✍ኢብኑ ጀሚል 🌙Ibnu jemil channel (أبو الدرداء)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ሀቅ ከማንም ከመጣልህ ተቀበል!!
💫በምትዘው አቃም ላይ መረጃ ይኑርህ!!
💫ሰውን ተከትለህ መረጃ ሳይኖርህ አቃም አትመሰርት!!
💫ወደ ሀቅ ጎዳና ከመጣክ አትወዛወዝ
👇ይህ የአቡደርዳእ /ኢብኑ ጀሚል የተሌግራም ቻናል ነው።በአላህ እገዛ የተለያዩ ት/ቶች ይለቀቁበታል።
ጥቆማ
@Ibnujemil13
"""""""""""""""""""""
https://t.me/ibnujemilchannel

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🌹ካንተ ምንም መልካም ሳይፈልግ በችግርህና በደስታክ ግዜ የወደደክ፣ ላንተ በውስጡ መጥፎ ሳይሸርብ በቁጣህና በደስታክም ግዜ የታገሰክ የሆነ አካል ጓደኛ ማለት ይህ ነው።

📚ኢብኑ ሀዝም አል ኡንዱሊሲይ


👌ትክከለኛ ጓደኛ ይታገሰሃል!!

من أحبَّك في عسرِك ويُسرك دون أن ينتَظر
منك معروفًا، واحتمَلك في غضبِك وسرُورك،
دُون أن يُضمِر لك سوءا، فذلِك هو الصَّديق.
- ابن حزم الأندلسي.

🏝https://t.me/ibnujemilchannel


🌹የምሽት ግብዣዬ!

ሱረቱ መርየም

🎙ቃሪእ ሉዕዩን አልኩሺይ

በወርሽ ነው ቂራኣው ።ተሳስቷል ትላለህ አታፍርም!

https://t.me/ibnujemilchannel


Репост из: قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
قال الإمام الشافعي رحمه اللّٰه:

"أرفع الناس قدراً من لا يرىٰ قدره، وأڪثرهم فضلا، من لا يرىٰ فضله".

*📚 سير أعلام النبلاء (١٠/٩٩)*


የሙነወር ልጅ ማምታቻ እስከ የት?!
—————
የሙነወር ልጅና የቡድኑ ዋና ዋና አባላት ከነበሩበት ጠንካራ የሱንና አቋምና በቢድዐህ ባለ ቤቶች የሰልላ ሰይፍ ሆነው ከማስጠንቀቅ ፈፅሞ ባልተጠበቀ መንገድ ቁልቁል ሲወርዱ (የተምይዕ ዋሻ ሲሆኑ) ከታላላቅ የሱንና መሻይኾችና ኡስታዞች ለሚደርስባቸው በማስረጃ የታገዘ ጠንካራ ምላሽ ተደናግረው ከትክክለኛ ማስረጃ የተራቆቱ በመሆናቸው መቋቋም ሲያቅታቸው ቲፎዞዎች እንዳይበተኑባቸው፣ የትቢትና በባጢል ላይ የጭፍን እልህ (ደራ) ባለ ቤት የሆነው የሙነወር ልጅ የሚደርስባቸውን ጠንካራ ምላሽ ይመክትልኛል ብሎ የያዘው መንገድ (ስልት) "በማስረጃ ማሳመን ካልቻልክ አደናግር" የሚለውን አባባል ነው።
ይህ የትም አያደርሳቹም!! ቲፎዞ እንዳይበተን ተጨንቆ ባለ በሌለ ሀይል ስራዬ ብሎ ለማደናገር መሯሯጡና አድፍጦ መጠበቁ የባጢልና የፖለቲካ ባለ ቤቶች መገለጫ ነው!!። ከእልህና ከትቢት ውጥረት ውጡና ትላንት የነበራችሁበት የሐቅ አቋም ላይ ሁኑ!! ለዱኒያቹም ለአኼራቹም የሚጠቅማቹ እሱ ነው።

