#ወግ በ #ፍቅር♥️
በድሮ ዘመን ነው አሉ አምላክ ባህርያቶችን በሙሉ ሰብስቦ በአንድ አስቀመጣቸው። እነሱም ፍቅር ፣ እብደት ፣ ውሸት ፣ እውነት ፣ ተንኮል ፣ ቅናት ፣ ትዕቢት ፣ ምቀኝነት ነበሩ።
ከለታት በአንዱ ቀን እነዚ ባህርያት ለምን አኩኩሉ አንጫወትም ብለው ተማከሩ.. ከዚያም እጣ ሲጣል #እብደት ላይ ደረሰ #እብደትም ቆጠራ ጀመረ አ-ኩ-ኩ-ሉ አለ አልነጋም አሉ ባህርያት አ-ኩ-ኩ-ሉ... አልነጋም .... ሁሉም ተደበቁ #ምቀኝነት ሲደናበር ሳይደበቅ ቀርቶ #እብደት አ-ኩ-ኩ-ሉ ሲል #ውሸት ነጋ አለ #እብደት ሁሉ የተደበቁ መስሎት ተነሳ #ምቀኝነት በውሸት ምክንያት ተያዘ አንደኛ ተባለበት… … #እብደት ፍለጋውን ቀጠለ .. መጀመርያ #ምቀኝነትን ከዛ #ትዕቢትን ከዛ #ቅናት .. እያለ ሁሉንም አንድ በአንድ አገኛቸው #ፍቅር ን ግን ሊያገኘው አልቻለም ሁሉም ቦታ ፈለገው ... #ቅናት በፍቅር ቀንቶ ለእብደት በጆሮው ፅጌሬዳ ውስጥ ተደብቋል አለው #እብደትም ቸኩሎ #ፍቅርን ለመያዝ ዘሎ ፅጌሬዳ ውስጥ ሲገባ የፅጌሬዳው እሾህ የፍቅርን አይን ይወጋውና #ፍቅር አይኑ ይታወራል ... ያኔም አምላክ ጩኸት ሰምቶ ሲመጣ የፍቅር አይን መጥፋቱን ያያል ከዚያም #እብደት ይህንን አድርጓልና እስከዘላለም ፍቅርን እንዲመራ #ቅናትም የፍቅር ተገዢ እንዲሆን ፈረደባቸው።
... ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ፍቅር በእብደት መመራት ጀመረ።
……እናም #ያፈቀረ በእብደት ይመራል ማንም ምንም ቢል አይገደውም ... በራሱ አለም በሔደበት ሁሉ ያብዳል .. #እብደት ነፃነት ነውና #ፍቅር በነፃነት ይመራል .. ቅናትንም ለራሱ ያስገዛል ... ሁሉንም ባህርያት እንዲገዙለት ይቻለዋልና
#ፍቅር_ባለበት_ሀይል_ሁሉ_በፍቅር_ይሆናሉ!!
@ba_Jordanos