ይቅደም ታዉሂድ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ ቻናል የሰለፊይ ዳዒዎች እና መሻይኮች ትምህርት ሙሓደራዎች ፈታዋዎች ፁሁፎች የሚሰራጭበት ቻናል ነው

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


እንኳን አደረሳችሁ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
وعيد مبارك
أعاده الله عليكم وأنتم في صحة وعافية وإيمان
እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል_አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን
ሁሌም በዒማን እና በአፊያ ጠብቆ እንዲያደርሳችሁ አላህን እንለምነዋለን።


. عيد مبارك
EID MUBAREK
ኢድ ሙባረክ


👉 ለዐረፋ ተጓዦች
የተከበራችሁ ሙስሊም እህትና ወንድሞች ቤተሰቦቻችሁን ለማስደሰትና በአሉን ከእነርሱ ጋር ለማሳለፍ በጉዞ ላይ ያላችሁ በሙሉ ከሁሉም በፊት ለዚህ ያበቃችሁና ለዒደል አድሓ ዋዜማ ያደረሳችሁን አላህን ማስደሰት አለባችሁ ። አላህን ማመስገን እንጂ ማመፅ ኒዕማውን መካድ ነው ። በዚህ በተከበረ አላህ መላኢካዎች ዘንድ ባሮቼን ተመልከቷቸው ምን ፈልገው ነው እኔን የሚያወድሱት እናንተ ምስክር ሁኑብኝ የተመኙትን ሰጥቻቸዋለሁ ከሚፈሩትም ጠብቄያቸዋለሁ በሚልበት ቀን በዘፈን ከአጅ ነብይ ጋር በመተሻሸት በጩኸት ልናምፀው አይገባም ። የአላህ ቀድር ሆኖ አጀል ቢደርስ በነበራችሁበት ሁኔት ነው የምትቀሰቀሱት ። ጉዟችሁ አላህን በማወደስ ቁርኣን በመቅራት ዱዓእ በማድረግ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል መሆን አለበት ። ቤተሰቦቻችንም ወደ አላህ እንዲቃረቡ ከሽርክና ከቢዳዐ እንዲርቁ ዳዕዋ ማድረግ ዘፈን ሳይሆን ሐዲስ እንዲሰሙ መጋበዝ ያስፈልጋል ። አገርቤት ከዒድ ማግስት ጀምሮ ወንድና ሴት ተቀላቅሎ ሙሽራ ቤት ወይም ሜዳ ላይ የሚጨፈረው ጭፈራ ከአላህ ጋር የሚያጣላ አኼራ የሚያጠፋ እንጂ ደስታ የሚያመጣ አይደለም ። የሙስሊሞች ደስታ አላህን በማስደሰት ነው መሆን ያለበት ። እነዚህ ተግባሮች ዝሙት እንዲስፋፋ በሽታ እንዲሰራጭ የአላህ ቁጣ እንዲፋጠን የሚያደርጉ ናቸው እንራቃቸው ። አላህ ሐቁን አውቀን የምንከተለው ባጢል አውቀን የምንርቀው ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka


ታላቅ የሆነ ምንዳ እንዳያመልጣችሁ!!
የዚል-ሒጃ 9ኛው ቀን የውሙ ዐረፋ ፆም
–––––
አላህ ባሪያዎቹን በብዛት ነፃ የሚያወጣበት ታላቅ የሆነ የዐረፋ (ዙልሂጃ 9ኛው) ቀን ነው

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“አላህ ባሪያዎቹን በብዛት ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት እንደ ዐረፈ ቀን አንድም ቀን የለም!…” [ሙስሊም ዘግበውታል]

የዐረፋን (ዚል-ሂጃ 9ኛውን) ቀን መፆም ያለፈውን 1 አመት እና የቀጣዩን 1 አመት ወንጀል ያብሳልና የነገው እለተ ሰኞ 9ኛው የዚል-ሒጃ ቀን ነውና ፆሙ እንዳያመልጣችሁ!!

