ሴት ልጅ ወደ ሐጅ ስትሄድ መንገድ ላይ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ቢያጋጥማት መንገዷን ትቀጥላለችን?
||
||
➫ይህ በኢህራም ወቅት ከሆነ ያጋጠማት ልክ እንደ ሌላዋ ጦሀራ ሴት ኢህራም ታደርጋለች ምክንያቱም የኢህራም መጀመር ጦሀራ መስፈርት አይደረግለትም! ሙግኒ ጥራዝ 3 ገፅ 293_294 ላይ እንድህ ይላል፦ የዚህ መታጠብ ተገቢ ነው ምክንያቱም የሐጂ ስርዓት ስለሆነ የወር አበባና የወሊድ ደም ባለቤት ሴት ላይ የጠነከረ ነው ይህን አስመልክቶ የሚከተለው ሀድስ መጥቷል!
ጃቢር ረድየላሁ አንሁ እንድህ ይላሉ፦
"ዙል ሑለይፋ ስንደርስ አስማዕ ቢንት ኡመይስ ሙሐመድ ኢብኑ አቡበክርን ወለደች ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለባት ወደ አሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ ላከች!
ነአሏህ መልዕክተኛም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንድህ አሏት፦"ታጠቢና በጨርቅ አስረሽ ኢህራም አድርጊ።"(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
||
||
➫ከኢብኑ አባስ ረድየላሁ አንሁማ በተዘገቡት ሀድስ ነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ፦
➫የወር አበባ ያለች ሴት እና የወሊድ ደም ያለባቸው ሴቶች ወደ ኢሕራም ቦታ በመጡ ጊዜ ይታጠቡና ኢሕራም ያደርጋሉ ከዚያም በካዕባ ዙሪያ መዞር ሲቀር ሁሉንም የሐጅ ተግባራት ይፈፅማሉ!! (አቡ ዳውድ ዘግቦታል)
➫ዓኢሻ ረድየላሁ አንሀ የወር አበባ ላይ ስለነበረች ነብያችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ለሐጅ ኢሕራም ለማድረግ እንድትታጠብ አዘዋታል!
➫የወር አበባ እና የወሊድ ደም ያለባቸው ሴቶች በዚህ ሁኔታ እያሉ መታጠባቸው ንፅህናቸውን ለመጠበቅ ነው እንደዚሁም በሰወች ጋር ሲቀላቀሉ መጥፎ ጠረን እንዳይኖርና ነጃሳውን ለማስወገድ ነው!!
➫የወር አበባ የወሊድ ደም ሐጅ ከሀረሙ በኋላ ከሆነ የመጣው በኢሕራማቸው ላይ ምንም አይነት ችግር አያመጣም! #ሙሕሪም ሆነው በመቆየት ሐጅ ላይ የተከለከሉ መገሮችን ከመፈፀም ይቆጠባሉ ከወር አበባና ከወሊድ ደም ፀድተው እስኪታጠቡ ድረስ #በካዕባ_መዞር_አይችሉም!!
➫ከወር አበባ ወይም ከወሊድ ደም ሳይፀዱ የአረፋ ቀን ከደረሰ እና ኢሕራም ያደረጉት በሐጅ ከዚያም በኡምራ(ተመቱዕ) ከሆነ እሱን ትተው ሐጅ እና ኡምራን አንድ ላይ አድርገው (ቂራን) ያደርጉታል!!
#ለዚህም_ማስረጃ፦ በርካታ ሀድሶች ሲኖሩ ከነዛም መካከል ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሀድስ ነው!
➫ዓኢሻ ረድየላሁ አንሀ በዑምራ ኢሕራም አድርጋ የወር አበባ መጣባት እያለቀሰች እያለ ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ገቡ "ምንድነው የሚያስለቅስሽ? የወር አበባ ያየሽ ይመስላል" ሲሏት እርሷም "አዎ" አለቻቸው!
እሳቸውም "ይህ እኮ አሏህ የአደም ሴት ልጆችን የፈጠረበት የሆነ ነገር ነው በካዕባ መዞር ሲቀር ሓጃጆች የሚሰሩትን ሁሉ ስሪ" አሏት። (ቡኻሪና ሙስሊሞ ዘግበውታል)
#በዚሁ_ርዕስ_ይቀጥላል_ኢንሻ_አሏህ!
https://t.me/https_Asselfya