#ወልድያ!
የወልዲያ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሏቸው በነበሩ ህጎች ላይ ማሻሻያ አደረገ!
የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት ከነገ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የባጃጅ ማህበራት ፈረቃን በሚመለከት አስቀምጧቸው በነበሩ ህጎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
በዚህም መሰረት:-
▪️1. የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በቀን 1 የባጃጅ ማህበር ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ተቀምጦ የነበረውን አሰራር በማሻሻል ከነገ ጀምሮ በቀን 2 የባጃጅ ማህበራት አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።
በመሆኑም ነገ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የጁና ፅናት የባጃጅ ማህበሮች እንዲሰሩና በቀጣዩ ቀን ማለትም ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ሀገሬና ብሌን የባጃጅ ማህበራት እንዲሰሩ በዚህ ፈረቃ መሰረት በቀን 2 የባጃጅ ማህበሮች አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኖ ማሻሻያ ማድረጉን የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።
ማሳሰቢያ:- ማንኛውም ማህበር የሌለው እና ዜሮ ዜሮ ባጃጅ በስምሪቱ እንዳይገኝ ሲል የከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳስቧል። ከዚህ በፊት የከተማዋን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በከተማዋ የፀጥታ ምክር ቤት የተቀመጡ ክልከላዎች ባሉበት የሚቀጥሉ ይሆናል።
የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
@addis_news