ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


በዚህ channel ውስጥ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና የየዕለቱን ስንክሳር ያገኛሉ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций
















✞እንኳን አደረሳችሁ!


(በዓለ ማርያም ድንግል)

❖ወላዲተ ክርስቶስ እግዚእ
❖ጸዋሪተ አምላክ ግሩም
❖እመ ብርሃን
❖እመ እግዚአብሔር ጸባዖት
❖እመ #አማኑኤል
❖እመ ንጉሥ
❖እመ ምሕረት . . .

•በዓለ #ጌና ስቡሕ ወውዱስ!

✝ ኦ ማርያም! በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ::
እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን::
ወስቴ ሕይወት ዘበአማን:: ✝ (አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ)

" ማርያም (እመቤታችን) ሆይ! ስለዚህ ነገር እንወድሻለን::
ከፍ ከፍ እናደርግሻለን::
የጽድቅ መብልን : የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና:: "

✝እናከብርሻለን !
✝እናገንሻለን !
✝ለክብርሽም እንገዛለን !

✝ የአምላክ እናት ጣዕሟ : ጸጋዋ : በረከቷ ሁሉ በዝቶ ይደርብን !!

👉 እምዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ(ገብረ መድኅን)


✝✞✝ ኦ! ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት::
ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ:: #ድንግል_ወለደቶ_ለገባሪሃ:: ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ . . . ✞✝

👉 ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል!
🌿 ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው::
📜 ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው::
✝ እርሱም_እናቱን_ፈጠረ:: ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ::
✝ ተዋርዶ በእኛ ባሕርይ ተወለደ::
✝ እርሱም እኛን ስለ መውደዱ ፈጠረን::

📜 ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ #ኤፍሬም_ሶርያዊ ቁ. 2






ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፳፰

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሃያ ስምንት በዚች ዕለት የገና በዓል ሆነ ይኸውም የልደት በዓል ነው።


   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
        ዕለተ ጌና በዓል
   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ይህም እንዲህ ነው በአምላካችን በረቀቀ ጥበቡ ሰዎች ሁሉ ይቈጠሩ ዘንድ ስማቸውንም ይጻፉና ይመዘገቡ ዘንድ ከንጉሥ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ፤ ስለዚህም ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም ጋር ሊቈጠር ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም የርሱንና የቡርክት ድንግል ማርያምንም ስም ሊአስመዘግብ ወጣ፤ እርሱ ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ወገን ነውና ቤተልሔምም የዳዊት ቦታው ናትና።

❖ የከበረ ወንጌል እንደተናገረ ከዚህም በኋላ ከዚያ ሳሉ የምትወልድበት ቀን ደረሰ የበኲር ልጅዋንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሠረችው በጨርቅም ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ለማደሪያቸው ቦታ አልነበራቸውምና።

❖ በዚያም ሰፈር እረኞች ነበሩ ሌሊቱንም በየተራቸው ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ አጠገባቸው ቆመ የእግዚአብሔርም ብርሃን በላያቸው በራ ታላቅ ፍርሀትንም ፈሩ መልአኩም ለእናንተና ለመላው ዓለም ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ አላቸው።

❖ እነሆ ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን የሆነ ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋልና፤ ለእናንተም ምልክቱ እንዲህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱን ታሥሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ አላቸው።

❖ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው በጎ ፈቃድ እያሉ መጡ፤ ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ባረጉ ጊዜ እነዚያ እረኞች ሰዎች እርስበርሳቸው ኑ ወደ ቤተ ልሔም ሔደን ይህን እግዚአብሔር የገለጠልንን ነገር እንወቅ አሉ።

❖ ፈጥነውም ሔዱ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝቶ አገኟቸው። አይተውም የነገሩዋቸው ስለዚህ ሕፃን እንደሆነ አወቁ እረኞች የነገሩዋቸውን የሰሙ ሁሉ አደነቁ፤ እረኞችም ለሕፃኑ ሰግደው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቦታቸው ተመለሱ።

