الشباب السلفيين


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




ከአመታት በፊት በአሕባሽ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በተቀጣጠለበት ወቅት ነው። የሆነ ታዋቂ ሸይኽ አሕባሾችን አጥብቆ ሲኮንን ሰማሁትና
"ግን ለምንድን ነው አሕባሽን የምትቃወሙት?" አልኩት።
"እንዴ ሙሐመድ አሕባሽኮ የጀህምያና የሙርጂ ዐቂዳ አለባቸው። በዚያ ላይ ዑለማዎችን ያከፍራሉ፣ ሶሐባ ይሳደባሉ…" አለኝ።
"እና ለዚህ ነው የምትቃወሟቸው?" አልኩት።
"አዎ!" አለኝ ጫን አርጎ።
"አይመስለኝም" አልኩት።
"እንዴት እንደዚያ ትላለህ?" አለ በግርምት።
"ተመሳሳይ ጥፋት ያለበት ሌላ ሰው ቢኖር ታወግዛላችሁ?" አልኩት።
"አዎ! ጥፋቱ ካለ ከሰውየው ምን አለን?" አለኝ።
"ጥሩ! እንግዲያው ቅድም የተዘረዘሩት የአሕባሽ ጥፋቶች ሰይድ ቁጥብ ላይ ይገኛሉ። ከሱ ታስጠነቅቃላችሁ?" አልኩት።
"አይ" አለና ይቺን አንቀፅ አነበበልኝ:
(تِلْكَ أُمَّةٌ قَدْ خَلَتْ ۖ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَلَكُمْ مَا كَسَبْتُمْ ۖ وَلَا تُسْأَلُونَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ)

"ይህች በእርግጥ ያለፈች ሕዝብ ናት፡፡ ለርሷ የሠራችው አላት፡፡ ለናንተም የሠራችሁት አላችሁ፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት አትጠየቁም፡፡"

"እንዴ! ዐብደላህ አልሀረሪስ በህይወት አለንዴ? ታዲያ ለምን ዝም አንልም?" አልኩት።

"አይ ሰይድ ቁጥብ ብዙ ለኡማው ያበረከተው ነገር አለ" አለኝ።
"ዐብደላህ አልሀረሪንም ተከታዮቹ እንደዚያ ይሉታል" አልኩት።
ከዚህ በሁዋላ ውይይቱን አልቀጠለም። "እስኪ ሌላ ጊዜ እናወራለን" ብሎኝ ተነስቶ ሄደ። ከዚያ በሁዋላ ተገናኝተን አናውቅም። በየሄደበት "መድኸልዮች" እያለ እንደሚያጠለሽ እሰማለሁ። ዛሬ ደግሞ ነፋሱን ተከትሎ አሕባሽን ከመቃወም እንደሚታቀብ እገምታለሁ። ከኖርን እናያለን፣ ኢንሻአላህ። የዥዋዥዌ ጀማዐ አባላት አብይ ባህሪ!!

ኢብኑ ሙነወር( ሀፊዞሁሏህ)

@nuredinal_arebi


ተቃራኒ ፆታን መጨበጥ

ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ በእስልምናችን እንዴት ይታያል?

عن معقل بن يسار يقول : قال رسول الله ﷺ : " لئن يطعن في رأس أحدكم بمخيط من حديد خير له من أن يمس امرأة لا تحل له "
رواه الطبراني في " الكبير " ( 486 ) .والحديث : قال الألباني عنه في " صحيح الجامع " ( 5045 ) : صحيح .

"ከእናንተ አንዳችሁ የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ: አናቱን ከብረት በሆነ ወስፌ ቢወጋ ይሻለዋል"

وعن عروة أن عائشة أخبرته عن بيعة النساء قالت : " ما مس رسول الله ﷺ بيده امرأة قط... " .رواه مسلم ( 1866 ) .

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች:– "የአላህ መልክተኛ ﷺ በፍፁም አጅነቢይ ሴትን ነክተው አያውቁም..."

قال رسول الله ﷺ : " إني لا أصافح النساء إنما قولي لمائة امرأة كقولي لامرأة واحدة " .رواه النسائي ( 4181 ) . وصححه الألباني " صحيح الجامع " ( 2513 ) .

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ግን እንዲህ አሉ “እኔ (አጅነቢይ) ሴቶችን አልጨብጥም፡፡ ለመቶ ሴቶች የምናገረው በተናጠል ለአንዲት ሴት እንደተናገርኩ ነው::”

قال الإمام النووي : ولا يجوز مسها في شيء من ذلك .
" المجموع " ( 4 / 515 ) .

