የሶስት ሰው ቅኔ
(ኤፍሬም ስዩም)
አንድ ሰው ተቀኘ…….
በኔ ግጥም ላይ የግጥሜ ስዕል ሴት ልጅ አይደለችም
የብዕሬ ምናብ ውበቷ አይሆንም
የትም ሴት ይገኛል የትም ሀገር የለም
የትኞቹም ሴቶች እንዳገር ሴት ናቸው
የትም ሀገሮች ግን ከወንዜ ልዩ ነው
በኔ ግጥም ላይ ሀገሬ ናት ጥጉ
ህዝቧ ነው ምሽጉ
እንባዋን ማጠብ ነው ድርሰቴ ወደቡ
ሴት ልጅ አይደለችም የግጥሜ ሀሳቡ
ሌላ ሰው ተቀኘ……..
በኔ ጽሁፍ ላይ የቅኔዬ ሀሳብ ሀገሬ አይደለም
የትም ሀገሬ ነው ላገር አልቀኝም
ስላገር አልዘፍንም ስላገር አልስልም
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ውበቷን መኳል ነው ቀለሜ ልማዱ
ፍቅሯን መተረክ ነው ፊደሌ መንገዱ
ከሴት እቅፍ ውጭ መነሻ የለኝም
ከሴት እቅፍ ውጭም መድረሻ የለኝም
ከሴት ውበት ሌላ ሀገሬ አትሆንም የድርሰቴ ጥጉ
የግጥሜ ወጉ
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ሴት ልጅ ናት ቅኔዬ
ሶስተኛው ተቀኘ………
በኔ ድርሰት ላይ
የግጥሜ ምናብ ሴት ልጅ አይደለችም
ስለ ሴት ጽፌያለሁ
የፍቅሯም ትኩሳት ሀሳቤን አይሞላም
ይህንም አውቃለሁ
ስለ ሴት ልጅ ውበት ስለ ፍቅሯ ጽናት የጻፍኩትኝ ካለም
የጻፍኳትን አይነት ሴት ልጅን አላውቅም
ዳግም በኔ ቅኔ የግጥሜ ሀሰር ሀገሬ አይሆንም
ስላገር ጽፊያለሁ
አንድ አገርን ብቻ ልቤ አያፈቅርም
ይህንም አውቃለሁ
የተፈጥሮ ሀብቷ ፍጹም ድህነቷም
ሌላ አገር አይጠፋም
ሀገሬ የትም ነው ያረፍኩበት ሁሉ
ሰው እግሩ ነው እንጅ ልቡ አለ ከሁሉ
እናም በኔ ቅኔ ቅኔ የሚባለው
ሴትና ሀገርን ባንድነት አስሮ
የዘር ግድቦችን ኬላወችን ሰብሮ
ብዙ ልዩነትን ባንድ ሀረግ ቋጥሮ
ግኡዝ ተፈጥሮ ነው ቅኔዬ ማረፊያው
የግዛብሄር ስእል ነው እንባዬ ማበሻው
የሰማይ ውበት ነው ልቤ መደነቂያው
ጸሀይና ባህር ያድማስ ስእላት
ሽራፊ ጨረቃ የሰማይ ከዋክብት
የባህር እርጋታ የውቂያኖስ ሁከት
እኒህ ናቸው ቅኔ እኒህ ናቸው ድርሰት
እኒህ ናቸው ስእል እኒህ ናቸው ውበት
ስለነዚህ ሲጻፍ የዘር ግድብ የለም
ወንዝ አያሰጥመንም
በነዚህ ውበቶች የሴት ውበት አለ
የመልከ ጥፉን ሴት ስሜት ያልበደለ
በተፈጥሮ ውበት የሰው ውበት አለ
ጥቁርና ነጩን ባንድነት ያዘለ
እነዚህ ፍጥረታት የሌሉበት የለም
የትም ሀገር አሉ የትም ይታያሉ
ኬላ ይጥሳሉ
ላንዳገር አይደለም ላለም ይጮሃሉ
ስለዚህ ግጥሜን ላንዳገር አልሰጥም
በወሰን አልገልም በግድብ አልይዝም
ሽራፊ ጨረቃ የተፈጥሮ ውበት ክዋክብቶች ሳሉ
ኬላ ላለው አገር
ላንድት ሴት ዘርፋችሁ
ቅኔን አትበድሉ!