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ እለተ ዐረፋ ጾም ተጠይቀው እንዲህ በማለት መለሱ:- "ያለፈውን እና የቀጣዩን አመት ወንጀል ያስምራል።” [ሙስሊም ዘግበውታል]

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህም ብለዋል:-
“የዐረፋን ቀን መፆም ከፊቱ ያለውን አንድ አመት እና ከኋላው ያለውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አድርጋለሁ።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 3853]

ምርጥ (በላጭ) ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነውና ነገ ፆመኛ የሆነችሁም አጋጣሚ በበሽታና መሰል ከባድ ምክንያቶች መፆም የማትችሉም ካላችሁ ዱዓ ላይ በርቱ!!

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“ምርጥ (በላጭ) ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው፣ ከተናገርኩት ነገር ሁሉ በላጩ እኔና ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት የተናገሩት ላ! ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ! ሸሪከ ለሁ, ለሁል ሙሉኩ, ወለሁል ሀምድ, ወ ሁዋ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር (የሚለው) ነው!!። ትርጉሙም:- ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም! እርሱም ብቸኛ ነው፣ ለእርሱም ምንም ተጋሪ የለውም!፣ ንግስናም ለእርሱ ነው፣ ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ነው፣ እርሱም በሁሉ ነገር ላይ ቻይ የሆነ ነው።” (የሚለው ታላቅ የሆነ የተውሒድ ቃል ነው) [ትርሚዚይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ነው ብለውታል።]

ነገ እለተ ሰኞ ሐምሌ 12/2013 ዚል-ሒጃ 9ኛው የዐረፋ ቀን ነውና አደራ በፆሙም በዱዓውም አትዘናጉ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: ዚል-ሒጃ 8/1442 ዓ.ሂ

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




አደራ ለአረፋ ተጓዦች
____________
አረፋ ላይ ብዙ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለዝያራ እና በአሉን አብሮ ለማሳለፍ ከፍተኛ ዝግጅትና ጉዞ ይደረጋል።

በዚህ ጉዞ ላይ ለቤተሰቦቻችን ትካዜና ራሀባቸውን ለማጥፋት ከምንጥረው በላይ ዱንያም አኼራቸውን የሚያስተካክልላቸው የሆነውን ተውሂድ በሚገባቸው መልኩና ቋንቋ እናስተምራቸው።

ማህበረሰቡ አሏህ ያዘነለት ሲቀር በርካታ ችግሮች አሉበት
=> ተውሂድን ባለማወቅ ሽርክ ላይ የወደቀ
=> ሶላታቸውን የማያስተካክሉ
=> ውዱእ ማድረግና ፋቲሃ መቅራት የማይችሉ
=> ፆም በስርአቱ የማይፆሙ በርካቶች ናቸው።
_____________________

https://t.me/joinchat/Sn62xstw8Nvq1swV




☪ ማስታወሻ ☪

የዓረፋ ቀን ፆም
ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰሊም
እንዲህ ብለዋል :-
የዓረፋ ቀን ፆም ያለፈውንና
የሚመጣውን አመት ወንጀል
ያብሳል።

ሙስሊም ዘግበውታል. 11261

በአላህ ፈቃድ የዓረፋ ቀን ዙልሂጃ 09-1442 የሚሆነው ሰኞ ስለሆነ ሰኞን ዙልሂጃ ዘጠነኛዋን ቀን መፆም የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ረሱላችን ﷺ የነገሩን ስለሆነ ማንኛውም ሙስሊም ወንድ ሴት ሳይል ይህን ትልቅ አጅር እንዳያመልጠን ምክንያቱም ለቀጣዪ አመት በህይወት ላንኖር/ይችን አለም በሞት ልንሰናበታት እንችላለን እና ሁላችንም ልንፆመው ይገባል በማለት ለማስታወስ እወዳለሁ ።

የዓረፋ ቀን ፆም በኢትዩ… የቀን አቆጣጠር ሐምሌ #12 #ሰኞ ለት ይውላል ።

📌 የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
⤵️Join us ↪️ share
⤵️ join
🌐 https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy


✅የ9ለኜይ አያም ሶመን ሱሚኖት🟡

عن أبي قتادة الأنصاري رضي الله عنه ،
أن رسول الله ﷺ قال :

((صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ))

📒[رواه مسلم]
 
አቡ ቀታደህ አላህ ቢለክ የውደድኒ ሉክተኛይ ﷺ

ያርዱል አረፈ አያመ ሶመነ ተሳሉይሙ
《ያለፈሚ አይዶ ዪመጫነሚ ዘማነ ወንጀለ ኢሚሻን/ያቴድጋን ባሉ》ባለ።

📒ኢማሙ ሙስልም

https://t.me/tewhid_sune
https://t.me/tewhid_sune






አሰለሙ አሌኩም ወራህማቱለሂ ዋበራከቱሁ ሰለም ነቹህ ኢንዴት ነቹሁ እንኳን1442ኛው ዓ:ሂ ለዙልህጃህ ወር በለሰም አዳረሰቹሁ ኢየለን አንድ ምነስታውሰቹ ነጋር ቢኖር በስልጤ ዞን በቅልጦ ዋራዳ ቀበሌ አደዘርአቤቾ ለጎዳ ነወሪ ለሆነቹ እነ አድስ አበበ ለለቸሁ ዘንድሮ አለህ ከላ የኢድ ሰላት የምንሰግዳው በጎዳ መሆኑን ኢየገለፅን በታለቅ ደስታ ናው !!! አለህ በሰለም የድርሰን:


[ለዒድ አል አድሃ በዓል የሀገር ቤት ጉዞ ክፍል አንድ።]

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው!

ለሙስሊሞች መደሰቻ ሁለት ትላልቅ በአላትንና የጁምዓ እለትን ለደነገገው ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!!
በዚህ በተከበረው #የዙል_ሒጃ ወር አቅማቸው የፈቀደላቸው ሰዎች የጉዞውን ጣጣ ለቻሉ ሰዎች የተከበረውንና መጎብኘቱ ግዴታ የሆነውን የአላህን ቤት ለመጎብኘት የሚጓዙት በርካቶች ናቸው፣ ይህን ያልቻሉ ደግሞ ቤተሰባቸው የተለያዩ ክ/ሀገራት ያሉ ወገኖች ከቤተሰባቸው ለማሳለፍ ወደተለያዩ ክ/ሀገራት ይጓዛሉ፣ ምን ያምር ጉዞ!
ይህ ጉዞ ለመልካም ነገርና ለቤተሰብ ዝያራ በመሆኑ የሚያስደስት ቢሆንም፣ ተጓዦች አላህን አያምፁበትም ፍፁም ነው ማለት ግን አይደለምና ከእነዚህ ስህተቶች እንዲቆጠቡ ማስታወሱ ግዴታ ነው።


እንዲያውም ገና ጉዞው ሲጀመር በተከበረው ዘጠነኛው ቀን ያንን ቀን መፆሙ ያለፈውንና የሚቀጥለውን ዓመት ወንጀል ያስምራል በተባለው ቀን አላህ ሀራም ያደረገውን የከበደ ወንጀል ጫት እየበላ የሚጓዘው ህዝብ አብዘሃኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም! እንዲያውም በጠቅላላ ማለት ይቻላል! ጥቂት አላህ ያዘነላቸው ባሪያዎቹ ሲቀሩ።
በዚሁ አጋጣሚ ጫትን ለማይቅሙት ለጥቂቶች አንድ መልዕክት አለኝ:– ( ከሚቅሙ ሰዎች ጋር ተቀላቅላችሁ የምትሔዱ ካላችሁ በራሳችሁ ላይ አንድ ግዴታ ነገር ጥላችኋል፣ እሱም የተወገዘን ነገር ማውገዝ ነው! አላህ ሀራም ያደረገው ነገር ሲተገበር ዝም ካላችሁ እንደ ዱዳ ሸይጣን መሆናችሁን አትዘንጉ! ማውገዝ ወይም መከልከልና ደዕዋ ማድረግ ካልቻላችሁ ጫት ከማይቅሙና ዘፈን ከማይከፍቱ ከቢጤዎቻችሁ ነው መሄድ ያለባችሁ።)

