#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 4
#እስላማዉ_እይታው👇
#ባይብል_በቁርአን
ክርስቲያኖች ‹‹ቁርዓን መጽሀፍ
"ቅዱስ"ን እውነተኛ ይለዋል›› የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ ተያይዞ ደግሞ የሚቀርበው ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ" ስለ መበረዙ ቁርዓንም ሆነ ሀዲስ እንዲሁም ኢስላማዊ
ምንጮች የሚሰጡት ፍንጭ የለም›› የሚለው ነው፡፡
የመጀመሪያውን አስመልክቶ ባይብል ትክክለኛ ለመሆኑ ኢስላም ይናገራል የሚለው
(በርግጥ የትኛው መጽሀፍ "ቅዱስ" ለማለት እንደፈለጉ አይታወቅም። የኦርቶዶክስ 80 አሀዱ አልያም የካቶሊኮች 73
ወይንም የፕሮቴስታንቶች
66 መጽሀፍ የትኛውን እንደሆነ አይታወቅም ይህ ግን የሚወሰነው እንደምትወያዩት ሰው ማንነት ነው) የተሳሳተ ምልከታ ነው፡፡ ክርስቲያኖች በአንድ ወቅት ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ"›› የተባለ ጥራዝ እንደነበርና ከጊዜያት በኋላ እንደተበረዘ ፣እንደምናምን ያስባሉ ይህ ግን የተሳሳተ አረዳድ ነው፡፡ ቁርዓን ከጅማሮው ‹‹መጽሀፍ "ቅዱስ"››ስለሚባለው ጥራዝ አያወራም፡፡የቆሮንቶስ፤ የማቴዎስ
የሮሜ ወዘተ የሚባሉ ኦሪጅናል መለኮታዊ መጽሀፍት ኖረው ኋላ ተበረዙ የሚል እምነት የለንም፤ መጀመሪያውኑ እነዚህ መጽሀፍት #የግለሰብ_ድርሳናት እንጅ #መለኮታዊ_አልነበሩም፤
ተያይዞ የሚነሳው ‹‹ታዲያ በየትኞቹ ነው የምታምኑት›› የሚለው ነው፡፡
👇
እኛ ሙስሊሞች ለሙሳ በወረደለት ተውራት (ኦሪት) ፤
ለዳውድ በወረደለት ዘቡር (መዝሙር)
እንዲሁም ለኢሳ በተወረደለት ኢንጅል (ወንጌል) እናምናለን፡፡
እነዚህ መለኮታዊ መጽሀፍት አሁን ክርስቲያኖች ‹‹መጽሀፍ ቅዱስ›› ብለው በሰየሙት መጽሀፍ ውስጥ የሚፈልጉትን መርጠው ያካተቷቸው ቢሆንም
ኦሪጅናልነታቸውን አጥተው የሰው እጅ ገብቶባቸዋል፡፡ ጥቂት ከብረዛ የተረፉ መለኮታዊ ቅሪቶች ቢኖሩም በይዘት ደረጃ ግን ጥቅል በሚባል አገላለጽ የተበረዙ ናቸው፡፡
ኦሪጅናሉን ከተበረዘው ለይተን የምናውቅበትን መፅሃፍ ከሺ አመታት በፊት ወርዶልናል።
አዎ ቁርአን በባህሪው ያለፉትን መለኮታዊ መፅሃፍት የያዙትን እውነት የሚገልፅ የተበረዘውን ከእውነቱ የሚለይ አረጋጋጭና ተጠባባቂ መፅሃፍ ነው።
ያለፉት መለኮታዊ መፅሃፍቶች ጊዜያቸውን ጨርሰው በቁርአን ኪዳን ዘግተውታል።
ልክ…
«ፀሃዮዋ ወጥታለች ኩራዝህን አጥፋ»እንደተባለው።
Quran
👉 #The_last_testment👈
በአጠቃላይ ቁርአን ላይ ኢንጂል ፣ዘቡር፣ተውራት ብሎ ሲያወራ አንድናአንድ የሚያመለክተው ከላይ የወረዱትን ነው።
- «…ለዳውድም ዘቡርን #ሰጠነው፡፡»4፡163
