“ ለሀገሬ ወርቅ አመጣለሁ ብዬ እየሰራሁ ነው “ ፅጌ ዱጉማ
ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የ 800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር የምትጠበቀው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለሀገሯ ወርቅ ለማስመዝገብ እየሰራች መሆኑን ተናግራለች።
“ በኦሎምፒክ ሀገሬን በመወከሌ ደስ ብሎኛል “ የምትለው አትሌት ፅጌ ዱጉማ “ ለሀገሬ ወርቅ አመጣለሁ ብዬ እየሰራሁ ነው " ስትል ለውድድሩ በትኩረት እየተዘጋጀች መሆኑን ገልፃለች።
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወክለው አትሌት ፅጌ ዱጉማ “ ፈጣሪ ተጨምሮበት ጥሩ ውጤት አመጣለሁ ብዬ በተስፋ እጠብቃለሁ።" ስትል ትናግራለች።
አትሌት ፅጌ ዱጉማ በግላስኮው በተደረገው የ 2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ በርቀቱ ተሳትፋ የወርቅ ሜዳልያ ማሳካቷ አይዘነጋም።