,,,ድርሳነ 'ግጥም' ⁣📚


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ግጥመትና አጫጭር ድርሳኖች በሰፊው ይደርሶታል,,,
'መፅሀፍ አለሜ' 1 @rasnflega

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


👍 #ቆንጆ_ነኝ 😳

"ቆንጆ ነኝ" ባይ ማነሽ....?

በውበትሽ ማርከሽ
ንጉስን ከዙፋን ፥ ማውረድ ሳትችዪ
ማነሽ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፥ አቤት የምትዪ?

ድሮ ድሮ እኮ
የሴት ልጅ ውበቷ ፥ ዙፋንን ያስረሳል
ያንዲት ሴት ቁንጅና ፥ ካንድ ጦር ይብሳል።

ድሮኮ ድሮኮ
መንግስት ህዝብ ላይ ፥ በስልጣን ሲለግም
ከዙፋን ለማውረድ
አንዲት ቆንጆ እንጂ ፥ ትግል አያስፈልግም።

ድሮኮ ድሮኮ
ፈጣሪ የሾመው ፥ ጥበብን አድሎት
ዙፋኑን እንዳይለቅ
"ቆንጆ አታሳየኝ" ነው ፥ ያንድ ጠቢብ ፀሎት።

ንጉስን ለማውረድ ፥ህዝብ ሲያጣ አቅም
እኛው ከኛው ጦር ጋር ፥"ልቀቅ አንለቅም"
እየተባባልን ፥እርስ በርስ ብናልቅም
ቆንጆ ስንል አቤት ፥ ያለንን አናውቅም።

ንጉስን ከዙፋን
በውበትሽ ማርከሸ ፥ ማውረድ የማትችዬ
አንዳችም ደም ሳይፈስ ፥ ህዝብ የምታስጥዬ
ማነሽ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፣ "አቤት"የምትዪ

✍በላይ በቀለ ወያ

@poems_Essay


🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ንፋሷ ከወደኔ ነፈሰች።የእስንፋሷ ጥልቀትም ከእውነት መንደር አኖረኝ። የእፍታዋም ትርጉም እንዳዲስ መፈጠር አይደለምን,,,
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿


#ሞገስ


ጭኖብኝ

ሄደች ሄደችና ተመልሳ መጣች
እራሷ ጥላ ሄዳ ፈልጋ እንዳጣች
ምን ልበላት እስቲ ይቺን ወዶ ዘማች
እቺ ወዶ ዘማች....
ያጣችው ገብቶኛል
የጠፋውት እኔ እውነቱ ታውቶኛል
እንኩዋን ጠፍቼባት አቅፋኝም በርዶኛል

@poems_Essay


የዜግነት ቀብር
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እምዬ ኢትዮጵያ
ወንደላጤኮ ነሽ ፣ ተከራይቶ ኗሪ
ትሪ-ሊየን ሸሽቶሽ
ከቤትሽ ይገኛል ፣ ያልታጠበ ትሪ
እኛ ባንቺ እንኩራ ፣ አንቺ በኛ እፈሪ😂
👇👇👇👇👇
@poems_Essay


🖤ውብ ❤️

#የሴት_ልጅ
(አባ ፀጋዬ ገ/መድህን)

የሴት ልጅ ይለኛል ያዋረደኝ መስሎት፣
ስድብ እና ሙገሳ መለየት ተስኖት።
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ያውም የጀግናዋ፣
ጎንበስ ቀና ብላ ለልጇ ነዋሪዋ፣
ዘጠኝ ወር ሳልከፍል በሆዷ ተኝቼ፣
በጀርባዋ አዝላኝ እስክሄድ በእግሮቼ፣
ተደፍታ ስታነድ ምግቡን ለማብሰል፣
እንጀራ ስትጋግር ፊትዋ መስሎ ከሰል፣
ሳጠፋ ገስፃ እንዳልኮራ መክራ፣
በርታ እያለችኝ ሁሌም እንዳልፈራ፣
አይዞህ አልከፋም ሴት ያሳደገኝ ነኝ፣
ስድብ ከመሰለህ ደጋግመህ ስደበኝ፣
አልቀየምህም በስሟ ስትጠራኝ፣
እውነቱን ልንገርህ አዎ የሴት ልጅ ነኝ ።


ቀጥረሽኝ....
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!