«…ተውራትና እንጂልንም #አውርዷል»3:3
📌ለነማቴዎስ ሉቃስ… ወዘተ ከላይ #አልወረደላቸውም_ከታች በራሳቸው ነው የፃፉት።
"ተህሪፍ"
2- የአረብኛ ‹‹ተህሪፍ›› አገላለጽ
ይህ ተህሪፍ የሚለው ቃል ቁርዓን ውስጥ በይበልጥ አይሁዶችና ክርስቲያኖች መጽሀፋቸውን
እንደበረዙ በሚያትቱ ቦታዎች ውስጥ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ‹‹ተህሪፍ›› የሚለው ቃል ‹‹ብዕርን
በመጠቀም አንድን ቃል ወደ ሆነ አቅጣጫ #ማዘመም_(መቀየር)›› እንዲሁም ‹‹#ለራስ_ስሜት
በሚመች መልኩ ቃላትን #መጠምዘዝ›› የሚሉ
ፍችዎች አሉት፡፡
(አርረጊብ አለኢስፈሃኒ፣
አልሙፋራዳት ፊ ገሪቢል ቁርዓን ጥራዝ 1 ገጽ 122)
በተመሳሳይ አሸህራሳታኒ ስለተህሪፍ ምንነት
ሲገልጹ ‹‹የተጻፈን ቃል #የተዛባ_ትርጉም ይሰጥ
ዘንድ መቀየር›› በሚል ያስቀምጡታል፡፡ ይህን
አገላለጽ ሸይሁል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እቅቲዳአ ሲራጠል ሙስተቂም ሙኻለፈት
አስሀበል ጃሂም ገጽ 8 ላይ በመግለፅ ይጋሩታል፡፡⬇️
‹‹በቋንቋ ደረጃ - መለወጥ ወይንም #ማዛባት የሚል
ፍቺ ሲኖረው ቴክኒካል ፍችው ደግሞ ጹሁፍን በቃልም ይሁን በትርጉም ደረጃ #መቀየር የሚል
ነው››
📚 (Shaikh ul-Islaam Ibn Taymiyyah,
Creed of Hamawiyyah - Chapter 3: The
Way of Ahl us-Sunnah Concerning
Allaah's Attributes
ስለዚህም በዚህ ተህሪፍ በሚለው አገላለጽ ቁርዓን በግልጽ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ቅዱሳን
መጽሀፍትን በጹሁፍ ደረጃ ሳይቀር
መልእክታቸውን ያዛቡ እንደነበር ጠቁሞናል፡፡
ይህን አስመልክቶ የኢማሙ ማሊክን ሙወጣዕ
በተነተነበት ድርሳኑ አልባጂ እንዲህ ያብራራዋል፡፡
‹‹ እነሱ (አይሁዶች) ቃላትን አላህ ካስቀመጠበት ቦታ ውጭ #ይለውጡ ነበር በዚህም አሰላሙ አለይኩም (ሰላም በናንተ ላይ ይሁን) ማለት ሲገባቸው/ ሲኖርባቸው አሳሙ አለይኩም (ሞት በናንተ ላይ ይሁን) ይሉ ነበር››
📚 አል ሙንተቃ ሸርህ ሙወጣዕ
ማሊክ፣ ኪታብ አል ጃሚዕ ባብ ማጃዐ ፊ አሰላም አለል የሁዲ ወነስራኒ ለሀዲስ ቁጥር 1514
የተሠጠው ማብራሪያ
አል ባጂ በዚህ ማብራሪያቸው እንደሚገልጹት
አይሁዶች ‹‹አሰላሙ አለይኩም›› በሚለው ፈንታ
‹‹አሳሙ አለይኩም›› የሚለውን ቃል በመጠቀም ትርጉሙን ብቻ ሳይሆን ቃሉንም ይቀይሩ እንደነበር ነው፡፡ ከዚህም እንደምንረዳው ይቀይሩ የነበሩት ትርጓሜ ብቻ ሳይሆን ቃልንም ጭምር እንደሆነ ነው፡፡
ይጥላል።
Join now. and share to all!
ሊንኩ ይኸው
https://t.me/joinchat/AAAAAE90idLYrtXA9FQl4g