🔸የሙነወር ልጅ ትላንት ከሶስት/ከአራት አመታት በፊት፣ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ (የነሲሃ) አመራሮች በድብቅ እየተሸማቀቁ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር በኢፍጣር ሰኣት የተነሱትን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቆ "ነጭ ነጯን እንናገራለን" በማለት የጀመረውን ምላሽ የት አደረሰው? ወይስ የመርከዙ ሰዎች ከዛ በኋላ ደንግጠው ተውበት አድርገው ትተውት ወደ ሱናው ተመልሰው ነው?! በጭራሽ!!
የመርከዙ ሰዎችማ ከትላንቱ መደባበቅ ወጥተው ስለ ዲናቸው ጠንከር ያለ እውቀት ለሌላቸው ነጋዴዎች እንኳን ግልፅ በሚሆን መልኩ በአደባባይ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደባለቃቸውን አውጀዋል። በኮንፈረንሶቻቸውና በተለያዩ ዝግጅቶቻቸው ከአል ኢኽኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ከቱባ ቱባ መሪዎች ከነ ጀይላን፣ ኢብራሂም ቱፋና ሙሀመድ ሃሚዲን… መሰሎች ጋር ሆነው አንድ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ሆነው ፎቶና ቪዲዮ በመልቀቅ ለህዝቡ በግልፅ አሳይተዋል። ከዚህም ባሻገር በየ ቦታው (በከተማ በገጠሩ) ከኢኽዋኖች ጋር ሆነው መጅሊስ ውስጥ ተሰግስገው የመንግስት የፀጥታ አካላትን በማሳሳት የሰለፊያ ደዕዋን ለማደናቀፍ እየታገሉ ነው። በነዚህ ሰዎች ላይ ብዕርህ ለምን ደለዶመ?!

🔸 የሙነወር ልጅ ሆይ! እስቲ ልጠይቅህ ለማደናገር መፍጨርጨርህን ትተህ በግልፅ ተናገር፣ ዛሬ ላይም እነዚህ የመርከዙ አመራሮች አንተ ዘንድ ሰለፊይ ናቸው?!
የጀርህና ተዕዲልን ነጥብ ጉዳይ አቆየውና ይህን ጥያቄ መልስ፣ ምክንያቱም አንተ ስለ ጀርህና ተዕዲል ነጥብ የእውቀቱም ሽታ የለህም!! ለዚያም ነው "ውሃ ሲወስድ ውሃ ይጨበጣል" እንደሚባለው፣ ጭልጥ ወዳለው የተምይዕ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በዚህ ርእስ ላይ ይረዳኛል ያልከውን አሰስ'ገሰሱን ኮተቱን ሁሉ ምኑንም ከምኑም ሳትለይ ከተለያዩ ዌብሳይቶች እየለቃቀምክ የነበረው። ይህ አላዋጣ ሲልህ ነው
ሰለፊዮችን አድፍጠህ ጠብቀህ የተቆራረጡ የሰለፊዮችን ቃላቶች እየመረጥክ በቃላት ስንጣ የተጠመድከው።
- ያ ሁሉ በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ የነበረህ ሀይል የት ገባ?! ተውበት አድርገው ሁላቸውም ሰለፊዮች ሆነው ነው ወይስ አንተ ወደ ባጢል ሰዎች ተውበት አድርገህ ነው በሱንና ሰዎች ላይ አንበሳ በቢድዐህ ሰዎች ላይ ሬሳ የሆንከው?!
ለቀድሞዎቹ ኢኽዋኖችና ለቅርብ ጊዜዎቹ የነሲሃ ቲቢ ባለቤት ኢኽዋኖች ሽንጥህን ገትረህ ትከላከላለህ፣ በቀድሞው አቋማቸው የፀኑ መፅሃፍህን መቅደም በማድረግ ሲያበረታቱህ የነበሩ ጠንካራ የሱንና መሻይኾችን ደግሞ የተለያየ ጥላሸት በመቀባትና ውሃ በማይቋጥሩ ነገሮች በመተቸት ሰዎች እንዲርቋቸው ለማድረግና ጭፍን ተከታይ ቲፎዞዎችህ እንዲቆዩልህ ትፍጨረጨራለህ!!። በዚህ ስልትህ ጭፍን ተከታዮችህን ከጥመት ቡድኖች ጋር እንዲግበሰበሱ አድርገሃል።
ይህ ነው አይን ያወጣ ያፈጠጠ ጥመትና የተምይዕ ዋሻ መሆን። ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571]
አላህ ከጭፍን ተከታይነትና በባጢል እልህ ውስጥ ከመግባት ጠብቆ እሱን እስክንገናኘው ድረስ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