@poems_Essay


የሶስት ሰው ቅኔ
(ኤፍሬም ስዩም)
አንድ ሰው ተቀኘ…….
በኔ ግጥም ላይ የግጥሜ ስዕል ሴት ልጅ አይደለችም
የብዕሬ ምናብ ውበቷ አይሆንም
የትም ሴት ይገኛል የትም ሀገር የለም
የትኞቹም ሴቶች እንዳገር ሴት ናቸው
የትም ሀገሮች ግን ከወንዜ ልዩ ነው
በኔ ግጥም ላይ ሀገሬ ናት ጥጉ
ህዝቧ ነው ምሽጉ
እንባዋን ማጠብ ነው ድርሰቴ ወደቡ
ሴት ልጅ አይደለችም የግጥሜ ሀሳቡ
ሌላ ሰው ተቀኘ……..
በኔ ጽሁፍ ላይ የቅኔዬ ሀሳብ ሀገሬ አይደለም
የትም ሀገሬ ነው ላገር አልቀኝም
ስላገር አልዘፍንም ስላገር አልስልም
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ውበቷን መኳል ነው ቀለሜ ልማዱ
ፍቅሯን መተረክ ነው ፊደሌ መንገዱ
ከሴት እቅፍ ውጭ መነሻ የለኝም
ከሴት እቅፍ ውጭም መድረሻ የለኝም
ከሴት ውበት ሌላ ሀገሬ አትሆንም የድርሰቴ ጥጉ
የግጥሜ ወጉ
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ሴት ልጅ ናት ቅኔዬ
ሶስተኛው ተቀኘ………
በኔ ድርሰት ላይ
የግጥሜ ምናብ ሴት ልጅ አይደለችም
ስለ ሴት ጽፌያለሁ
የፍቅሯም ትኩሳት ሀሳቤን አይሞላም
ይህንም አውቃለሁ
ስለ ሴት ልጅ ውበት ስለ ፍቅሯ ጽናት የጻፍኩትኝ ካለም
የጻፍኳትን አይነት ሴት ልጅን አላውቅም
ዳግም በኔ ቅኔ የግጥሜ ሀሰር ሀገሬ አይሆንም
ስላገር ጽፊያለሁ
አንድ አገርን ብቻ ልቤ አያፈቅርም
ይህንም አውቃለሁ
የተፈጥሮ ሀብቷ ፍጹም ድህነቷም
ሌላ አገር አይጠፋም
ሀገሬ የትም ነው ያረፍኩበት ሁሉ
ሰው እግሩ ነው እንጅ ልቡ አለ ከሁሉ
እናም በኔ ቅኔ ቅኔ የሚባለው
ሴትና ሀገርን ባንድነት አስሮ
የዘር ግድቦችን ኬላወችን ሰብሮ
ብዙ ልዩነትን ባንድ ሀረግ ቋጥሮ
ግኡዝ ተፈጥሮ ነው ቅኔዬ ማረፊያው
የግዛብሄር ስእል ነው እንባዬ ማበሻው
የሰማይ ውበት ነው ልቤ መደነቂያው
ጸሀይና ባህር ያድማስ ስእላት
ሽራፊ ጨረቃ የሰማይ ከዋክብት
የባህር እርጋታ የውቂያኖስ ሁከት
እኒህ ናቸው ቅኔ እኒህ ናቸው ድርሰት
እኒህ ናቸው ስእል እኒህ ናቸው ውበት
ስለነዚህ ሲጻፍ የዘር ግድብ የለም
ወንዝ አያሰጥመንም
በነዚህ ውበቶች የሴት ውበት አለ
የመልከ ጥፉን ሴት ስሜት ያልበደለ
በተፈጥሮ ውበት የሰው ውበት አለ
ጥቁርና ነጩን ባንድነት ያዘለ
እነዚህ ፍጥረታት የሌሉበት የለም
የትም ሀገር አሉ የትም ይታያሉ
ኬላ ይጥሳሉ
ላንዳገር አይደለም ላለም ይጮሃሉ
ስለዚህ ግጥሜን ላንዳገር አልሰጥም
በወሰን አልገልም በግድብ አልይዝም
ሽራፊ ጨረቃ የተፈጥሮ ውበት ክዋክብቶች ሳሉ
ኬላ ላለው አገር
ላንድት ሴት ዘርፋችሁ
ቅኔን አትበድሉ!