ኢማሙ ነወዊ በአልመጅሙእ
[4 / 515 )] ላይ እንዳሰፈሩት

« አጅነቢይ ሴት የትኛውም አካሏን መንካት አይቻልም»።

لا تجوز المصافحة ولو بحائل من تحت ثوب وما أشبهه والذي ورد بذلك من الحديث ضعيف :

በግርዶሽ (እጃቸው ላይ ጨርቅ በማድረግ) መጨበጥ ሴቶችን መጨበጥ ይቻላል ብለው የሚሉት ዶኢፍ ደካማ መረጃ ይዘው ነው እሱም

عن معقل بن يسار أن النبي ﷺ : " كان يصافح النساء من تحت الثوب " .

“ከእጃቸው ላይ ጨርቅ አድርገው ሴቶችን ይጨብጡ ነበር”

رواه الطبراني في الأوسط ( 2855 ) .
قال الألباني في " السلسلة الضعيفة و الموضوعة " 4 / 337 : ضعيف

قال الشيخ ابن باز – رحمه الله - :
"الأظهر المنع من ذلك ( أي مصافحة النساء من وراء حائل ) مطلقا عملا بعموم الحديث الشريف ، وهو قوله ﷺ : " إني لا أصافح النساء " ، وسدّاً للذريعة" .

( حاشية مجموعة رسائل في الحجاب والسفور صفحة " 69 " بتصرف ) .

ለተጨማሪ ፖስቶች ይህን

@nuredinal_arebi

ሊንክ በመጫን ጆይን ይበሉ።


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከጭፍን ተከታይነት መጠንቀቅ

ከሱንና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው፡፡ የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም፡፡ ዑለማዎቻችንን ስለወደድናቸው ብቻ ንግግራቸውን እንደወረደ አንወስድም፡፡ ይህንን በተግባር ያስተማሩን እራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው፡፡ ለአብነት ያክል የአራቱን አኢማዎች ንግግሮች እዚህ ላይ ላስፍር፡-

[ሀ] አቡ ሐኒፋ ረሒመሁላህ፡-

1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
2. “ከየት እንደወሰድነው ካላወቀ ለማንም አቋማችንን ሊወስድ አይፈቀድለትም፡፡”
3. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው፡፡”
4. “እኛ ሰዎች ነን፡፡ አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን፡፡”
5. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውንﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት፡፡”

[ለ] ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ፡-

1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡

[ሐ] ኢማሙ አሽሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

1. “አንድ የነብዩﷺ ሱንና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱንናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛﷺ ሱንና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛንﷺ ሱንና ተከተሉ፡፡ የኔን ንግግር ተውት፡፡”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
4. “እኔ ከተናገርኩት በተቃራኒ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ከአላህ መልእክተኛﷺ ትክክለኛ ዘገባ የመጣበት ርእስ ሁሉ እኔ በህይወት ሳለሁም ሆነ ሞቼ ከሱ ተመልሻለሁ፡፡”

[መ] ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ፡-

1. “የአውዛዒይ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ፡፡ መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው፡፡”
2. “ማሊክንም፣ ሻፍዕይንም፣ አውዛይን፣ ሠውርይን በጭፍን አትከተል፡፡ እነሱ ከያዙበት ያዝ፡፡”
እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ “ሲፈቱ ሶላት አንነቢይ” ኪታብ መግቢያ አካባቢ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ከማስረጃ ጋር አገናዝበን ሳይሆን የምንወደው ሸይኽ ስለተናገረ ብቻ የምንነፍስበት ጊዜ የለንም? አሁንስ ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ዝግጁ ነን? ለራሳችን እውነተኛ እንሁን፡፡
ከላይ ያለፉትን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል፡፡ የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው፡፡ “ማሊክንም፣ ሻፍዕይንም፣ አውዛይን፣ ሠውርይን በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር አስተውለነዋል? እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ከሆንክ መልሱ አይጠፋህም፡፡ እናም በተመሳሳይ እንበል፡፡
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ኢብኑ ኪሠርንም፣ ዘሀቢንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱርረሕማን ኢብኑ ሐሰንንም፣ ዐብዱልለጢፍ ኣሊ ሸይኽን፣ ሰዕዲንም፣ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ጃሚንም፣ መድኸሊንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ተማሪዎችንም የፈለገ ብትወዳቸው በጭፍን አትከተል፡፡ የሐቅ መለኪያ ሚዛንም አታድርጋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን፡፡
እዚህ ላይ ይህ ፅሑፍ ዑለማን ከማክበርና ትንታኔያቸውን ከመጠቀም ጋር የሚፃረር የሚመስለው ካለ የፅሑፉን መልእክት ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና መጠንቀቅ እንደሚገባ ማሳሰብ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአንዱ ዐሊም ትንታኔ ከሌላው የሚፃረርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም በጭፍን ልንከተል እንደማይገባ የሚያሳይ ነው፡፡ ዛሬ ግን ታላላቅ መሻይኾችን ቀርቶ በአካባቢያቸው የሚገኙ ዝቅ ያሉ አስተማሪዎችን ጭምር በጭፍን በመከተል የወደዱትን የሚወዱ፣ የጠሉትን የሚጠሉ፣ የነኩትን የሚነኩ፣ የፈቀዱትን የሚፈቅዱ፣ የከለከሉትን የሚከለክሉ፣ ያስጠነቀቁትን የሚያስጠነቅቁ ብዙ ናቸው፡፡ የሚከተሏቸው ሰዎች በሆነ ምክንያት አቋም ሲቀይሩም ያለምንም ማገናዘብ ሰልፋቸውን በመቀየር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይሄ ፈፅሞ ሊሆን አይገባም፡፡ አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)


ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ (አሏህ ይዘንለትና) እንዲህ ብሏል ፦

« ﻭﻟﻴُﻌﻠﻢ ﺃﻥَّ ﺍﻟﻤﺆﻣﻦ ﺗﺠﺐ ﻣﻮﺍﻻﺗﻪ ﻭﺇﻥ ﻇﻠﻤﻚ ﻭﺍﻋﺘﺪﻯ ﻋﻠﻴﻚ ، ﻭﺍﻟﻜﺎﻓﺮ ﺗﺠﺐ ﻣﻌﺎﺩﺍﺗﻪ ﻭﺇﻥ ﺃﻋﻄﺎﻙ ﻭﺃﺣﺴﻦ ﺇﻟﻴﻚ ،
ﻓﺈﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ ﺑﻌﺚ ﺍﻟﺮﺳﻞ ، ﻭﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻜﺘﺐ ؛ ﻟﻴﻜﻮﻥ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﻛﻠﻪ ﻟﻠﻪ ، ﻓﻴﻜﻮﻥ ﺍﻟﺤﺐ ﻷﻭﻟﻴﺎﺋﻪ ، ﻭﺍﻟﺒﻐﺾ ﻷﻋﺪﺍﺋﻪ ، ﻭﺍﻹﻛﺮﺍﻡ ﻷﻭﻟﻴﺎﺋﻪ، ﻭﺍﻹﻫﺎﻧﺔ ﻷﻋﺪﺍﺋﻪ ،ﻭﺍﻟﺜﻮﺍﺏ ﻷﻭﻟﻴﺎﺋﻪ ، ﻭﺍﻟﻌﻘﺎﺏ ﻷﻋﺪﺍﺋﻪ »

" ሙዕሚን(አማኝ) የሆነን ሰው ፤ ቢበድልህ እና ድንበር ቢያልፍብህ እንኳ መወዳጀት ፣
ካህዲ(ካፊርን) ደግሞ ፤ (ጥሩን) ቢሰጥህ እና ደግ ነገር ቢውልልህ እንኳ ጠላት መሆን የግድ(ዋጂብ) እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል ፣
(ምክኒያቱም) አሏህ (ጥራት ይገባውና) መልክተኞችን የላከው፣ መፅሃፍትንም ያወረደው ፥ ዲን(ሃይማኖት) ሁሉ ለአሏህ ሊሆን ፤
ውዴታ፣ ክብር እና ደግ ምንዳ ለአሏህ ወዳጆች ፤
ጥላቻ፣ ውርደት እና ቅጣት ድግሞ ለጠላቶቹ ሊሆን ዘንድ ነው። "

