፍረት ኩራት የማይዛት #የአላህ ባሪያ የሆነች !!#አዎ ይህች #እንስት ለኔ በቃል የማልገልፃት #ቆንጆ ነች ። ‼️

https://t.me/https_Asselfya




♻️ክፍል0⃣1⃣

በትምህርቱ የተዳሰሱ ነጥቦች

🖲ስለሼኽ አብዱሰላም በርጀስ ሼኽ ፈውዛ
የተናገሩት(ተቅዲም)


🖲የሰለፎችን መንገድ መከተል
ግዴታ ስለመሆኑ።


🖲አህሉሱና ወልጀማዓ እንደሌሎቹ
አንጃዎች የተበታተኑ አለመሆናቸው።

🖲 አህሉሱና ኢስላም፣ሱና ወይም ወደነዚህ ያመላከቱ ስያሜዎች እንጂ ሌላ
ስያሜ የሌላቸው ናቸው።


https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya




🎤 ቀኖቹ እየሄዱ ነው።
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➧ እነዚህ አላህ የማለባቸው በእነዚያ በታወቁ ቀናቶች ጌታችሁን አስታውሱ ብሉ የነብዩን ኡማ ያመላከተባቸው ልዩ ቀናቶች እያለቁ ናቸው።።

ምን ሰርተናል ባለፉት ቀናቶች ሁሉም የዒባዳ አይነቶች ከፊት ሆነው እኔስ እያሉ እንድንሽቀዳደም በሚገፋፉበት ጥቂት ቀናት ምን ሰራን ምንስ ወደ ኋላ አደረግን ለነገው ቤታችን ወይስ የበይ ተመልካች ልንሆን ነው?

እነዚህ ሰለፎች ያለ ሀይላቸውን ተጠቅመው ለአኼራ ስንቅ ሲያዘጋጁባቸው የነበሩት ቀናቶች በምን መልኩ እያለፉ ነው? በቀሩት ቀናት በመንችለው የመልካም ስራ አይነት እንትጋ አንዘናጋ ስንቅ ያስፈልገናል መንገደኞች ነን የሚቀበለን ዘመድ አዝማድ ሳይሆን መልካም ስራችን ነው።

በመሆኑም እንዳንቦዝን እንዳንተክዝ የሚያደርገን መልካም ስራ አብሽር የሚለን ከቀብር ጀምሮ አላህ ፊት እስክንቆም ሲራጥን ለመሻገር ሚዛናችን ከፍ እንዲል የስራ መዝገባችን በቀኝ እጃችን እንዲሰጠን የቀኝ ጓዶች እንድንባል ፈሪቁል ፊል ጀናህ ከሚባሉት ለመሆን ስንቅ ያስፈልገናል። ቀሪ ሒሳባችን አያስተማምንም እንትጋ አንዘናጋ ለዚህ ትልቁ አጋጣሚ እነዚህን የቀሩት ቀናቶች መጠቀምን አማራጭ የሌለው ተግባራችን እናድርግ አላህ ለመልካሙ ሁሉ ይወፍቀን።

http://t.me/bahruteka


📚የቁርአን ተፍሲር
➖➖➖➖➖➖
{{በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ }}

☄ሱረቱ’ናስ እና ሱረቱል ፈለቅ☄


🪧 ክፍል ሁለት 🪧
https://t.me/https_Asselfya


📚የፊቂህ ትምህርት
〰〰〰〰〰〰
🎙 በኡስታዝ ሲራጅ ንጋቱ

📔መትን አቢ ሹጃዕ

📪ክፍል አንድ

https://t.me/https_Asselfya


➷💎ኡኽታዬ ኒቃቢስት ሆነሽ ግና ከእነኚህ ነገራቶች ራስሽን ካላፀዳሽ ይህ የኒቃብ ውበትሽን ያደበዝዝብሻልና ተጠንቀቂያቸው አደራ

↪️ 1/ ወሬ ማብዛት ማይጠቅም ተራ ዝባዝንኬን ነገር......!