ታዲያ በጥቅልሉ ጫትን በየተኛውም ጊዜ የምትቅሙ ሰዎች አላህን ልትፈሩ ይገባል!!
↪️ ጫት የሰውነት አካልን ጎጂ መሆኑን ታምኑበታላችሁ! እራስን የሚጎዳ ነገር መጠቀምን ደግሞ አላህ ሀራም አድርጓል!!
↪️ ጫት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ገንዘብን እንደምያባክን ታውቃላችሁ!!
አባካኞች የሸይጧን ጓዶች መሆናቸውን ደግሞ አላህ በቁርዓኑ ተናግሯል።
↪️ ጫት አዕምሮን እንደሚቀይር ታምናላችሁ! አዕምሮን የሚቀይር ነገር ደግሞ ከአስካሪ መጠጥ ነው።
የአስካሪ መጠጥ በኢስላም ሀራምነቱ ደግሞ እንኳን ለሙስሊሞች ለከሀዲውም ግልፅ ነው!!

እነዚህ ጥቂት ጫትን ሀራም የሚያደርጉት ነጥቦች አብዘሃኛው ጫት ቃሚ ለእውነት ሲባል ብሎ ያመነባቸው እንጂ ከራሴ የሆኑ ፈጠራዎች አይደሉም።
ከላይ ለጠቀስኳቸው ነገሮች ማስረጃን ያልጠቀስኩት ከምንም በላይ ማስረጃው ግልፅና የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ፅሁፉ እንዳይረዝም ብዬ ነው።

➡️ከዚህ ጉዞ ሌላው ጥፋትና ከባድ ወንጀል ዘፈን እየተደመጠ መጓዙ ነው!!
በዘፈን ሀራምነት ሙስሊም ሆኖ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፣ አውቆ ማጣመም ፈልጎ ካልሆነ በስተቀር! ምናልባትም ከአንዳንድ ጠሞ አጥማሚዎች ብዥታ የሚወድቅበት ሊኖር ስለሚችል እስቲ በጥቂቱ የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እንመልከት:

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:–
{وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ}
الإسراء ٦٤
{ከእነሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል።}
አል ኢስራዕ 64
(በድምፅህ አታል) የሚለውን በዘፈንና በአሎባልታ ጫወታ በዛዛታ ማለት ነው ተብሏል። ኢብን ከሢር የተባለው የቁርዓን ማብራሪያ ላይ ይህን አንቀፅ በሚያብራራው ቦታ ይመልከቱ።
አላህ የመልካም ባሪያዎችን በህሪ ሲገልፅ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:–


{وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا}

الفرقان ٧٢
{እነዚያም በውሸት የማይመሰክሩ፣ በውድቅ ቃልም ተናጋሪ አጠገብ ባለፉ ጊዜ የከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው።}
አል ፉርቃን 72
(ውድቅ ቃል) በማለት የተጠቀሰው ዘፈን ነው ተብሏል። ኢብን ከሢርን ይህን የቁርዓን አንቀፅ በሚያብራሩበት ቦታ ይመልከቱ።

አላህ በተቀደሰው ቃሉ ሙሽሪኮች ቁርዓን ከመስማት እንቢተኛ መሆናቸውንና ለቁርዓን ጀርባ መስጠታቸውን ስያወግዝ እንዲህ ብሏል:–
{أَفَمِنْ هٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ{٥٩}وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُون {٦٠}وَأَنتُمْ سٰمِدُونَ}
النجم ٥٩–٦١
{ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን? ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? እናንተ ዘንጊዎች ናችሁ።}
አንነጅም 59–61
(እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ) የሚለውን ታላቁ ሷሃባ አብደላህ ኢብን አባስና ሱፍያን አስሰውሪ…የመሳሰሉ ሌሎችም (እናንተ ዘፋኞች ናችሁ) ማለት ነው የተፈለገበት በማለት ተናግረዋል። ኢብን ከሢር የቁርዓን ተፍሲርን ይመልከቱ።