መቸም ብሆን አትተክዝ።ዱንያ በፍላጎታችን አይደለችም።እሷ’ማ ብሆን በአላህ ትዕዛዝ ናት።የአላህ ትዕዛዝ ሁሉም መልካም ነው።

አይዞህ አትጨነቅ።መጨነቅ ትርፉ ድካም ነው።ጉዳይህን ለአላህ ስጥ።እስከቻልክ ለመቀየር ሞክር።ዱዓም አክልበት።ከአላህ ትዕዛዝ ውጭ የምትሆንበት ቅፅበት የለም።አላህ ረስቶህም አይደለም።ኦሮፋም አሰልፎክ አይደለም።ይልቅ ላንተ ይበጃል ያለው ነገር ግዜው ስላልደረሰ ነው።ገና አላህ ካኖረህ ብዙ አመታትን ትኖራለህ።"ከዚህ ቦኃላ የተፃፈው ብመጣልኝስ ምን ላደርገው ነው "አትበል።

ግዜ የማይፈጀው ሀሳብ እንጂ የትኛውም ነገር ግዜ ይፈጃል።እንዲሁም የትኛውም ዱንያዊም ሆነ ኣኼራዊ ጉዳይ ቁጭ ብለህ አንተ ጋ አይመጣም።ቁጭ ብለህ የሰማይ ምድሩን አትመኝ።በቻልከው ልክ ለመቀየርና ለመቀያየር ጥረት አድርግ።እንደ ታፔላ አንድ ቦታ ላይ ተለጥፈህ ግዜህን አታቃጥል።ያለ ልፋት የሚመጣ ነገር ብኖር ሀሳብና ጭንቀት ብቻ ነው።ለውጥ እንጂ ነውጥ አይበግርህ።በቻልከው ያክል የሚያስተክዙህንና የሚያስከፉ ሰዎችን ለመራቅ ሞክር።የሚያቆሽሽህንና የሚያንቋሽሽህን ችላ በለው።

የሚያስጨንቃቸውና የሚያስከፋቸው ውጤትህና ለውጥህ እንጂ ውድቀትህና ውድመትህ አይደለም።ባንተ ውድቀትና ውጥረት ደስታ የሚያገኝ አካል ካለ ደስታውን አትቀማው።

የሱን ደስታ ለመቀማት ብለህ ሳይሆን ለራስህ ብለህ ራስህን አድን።መሬት ቢንቀጠቀጥ ሰማይ ቢፈርስ በሀያሉ ጌታ የተመካ ሰው ሊጎዳ አይችልም።ሁሌም ክፋት ለሚሰሩብህ ሰዎች ዱዓ አድርግላቸው።በዝምታህም ውስጥ ምክር ለግሳቸው።ባንተ ላይ የተፃፈው እንጂ ስላልተፃፈው ነገር ስልጣን እንደሌላቸው አስረግጠህ ንገራቸው።ጉዳትም ሆነ ጥቅም በሀያሉ ጌታ መሆኑ አንተን ያኮራሃል ።

አልሀምዱ ሊሏህ!!

🏝https://t.me/ibnujemilchannel


🌹አስብላት አታከላፍታት

በጀርባዋ ልጅ ተሸክማ ገበያ ስትገባ ፣ከኒቃብ ከጂልቧቧ ስትወለካከፍ ገበያ ከመግባት ካፈርክ ገና አልገባህም ማለት ነው።ለወንድ ልጅ ገበያ ገብቶ ቅቤ መግዛትም ሆነ ዘይት መግዛት ሽንፈት አይደለም።ከቀድሞ ታሪክ ምሳሌ ብንወስድ አብዱረህማን ብን ዐውፍ ረዲየሏሁ ዐንሁ መዲና ገበያ ላይ ቅቤ ነጋዲ ነበር።ምስት ያገባም ግዜ ቢዝነሱ እሱ ነበር።


وَمَا أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ الْمُرْسَلِينَ إِلَّا إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ الطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِي الْأَسْوَاقِ ۗ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ ۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًا

ከአንተ በፊትም ከመልክተኞች እነሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም፡፡ ከፊላችሁንም ለከፊሉ ፈተና አድርገናል፡፡ ትታገሳላችሁን ጌታህም ተመልካች ነው፡፡

አልፉርቃን 20

ታዲያ! ገበያ ለመግባት አፍረህ ባለቤትህ እርጉዝ ሆናና ልጅ አቅፋ ገበያ ስትገባ ራስህን ከነብያት መነፀር በምን መነፀር አይተህ ነው? ነብዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤታቸው ውስጥ የሚሰራን ስራ ያግዙ ነበር።አዛን ስደርስ ወደ ሶላት ይቆሙ ነበር።ገበያ ገብተህ ስለተገበያየህ ከደረጃህ አንዳችም የምቀንሰው ነገር የለም። ቅቤም አይደለህም አትቀልጥም።