@poems_Essay


ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
(በእውቀቱ ስዩም)

" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ: ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ: ታጠበ ሸሚዜ::
ገደብ ጫፍ በሌለው: በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ: ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ: ከፎቅ ላይ አልወድቅም::
በሀኪሙ ስተት :በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ: ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ: እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር: ሽጉጤን አልጠጣም::
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ : ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ: ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ: ከመሞት ምን ሊገኝ?፡

@poems_Essay


የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ያባቴን ማንነት ፣ ድንገት ስጠይቃት
እንባና ትዝታ ፣ እየተናነቃት
እንዲህ ትለኛለች...
"አንተን በመሀፀን ፣ እኔን በእርግዝና
ልጁን እና ፍቅሩን ፣ ክዶ ሄዱዋልና
አንተን ለማሳደግ...
ታክቶኝ የለመድኩት ፣ የብዙ ሰው ገላ
አንተን ካሳደገህ...
ሁሉም አባትህ ነው!
ከፍሎኝ የሚተኛ ፣ ወንድ አዳሪው ሁላ።"
ብላ የምትነግረኝ
የሴተኛ አዳሪ ፣ የተከፋይ ልጅ ነኝ ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይሄ ነው ታሪኩዋ...
ሴት አዳሪነቱዋን፣ ቀድሞ ያስጀመራት
የሆነ ዘመን ላይ ፣ ፍቅረኛ ነበራት
"የዘላለሜ ነሽ" ብሎ የሚነግራት ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሆነ ዘመን ላይ...
"አረገዝኩ" አለችው ፣ ማስረገዙን ካደ
ዘላለም ስታምነው...
እኔን በመሐፀን ፣ እሷን በችግር ላይ ፣ ጥሎ ተሰደደ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሆነ ዘመን ላይ...
እኔ ተወለድኩኝ ፣ እሱዋ ተቸገረች
እኔን ለማሳደግ....
ከብዙ ወንዶች ጋር ፣ መተኛት ጀመረች።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከዛን ቀን ጀምሮ....
ሲመሽ ትወጣለች ፣ በፍጥነት ተኩላ
ማልዳ ትመጣለች ደክሙዋት ተጎሳቁላ
አንተን ካሳደገህ...
ከፍሎ ተኚ ሁሉ ፣ አባትህ ነው ብላ።


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ

@poems_Essay


ቀረሽ እንደ ዋዛ
--------------------
(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)
እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ዛፍ ሐረጎች፣
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ።
ስጠብቅ ----- ስጠብቅ
“ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ፣
ሳይ ማዶ፣
የልጅነት ዓይኔ ሟሟ እንደ በረዶ።”
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ባዘን ሳንጎራጉር
ትመጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ስዞር
ብርድ አቆራመደኝ።
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ----- ያውቃሉ።
መስኮቶች ጨልመው፣
ቤቶች ተቆልፈው፣
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ----- ያያሉ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ---- ያውቃሉ።
* * *
ከ"መንገድ ስጡኝ ሰፊ" የግጥም መድብሉ የተጨለፈ