ከወገናችን ሰው ሁኖ ለጐበኘንና ይቅር ላለን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

            አርኬ
✍️ሰላም ለበዓለ ጌና ዘኢኮነ ንትጋ። እምልደተ ክርስቶስ ሰዓተ ጸጋ። እስመ አልጸቀት ወበጽሐት ከመ ትለዶ በሥጋ። ዮም ለተጽሕፎ ምስለ ብዙኃን እንግልጋ። ሀገረ ዳዊት ማርያም ዐሪጋ።


   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)
   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ በዚችም ዕለት ደግሞ ከእንዴናው አገር ሰዎች መቶ ሃምሳ ወንዶች ሃያ አራት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ፤ እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ።

❖ ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት፤ በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና።

❖ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ፤ የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው።

❖ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

            አርኬ
✍️ሰላም ለክሙ ማኅበራነ ዕደው ወአንስት። ዘኮንክሙ ስምዐ ዘበሃይማኖት። ነጺረክሙ ገሀደ ግብረ ጳውሎስ ሰማዕት። እምድኅረ መልሕዎ ዐይኖ በዓውደ መኰንን መስሕት። ከመ ኅብረ ገጹ ብሩህ ወዐይኑ ክሡት።


በዚችም ቀን የአባቶቻችን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ መታሰቢያ ነው ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                አርኬ
✍️ሰላም ለክሙ ክቡራን ዕደው። እምዕጓለ እመሕያው። አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ዘዝክርሙ ፍትው። እም ሥጋክሙ መዋቲ ከመ ሥጋ ኲሉ አበው። በሀገረ ዳዊት ዮም ተወልደ ሕያው።


📌 ታኅሣሥ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አማኑኤል አምላካችን
2.በዓለ ጌና ስቡሕ
3.ዕለተ ማርያም ድንግል
4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)

📌 ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

✍️" የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ልጅም ትወልዳለች ፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፤ በነቢይ ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል ፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው"

📖ማቴ 1፥20


ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።

ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።



ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።

እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። 


───────────
                   Channel
 🧲 https://t.me/religious_books_lover






የዕለቱ የወንጌል ክፍል
ዮሐንስ 10:1-22

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኩል የሚ ገባ ሌባ፥ ወንበዴም ነው። በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍ ትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እር ሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አው ጥቶም ያሰማራቸዋል። 'ሁሉንም አውጥቶ ባሰ ማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፤ በጎ ቹም ይከተሉታል፤ ቃሉን ያውቃሉና። *ሌላ ውን ግን ይሸሹታል እንጂ አይከተሉትም፤ የሌ ላውን ቃሉን አያውቁምና።” ጌታችን ኢየሱ ስም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገ ራቸውን አላወቁም። "ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አላ ቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። #ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦ ችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ነገር ግን፣ በጎች አልሰሙአቸውም። እውነተኛዉ የበጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩልም የሚገባ ይድናል፤ ይገ ባልም ይወጣልም፤ መሰማርያም ያገኛል። ፤ሌባ ግን ሊሰርቅና ሊያርድ፥ ሊያጠፋም ካልሆነ በቀር አይመጣም፤ እኔ ግን የዘለዓለም፤ ሕይ ወትን እንዲያገኙ፥ እጅግም እንዲበዛላቸው መጣሁ። “ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። "ጠባቂ ያይደለ፥ በጎ ቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵ ላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋ ልም። "ምንደኛስ ይሸሻል፤ ስለ በጎቹም አያ ዝንም፤ ምንደኛ ነውና። "ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን መንጋዎቼን አውቃለሁ፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል። አብ እኔን እንደሚያው ቀኝ እኔም አብን አውቀዋለሁ፤ ለበጎችም ቤዛ አድርጌ ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ። "ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነር ሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ። ”ስለዚህም፤ አብ ይወድደ ኛል፥ እንደ ገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰ ጣለሁና። *ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ ነገር ግን እኔ በፈቃዴ እሰጣታለሁ፤ እኔ ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ እወስዳት ዘንድ ሥልጣን አለኝና፤ ይህንም ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበ ልሁ።” አይሁድ ለሁለተኛ ጊዜ ስለ መለያየታቸው "ስለዚህም ነገር አይሁድ እንደገና እርስ በር ሳቸው ተለያዩ። “ከእነርሱም ብዙዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብዳል፤ ለምንስ ታዳምጡታላችሁ?” አሉ። ሌሎችም ይህ ነገር ጋኔን ከያዘው ሰው የሚገኝ አይደለም፤ ጋኔን የዕዉሮችን ዐይን ማብራት ይችላልን?” አሉ..........