ምስትህ መንግድ ላይ ከጂልባብና ከኒቃብ እስከምትወለካከፍ ድረስ ራስህ መኮፈስ ተገቢ አይደለም።ወንድነት ሌላ ገበያ መግባት ሌላ ነገር ነው።ገበያ መግባት ሙሩኣን ማጣት ብሆን ኖሮ አሽረፉል ኸልቅ ወደ ገበያ ድርሽ ባላሉ ነበር።ያ የወንዶች ወንድ የነበረው ዑመርም ገበያ ባልገባ ነበር።መግባቱም በኢስላም ታሪክ ከጀግነንቱና ከወንድነቱ የቀነሰው የለም።

እስከቻልክ ድረስ ለባለቤትህ የሚያስፈልገውን ነገር ራስህ በማቅረብ ሚትስህን ከሰዎች ዐይን ሰተር ብታደርጋት ትመሰገናለህ እንጂ አትወቀስም።ቅቤና አይቤም ገዝተህ ብታመጣ ምን ትሆናለህ??

አይዞህ "ሴታሴት" የምሉህ ሰዎች ስላልቀሩና የነብያት ታሪክ ስላላወቁ ነው።

እና’ማ!አደራህን ልጅ ያለቅስባታ፣ቤት ስራ ወጥሯታል፣ብዙ ችግሮቿን እያየህ ገበያ ከመግባት አትፈር እሺ!

ፋራ ያለህ ሰው ራሱ ፋራ ነው።ስጀምርም ንገረኝ ካልከኝ እቤቷ ውስጥ ያቀረብከውን ነገር ከማቅረብ ውጭ ወደ ገበያ መሄድ ያንተ ስራ ነው።



وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَىٰ ۖ وَأَقِمْنَ الصَّلَاةَ وَآتِينَ الزَّكَاةَ وَأَطِعْنَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيُذْهِبَ عَنكُمُ الرِّجْسَ أَهْلَ الْبَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِيرًا

በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው፡፡

[አህዛብ 33]

🏝https://t.me/ibnujemilchannel


⚠️ عيد باطل... تهنئهم على الباطل ‼️


ሴትን ልጅ አዛ ከሚያደርግ ነገር፣ከህመም በእርግዝና ግዜም ሆነ በምትወልድበት ግዜ ወይም ከዝያ ቦኃላ በሚታሳድግበት ግዜ የሚገጥማት የሆነው ነገር ይህን ከጌታዋ (ጋር) ከተሳሰበችበት እሱ ለደረጃዋ ከፍታና ለወንጀሎቿ ማበሻ መሆኑን ልታውቅ (ይገባል)።

ኢብኑ ዑሠይሚን


🏝https://t.me/ibnujemilchannel


አል–ሐምዱ ሊላህ!!

በዋልከልን ፀጋዎች ላይ ሁሉ ደስተኞች ነን። የእኛ ምስጋና ባንተ ስልጣን ላይ የምጨምረው የለም።ባናመሰግን የምንጎዳው እኛው ነን።

አል –ሀምዱ ሊላህ! በፀጋዎቹህ መልካሞች ይሞላሉ።

الحمد لله حمدا كثيرا مباركا فيه كما يحب ربنا ويرضاه.


ኢብኑ ሙነወር በራሱ ብዕር የሚከተሉትን መስክሯል፦
👉 ኢብኑ ሙነውር ድንበር አላፊ መሆኑን
👉 ኢብኑ ሙነውር አስቀያሚ ባህሪ እንዳለው
👉 ኢብኑ ሙነውር ነውረኛ ግለሰብ መሆኑን በአግባቡ ተናግሯል።

✅ ምክንያቱም ሰሞኑን ሸይኽ አብዱልሐሚድ ባስተካከሉት ነጥብ «ብየም ከሆነ ተመልሻለሁ» ባሉበት ነጥብ መነሻ አድርጎ “ወፈፌ” እያለ የአደበ-ቢስ ወይም ስርዓት-አልባ ሰው ገለፃ አስቀምጧል። ስለዚህ ራሱ እንዳለው «ድንበር አላፊ መሆኑን፣ አስቀያሚ ባህሪ እንዳለው፣ ነውረኛ ግለሰብ እንደሆነ አረጋግጠናል።

بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ
በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡
[አል-ቂያማህ - 14]