✅ እርግፍ አድርገሽ ተይው በቃ መናገር ባለብሽ ጊዜ ተናገሪ ዝም ማለት ባለብሽ ጊዜ ደግሞ ዝም በይ! ለሁሉም ነገር ሚዛናዊ መጠነኛ_መካከለኛ ሁኚ!
"ዝምታን"አብዢ ይህ አንዱ የመዋቢያሽ ዋናው ኮስሞቲክስሽ ነው! ዝምተኛ እንስት ሁኚ ያኔ ሰላም ታገኚያለሽ ተወዳጅም ትሆኚያለሽ

💎 የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦

♻️ ለዱንያውም ሆነ ለአኺራው የማይጠቅመውንና የማይመለከተውን ነገር መተው ለአንድ ሰው የመልካም ሙስሊምነቱ አንድ መገለጫ ነው።”ነብዩ ሙሃመድ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)

[ትርሚዚና ሌሎችም የዘገቡት ሃዲስ ነው!!

↪️ 2/ ሚስጥርሽን/የህይወት ታሪክሽን/እንዲሁም የወደፊት እቅድሽን ላገኘሻት ለተዋወቅሻት ሁሉ ማውራት መዘክዘክ.......!

♻️ ልብ በይ እህቴ፦ ይህ የአንቺን ምንነት በቀላሉ ያስገምታል _ማለትም ደግሞ ወሬኛ ናት_ሚስጥር መጠበቅ አትችልም_ዝርክርክ ናት..... ብዙ ነገር ናት ያስብልሻል በራስሽ ጊዜ ክብርሽን ታጫለሽ_ሁሉም ይርቅሻል ለምን? ምክኒያቱም አንችነትሽን አንብበው ተረድተው ጨርሰዋላ¡ አየሽ አይደል_ስለዚህ ከዚህ በኋላ ቁጥብዬ እንስት ለመሆን ሞክሪ ያለፈን መመለስ ስለማይቻል የልብ ጎደኛሽንም ጠንቅቀሽ እወቂ ጠይብ።

↪️ 3/ ለራስሽ ከኢልም ቦታ ርቀሽ በማታውቂው መስኣላ ውስጥ ገብተሽ መከራከር / መዘባረቅ.....!

♻️ ይህም እንደዚሁ አደጋ ላይ ይጥልሻል ስለዚህ በመጀመሪያ ለመማር ሞክሪ ሁሉንም ትደርሽበታለሽ "እውቀት ከንግግርም ከተግባርም በፊት ይቀድማልና" በማታውቂው ነገር አትናገሪ!!

💎 ምክኒያቱም ያለእውቀት መናገር መዘዙ የከፋ ነው ሳታውቂ ምንአልባትም በረሱል ላይ ውሸት ልትቀጥፊ ያላሉትን ብለዋል ልትይ ትችያለሽ! ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦

✅ አሊይ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዳወሱት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡- ‹‹በኔ ላይ ውሸት አትናገሩ፣ በኔ ላይ (ሆን ብሎ) ውሸት የተናገረ መቀመጫው ገሃነም መሆኑን (ይገንዘብ)፡፡››

(ቡኻሪ ዘግበውታል)

↪️ 4/ በጣም ኮስታራ መሆን / ከልክ ያለፈ ንፉግ /ስስታም መሆን፦
ይሄም ያስጠላብሻል እህቴ ኮስታራ ስስታም አትሁኚ ፈገግታ አብዢ ያለሽንም ሳትሰሰቺ ሊወጂሂላህ ስጭ "ስጥ ይሰጥሃል"አይደል ሚባለው!!

↪️ 5/ከልክ ያለፈ ቀልድ ማብዛት_ሳቅ ማብዛት

✅ ልብሽን ያደርቀዋል ተጠንቀቂ እህቴ ሞት አለብሽ_ቀብር.....ኧረ ብዙ ጣጣ ያለብን ደካማ ሰዎች ነን ለዚህም ነው ረሱል እኔ ማውቀውን ነገር ብታውቁ ኖሮ ቲንሽ ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር ያሉን!!
እናም ለሁሉም (ወሰጥ) መካከለኛ ሁኚ