[መጅሙዕ አልፈታዋ ጥ 28 / ገ 209]
✍abu fewzan

@nuredinal_arebi






ከወንድማችን☞ ኢብኑሙሐመድዘይን
ሚዛናውይ እንሁን ሌሎች ሰዎች ባጠፉት ጥፋት ዲንና ባልተቤቶቹ ላይ ጭፍን ጥላቻ አይኑረን
ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ )
እንዲህ ይላሉ:-
«የፂም ባልተቤትን ሲዋሽ ካየህው
የፂም ባለቤትን ሲከዳ ካየህው
የፂም ባልተቤትን ሲሰርቅ ካየህው
ነውሩ ያለው በፂሙ ላይ አይደለም
ይልቁንም ነውሩ ያለው በፂሙ ባለቤት ላይ ነው
ፂምማ ነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ካዘዙባት እና ግዴታ ካደረጓት ሱናዎች ናት"
ምንጭ [ኢጃበቱ ሳኢል ገፅ 222]
________________________
_
እኔም አልኩ
የምትዋሽ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
የምትሰረቅ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ዝሙት የምትሰራ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ነገር ከወዳ ወዲህ የምታመላልስ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ሰው የምታማ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ሀያእ የቀለላት ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ነውሩ ያለው በኒቃቡ ላይ ሳይሆን በኒቃብ ለባሿ ላይ መሆኑን እወቅ።
ኒቃብ ለባሾች በሚያጠፉት ጥፋት ኒቃብ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያደረባቸው ብዙ ሰዎች አሉ
እናንተ ኒቃብ ለባሾች ባጠፉት ጥፋት በኒቃብ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያሳደራችሁ ሰዎች ሆይ!
ኒቃብ ለብሰው ከላይ የዘረዘርኳቸውን እና ሌሎችንም ከለበሱት ኒቃብ እና ጅልባብ ጋር ሊሄድ የማይችል ሀያእ የጎደለው እኩይ ተግባር የሚፈፅሞ ዋልጊዎች እንዳሉ ሁሉ
# ኒቃብ ለብሰው ከሀራም የሚጠነቀቁ
የታዘዙትን በቻሉት መጠን የሚተገብሩ
ሀያእ የተሞሉ በጥቅሉ አላህን የሚፈሩ
የአላህ ባሮችም እንዳሉት አትዘንጉ
እኛ ሰውን ግልፅ ባደረገው ነገር ስለሆነ ልናውቀው የምንችለው ኒቃብ የለበሱ እህቶችን ከተገላለጡት የበለጠ ማክበርም መውደድም ይገባናል
ምናልባች ኒቃብ ለብሳ እኩይ ተግባር ስትሰራ ካየናት ኒቃቡን አልያም ኒቃብ ለባሾችን ሳይሆን በጅምላ መወረፍም ይሁን መጥላት ያለበን ያችኑ ኒቃብ ለብሳ እኩይ ተግባር ስሰራ ያየናትን መሆን አለበት።
______________________
_
በጥቅሉ በዲን ዙሪያ በሸሪአ በዟሂር
እንዲተገበሩ የታዘዝነውን ነገር የሚተገብር ሰው የተለያዩ ሀራሞችን ሲፈፅም ካየነው ማውገዝም ሆነ መጥላት ያለብን ያንኑ ሀራም የሰራውን ሰው ብቻ መሆን አለበት።
የጅምላ ጭፍጨፋ አይጥ ባጠፋ ዳዋ ተመታ ነገር አካሄድ ፍትህም አይደለም
ከዚህም አልፎ የአለማቱን ጌታ ቁጣ ሊያመጣብን ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልገናል።

