የ«ኺላፍ» ጉዳዮች! ባጭሩ..
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
በሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚነሱ ውዝግቦች ሊኖረን የሚገባውን ምልከታ በሁለት ከፍለን ልናይ እንችላለን፦
- በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ሸሪዓዊ ፍርድ በግልጽ ቁርአናዊና ነቢያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የፀደቀ እንደሆነ የትኛውም ዓይነት ውዝግብ የሚስተናገድበት መድረክ አይኖርም፤ ብይኑንም ያለምንም ማንገራገር ተቀብሎ ማስተናገድ የግድ ይሆናል። ይህንን እውነታ ከተረዱ በኋላ በአጀንዳው ላይ ከተመለከተው ሸሪዓዊ አስተምህሮት ጋር የሚጣረስ አቋም ማንፀባረቅ አላህ ከዘረጋልን ቀጥተኛ ጎዳና ማፈንገጥ በመሆኑ ለውግዘት ይዳርጋል!
አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል:—
{ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﺸَﺎﻗِﻖِ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﻣِﻦْ ﺑَﻌْﺪِ ﻣَﺎ ﺗَﺒَﻴَّﻦَ ﻟَﻪُ ﺍﻟْﻬُﺪَﻯ ﻭَﻳَﺘَّﺒِﻊْ ﻏَﻴْﺮَ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻧُﻮَﻟِّﻪِ ﻣَﺎ ﺗَﻮَﻟَّﻰ ﻭَﻧُﺼْﻠِﻪِ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﻭَﺳَﺎﺀَﺕْ ﻣَﺼِﻴﺮًﺍ {
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : 115
«(የ)ምራቻ (መንገድ) ከተገለጠለት በኋላ መልዕክተኛውን የሚፃረርና ከሙእሚኖች መንገድ ሌላ የሚከተል የመረጠውን (ጥመት) እናሸክመዋለን! (ወደ ዞረበት እናዞረዋለን)፤ ጀሀነምም እናስገባዋለን፤ ከመመለሻነቷ (አንፃር)ም የከፋች ሆነች!»
ታዋቂው የኢስላም ጠቢብና ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦
« ﻣَﻦْ ﺧَﺎﻟَﻒَ ﺍﻟْﻜِﺘَﺎﺏَ ﺍﻟْﻤُﺴْﺘَﺒِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟﺴُّﻨَّﺔَ ﺍﻟْﻤُﺴْﺘَﻔِﻴﻀَﺔَ ﺃَﻭْ ﻣَﺎ ﺃَﺟْﻤَﻊَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺳَﻠَﻒُ ﺍﻟْﺄُﻣَّﺔِ ﺧِﻠَﺎﻓًﺎ ﻟَﺎ ﻳُﻌْﺬَﺭُ ﻓِﻴﻪِ ﻓَﻬَﺬَﺍ ﻳُﻌَﺎﻣَﻞُ ﺑِﻤَﺎ ﻳُﻌَﺎﻣَﻞُ ﺑِﻪِ ﺃَﻫْﻞُ ﺍﻟْﺒِﺪَﻉِ ..»
«ግልፅ ያለውን (የ)ቁርኣን (አስተምህሮት)፣ የተሰራጨውን ነብያዊ ፈለግ አሊያም የዚህ ህዝበ-ሙስሊም ቀደምት ትውልዶች (በአንድ አቋም) የተስማሙበትን ጉዳይ ይቅርታ ሊደረግለት በማይገባ መልኩ (ዑዝር በማያሰጥ መልኩ) የጣሰ የቢድዓ አንጃዎች በሚስተናገዱበት (እይታ) ይስተናገዳል።»
(መጅሙዑ’ል-ፈታዋ [24/172]).
ለዚህ ክፍል ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ድንጋጌዎች አሉ፤ ከአላህ በቀር ማንንም (የአምልኮ ጥሪ) አለመጣራት፣ የአላህ ስሞችንና ባህሪያቱን መልዕክታቸውን ሳያዛቡ በተገቢው መልኩ ተቀብሎ ማስተናገድ፣ ኢማን መልካም ንግግርንና ተግባርን እንደሚያካትት ማረጋገጥ፣ በቀደር በአግባቡ ማመን…ወዘተ።
በእነኚህ ከእምነት ህልውና ጋራ ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሚሰጠውና ይሁንታ የሚቸረው “ኺላፍ” (ውዝግብ) የለም!