@poems_Essay


ይህ ሁሉ የሆነው
ትናንት ነው
ስልሽ
አመታት አልፎታል ብለሽ ያወራሽው
ያለፉትን ቀናት እንደምን ቆጠርሽው?
ጨለማ ብርሃን የተፋለሱብን
ወንዝ ላቦቻችን የተፋሰሱብን
አዋሽ ላብ
ተከዜ ላብ
ዮርዳኖስ ላብ
የተጠመቅነው
የተቀመጥነው
የተደረደርነው
በጠቢብ ስሜት
ተነጥለን ኖርን ከወልቤት።
ቤቴ ሆንሽ
ቤተልሔም
ቤቴ ሆንሽ
ላሊበላ
ቤቴ ሆንሽ ማደሪያዬ
ቤቴ ሆንሽ መክረሚያዬ
ሱባኤ የምገባልሽ
ጉባኤ የምረታልሽ
ቅኖና ስግደቴ
ምነና ስደቴ
የሆንሽ የሆንኩት
ከቀመር ያመለጥን
ከመንፈስ የሮጥን
የተቃቅፍነው
የተፋፋቅነው
የጠፋብን እንሆነው
እርቃን ያልከለልነው
እንደሔዋን እንደአዳም
የተሻማነው ወዝ አድኖን ካመዳም
እንደአዳም እንደሔዋን
ሕይወትን አሳየናት ልኳዋን።
ታዲያ
ትናንት ነው
ስልሽ
አመታት አልፎታል ብለሽ ያወራሽው
ያለፉትን ቀናት እንደምን ቆጠርሽው?
አለፉ ነው ያልሽው
ትዝታ ነው ያልሽው
አመታት ነው ያልሽው
ልትሽሪው ሽተሽ ትዝታ በማለት
ሰከንድ አይረሳም እንኳንስ ያንዕለት
ሰው መሆን ማለትስ
ላዩን ልውስ ልውስ
ነበር ማለት ብቻ ናፍቆትን ላይፈውስ
አመታት ነው ያልሽው እንደሻረ ቁስል
ቆይቷል የምትይ እኔ ትናንት ስል።።
.
ትናንት መቼ ነው?

* * * * * * * * * *
ኤልያስ ሽታኹን

@poems_Essay


ነበር,,, አሁንሽ ላይ

አሁን ህይወትሽ ላይ,,,
ስሜን ስትጥይው እንዲው እንደዘበት፣
ስለኔ ሲነሳ,,,
ትከቺሻለሽ አሉ አላፊ የሆነ ቃላት
ያኔ,,, ትናት,,, ድሮ,,, በነበር,,, አንደበት
በነዚው ውስጥ አለው በአፍሽ መቀነት።
:
ሁሌም በወግሽ ላይ,,,
ይህ ሁሉ ያኔ
ይህ ሁሉ ድሮ°°°
ይህ ሁሉ ትናት በነበር ቢወሳ
ነፍሰ_ስሜ ወድቆ እረሳችኝ ስል ዳግም ከተነሳ።
:
ጥርጣሬ አለኝ ሁሌም ከምስቂያት ከዛ ሳቅሽ ጀርባ
ከትዝታ ጉርጓድ,,,
ናፍቆት እየበላት ከደከሙ አይኖች የምትፈስ እንባ።
:
ጥርጣሬ አለኝ,,,
'ረስቼዋለው ከምትል ቃለ_ገፅ
የማትረሺው አለ ያውም ትልቅ መፅሀፍ
ያሁን እኔነቴን በጉልህ የሚፅፍ
ማታ ምትቃርሚው ማለዳ ሚገለፅ
አለ ትልቅ ፀፀት ማጣት ያቆሰለው በቃሉ ሚታነፅ።
:
ተወዛግቦ ቢገኝ ከከንፈርሽ መሀል
ያኔ ድሮ ትናት የነበሮችሽ ቃል
ትርጓሜው ጠፍቶሽ ጥላቻሽ ቢነደል
ካፍ ላይ ባይገጥም የልብሽ ላይ ፊደል
ክብር ለትዝታሽ የመራራቅ ወሰን እድሜ አስተምሮሻል
ኖረን ስጠፋብሽ ስታጪኝ ታውቆሻል።