@nuredinal_arebi


አሕባሽ ለሀገር ጥፋት
>>>>>>>>>>>>>>>>>
- በርግጥ ይለምናሉ፡፡ ግን በብዛት በህይወት ያለ ሰው አያስቸግሩም! ከሞተ ሰው ነው የሚለምኑት!(ቡግየቱጧሊብ፡ 8፤ ሶሪሑልበያን፡ 57-58፤ አደሊሉል ቀዊም፡ 173) ወይም ከድንጋይ ነው በረካ የሚፈልጉት!!(ሶሪሑልበያን፡ 58፤ ኢዝሃሩል ዐቂደቲሱኒያህ፡ 244)
- በስራ ቦታዎች ላይሆንላቸው ተፍ ተፍ በማለት የስራ ቦታዎችን አያጨናንቁም፡፡ ይልቅ ጫት ነው የሚቅሙት፡፡ እስኪ ዐስር ሶላት ላይ የማይገኙ የሱፍያ ኢማሞችን ቁጠሩ፡፡ እንግዲህ በየቀኑ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያስገቡትን አስቡት?
- አሕባሽ ለውበት፡- ዐብደላህ አልሀረሪ፡ ሒጃብ የሰውነትን ቀለምና ፀጉርን ከሸፈነ ይበቃል ብሏል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 104(አዲሱ እትም፡137))፤ ተማሪው ኒዛር ሐለቢ፡ ሴቶች ወጣቶቻችን በጂንስ ይዋባሉ፤ ምክኒያቱም እኛ ሰውነትን መሸፈንም ፋሺን መከተልም በተመሳሳይ ጌዜ እናስገኛለን ብሏል(አልሙስሊሙን ጋዜጣ ቁጥር፡407፣ 1992)፤ ሴት ሽቶ ተቀብታ መውጣቷን ፈቅዷል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 351(አዲሱ እትም፡446))
አሕባሽ ሙድ የገባው፡- ከአጅነቢይ ጋር በእጆቻቸው መካከል የሚለይ ነገር አድርጎ መጨባበጥን ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 144)፤ የሴቶችና የወንዶችን መቀላቀል ፈቅዷል(ሶሪሑል በያን፡ 178-179)፤ በስሜት ካልሆነ ሴትን ለረጅም ጊዜም ቢሆን መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡224፣287፣288(አዲሱ እትም፡280፣266፣267))፤ ቤተሰብ ከሆነች ደግሞ ከእንብርት እስከ ጉልበት ካለው ውጭ መመልከት ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡290(አዲሱ እትም ላይ ግን አውጥቶታል)፤ ወንድ ወይም ሴት መሆኑ ከማይለይ ፍናፍንት ጋር በረመዷን ግንኙነት ማድረግ ፆም አያበላሽም(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 192(አዲሱ እትም፡243))፤ ብልት ከተሸፈነ በፓንት ሶላት መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 139)
- አሕባሽ የቴክኖሎጂው ትውልድ፡- የአለም ቅርፅ ላይ አዲስ ግኝት አግኝተው ቂብላ ሊቀይሩ ተውተርትረዋል፡፡
- አሕባሽ ዘመኑን የቀደመ የህክምና ግኝት ባለቤት፡ አንድ በርሜል ውሃ ውስጥ አንዲት ፀጉር ብቻ በመክተትና በመርጨት ለበርካቶች ፈውስ ይሰጣሉ፡፡ ቂቂቂ.. በዚህም ለህክምና የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን በማስወገድ ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ያበረክታሉ፡፡
- አህባሽ ለአእምሮ ንቃት፡- በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100(አዲሱ እትም፡131-132))፡፡ የትኋንና የቅማል ደም ግን ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው ይላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119))፣ ኢስቲንጃን ከውዱእ በኋላ ማድረግ ይቻላል(ቡግየቱ ጧሊብ፡134) ታጥቦ ጭቃ አሉ እማማ እንትና፡፡
- አሕባሽ ለድህነት ቅነሳ፡ ከወረቀት የብር ኖት ዘካ የለም(ቡግየቱ ጧሊብ፡160፣ 169(አዲሱ እትም፡207))
አሕባሽ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት
- የካፊርን ገንዘብ መስረቅ ይቻላል(ካሴት ቁጥር፡2)፣ በቁማር መብላት ይቻላል(ሶሪሑል በያን፡133-134)፡፡ ቢሆንም ችግር በማይፈጥር መልኩ ስለሚሰራ ብዙም የሀገርን ሰላም አያናጋም (እዚጋ ትእምርተ-ስላቅ ጨምራችሁ አንብቡ፡፡ የት እንዳለች ስለማላውቅ ነው)
አሁን ይሄ ነባሩ እስልምና ነው? የት የነበረው?
✍ኢብኑ ሙነወር
@nuredinal_arebi


⇙قال شيخ الاسلام ابن تيمية رحمه الله

الْعَالِمُ يَعْرِفُ الْجَاهِلَ ؛ لِأَنَّهُ كَانَ جَاهِلًا ، وَالْجَاهِلُ لَا يَعْرِفُ الْعَالِمَ ؛ لِأَنَّهُ لَمْ يَكُنْ عَالِمًا

(مجموع الفتاوى 13/235)

⇘ኢብኑ ተይሚያህ አላህ ይዘንላቸውና
አሊም ጃሂል ፟(መሀይምን) ያውቃል ምክናአቱም መጀመሪያ ላይ ጃሂል ሆኖ ስለነበር ጃሂል ግን አሊምን አያውቅም አሊም ሆኖ ስለማያውቅ🌺

@nuredinal_arebi


# ዕውቀት ባለቤቱን ጠባቂ ሲሆን ……… የሃብት ባለቤት ግን ሀብቱን ጠባቂ ነው ።
#ዕውቀት ያለው ሰው ብዙ ጓደኞች ሲኖሩት …… ሃብት ያለው ግን ብዙ ጠላቶች ይኖሩታል ።
# እውቀት በተጠቀሙበት ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ……ሃብት ግን እየመነመነ ይሄዳል