ከአብደላህ ኢብን መስዑድ በጠንካራ ሰነድ (ዘፈን በልብ ውስጥ ንፋቅን እንደሚያበቅልም) ተዘግቧል።

ስለ ዘፈን ሀራምነት የተለያዩ እጅግ በርካታ (ሷሂህ/ትክክለኛ) ሀዲሶች አሉ! ጊዜን ለመቆጠብና ፅሁፉ እንዳይረዝም ከሀዲስ ምንም አልጠቀስኩም።
ነገር ግን እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው የቁርዓን አስረጂዎች አይበቁኝም ያለ ሰው ተጨማሪ የቁርዓን አስረጂዎችንና የሐዲስ አስረጂዎችን አድራሻዬን ፈልጎ በአላህ ፈቃድ በሰፊ ጊዜ መጠየቅ ይችላል።

✍🏻 [ኢብን ሽፋ Ibn shifa]

https://t.me/joinchat/Sn62xstw8Nvq1swV


በታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ምክር እንጠቀምበት!!
———
እንዲህ በማለት የዲን ተማሪ የሆኑትንም ያልሆኑትንም ይመክራሉ:-
«ለእውቀት ፈላጊውም ሆነ እውቀትን በመፈለግ ላይ ለሌለው ሰው የሚገባው ነገር፣ ያወቀውን ሱና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ግልፅ ማድረግ (ማብራራት) ነው። እኔ አዋቂ (ዓሊም) አይደለሁም አትበል፣ አዎን ዓሊም አይደለህም፣ ነገር ግን አንተ ዘንድ እውት አለ፣ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- "ከእኔ የሰማችሁት (አንድ) አንቀፅ ቢሆን እንኳን አድርሱት።" ሰዎች አጋጣሚዎችን ሊጠቀሟቸው ይገባል። ሱናን ለማሰራጨት እድሉ በተመቻቸልህ ቁጥር አሳራጫት፣ አላህ ዘንድ መልካም ምንዳ ይኖርሃል፣ እስከ እለተ ትንሳዔ የሰራበት ሰው ምንዳም አለህ።» [ምንጭ:- ሸርህ ሪያዱ ሷሊሂን ሀዲስ ቁ. 741]
ትርጉም:- ✍🏻ኢብን ሽፋ

#join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa


👉 የዘጠኙ ቀን ፆም
አላህ ለባሮቹ ከቸረው ከሰጠው በረከት ውስጥ አንዱ በዙል ሒጃ ወር የመጀመሪያዎቹ ዐስር ቀኖች ውስጥ ያደረገው አምሳያ የሌለው ምንዳና ቱሩፋት ነው ። እነዚህን ቀኖች አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ : –
عن ابن عباس– رضي الله عنهما –قال : قال رسول الله صلى الله عليه وآله وسلم :
"مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهَا أَحَبُّ إِلَى اللهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ" يَعْنِي أَيَّامَ الْعَشْرِ، قَالُوا : يَا رَسُولَ اللهِ، وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ قَالَ: "وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ".
أخرجه أبو داود وابن ماجه وغيرهما.

" ከእነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነበት አንድም ቀን የለም ( የዙል ሒጃ ዐስሩ ቀኖች ) አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን? አሉዋቸው ። በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን, ምናልባት አንድ ሰው ነፍሱንና ገንዘቡን ይዞ ወጥቶ በምንም ነገር ካልተመለሰ እንጂ "
ይህ ሐዲስ መልካም ስራ የቱ እንደሆነ አልገደበም የትኛውም አይነት መልካም ስራ ያካትታል ። ይሄኛው መልካም ስራ እዚህ ውስጥ አይገባም የሚል ሰው ማስረጃ ይጠየቃል ካላመጣ ተራ ወሬ ነው የሚሆነው ። በእነዚህ ቀናቶች መፆም ከመልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው ። እያንዳንዱ ቀን ራሱ የቻለ ስለሆነ አንድ ላይ መፆም አይፈቀድም ማለትም ከልብ ወለድ መናገር ነው የሚሆነው ። ነብዩን አስመልክቶ እናታችን ሐፍሳ ይፆሙ ነበር ስትል እናታችን ዓኢሻ ደግሞ ፆመው አያውቁም ትላለች ዑለሞች በዚህ ዙሪያ የተለያየ ማስማሚያ አቅርበዋል ። ነገር ግን የሳቸው መፆምም ይሁን አለመፆም ንግግራቸውን አይፃረርም ። አልፆሙም ቢባል እንኳን መፆም አይቻልም ማለት አይደለም ። ምክንያቱም ለኡማቸው የሚጠቅመውን በቃላቸው አረጋግጠዋልና, አብዛኛዎች የፍቅህ ሊቃውንቶች መፆሙ ሱና ነው ይላሉ ። የዘመናችን ትላልቅ ዑለሞች እንደነ ሸይኽ
ኢብኑ ባዝ ፣ ዑሰይሚንንና ፈውዛን የመሳሰሉ መፆሙ ከመልካም ስራ መሆኑን አረጋግጠዋል ። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በየአመቱ ንትርክ መፍጠርና አማኞችን ግራ ማጋባት አያስገልግም ።
አላህ ለምልካም ስራ ያግራን ።
http://t.me/bahruteka