#ሞገስ

@poems_Essay


🖊የብዕር አንደበት🖊

ያ ገጣሚ ባልሽ ግጥም እሚወደው
ግጠም አትበይው እመሙ እሱ ነው
ተድላ የላይ ደስታ ቢመስልም ግጥመቱ
አገጣጠሙ ነው ሲቃና ጉዳቱ

በግጥም መስመሩ ውድነት ያበዛል
ላንቺ አነባበብ ግጥም ይመስልሻል
በግጥም መስመሩ ኩራትን ይሰራል
ባንቺ ሀስተሳሰብ ቅመም ይመስልሻል
በድብቅ ፊደላት ሀረጉን ያሰፍራል



እና ገጣሚሽን ያለግጣም ግጠም
ፃፈኝ አትበይው
በብዕር አንደበት ሲቃን አታስምጪው
ወይ እጁን ስበሪው ብዕሩን ንጠቂው
ወይም አታስጠጊው ከአጠገብ አርቂው
አልያም አድምጭው ጆሮ ዳባ አትበይው

#ሞገስ

@poems_Essay


የምኖረው ለሷ ፣ ምትገለኝ ለነፍሱ
የታገላት ልቤ ፣ ሚያሸንፋት ኪሱ
የተበደልኩ እኔ
የምትከሰው እሷ ፣ የሚዳኘን እሱ
አለመገጣጠም ፣ ግጥም ነው በራሱ።

በላይ በቀለ ወያ

@poems_Essay






####እንዲህ ያደርገኛል####
:
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ሰውነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል፣
ኮቴ እንደመብረቅ እንደአንዳች ፍንዳታ የጆሮዬን ታንቡር
ደርሶ ይጠልዘኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
ጥሞናዬ ረቆ፣
መንፈሴን አምጥቆ፤
የሷን ኮቴ ናፍቆ፣
የፍቅሬን አካሄድ ሰበር ሰካውን
ከርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አውቆ፡፡
በናፍቆቷ ድጋን
በጉጉት ፍላፃ
ተወርዋሪው ልቤ
ተወጥሮ ከሮ፣
ጅስሜ እንደአሞራ
እንደብርቱ ንስር
ክንፍ አውጥቶ በሮ፡፡
ምድርና ሞላዋን
አለምን ይቃኛል፣
ከፍቅሬ በስተቀር
ሁሉም ከንቱ ከንቱ
ከንቱ ውቱ ይለኛል፡፡
እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት እንዲህ ያደርገኛል፣
በፍቅሯ ልዕልና በፍቅር ፅናቴ፣
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ በአቴ፣
ከመላዕክ ረቅቄ፤
ከፃድቅ ፀድቄ እጠብቃታለሁ፣
እመጣለሁ ብላኝ
መች ተኝቼ አውቃለሁ፡፡
አለም ግዜ ፀሀይ ሁሉም ቀጥ ብለው፣
የኪዳኔን ታቦት ፅላቴን አክብረው፣
ይማፀኑልኛል፤
ይማልዱልኛል፤
ይህ ምስኪን ፃዲቅ ሰው፣
ከአለም የመነነው
ባዕቱን የዘጋው፣
ፀሀይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተው፣
እመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገዪ ነው፤
እንዳትቀሪበት ነው፡፡
ብለው ይሉልኛል
ጨረቃ ከዋክብት
ይማልዱልኛል፣
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያውቁልኛል፣
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ፤
ካይን ያውጣህ ይሉኛል፡፡
አንድ አንዴም ሽው ሲል
እንዲህ እሆናለሁ፣
ከቤቴ ቁጭ ብዬ
በሀሳብ እመጥቃለሁ፣
እሷን እየጠበኩ
እፈላሰማለሁ፤
እላላሁ፣
ይሄ ሁሉ ጥሞና
ይሄ ሁሉ ብቃት፣
ለሌላም ለሌላም
ቢሆን ምን አለበት፣
አዬ ግዜ ደጉ
አዬ ወጣትነት እላለሁ፡፡
እድሜ ለሷ ፍቅር
መንፈሴን ቀጥቅጦ
ልቤን ለሚገዛው፣
በሌላማ ግዜ
በጥልቅ ለመመሰጥ
አዕምሮዬን ባዘው፣
መች እሺ ይለኛል፤
መች እሺ እላለሁ፤
መች እሺ እለለሁ፡፡