የሚነሳ ማምታቻ፦
👉 ምናልባት ሸይኽ አብዱልሐሚድ የሰጡት ማስተካከያ ሳይደርሰው ቢሆንስ? የሚል ሀሳብ ከተነሳ የሚከተሉትን እላለሁ፦
❶ኛ በኔ ግምት ይደርሰዋል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ከማንም በላይ ለሚዲያ Active ነውና። በተጨማሪም ይህንኑ ተግባር ከዚህ በፊት ፈፅሞ ሰዎችን እንዲጠሉ ለማድረግ ተጠቀመበት እንጂ ማስተካከያ አላደረገም። ስለዚህ የሸይኽ አብዱልሐሚድ ማብራሪያ ያልደረሳቸውን ሰዎች ሸይኹን እንዲጠሉ ማድረግ ዋና ፍላጎቱ ነው።

ኢብኑ ሙነወርና ግብረአበሮቹ ከዚህ በፊት ልክ የአሁኑን አምሳያ ማጭበርበሪያ ሲያሰራጩ አላህን ፍሩ በተመለሱበት አትውቀሱ ብለናቸው ነበር ግን ግፋቸውን አላስተካከሉም።
ተመልከቱ ➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/8723

ሌላኛውን እዩት ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/7993

👌 ስለዚህ ሰዎቹ እንደምንም ተፍጨርጭረው የመረጃ እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ማታለል ዋና አላማቸው ነው።

❷ ሸይኹ ያስተካከሉበት ካልደረሳቸው ይሄው ልከንላቸዋልና ያስተካክላሉ። ካልሆነ ግን እንዳሉትም ነውረኞች ናቸው!


····ከመንገድ ሰዎች ሰዎች በአላህ ላይ አንድን ንግግር አልተናገሩም የክርስቲያኖች ከሱ በላይ አስጠሊ ብሆን እንጂ።ለዚህም ነው ሙዓዝ አከብኑ ጀበል እንዲህ ይል የነበረው፦
«አትዘኑላቸው ምክንያቱም ከሰው ልጆች ማንም ያልተሳደባትን ስድብ በእርግጥም እነሱ አላህን መስደብን ሰድበዋልና»።ለዚህም ነው አላህ በቁርኣን ውስጥ በአላህ ላይ ቅጥፈታቸውን ከሌሎች ቅጥፈት ይልቅ ያገዝፈዋል።

📚አልጀዋቡ–ሶሒሕ ሊመን በደለ ዲነል መሲሕ

🏝https://t.me/ibnujemilchannel


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
حكم المشاركة في أعياد النصارى وغيرهم من الكفرة

በክሪስቲያኖችና በሌሎችም በዓል ላይ የመቀላቀል /የመጋራት ፍርዱ።

ኢብኑ ባዝ

🏝https://t.me/ibnujemilchannel


« طُوبى لِمَن أصلَـح نفْسه قبْل رَمضـان ».

لطَائف المَعارِف .






ኢብኑ ሙነወርን ተውት ምክንያቱም እሱ እልህ እስኪፈነዳ የሚወጥረው በእልህ የተሞላ ለመበቀል ሲል የማይቋርጠው ገመድ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ስለዚህ እልሁ እስኪለቀው ተውት ይለፍልፍ!
➶ ከድሮዎቹ ሙመይዓዎች አንደ የተናገረው!

👌 ኢብኑ ሙነወር ያኔ ኢብኑ መስዑዶችን ሲያንኮታኩት ከላይ ያለውን ፅፈው ነበር። በወቅቱ ሳየው ተናድጄ ነበር። በተደጋጋሚ ቢስተዋልኩት ባህሪው ግን እውነትም እልህ የወጠረው መበቀል የሚወድ ሚስኪን ግለሰብ ነው።

👌 እልህ በወጠረው ስሜቱ ምክንያት ፍትሃዊነት ይሰወርበታል። አላህን መፍራት ተራ ይሆንበታል። ጥንቁቅነቱ ገደል ይገባል። እልህ ከባድ በሽታ ነው። የበቀል ሱል ከባድ ቫይረስ ነው። በዚህ ጥቂት አመታት በርካታ ነጥቦች ላይ ታዝበነዋል።

👉 ሰሞኑን ሸይኽ አብዱልሐሚድ ማብራሪያ ባደረጉበት ጉዳይ አንፅቶ ወፈፌ እያለ ሲሳደብ ሳይ ገረመኝ! ምን ያክል የሞራል ውድቀት ውስጥ እንደሰመጠ አስተዋልኩ።