👉ዕብራውያን 13:16-ፍጻሜ
👉1 ጴጥሮስ 2:21-ፍጻሜ
👉ሐዋ.ሥራ 11:22-ፍጻሜ

👉ቅዳሴ ዘእግዚእነ

ምስባክ
መዝሙር 78:1-2

ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ለእስራኤል አጽምዕ

ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ


ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርእየ


📌 ታኅሣሥ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

 1.ቅዱስ አብሳዲ ሰማዕት
2.አባ አላኒቆስ ሰማዕት
3.አባ በግዑ ጻድቅ
4.አባ ፊልዾስ

📌 ወርኀዊ በዓላ

 1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

✍️"መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል፤ እላችሁአለሁ እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆና

ል" 📖ሉቃ 15፥3-
7

ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተ
ርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ
ሕፃን።
 ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክ

ርስቶስ።
ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋ

ና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ
ቦታ ባርኩ።
 ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ

ነት ይማረን።

https://t.me/religious_books_lover


በዚችም ዕለት የአባ በግዑና የአባ ፊልጶስ የሰማዕታት ፍጻሜ የሆነ የኖላዊ መታሰቢያቸው ነው። የመድኃኒታችንም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አባ በግዑ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ አባ በግዑ በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፤ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፤ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው ሀገር ይገባል፡፡
❖ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፤ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፤ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፤ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡
❖ በእንደዚህ ያለ የውንብድና ሥጋ ብዙ ዓመታት ከኖረ በኋላ አባ በግዑ በስም ክርስቲያን ነበረና ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንፈስ አነሳስቶት ወደ ቤተክርስቲያን ሄደ፤ ካህኑም ባየው ጊዜ ከመንገድ ገለል አደረገውና
✍‹‹የሕይወት ዘመንህን ሁሉ በከንቱ አሳለፍክ ዛሬ ስማ ልንገርህ፣ በዘመንህ ፍጻሜ እግዚአብሔር ይጎበኝሃል፣ በመንፈስ ቅዱስም ያድርብሃል፣ ፍጹም መነኩሴ ትሆናለህ፣ በብዙ መከራና ተጋድሎ ትኖራለህ በዚያም የነፍስህ መዳኛ ይሆናል፣ እግዚአብሔርንም ደስ ታሰኘዋለህ›› አለው፡፡

❖ ከዚህም የበዛውን ብዙ ነገር ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ ቁርባን ተቀበለ፤ ወደ ቤቱም ከተመለሰ በኋላ ካህኑ የነገሩትን እያሰበ
✍‹‹እስከመቼ በስንፍናዬ እኖራለሁ እስከመቼስ የነፍሴን መዳኛ ሳላስብ እኖራለሁ …›› እያለ አሰበ፡

