ህዝብ ግን ተጨንቋል
ልጅ አባቱን " ፕሬዜዳንት ማለት ምን ማለት ነው? " ብሎ ይጠይቃል።
አባት: _ " ፕሬዜዳንት ማለት መሪ ማለት ነው። አሁን ለምሳሌ እኔ የዚህ ቤት ፕሬዜዳንት ነኝ።" ብሎ ይመልስለታል።
ልጅ ጥያቄውን አላቆመም።
ልጅ:_ " እናቴስ ምንድን ናት?"
አባት:_ " እናትህ ገንዘብ ሚኒስቴር ናት።"
ልጅ:_ " አያቴስ?"
አባት:_ " አያትህ ሰላይ ናት።"
ልጅ አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ " እኔስ ምንድን ነኝ?"
አባት:_ " አንተ ህዝብ ነህ።" ብሎ ይመልስለታል።
በሌላ ጊዜ አባት ስራ ሄዶ መኖሪያ ቤታቸው ሌላ ሰው ይመጣል። ከዛም ልጅ ተደብቆ አባቱ መስሪያቤት ይደውልና ምን ቢል ጥሩ ነው?
.
.
.
.
" ሄሎ አባዬ! ትሰማኛለህ? እቤታችን ሌላ ፕሬዜዳንት መጥቷል፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ሽር ጉድ እያለ ነው፣ ሰላይ ያንቀላፋል፣ ህዝብ ግን ተጨንቋል።
👑
@habeshavibe_500k❤️
@habeshavibe_500k