👌 ከዙሪያው ያሉ ደጋፊዎቹ ተው ተው ተው በማለት አይመክሩትም። አብዛኞቻቸው ሸይኹ ያስተካከሉት ነጥብ መሆኑን ያውቃሉ  ግን ዝምምምም! ምክንያቱም አላማቸው ሸይኽ አብዱልሐሚድ መጣል ነውና! ሳያውቁት "አልጋያህ ቱበሪሩል ወሲላህ" ወደሚለው የኢኽዋኖች መርህ የገቡ ይመስላል።

✅ አብዛኞቹ ራሱ ኢብኑ ሙነወርን ጨምሮ በሸይኹ እየቀጠፉ መሆኑን ያውቃሉ ግን ጉዳዩ የማይደርሰውን ሰው ለማጭበርበር በሚል ቅጥፈታቸውን ይሸላልሙታል።

🏝 ወዮላችሁ والله ወዮላችሁ ዛሬ ለሙሪዶችህ ሸላልመህ ነገስ? ከሀያሉ ፊት ምን ታደርግ? አላህን ፍሩ!!!

ተመከር ይጠቅመሃል ↙️↙️↙️
https://t.me/AbuImranAselefy/9246


~> ምክር ለኢብኑ ሙነወር
∬₸₸₸₸₸₸₸₸₸₸₸∬

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል-ሐበሺ አስ-ሲልጢይ አላህ ይጠብቃቸው!

የአኺ ኢብኑ ሙነወር ሆይ! ቆም በልና ራስህን ተመልከት ወላሂ ለነፍስህ መከላከል አይጠቅምህም፤ ምንም አያደርጉልህም!

ሱናን አስፋፋ፣ ተውሂድን አስፋፋ፣ አትዋሽ፣ አታጭበርብር እስኪ ራስህን ቆም ብለህ አስተውል!

ወላሂ እዚህ ያደረሰህ ለምን እንዲህ ይሉኛል የሚለው ራስን የመከላከል ዘይቤ ነው።

✅ ለራስ ሲሉ መበቀል ሰለፍያን የበታተነ፤ በሰለፍዮች መካከል ጥላቻን ያስፋፋ እና አንድነታቸውን ያንኮታኮተ ነው።

በቢድዓ ሰዎች ላይ በፍትህ እና በመልካም ሁኔታ የተመዘዘ ሰይፍ ሁን! ይህ ካንተ የሚጠበቅ ነው። ከሸይጧን ውስወሳዎች ተጠንቀቁ!

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

ሀሳብ  ካለዎ 
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot


📌 ‏قال ابن عثيمين رحمه الله :

لتعلم ‌‎المرأة⁩ أن ما يصيبها من أذى وألم في حال الحمل أو عند الوضع أو في الحضانة بعد ذلك

فإنما هو رفعة في درجاتها وكفارة لسيئاتها إذا احتسبت هذا على الله سبحانه وتعالى.

‌⁩ (فتاوى نور على الدرب ج11 ص280)

ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ


የወጭ አይነቶች፦

🚦የራስ ወጭ ለራስ…

🚦የአባት ወጭ ለልጆች…

🚦የልጆች ወጭ ለወላጆች…

«አንተም ገንዘብህም የአባትህ ነው።»

የባል ወጭ ለሚስቶች…

👌ተክሽና የቀረበች ከደርስ ተወስዷ።

👂ትደመጥ


🎙ኢብኑ ጀሚል


🏝https://t.me/ibnujemilchannel


የሙነወር ልጅ ማምታቻና የሸይኽ ዐብዱልሀሚድ (ሀፊዘሁላህ) መልስ

🔹የዲን አጭበርባሪው የሙነወር ልጅ፣ አንድ በክርክር መሃል ከሸይኽ ዐብዱልሀሚድ ተቆርጣ የወጣችን የቆየችና ከዚህ በፊት መልስ የሰጡባትን ድምፅ ለቆ ቲፎዞዎቹን ለማምታት ሲሞክር "የሚጮሁትን የማይኖሩ…" በማለት ይቃዣል።

ከሸይኽ ዐብዱልሐሚድ (ሀፊዘሁላህ) ተቆርጦ ሲበተን ለቆየው ድምፅ ወንድማችን ኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሀፊዘሁላህ) ጠይቋቸው ሸይኹ የሰጡትን መልስ ከራሳቸው አንድበት አድምጡት።
#join ⤵️ ቴሌግራም
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Показано 20 последних публикаций.