፡ ❖ ከዚህም በኋላ ከዘመዶቹ ተለይቶ ከሀገሩ ወጥቶ ሄደና ወደ ባሕር ዳርቻ ደርሶ የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተክርስቲያን እጅ ነሣ፤ ከመነኮሳትም ማኅበር ገብቶ እነርሱን ማገልገል ጀመረ፡፡
❖ ዓቢይ ጾም ሲመጣም ከሰኞ እስከ ቀዳሚት ሰንበት ምንም ሳይቀምስ የሚጾም ሆነ፤ ውኃንም ሳይጠጣ ኖረ ማንም ሰው ሳያውቅብ ለ5 ወር ምንም ውኃ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡
❖ ከ5 ወር በኋላም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ አባ በግዑ መጣና ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሰላም ለአንተ ይሁን በምን ትታወካለህ ምንስ ያሳዝንሃል ››አለው፤ አባ በግዑም ‹‹ጌታዬ ከውኃ ጥም የተነሣ በጣም ስለተጨነቅሁ ነው›› አለው፤ መልአኩም ነጥቆ ወደ ገነት ወሰደውና ከገነት ቅጠል አንሥቶ አቀመሰው፤ ወዲያም የአባ በግዑ ሰውነት ታደሰች፡፡
❖ ከዚህም በኋላ ‹‹ውኃ ሳልጠጣ ተጋድሎዬን እፈጽም ይሆን›› የሚለው የኅሊና መታወክ ከእርሱ ጠፋለት፤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ በግዑ ለሚወደው ለአንድ ወዳጁ ለማንም እንዳይናገር በእግዚአብሔር ስም ካስማለው በኋላ ለ5 ወር ምንም ውኃ እንዳልጠጣ ምሥጢሩን ነገረው፤ ያ ወዳጁም ይህን ሲሰማ ደንግጦ አለቀሰ፡፡
❖ አባ በግዑም አብሮት አለቀሰ፤ ወዳጁም ‹‹እስከ ዛሬ ከውኃ የተከለከለ በማን ዘንድ ሰማህ አሁንም ቅዱሳን መነኮሳትና አበ ምኔቱ አያምኑህም፤ ይህን ምሥጢር ዛሬ ብሸሽግ በመጨረሻ ይገለጣል፤ ሕዝቡ ነገሥታቱና መኳንንቱም ይህን ነገር ይሰማሉ ነገር ግን አያምኑም፤ አሁንም የምነግርህን ስማኝና ትኅርምቱን ትተህ ውኃ ጠጣ›› አለው፡፡
❖ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑም ‹‹የነገርከኝ ሁሉ እውነት ነው ሐሰት የለውም ነገር ግን እኔ ከዚህ በኋላ እስክሞት ድረስ ዳግመኛ ውኃ እንዳልጠጣ ስለ እግዚአብሔር ትቻለሁ፤ ሰዎች ባያምኑ እኔ ምን ገዶኝ ነገር ግን በዚህ ገድል እግዚአብሔር ረዳት ይሆነኝ ዘንድ ጸልይልኝ›› አለው፡፡
❖ ‹‹አበ ምኔቱን ጥራልኝ›› አለውና ጠራለት፤ አባ በግዑም አበ ምኔቱ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ሲመጣ በፊቱ ሰገደለትና ‹‹አባቴ ሆይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እፈጽም ዘንደ በላዬ ላይ ጸልይልኝ›› አለው፤ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ከበዓቴ አልወጣም ሰውም ወደኔ አይገባም›› አለው፡፡
❖ አቡነ ኢየሱስ ሞዐም በላዩ ከጸለየለት በኋላ ‹‹ለእኔም ጸልይልኝ›› አለው፤ አባ በግዑም በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን በአባ ኢየሱስ ሞዐ እጅ ቁርባንን ከተቀበለ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በብረት ችንካር ታስሮ ብቻውን ዘግቶ በጽኑ የተጋድሎ ሕይወት ኖረ፤ በዓቱንም ዙሪያውን መውጫ መግቢያ እንዳይኖረው መረገው፤ ለምግብ የሚሆነውን የዛፍ ፍሬና የሜዳ ቅጠል ማስገቢያ የሚሆን ትንሽ ቀዳዳን አበጃና ያ ወዳጁ ያስገባለታል፡፡
❖ መቆምም አይችልም ነበርና መነኮሳቶቹ ለቁርባን በቃሬዛ አድርገው ወደ ቤተክርስቲያን ይወስዱት ነበር፤ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ በእንደዚህ ዓይነቱ ለመስማት በሚከብድ እጅ የበዛ ጽኑ ተጋድሎ ካደረገ ከብዙ ድካም በኋላ በዚህች ዕለት ታህሳስ 27 ቀን ዐረፈ፡፡
❖ ነቢይ ኢሳይያስም የሜዳ ጎመን እየቆረጠ ከእርሱም እየተመገበ ውኃም እየጠጣ በተራራ እየጾመ ኖረ፤ እግዚአብሔር ስሙን ‹የበረሃ ኮከብ› ብሎ የጠራው የመነኰሳት በኩር የሆነ አባ እንጦንስና አባ መቃርስም በደረቅ ኅብስትና በውኃ ብቻ ሲጋደሉ ኖሩ፤ እኚህ ምድራዊያን ሲሆኑ ሰማያውያን ሆኑ፡፡
❖ ነቢይ ኤልያስም በኅብስትና በውኃ ብቻ በምድረ በዳ ሲጋደል ኖረ፤ ይህ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ግን ሰባት ዓመት ሙሉ ውኃ ሳይቀምስ ኖረ፤ ከመነነ በኋላ እስከሞተበት ዕለት ድረስ እህል የሚባል አልቀመሰም፤ እርሱ ግን ራሱን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያደርግና በትህትናም ሆኖ ስለ ኃጢአቱ ሁልጊዜ ያለቅስ ነበር፡፡
❖ ይህም የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ይህን ሁሉ የተጋደለ በራሱ ኃይል አይደለም፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው እንጂ፤ አንተም ወንድሜ ሆይ ራስህን ዕወቅ፤ ምንም ተጋድሎን ብታደርግ ጾምኩ፣ ተራብኩ፣ ስለ እግዚአብሔርም ብዬ ራሴን አደከምኩ፣ እግዚአብሔርንም ስላገለገልኩ በሥራዬም እድናለሁ አትበል፤ መጨረሻህን አታውቅም አንተ ግን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ራስህን ኃጥእ አድርግ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ያጸድቅሃልና፤ ወዳጄ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትመሰገን ራስህን አታመስግን፤ ሌሎችም ያመሰግኑህ ዘንድ አትውደድ፤ ክብር ታገኝ ዘንድ ትሕትናን ገንዘብ አድርግ››
የእግዚአብሔር ሰው የአባ በግዑ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፤ በጸሎት ይማረን...




