መውሊድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
“መውሊድ” مَوْلِد የሚለው ቃል "ወለደ" وَلَدَ ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ልደት” ማለት ነው፥ "የልደት ቀን፣ ቦታ እና በዓል እራሱ "መውሊድ" ይሉታል። በተለይ ነቢያችን”ﷺ” ተወለዱት ተብሎ የሚከበርበት ቀን "መውሊድ" ይባላል። ይህንን የመውሊድ እሳቤ ለማወቅ ከዝንባሌ ነጻ ሆነን ስለ ሸሪዓችን ጠንቅቀህ ማወቅ ይጠበቅብናል፥ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፥ መፍረድ ያለብንም ከአላህ በወረደው ሸሪዓህ ብቻ ነው፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا
እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፥ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው። “አሕካም” أَحْكَام ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።
እነዚህ ሕግጋት ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መሠረት ብቻ ዒባዳህ ይፈጸማል። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን፥ ዒባዳህ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። “ኢትባዕ” إِتْبَاع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም፥ ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል*፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል። “ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *"አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው"*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ” مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ” . قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ . فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ” .
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ”
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *"በሁለቱ በአል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ .https://t.me/wequl_Rebi_zidni_elmenhttps://t.me/wequl_Rebi_zidni_elmen