اسلام عليكم ورحمت الله وبركاته
بــــــــسم الله الرحمان الرحيم.
#ባይብል_አልተበረዘምን?
ክፍል 8
#BONUS
የአሁኑ ባይብል ላለመበረዙ አንድም ዋስትና የለውም። ምናልባት ይህ አንቀፅ ሊነሳ ይችላል።ራእይ 22:18–19
18፤ በዚህ #መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
19፤ ማንምም በዚህ #በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት #ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
እነዚህ አንቀፆች በፍፁም ስለ መፅሃፍ "ቅዱስ" አያወሩም።
1⃣ኛ, «በዚህ_መፅሃፍ…»ሲል የራሱን የራዕይ መፅሃፍ እንጂ ስለ ሌሎቹ በፍፁም አያወራም።
2⃣ኛ, ባይብል ሙሉ ለሙሉ ተዋቅሮ የተዘጋጀው ቆይቶ ነው።
3⃣ኛ,ለባይብል ነው ብንል እንኳ አንቀፁ "ቅጣትና እርግማን ይወርድበታል" አለ እንጂ ፈጣሪ ከመብበረዝ ይጠብቀዋል አላለም።ዋስትና አልገባለትም
🖌ባይብል ያለ ዋስትና ከቀጠለ…
አላህ አያድርገውና…፤ነብዩ ሙሃመድን ሰላም ይስፈንባቸው
በአሉታዊ መልኩ አንቀፅ መጨመሩ አይቀርም።
🖌በአሁን ሰአት ከመቶ አይነት በላይ የሚቆጠሩ የባይብል ቅጂዎች ይገኛሉ።
2ቱን በመውሰድ አነፃፅረን እንመልከት 👇
ኪንግ ጀምስ ቨርዥን KJV(የ1611) ይህ እትም የቅርብ ግዜ ፅሁፎችን ተመስርቶ የተፃፈ ነው።Based on later manuscripts
ሪቪያዝድ ስታንዳርድ ቨርዥን RSV(1952).ይሄ ደግሞ #በጣም ከቆዩ ፅሁፎች ተመስርቶ የተፃፈ ቅጂ ነው።(Based on #most_ancient_manuscripts)
ይህንን ከተረዳን ወዲህ አንድ ምሳሌ ወስደን እናነፃፅራቸው።
1ኛ ዩሃንስ 5:6–8
የ(KJV)ው እንዲህ ይላል።
6: This is he that came by water and blood, even Jesus Christ; not by water only, but by water and blood. And it is the Spirit that beareth witness, because the Spirit is truth.
7: For there are three that bear record in heaven, the Father, the Word, and the Holy Ghost: and these three are one.
8: And there are three that bear witness #in_earth, the Spirit, and the water, and the blood: and these three agree #in_one.
👉ትርጉሙ
6፤ በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
7፤በሰማይም የሚመዘግቡት አባት ቃል እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት ናቸውና ሶስቱም አንድ ናቸው።
8፣ #በምድርም የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም #በአንድ ይስማማሉ።
የሪቫይዝዱ እንዲህ ይነበባል።
6: This is he who came by water & blood, JesusChrist; not with the water only, but with the water & the blood.
👇እዚህ ጋር አንቀፅ7 ይጀምራል።
👉 and the Spirit is the witness, because the Spirit is the truth.
8,and there are 3 witness, the spirit,the water and the blood and these 3 agree.
👉ትርጉሙ
6፤ በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።
👇እዚህ ጋር አንቀፅ 7 ይጀምራል
👉መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
8፤ የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም ይስማማሉ።
❗️አስተውሉ የሪቫይዝዱ ቅጂ በጣም የድሮ ቅጂን ተመስርቶ ነው የተፃፈው።የKJV ግን ቀረብ ባሉ ነው የተፃፈው።
❗️የ KJVው ቅጂ 7ኛ አንቀፅ የ በባይብል ላይ የተሰነቀረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን የደረሱበት የክርስቲያን ሊቃውንት አንቀፁን ከማካተት ተቶጥበዋል።
በኬጄቪ ቅጂ በ8 ኛው አንቀፅ ላይ ደግሞ #በምድርም እና #በአንድ የሚሉ አዲስ ቃላት ተጨምሯል።
❗️ሪቫይዝዱ እነዚህን ከመጨመር ታቅቧል።የአምላክን «አንድም ሶስትምነት» የሚገልፀው ይኽው የ ኬጄቪ ቅጂ 7ኛ አንቀፅ በሌሎችን ቅጂዎች ውስጥ አይገኝ ም።በ The New International Version 1984,The New American Bible 1986,The Living Bible 1971,The New Jerusalem Bible 1985,The New English Bible 1972, The American Standard Version 1901,The New American Standard Bible 1977,The Good News Bible (TEV) 1971
🖌ማርቆስ 16፣15«እንዲህም አላቸው፡— ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
ይህ አንቀጽ አዲስ የተጨመረ እንጂ በድሮ ባይብል ውስጥ ሰፍሮ አናገኝም፡፡ቀለል ባለ አማርኛ የ1980 እትም መጽሃፍ "ቅዱስ" ከህዳጉ/ከግርጌ/ ማስታወሻ ላይ የተጻፈውን ይመልከቱ፡፡ እንዲህም ይነበባል፡-
«አንዳንድ ቅጂዎችና የጥንት ትርጉሞች ከቁጥር 9-20 ያለውን ክፍል አይጨምሩም፡፡»ይላል።
🖌NRV ቅጂ ላይ ማቴ 17:21
ማቴ 18:11 ማቴ 23:14 ዩሀ 5:4
ተሰርዟል።
🖌KJV ቅጂ ላይ ዩሀ3:16
John 3 (KJV) - ዮሐንስ
16: For God so loved the world, that he gave his only #begotten Son,ሌሎች ቅጂዎች" #begotten"የሚልቃል ከመጨመር አሁንም ታቅበዋል።
ቃሉ በጣም አሳፋሪ ነው። ቢጋትን የሚለው ቃል በግብረ ስጋ ግንኙነት ለተገኘ ነገር ለመጠቆም የሚያገለግል ቃል ነው።
📌መደምደሚያ
🖌የአንድ እምነት ምሰሶ…እምነቱን የሚመራበት መፅሃፍ ነው። መፅሃፉ ከሰው እጁ ተጠብቆ ይቆይ ዘንድ ከፈጣሪ ዋስትና ያስፈልገዋል።ለመጠበቁ ዋስትና ከሌለው እምነቱን ያፈራርሰዋል።
የመጨረሻው የአምላክ ኪዳን
ቁርአን ብቻ ነው።
በአላህ ፍቃድ ተጠናቀቀ።
👉REMEBER,THE LAST TESTMENT IS QURAN❗️👈
Join and share to all.👇
@only_islam1