@nuredinal_arebi


የ«ኺላፍ» ጉዳዮች! ባጭሩ..
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
በሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚነሱ ውዝግቦች ሊኖረን የሚገባውን ምልከታ በሁለት ከፍለን ልናይ እንችላለን፦
- በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ሸሪዓዊ ፍርድ በግልጽ ቁርአናዊና ነቢያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የፀደቀ እንደሆነ የትኛውም ዓይነት ውዝግብ የሚስተናገድበት መድረክ አይኖርም፤ ብይኑንም ያለምንም ማንገራገር ተቀብሎ ማስተናገድ የግድ ይሆናል። ይህንን እውነታ ከተረዱ በኋላ በአጀንዳው ላይ ከተመለከተው ሸሪዓዊ አስተምህሮት ጋር የሚጣረስ አቋም ማንፀባረቅ አላህ ከዘረጋልን ቀጥተኛ ጎዳና ማፈንገጥ በመሆኑ ለውግዘት ይዳርጋል!
አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል:—
{ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﺸَﺎﻗِﻖِ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﻣِﻦْ ﺑَﻌْﺪِ ﻣَﺎ ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﻟَﻪُ ﺍﻟْﻬُﺪَﻯ ﻭَﻳَﺘَّﺒِﻊْ ﻏَﻴْﺮَ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻧُﻮَﻟِّﻪِ ﻣَﺎ ﺗَﻮَﻟَّﻰ ﻭَﻧُﺼْﻠِﻪِ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﻭَﺳَﺎﺀَﺕْ ﻣَﺼِﻴﺮًﺍ {
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : 115
«(የ)ምራቻ (መንገድ) ከተገለጠለት በኋላ መልዕክተኛውን የሚፃረርና ከሙእሚኖች መንገድ ሌላ የሚከተል የመረጠውን (ጥመት) እናሸክመዋለን! (ወደ ዞረበት እናዞረዋለን)፤ ጀሀነምም እናስገባዋለን፤ ከመመለሻነቷ (አንፃር)ም የከፋች ሆነች!»
ታዋቂው የኢስላም ጠቢብና ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦
« ﻣَﻦْ ﺧَﺎﻟَﻒَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺍﻟْﻤُﺴْﺘَﺒِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺴُّﻨَّﺔَ ﺍﻟْﻤُﺴْﺘَﻔِﻴﻀَﺔَ ﺃَﻭْ ﻣَﺎ ﺃَﺟْﻤَﻊَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺳَﻠَﻒُ ﺍﻟْﺄُﻣَّﺔِ ﺧِﻠَﺎﻓًﺎ ﻟَﺎ ﻳُﻌْﺬَﺭُ ﻓِﻴﻪِ ﻓَﻬَﺬَﺍ ﻳُﻌَﺎﻣَﻞُ ﺑِﻤَﺎ ﻳُﻌَﺎﻣَﻞُ ﺑِﻪِ ﺃَﻫْﻞُ ﺍﻟْﺒِﺪَﻉِ ..»
«ግልፅ ያለውን (የ)ቁርኣን (አስተምህሮት)፣ የተሰራጨውን ነብያዊ ፈለግ አሊያም የዚህ ህዝበ-ሙስሊም ቀደምት ትውልዶች (በአንድ አቋም) የተስማሙበትን ጉዳይ ይቅርታ ሊደረግለት በማይገባ መልኩ (ዑዝር በማያሰጥ መልኩ) የጣሰ የቢድዓ አንጃዎች በሚስተናገዱበት (እይታ) ይስተናገዳል።»
(መጅሙዑ’ል-ፈታዋ [24/172]).
ለዚህ ክፍል ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ድንጋጌዎች አሉ፤ ከአላህ በቀር ማንንም (የአምልኮ ጥሪ) አለመጣራት፣ የአላህ ስሞችንና ባህሪያቱን መልዕክታቸውን ሳያዛቡ በተገቢው መልኩ ተቀብሎ ማስተናገድ፣ ኢማን መልካም ንግግርንና ተግባርን እንደሚያካትት ማረጋገጥ፣ በቀደር በአግባቡ ማመን…ወዘተ።
በእነኚህ ከእምነት ህልውና ጋራ ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሚሰጠውና ይሁንታ የሚቸረው “ኺላፍ” (ውዝግብ) የለም!
በርግጥ ከመጀመሪያዎቹ ምርጥ ትውልዶች በኋላ ከመጡት የኋለኞቹ ሊቃውንት መካከል አንዳንዶቹ እንደሌሎች ርዕሶች ሁሉ በዚህኛውም ላይ በተለያዩ ምክንያቶችና ተፅዕኖዎች የተነሳ ስህተት ላይ መውደቃቸው ይታወቃል። ይህ አቋማቸው ግን እንደ ስህተት ታይቶ በሌሎች ልሂቃን በአግባቡ ይታረማል እንጂ የቀድሞዎቹን ትውልዶች (ሰለፎች) ስምምነት የሚንድ “ኺላፍ” በፍፁም አይሆንም!
አዎን! እውነትን ፍለጋ ለተሳሳቱ ዓሊሞች የሚሰጠው ማስተካከያ ክብራቸውን በሚጠብቅ ስርዓትና ሂደት እንጂ በቢድዓ አራማጅ ጎጠኞች ላይ እንደሚደርሰው ውግዘት አይደለም! ሆኖም ስህተት ማንም ይስራው ማን ሁሌም ስህተት ነው! ስህተት ሁሉ ደግሞ የመደበኛ «ኺላፍ» ሚዛን ላይ አይሰቀልም፤ አጀንዳው በግልጽ ቁርአናዊና ነብያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የተዘጋ የአንድነት ርዕስ እንጂ የኺላፍ ርዕስ አይደለምና! አለበዚያ ማንም በዲን ስም ያሻውን አቋም ያለተቃውሞ እንዲያራምድ ሰፊ በር መክፈት ይሆንብናል!
ስለሆነም እንዲህ የፀኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን እንደ “ተራ የኺላፍ ርዕስ” ወይም እንደ “ፍሬ-አልባ ውዝግብ” መቁጠር የቀደምት ምርጥ ትውልዶችንና ተተኪ መሪዎችን የክፍለ-ዘመናት ልፋት፣ ገድልና መስዋትነትን ከንቱ ማድረግና አደራቸውንም መብላት መሆኑን ማወቅ ያሻል!
- በርዕሶቹ ላይ የሚጠቀሱት ማስረጃዎች የሚጠቁሙትን መልዕክት በተመለከተ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት በግንዛቤ ልዩነት የተለያየ አቋም ያንጸባረቁ ከሆነና ጉዳዮቹ በዑለማዎች ዘንድ ሸሪዓዊ ምልከታን (“ኢጅቲሃድ”ን) የሚያስተናግዱ መሆናቸው የታወቀ እንደሆነ አንድ ዓሊም ከዚህ በፊት ከነበሩት የዑለማዎች አቋሞች አንዱን ቢመርጥ፣ ብሎም ቢሳሳት ፍርዱ እንደሙሉ ጥፋት ተወስዶ አይኮነንም፤ መልዕክተኛው ( ﷺ ) እንደዚህ ብለዋል፦
« ﺇِﺫَﺍ ﺣَﻜَﻢَ ﺍﻟْﺤَﺎﻛِﻢُ ﻓَﺎﺟْﺘَﻬَﺪَ، ﺛُﻢَّ ﺃَﺻَﺎﺏَ ﻓَﻠَﻪُ ﺃَﺟْﺮَﺍﻥِ، ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺣَﻜَﻢَ ﻓَﺎﺟْﺘَﻬَﺪَ، ﺛُﻢَّ ﺃَﺧْﻄَﺄَ ﻓَﻠَﻪُ ﺃَﺟْﺮٌ »
«አንድ ፈራጅ ሲፈርድ (እውነታን ለመረዳት) ተጣጥሮ ትክክል ከሆነ ሁለት ምንዳ (አጅር) አለው፤ ሲፈርድ (እውነታን ለመረዳት) ተጣጥሮ ከተሳሳተ ደግሞ አንድ አጅር አለው!»
[አል-ቡኻሪይ (7352) ፣ ሙስሊም (1716)]
ሆኖም የላይኛው ሐዲሥ እንደሚያስረዳው በዚህኛውም ርዕስ ላይ ቢሆን እውነትን ለማወቅ ሁሉም እንደየአቅሙ መጣር ይጠበቅበታል።
አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን!
ኡሥታዝ ኢልያሥ አህመድ