በርግጥ ከመጀመሪያዎቹ ምርጥ ትውልዶች በኋላ ከመጡት የኋለኞቹ ሊቃውንት መካከል አንዳንዶቹ እንደሌሎች ርዕሶች ሁሉ በዚህኛውም ላይ በተለያዩ ምክንያቶችና ተፅዕኖዎች የተነሳ ስህተት ላይ መውደቃቸው ይታወቃል። ይህ አቋማቸው ግን እንደ ስህተት ታይቶ በሌሎች ልሂቃን በአግባቡ ይታረማል እንጂ የቀድሞዎቹን ትውልዶች (ሰለፎች) ስምምነት የሚንድ “ኺላፍ” በፍፁም አይሆንም!
አዎን! እውነትን ፍለጋ ለተሳሳቱ ዓሊሞች የሚሰጠው ማስተካከያ ክብራቸውን በሚጠብቅ ስርዓትና ሂደት እንጂ በቢድዓ አራማጅ ጎጠኞች ላይ እንደሚደርሰው ውግዘት አይደለም! ሆኖም ስህተት ማንም ይስራው ማን ሁሌም ስህተት ነው! ስህተት ሁሉ ደግሞ የመደበኛ «ኺላፍ» ሚዛን ላይ አይሰቀልም፤ አጀንዳው በግልጽ ቁርአናዊና ነብያዊ አስተምህሮቶች የተቋጨና በቀደምት ዑለማዎች ሙሉ ስምምነት የተዘጋ የአንድነት ርዕስ እንጂ የኺላፍ ርዕስ አይደለምና! አለበዚያ ማንም በዲን ስም ያሻውን አቋም ያለተቃውሞ እንዲያራምድ ሰፊ በር መክፈት ይሆንብናል!
ስለሆነም እንዲህ የፀኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን እንደ “ተራ የኺላፍ ርዕስ” ወይም እንደ “ፍሬ-አልባ ውዝግብ” መቁጠር የቀደምት ምርጥ ትውልዶችንና ተተኪ መሪዎችን የክፍለ-ዘመናት ልፋት፣ ገድልና መስዋትነትን ከንቱ ማድረግና አደራቸውንም መብላት መሆኑን ማወቅ ያሻል!
- በርዕሶቹ ላይ የሚጠቀሱት ማስረጃዎች የሚጠቁሙትን መልዕክት በተመለከተ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት በግንዛቤ ልዩነት የተለያየ አቋም ያንጸባረቁ ከሆነና ጉዳዮቹ በዑለማዎች ዘንድ ሸሪዓዊ ምልከታን (“ኢጅቲሃድ”ን) የሚያስተናግዱ መሆናቸው የታወቀ እንደሆነ አንድ ዓሊም ከዚህ በፊት ከነበሩት የዑለማዎች አቋሞች አንዱን ቢመርጥ፣ ብሎም ቢሳሳት ፍርዱ እንደሙሉ ጥፋት ተወስዶ አይኮነንም፤ መልዕክተኛው ( ﷺ ) እንደዚህ ብለዋል፦
« ﺇِﺫَﺍ ﺣَﻜَﻢَ ﺍﻟْﺤَﺎﻛِﻢُ ﻓَﺎﺟْﺘَﻬَﺪَ، ﺛُﻢَّ ﺃَﺻَﺎﺏَ ﻓَﻠَﻪُ ﺃَﺟْﺮَﺍﻥِ، ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺣَﻜَﻢَ ﻓَﺎﺟْﺘَﻬَﺪَ، ﺛُﻢَّ ﺃَﺧْﻄَﺄَ ﻓَﻠَﻪُ ﺃَﺟْﺮٌ »
«አንድ ፈራጅ ሲፈርድ (እውነታን ለመረዳት) ተጣጥሮ ትክክል ከሆነ ሁለት ምንዳ (አጅር) አለው፤ ሲፈርድ (እውነታን ለመረዳት) ተጣጥሮ ከተሳሳተ ደግሞ አንድ አጅር አለው!»
[አል-ቡኻሪይ (7352) ፣ ሙስሊም (1716)]
ሆኖም የላይኛው ሐዲሥ እንደሚያስረዳው በዚህኛውም ርዕስ ላይ ቢሆን እውነትን ለማወቅ ሁሉም እንደየአቅሙ መጣር ይጠበቅበታል።
አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን!
ኡሥታዝ ኢልያሥ አህመድ
@nuredinal_arebi