“ ሀገሬን🇪🇹 ላገልግል ባልኩኝ ሰው ሀገር ሜዳ ላይ ጣሉኝ “ አሰልጣኝ አለሙ ዋቅጅራ
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በፓሪስ ኦሎምፒክ ወደ ስፍራው ባቀኑ አመራሮች ፣ አትሌቶች እና አሰልጣኝ የሚቀርቡበት ቅሬታዎች ቀጥሏል።
የ 800ሜ የአለም ሻምፒዮናዋ አትሌት ፅጌ ድጉማ አሰልጣኝ አስቀድሞ የተሰጠው የይለፍ ማለፊያ #እንደተሰረዘበት ገልፆል።
አሰልጣኝ አለሙ ዋቅጅራ “ የአትሌት ፅጌ ድጉማ አሰልጣኝ አይደለህም “ ተብያለሁ ሲል “ ወደ ኢትዮጵያ ተመለስ “ መባሉንም ተናግሯል።
አሰልጣኙ በምክንያትነት ያስቀመጠው የአትሌት ሂሩት መሸሻ መቀነስ ተገቢ አይደለም በማለቱ “ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ቂም በቀል ተነስተው “ ነው ብሏል።
እንቅስቃሴው መገደቡን የገለፀው አሰልጣኙ የራሱን አትሌት ፅጌ ድጉማን እንኳ ለማግኘት መከልከሉን አሳውቋል።
“ ከጓደኞቼ የይለፍ መግቢያ እየተዋስኩኝ እየተቀንቀሳቀስኩኝ እገኛለሁ ፣ ምክንያቱም አትሌት ፅጌ የኔ ቅርብ ክትትል እና ድጋፍ ያስፈልጋታል” አሰልጣኝ አለሙ ዋቅጅራ
በአራት አመት በሚደረገው እና ሀገራችን በጉጉት በምትጠብቀው በዚህ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ልዑክ ከፍተኛ ቅሬታዎች እየተነሱበት ይገኛሉ።
በስፍራው የሚገኘው ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኦሎምፒክ ኮሚቴ እየተነሱ ለሚገኙ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ተቆጥበዋል።
👉
www.melabets.com