@nuredinal_arebi


ኢብኑል ቀይም:
ልዩ የክረምት ትምህርት በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር


«من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين» رواه البخاري ومسلم

«አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል» ቡኻሪና ሙስሊም

መርከዙ ላይ በጠዋቱ ፈረቃ በተለያዩ ክፍሎች ተመድበው ከሚሰጡት ትምህርቶች በተጨማሪ ከዝሁር ሰላት በኋላ ከ8:00 እስከ 10:00 የሚቆዩ ተጨማሪ ኮርሶች ተዘጋጅተዋል

ለወንዶች እና ለሴቶች

ሰኞ
1 አቂደቱ አህሉሱና ወል ጀምዓ

በዶክተር አብዱ ኸይሬ

ማክሰኞ
2 ቀዋኢደል ፊቅህ

በኡስታዝ ሐሰን ምሰጋናው

እሮብ
3 አቂደቱል ዋሲጢያ

በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

ሐሙስ
4 ሂልየቱል ጣሊበል ዒልም

በኡስታዝ ጀማል ያሲን


በተጨማሪም በክረምቱ ቁርአን ነዘር ለመቅራት እንዲሁም የተጅዊድ እና የሂፍዝ ትምህርት ለመማር ለሚፈልጉ ወንድ ተማሪዎች 18 አደባባይ በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር በመምጣት መመዝገብ ትችላላቹ
የትምህርት ቀናት
ከሰኞ እስከ ሀሙስ

የትምህርት ሰአት
8 ሰአት እስከ 10 ድረስ

በአላህ ፍቃድ ከላይ ከተጠቀሱት ኮርሶች በተጨማሪ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የሚካሄዱ የኪታብ ቂራአት ኮርሶች ይኖሩናል