ከዱኒያ በላጮቹ ቀናቶች እነሆ ተጀምረዋልና አትዘናጉ ለዒባዳ ነቃ ነቃ በሉ!!
—————
የመጀመሪያዎቹ
አስር የዚል-ሒጃ ቀናቶች

—————
አምላካችን አላህ ችሮታውና እዝነቱ ሰፊ ስለሆነ ለባሪያዎች በመልካም ስራ ላይ የሚሽቀዳደሙባቸውን ቦታዎችና ቀናቶችን አንዱን ከሌላው በማበላለጥ እድሉን አስፍቷል። እለተ ጁምዓ ከሌሎች ቀናቶች በላጭ እንዲሆን አድርጓል። የረመዷንን ወር ከሌሎች ወራቶች በላጭና መልካም ስራዎች ውድ የሚሆኑበት ልዩ ወር አድርጎታል። ከረመዷን ወር ውስጥም የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ልዩና አማኞች ለመልካም ስራ በተለየ መልኩ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው በመታጠቅ መልካም ስራዎችን የሚሰሩባቸው ታላቅ ቀናት አድርጓቸዋል።

ልክ እንደዚሁ ከቀናቶች ውስጥ የመጀመሪያዎችን የዚል-ሒጃ ቀናት ውድና በእነዚህ አስር የመጀመሪያ የዚል-ሂጃ ቀናት የሚሰራን ስራ ከሌላው ጊዜ ሊወዳደር የማይችል ከፍተኛ ደረጃ የሰጠባቸው ውድ ቀናት አድርጓቸዋል።

ይህ የአላህ ለባሮቹ የዋለው ውለታና ትሩፋት ነው። ምክንያቱም የሰው ልጆች በተለያየ ምክንያት ተዘናግተው መልካም ስራ ውድና ልዩ ደረጃ የሚያስገኝበት ጊዜ ቢያመልጣቸው እድሜ ሰጥቷቸው በሌላው ጊዜ ከደረሱ ተሽቀዳድመው እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል። በሌሎች ጊዜዎች በአግባቡ ሳያመልጣቸው ተጠቅመው ከሆነም በውድ ጊዜዎች በመልካም ስራ ላይ መልካም ስራ በመጨመር ጌታቸው ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።

ታዲያ በሌሎች ጊዜዎች ሁሉ ከሚሰሩ መልካም ስራዎች በላጭና ውድ የሚሆንባቸው ልዩ ቀናት የዚል-ሂጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ናቸውና ነፍሲያችንና ሸይጧንን አሸንፈን በአግባቡ ልንጠቀምባቸው ይገባል።

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
“በየትኛውም ቀን የሚሰራ መልካም ስራ ከነዚህ ቀናት የበለጠ ስራ ከየት አለ?!፣” አሉ፣ ጂሃድም ቢሆን? ተብለው ተጠየቁ፣ “አዎ ጂሃድም ቢሆን” አይበልጥም፣ አሉና አክለውም እንዲህ አሉ:- “አንድ ሰው (ለጂሃድ) ራሱም ንብረቱም ወጥቶ በዚያው ራሱም ንብረቱም ያልተመለሰ ከሆነ እንጂ።” አሉ። ቡኻሪ 969 ላይ ዘግበውታል።

