ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
(በእውቀቱ ስዩም)
" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ: ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ: ታጠበ ሸሚዜ::
ገደብ ጫፍ በሌለው: በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ: ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ: ከፎቅ ላይ አልወድቅም::
በሀኪሙ ስተት :በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ: ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ: እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር: ሽጉጤን አልጠጣም::
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ : ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ: ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ: ከመሞት ምን ሊገኝ?፡
@poems_Essay
(በእውቀቱ ስዩም)
" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ: ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ: ታጠበ ሸሚዜ::
ገደብ ጫፍ በሌለው: በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ: ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ: ከፎቅ ላይ አልወድቅም::
በሀኪሙ ስተት :በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ: ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ: እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር: ሽጉጤን አልጠጣም::
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ : ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ: ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ: ከመሞት ምን ሊገኝ?፡
@poems_Essay