@poems_Essay

🥀


#አደን
( ደበበ ሰይፉ )
:
አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሣደድኳት።
ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል
በነብርና በቅጠል መሀል።

አቤት አለች ያልጠራኀት
የጠራኀት ድምፅም የላት።
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ ምላት ከኔ ርቃ።

አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የዕድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።
//

( ደበበ ሰይፉ፣ ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ )

@poems_Essay


#የሰካራም_ግጥም

የማብድ ቢመስለኝ ድንገት አንቺን ሳጣ
አረቄ ቤት ሄጄ አረቄ ስጠጣ
አንድ ግጥም ሰማሁ
ፍቅርሽን ከልቤ ነቅሎ የሚያወጣ።
ያውም "መንገድ በሚል
ለመንገደኛ ሰው ሰካራም የፃፈው
እዛጋ ቁጭ ብሎ,,,
"ከዳችኝ" እያለ የሚለፈልፈው
"መንገድ" የሚል ግጥም ጆሮዬን ገረፈው።
ጆሮዬ ሲገረፍ,,,
ጠባሳ ጣለብኝ ግጥሙን እንዳልረሳ
"መንገድ አያደርስም
መንገድ አይመልስም እግር ካልተነሳ!"
እያለ ይገጥማል,,,
ደጋግሞ ደጋግሞ ሌላ አይናገርም
እሱም ልክ እንደኔ,,,
አንዷ በመሄዷ ሳያጣት አይቀርም።
ብቻ ሰክሪያለሁ
ለመንገደኛ ሴት
የተፃፈ ግጥምን ጆሮዬ ያደምጣል
መሄድሽን ያየ
እንደሌለሽ ሲያቅ ሊኖረኝ ይመጣል
ይህ ነው መንገድ ማለት!
የሰካራም ግጥም ሰክሬ ስረዳው
መሄድ ሳይሆን ለኔ መርሳት ነው ሚጎዳው!

ረስቼሻለው!


በላይ በቀለ ወያ

@poems_Essay


ሂጂ ለመሄጃሽ

ፈርጥጪ
እሩጪ
ከእድሜሽ አምልጪ
ከራስሽ አምልጪ
ተጓዥ
ተቅበዝበዥ
ከገሀድ ብለጪ

ምንድ ነው ካ'ንድ መርጋት
ምንድነው ሰክኖ መጋራት
ምንስ ነው እድሜ ልክ
ለአንድ አጥር መንበርከክ
ወህደት በሚሉት ባ'ንድነት እስራት

ልብስሽ ብዙ ጠረን
ገላሽ ብዙ ገላን
ከንፈርሽ እልፍ ከንፈር
ፍቅርሽ ስንት ፍቅር

ይህን የለመደ ልብ መጓዝ ነው ያለበት
አርምሞ ባዳውን በሩቅ በመጋፋት

ሲሰራት
ሲሰራት
ካልነካችው ዳሰስ ካልታየው ሊስላት
ተንከራተቺ አላት
አንድ እሷን ፈጠረ ለአላፍ ፍጥረታት

ቤትሽ እርቀቱ ፈልቶልሽ ሸኚሽ
በፀፀት ቢሞላ የነበር ትዝታሽ
ፈፅሞ አታዝግሚ ፍጠኝ ለፍጥነትሽ
ባትደርሺም እንኳን ሂጂ ለመሄጃሽ

//ፈቅጃለው//


#ሞገስ

Показано 20 последних публикаций.

182

подписчиков
Статистика канала