@poems_Essay
(ኤፍሬም ስዩም)
አንድ ሰው ተቀኘ…….
በኔ ግጥም ላይ የግጥሜ ስዕል ሴት ልጅ አይደለችም
የብዕሬ ምናብ ውበቷ አይሆንም
የትም ሴት ይገኛል የትም ሀገር የለም
የትኞቹም ሴቶች እንዳገር ሴት ናቸው
የትም ሀገሮች ግን ከወንዜ ልዩ ነው
በኔ ግጥም ላይ ሀገሬ ናት ጥጉ
ህዝቧ ነው ምሽጉ
እንባዋን ማጠብ ነው ድርሰቴ ወደቡ
ሴት ልጅ አይደለችም የግጥሜ ሀሳቡ
ሌላ ሰው ተቀኘ……..
በኔ ጽሁፍ ላይ የቅኔዬ ሀሳብ ሀገሬ አይደለም
የትም ሀገሬ ነው ላገር አልቀኝም
ስላገር አልዘፍንም ስላገር አልስልም
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ውበቷን መኳል ነው ቀለሜ ልማዱ
ፍቅሯን መተረክ ነው ፊደሌ መንገዱ
ከሴት እቅፍ ውጭ መነሻ የለኝም
ከሴት እቅፍ ውጭም መድረሻ የለኝም
ከሴት ውበት ሌላ ሀገሬ አትሆንም የድርሰቴ ጥጉ
የግጥሜ ወጉ
ሴት ናት መነሻዬ ሴት ናት መድረሻዬ
ሴት ልጅ ናት ቅኔዬ
ሶስተኛው ተቀኘ………
በኔ ድርሰት ላይ
የግጥሜ ምናብ ሴት ልጅ አይደለችም
ስለ ሴት ጽፌያለሁ
የፍቅሯም ትኩሳት ሀሳቤን አይሞላም
ይህንም አውቃለሁ
ስለ ሴት ልጅ ውበት ስለ ፍቅሯ ጽናት የጻፍኩትኝ ካለም
የጻፍኳትን አይነት ሴት ልጅን አላውቅም
ዳግም በኔ ቅኔ የግጥሜ ሀሰር ሀገሬ አይሆንም
ስላገር ጽፊያለሁ
አንድ አገርን ብቻ ልቤ አያፈቅርም
ይህንም አውቃለሁ
የተፈጥሮ ሀብቷ ፍጹም ድህነቷም
ሌላ አገር አይጠፋም
ሀገሬ የትም ነው ያረፍኩበት ሁሉ
ሰው እግሩ ነው እንጅ ልቡ አለ ከሁሉ
እናም በኔ ቅኔ ቅኔ የሚባለው
ሴትና ሀገርን ባንድነት አስሮ
የዘር ግድቦችን ኬላወችን ሰብሮ
ብዙ ልዩነትን ባንድ ሀረግ ቋጥሮ
ግኡዝ ተፈጥሮ ነው ቅኔዬ ማረፊያው
የግዛብሄር ስእል ነው እንባዬ ማበሻው
የሰማይ ውበት ነው ልቤ መደነቂያው
ጸሀይና ባህር ያድማስ ስእላት
ሽራፊ ጨረቃ የሰማይ ከዋክብት
የባህር እርጋታ የውቂያኖስ ሁከት
እኒህ ናቸው ቅኔ እኒህ ናቸው ድርሰት
እኒህ ናቸው ስእል እኒህ ናቸው ውበት
ስለነዚህ ሲጻፍ የዘር ግድብ የለም
ወንዝ አያሰጥመንም
በነዚህ ውበቶች የሴት ውበት አለ
የመልከ ጥፉን ሴት ስሜት ያልበደለ
በተፈጥሮ ውበት የሰው ውበት አለ
ጥቁርና ነጩን ባንድነት ያዘለ
እነዚህ ፍጥረታት የሌሉበት የለም
የትም ሀገር አሉ የትም ይታያሉ
ኬላ ይጥሳሉ
ላንዳገር አይደለም ላለም ይጮሃሉ
ስለዚህ ግጥሜን ላንዳገር አልሰጥም
በወሰን አልገልም በግድብ አልይዝም
ሽራፊ ጨረቃ የተፈጥሮ ውበት ክዋክብቶች ሳሉ
ኬላ ላለው አገር
ላንድት ሴት ዘርፋችሁ
ቅኔን አትበድሉ!
@poems_Essay