↪️ 6/ ከአጅነቢ ወንድ ጋር ያለምንም ሀጃ መፃፃፍ!! ወይንም መጀናጀን!!
እህቴ ከዚህ ድርጊትሽ ተቆጠቢ ይብቃሽ አሏህ የፃፈልሽ ላይቀር ልብሽን በከንቱ አታድርቂው የዝሙት መዘዞችን መቼም ታውቂያቸዋለሽ አይደል? እሺ ደግሞም አትዘንጊ የዝሙት በሮች ብዙ መሆናቸውን....የእጅ ዝሙት አለ.....የአይን ዝሙት አለ....የምላስ ዝሙት አለ......!በቃሽ አሏህ የታመፀበት ነገር ወረቢል ካዕባ ፍፃሜው አያምርም ከወደደሽ ቶሎ ሀላሉ ያድርግሽ አስለን ከኒካህ በፊት _ማሬ_ስኳሬ_ ወተቴ .......ኩላሊቴ........ምኔ...ቅብርጥሴ እያለ እያለ እንዲሟዘዝ ማን ፈቀደለት ???? ውዱ እስልምናችን ይሄን ያወግዘዋልና ራቂ ከእንዲህ አይነት አጠሊታ ነገር ስለዚህ ያለፈውን በተውበት ከዚህ በኋላ ደግሞ አሏህን በመፍራት ተቆጠቢ ያለልሽን አታጪም የምትመኚውን አይነት ወንድ ከፈለግሽ በዱዓ እንጂ በchat አታገኚውም ስለዚህ የማንም ወጠጤ መደበሪያ አትሁኚ!!
አሏህንም ፍሪ!!
وقال تعالى

(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]!!

↪️ 7/ እህትሽ ሚያስደስታት ነገር ስታገኝ መመቅኘት? ለምን?

✅ እህትሽን ከምትመቀኚያት ዱዓ አድርጊላት ባስደስታት ነገር አሏህ በረካ እንዲያደርግላት ያኔ አሏህም ላንቺም ባላሰብሽው መንገድ የተመኘሺውን ነገር ሰጦ ያስደስትሻል የእርሱ ካዝና አያልቅምና

↪️ 8/ አሏህ ሲፈትንሽ ሶብር ማጣት_ማላዘን_......!!!
እህቴ ሆይ ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ምን እንዳሉ ላስታውስሽ እስኪ ፦
✅ “…ሙዕሚን(አማኝ ሰው) ነገሩ ሁሉ አስደናቂ ነው። ነገሩ ሁሉ መልካም ነው። ይህ ደግሞ ማንም ሊያገኘው የማይችል እና ለሙዕሚን ብቻ የተወሰነ ነው። ጥሩ ከገጠመው ያመሰግንና አጅር ያገኛል። መጥፎ ከገጠመው ደግሞ፣ ይታገስና የታጋሾችን አጅር ያገኛል።”

(ሙስሊም)

አጂብ ምን ያማረ አነጋገር ነው🌹ስለዚህ አለይኪ ቢሶብር እህቴ

↪️ 9/ከአጅነቢ ወንድ ጋር መቅለብለብ ቅብጥብጥ ማለት ማስካካት
እርእ...................!

ሀያዕ መወገድ!!
እህቴ ይህ የአማኝ ሴት መገለጫ አይደለም በተለይም ደግሞ ሰለፍይ ነኝ ከምትል ሴት ታቀቢ! ለወንድ ልጅ ሲጀመር ኮስታራ ሁኚ! ፊት አትስጪ! እሱን ከሚፈታትን ነገር ተቆጠቢ ሀያዕ ይኑርሽ ! ተቆጠቢ ስለሃያዕ መቼም ብዙ ተብሏል፦
ከነኚህም አንዱ፦

💎 አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ኢማን ከስልሳ በላይ ንዑስ ክፍሎች
አሉት፡፡ ‹‹ሐያእ›› አንዱ የ‹‹ኢማን›› ንዑስ ክፍል ነው፡፡››

(ቡኻሪ ዘግበውታል)

✅ ወሏሁ ዓዕለም🖋

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➷💎"ሀያዕ ከ ኢማን ነዉ
ይህ ምክሬ ላንቺ ለኔም ነው!"
ውዷ እህቴ ሆይ ተሸፈኚ

በሀያዕሽም ንግስት ሁኚ
🌸➖➖➖➖➖➖🌸
【ምክር ለሙስሊሟ እህቴ➧

https://t.me/menhajselefiya123


📓 የቃዒደቱል አንኑራንያ ደርስ ፨
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

🔆 الدرس الحادي عشر : تدريبات علی السكون

⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️⤴️

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/abuUseyminabdurehman/1325

Показано 20 последних публикаций.

649

подписчиков
Статистика канала