ይህ ማለት:- አንድ ሰው ለጂሃድ ወጥቶ በዚያው ሸሂድ ሆኖ ከነ ንብረቱ የቀረ ከሆነ ይህ ተግባር ከነዚህ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናት ከሚሰራ ዒባዳ ይበልጣል እንጂ ሌላ የሚበልጥ ነገር የለም ማለታቸው ነው።

ታላቁ ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
"በአስሩ የዚል-ሒጃ ቀናት መልካም ስራ ሲባል ፆምም ይካተታል፣ (እንደ አጠቃላይ ደግሞ) በአስሩ የዚል-ሒጃ ቀናት የሚሰራ መልካም ስራ ከረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነው። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን በዙል-ሒጃ በመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ሰዎች መልካም ስራ ከመስራት ይዘናጋሉ። ሰዎች እንደ ቀድሞው ልማዳቸው የተዘናጉ ሆነው አስሩ የዚል-ሒጃ ቀናት ያልፋሉ። ቁርኣን በመቅራት ላይ የተሻለ ሆነው አይታዩም፣ በሌሎች የዒባዳ ዘርፎች ላይም የተሻለ ንቃት ሲኖራቸው አይታዩም። ከፊሎች ተክቢር ማለትን ሁሉ ሲሰስቱ ትመለከታለህ።" [ሸርሁል ሙምቲዕ 6/470]

ኡድሂያ እርድ ለማረድ የነየተ ሰው ከዚል-ሒጃ የመጀመሪያ ቀን ከመግባቱ በፊት ካለው ሌሊት ጀምሮ አስረኛው የእርዱ ቀን ደርሶ ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከሰውነቱ ማንኛውንም ነገር መቁረጥም ሆነ መንቀል አይፈቀድለትም!። ጥፍርም ሆነ ፀጉር እንዲሁም ከቆዳው ክፍልም ቢሆን መቁረጥም አይፈቀድለትም!።

ከኡም ሰለመህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ተይዞ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“አንዳችሁ ኡድሂያ ማድረግ ከፈለገ አስሩ የዚል-ሒጃ ቀን ከገባ ከሰውነቱም ሆነ ከፀጉሩ አንድም ነገር አይንካ!።” በሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:- “አስሩ የዚል-ሒጃ ቀን ከገባ እርሱ ዘንድ ኡዱሂያ ማድረግ የሚፈልገው ነገር ካለ ፀጉርንና ጥፍሩን አይንካ።” ሙስሊም ዘግበውታል።

ከዒባዳዎች ሁሉ በላጭ በሆነው ዒባዳ ቁርኣንን በማንበብ፣ የወላጆች ሀቅ በመጠበቅ ወላጆችን በማስደሰት፣ በዱዓ ላይ በመጠንከር፣ በዚክር፣ በሶደቃ፣ ዝምድናን በመቀጠል… በሌሎች የተለያዩ በርካታ ዒባዳዎች ላይ በመበርታት አደራ!! የሰሩትን መልካም ስራ ከሚያዳክሙ ስህተቶችና ወንጀሎችም መቆጠብ ነው። አላህ ሁላችንም ለመልካም ነገር ይወፍቀን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: ዚል_ሒጀህ 1/1442 ዓ. ሂ

#join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ዙል ቀዕደህ 21/1442 ዓ. ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