Репост из: ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
✞ቅዱስ፥ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ✞

✝እንኳን አደረሳችሁ!

"ኦ ጻድቅ፥ ብእሴ እግዚአብሔር አባ #በግዑ፥ አስተምሕር በእንቲአነ ኀበ አምላከ ምሕረት፤
ኦ ገብረ እግዚአብሔር፥ ኄር ወምዕመን፥ ዘሦዕከ ርዕሰከ መሥዋዕተ ለእግዚአብሔር፥ ወተመክዓበ ዕሴትከ እምኀበ እግዚአብሔር።"

"ስብሐት ለአብ ዘአስተዳለወ ንስሓ ለኃጥአን፤
ወሰጊድ ለወልድ ዘጸገወ ዕሴተ ለምዕመናን፤
ወአኮቴት ለመንፈስ ቅዱስ ዘወሀበ ትዕግሥተ ለመስተጋድላን፤
ይእዜኒ ወዘልፈኒ፥ ወለዓለመ ዓለም፤
አሜን ወአሜን፤
ለይኩን ለይኩን!" (ገድለ አባ በግዑ)

ጣዕመ ንስሓውን ያሳድርብን!

ዝክረቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

🛑በቴሌግራም👉
https://t.me/zikirekdusn



Показано 20 последних публикаций.