1 በኡስታዝ ኢልያስ አህመድ

☞ _አልወረቃት ፊ ኢሱሊል ፊቅህ_

✍🏻 አቡልመዓሊይ አብዱልመሊክ አልጁወይኒይ

☞_ኪታቡ ኢዕቲቃዲ አህሊሱናህ_

✍🏻 አልሀፊዝ አቢበክር አህመድ አል ኢስማዒሊይ (277–371 ዓ.ሒ)

2 በኡስታዝ ጣሀ አህመድ

☞ _አል ወጂዝ ፊ ዓቂደቲሰለፍ_

✍🏻 _አብዱላህ ቢን አብዱልሀሚድ አል አሰሪይ_

3 በኡስታዘ ሙሀመድ ሰኢድ

☞ _አል ኡሱል ወልቀዋኢድ አልፊቅሂያህ_

✍🏻 ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ኡሰይሚን

አላህ ግዜያቸውን ለኢልም ከሚሰጡ፤ ያወቁትንም ከሚተገብሩ ባሮቹ ያድርገን፤ አሚን!

ለሌሎች ሼር በማድረግ ሃላፊነታችንን እንወጣ

ለበለጠ መረጃ
ነሲሀ የዕውቀት ማዕድ
https://t.me/nesihaposts


ከሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን ማእድ ይቋደሱ፡፡
1. ከቢድዐ እና ከጥመት ሰዎች ማስጠንቀቅ የተወገዘ ሃሜት
ነውን፡፡ ፈውዛንን ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/TWVEgRFRnA
2. ፈውዛን “ሙብተዲዖችን ዝም ማለትና ከነሱ አለማስጠንቀቅ
ከባድ የሆነ ሙስሊሞችን ማታለል ነው፡፡” ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/uKCeycDIvj
3. ከድሮዎቹና ከበዘመናዊ አንጃዎች ማስጠንቀቅ ፊትና
የሚፈጥር ነውን፡፡ ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/CVyqiwWFUO
4. ከሙብተዲዕ የሚያስጠነቅቁ ሰዎችን የሚተችና ከነሱ
የሚያስጠነቅቅ ሰው ብይኑ ምንድን ነው፡፡ ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/WZdGnEQGGE
5. ከተፃራሪዎች ማስጠንቀቅ በተመለከተ ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/uAPSpnplvJ
6. ፈውዛን “ከቢድዐ ዝም የሚል ሰው ዳዒያህ አይሆን፡፡”
ምከዚህ ያዳምጡ
7. http://t.co/9MZgr8A5bv
8. ፈውዛን ስለተብሊጎች፣ ኢኽዋኖች፣ ሰይድ ቁጥብ፣ ሐሰን
አልበና እና ጧሪቅ አስሱወይዳን ሲናገሩከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/RXBLBpOMYg
9. ፈውዛን ከኡሳማ ቢን ላደን ሲያስጠነቅቁ፡፡ ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/IyloTKUhix
10. ፈውዛን ከኢኽዋኒው ጧሪቅ አስሱወይዳን በስም
ሲያስጠነቅቁ፡፡ ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/lJbyfXUuOL
11. ፈውዛን ከዐብዱላህ አልሙጥለቅ ሲያስጠነቅቁ፡፡ ከዚህ
ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/vijhJfVVYQ
1.0. ፈውዛን “ከተክፊሮች የሚከላከል እንደነሱው ተክፊሪ
እንደሆነ አድርሱ፡፡” ከዚህ ያዳምጡ
http://www.safeshare.tv/w/QIuDdvQfsX
👇👇👇👇
📌📌ለቴሌግራም ይህን ይጫኑ

@nuredinal_arebi

https://t.me/joinchat/AAAAAFBtjlYSOyBktjK77Q
👇👇👇

ለዋትሳፕ ይህን ይጫኑ
https://chat.whatsapp.com/99eZfbtHxIzHgl1F2Hd8Ko📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌


አቂዳችነን ከሰለፎች እንደምንወስድ ሁሉ አኽላቃችነንም ከሰለፎች እንውሰድ።
ያረቢ አኽላቃችነን አሳምርልን።


Репост из: ኢብኑል ቀይም
ቁርኣን ህይወት ነው
ቁርኣን መመሪያ ነው
ቁርኣን ብርሃን ነው
ቁርኣን መድኃኒት ነው
ቁርኣን መከበሪያ ነው

እነዚህ ከቁርኣን መገለጫዎች የተወሰኑት ናቸው። በማንበብ፣ በመረዳት፣ በመማርና በመተግበር ከርሱ ጋር ጓደኝነቱን ያጠናከረ እርሱ እድለኛና ስኬታማ ነው።

@Ibnul_qeyem




Репост из: قناة الـعــــلـــم
بشرى.لطالب.العلم.tt

انشرالعلم
وانشروا القنوات التي تنشرالعلم





Показано 20 последних публикаций.

329

подписчиков
Статистика канала