{የዙል_ሂጃ አስር ቀናቶች ትሩፋት}
``````````

➧ ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው።
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፡–
=> "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ".
"ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስሩ የዙል ሒጃ ቀናቶች ናቸው።"

በሌላም ሀዲስ እንዲህ በማለት በእነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለውን ደረጃ ያስቀምጣሉ።

«ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،
قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟ قال
ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء»


«ከእነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዐላ የሚወደድበት ቀን የለም። አሉ
ሰሀቦችም…
በአላህ መንገድ ላይ መታገል (መጋደል) ቢሆንም? ብለው ሲጠይቋቸው…
አው በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም ግን አንድ ሰው ሲቀር አሉ…
እሱም በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረ ሲቀር አሉ
»

➩ እናንተ ሙስሊሞች ሆይ!
ለራሱ የሚጨነቅና ንቃተ ህሊና ያለው ሰው እንዲህ አይነት ብርቅዬ አጋጣሚዎችን በከንቱ አያሳልፍም።

➪ እኛንም አላህ ከሚጠቀሙ ያድርገንና በእነዚህ ቀናቶች ከዚህ በፊት ስናደርገው ከነበረው ለየት ባለ መልኩ ለመስራትና ለመጠቀም ራሳችንን ማነሳሳት አለብን እላለሁ።

አላህን አብዝተን በማውሳት
ተህሊል፣ ተክቢር፣ ተስቢህ እና
ተህሚድ በማድረግ ወደ አሏህ መቃረብ አለብን።


➩ አላህን አብዝተን በመለመን
➪ ሰደቃን በማብዛት
➩ ቁርዐንን አብዝተን በማንበብ
➪ የጀምዐ ሰላትን በመጠባበቅ
➩ ተጨማሪ(ሱና) የሆኑ ሰላቶችን በመስገድ
➪ የቻልነው በመፆም እና አጠቃላይ ኸይር ከተባለ ነገር ሰብስበን ተጠቃሚ ለመሆን ልንተጋ ይገባናል።

ታላቁ አሊም ኢብኑ ዑሰይሚን እንዳሉት
ብዙሃን ሰዎች የሚገርሙ ናቸው። ከረመዷን አሽረል አዋኺር ላይ የቻሉትን ያህል እየታገሉና እየሰሩ ይታያሉ ዙል ሂጃ ላይ ግን ምንም የተለየ ነገር ሲያከናውኑ አይታዩም በማለት ሀዘናቸውን ይገልፃሉ።

ከፊል ኡለሞች ከረመዷን አሽረል አዋኺር የዙል ሂጃ አስር ቀናቶች እንደ ሚያስበልጡስ ስንቶቻችን እናውቃለን?

ምንም እንኳን መስዐላው ዒብኑል ቀይም እንዳስቀመጡት……ቢሆንም
ከለሊቶቻቸው አንፃር የረመዷን አሽረል አዋኺር ሲበልጡ…
➽ ከቀኖቻቸው አንፃር የዙልሂጃ አስር ቀናቶች ይበልጣሉ።
➼ ማለት የፈለኩት ግን…ምን አልባት በቀጣዩ አመት ላንደርስበት እንችላለን
ብዙሃን ለአምናው ደርሰው ለዘንድሮው መድረስ እንደተሳናቸው እኛም እድሉን ሳንጠቀምበት ሊያልፈን አይገባምና በተቻለን እንበራታ የሚል ጥቆማ ለመስጠት ያክል ነው።

በተለይ ደግሞ...‼

አለማችን በፊትና ባህር እየዋኘች ባለችበት በዚህ ወቅት፦
➻ አላህ አስፈሪ የሆነ የፀሀይ ግርዶሽን ያክል ክስተት እና ለብዙሀን ህይወት ጤንነት ማጣት ምክንያት የሆነ ኮሮና የሚባል ወረርሽኝ በሽታ እያሳየ በሚያስፈራራበት ጊዜ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችን ማግኘት ማለት ከእድለኝነትም በላይ እድለኝነት ነው እናም ነቃ ብለን እንጠቀምበት።
➺ በመጨረሻም ለዒደል አድሀ ኡዱህያ ማድረግ የሚፈልግ ሰው የዙል ሂጃ ወር ከገባ ጀምሮ ፀጉሩንም ይሁን ጥፍሩን ከመንካት መቆጠብ አለበት።

ልክ መልዕክተኛው ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም እንዳሉት፡–
"فأراد أحدكم أن يضحي فلا يأخذن من شعره ولا من بشرته ولا من ظفره شيئا"
"ከእናንተ አንዳቹ ኡዱህያ ለማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ምንም ነገር እንዳይነካ"

አሏህ ከተጠቃሚወች ያድርገን አሚን

📝 kelifa [abuubeyda]

https://t.me/AbuImranAselefy]





Показано 20 последних публикаций.

177

подписчиков
Статистика канала