''በዚህ ሁሉ መዓት፡ ሚሊዮኖች ተፈናቅለው፡ ሚሊዮኖች ተርበው፡ ግሽበት ሀገሪቱን እግሯን እያሽመደመደ፡ በየቦታው ግጭትና ዘረፋ በርክቶ አንድ መሪ ቤተመንግስት ልገንባ ካለ ይህ ጥልቅ የሆነ የስነአእምሮ ህመም ነው። ይህ ሰው በጣም ታሟል። '' ከሰሞኑ የአንከር እንግዳ ሆነው የሚቀርቡ የስነልቦና ባለሙያ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ ነው። ወዳጄ ጋዜጠኛ ዘሪሁን ተስፋዬ ስለሰውዬው ሲገልጽ የኡጋንዳውን ሰው በላ መሪ ያስታወሳል። ኤዲያሚን ዳዳ ድንገት የክብር ጠባቂ ጦሩን ይጠራና ታንክ ይዞ ካምፓላ አጠገብ የሚገኝ ተራራ ላይ ይወጣል። ከዚያም ሚዲያዎቹን ጠርቶ 'የጎላን ኮረብታን ተቆጣጥረናል' ሲል ዜና ያስነግራል። አብይ ማለት ኤዲያሚን ዳዳን ቁርጥ ነው። የደቀቀችና የረሃብ ጉንፋን የምታስል ሀገር አናት ላይ ጉብ ብሎ፥ ፓርላማውን ጠርቶ 'ብልጽግናን ጨብጠናል' የሚል ወፈፌ!
https://t.me/mesaymekonnenet
https://t.me/mesaymekonnenet